፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ብሂለ አበው

@And_Haymanot

👉 "መሬት ሁን ከመባል ያነሰ የውርደት ቋንቋ የለም ሰው አምላክ ሆነ ከመባል በላይ የሚበልጥ የክብር ቋንቋ የለም"።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👉 "ከመጠኑ በላይ የሚመሰገንና የሚከበር ሰው ብዙ ኩነኔ ያገኘዋል ከሰው ዘንድ ከቁም ነገር ሳይቆጠር መልካም ሰርቶ ያለፈ ሰው ግን በሰማይ ታላቅ ክብር ይጠብቀዋል"። አባ አውር
👉 "በኃይል አብዝቶ መመገብ ከወጣትነት ጋር የኃጢአት ሐሳብን በግድ እንዲመጣ ያደርጋሉ"። ማር ይስሐቅ
👉 "ከሰዎች መካከል አንዱ እንደ ከንቱ እና ምንም እንደሌለህ እንደ አላዋቂ አድርጎ ቢቆጥርህ ከአፈር እንደተፈጠርህና ወደ እርሱም እንደምትመለስ ተናገር አንተ ወራዳ ከንቱ ብሎ ቢሰድብህም አንተ ራስህን አፈርና አመድ ነኝ ብለህ ጥራ እራሱን እንዲህ
ብሎ ከጠራው ከተከበረው አባት ከአባታችን አብርሃም የበለጥህ አይደለህምና"። ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ
👉 "ቤተ ክርስቲያን በጥምቀት አማካይነት አንድ የሆኑ ክርስቲያኖች የትንሳኤያቸውና የድኅነታቸው ምንጭ የክርስቶስ አካል ናት"። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👉 "ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ጽናት ብዛት ያስረዳል፤ ባልንጀሮች ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል የምቀኝነቱን ጽናት ያስረዳል"። ማር ይስሐቅ
👉 "የመጠመቂያውን ውኃ ተራ ውኃ አድርገህ አትመልከተው፤ በውኃው አማካኝነት የሚሰጠውን ፀጋ እንጂ"። ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም
👉 "ቂመኛ ከመሆን ተከልከል፤ ቂመኛ ሰው ሥጋ የለበሰ ሰይጣን ነውና"። አረጋዊ መንፈሳዊ
👉 "ቤተ ክርስቲያን መጠጊያችን ነች፤ ቤተ ክርስቲያን የኖህ መርከብ ነች፤ በውስጧ እንጠለላለን፤ ከውጪዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል"። ቅዱስ እንድርያስ
👉 "የንጉሡ የክብር ዘቦች በፊት ለፊት በተጠንቀቅ ሲቆሙ ወደ ግራም ወደ ቀኝም አይመለከቱም ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ሲቆም ሁል ጊዜ በፍርሃት ሆኖ እርሱን ሊመለከት ይገባል"። አባ ሰራጵዮን
👉 "ቅዱሳን ለመለኮታዊ ማዕጠንት የተቀጣጠሉ ዕጣን ሲሆኑ የተቀጣጠሉትም በፈጣሪያቸው ፍቅር ነው"። ማር ይስሐቅ
👉 "ሰው አገሩን ጥሎ በሔደ ጊዜ ሁሉ ያዝንለታል፤ ከርስቱ ከጉልቱ በተለየ ጊዜ ሁሉ ይራራለታል ያለቅሱለታል፤ ከመንግስተ ሰማያት ከተድላ፤ ከመዓዛ የተለየ ሰውማ ምን ያህል ለቅሶ ማልቀስ ምን ያህል ዕምባ ያፈስ ዘንድ የሚገባው ምን ያህል ይሆን"። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@And_Haymanot
የቅዱሳን አባቶቻችን ረድኤት በረከት አይለየን!!! አሜን
#መልካም_ዕለተ_ሰንበት
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
Join us
@And_Haymanot
@And_Haymanot