፩ ሃይማኖት
8.91K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?


#ይድረስ_ለተሃድሶ_መናፍቃን

@And_Haymanot

☞ "አጥብቀህ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት ተማር፥ ብሉያትን ሐዲሳትን በኦርቶዶክሳዊ መንገድ ምሥጢር አደላድል፤ እናም ጸልይ፤ ከሐሰተኛ፥ ከክህደት
ጽሑፎች ውጭ ሌሎችን አንብብ።" ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ✞✞✞


✞ በ4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ቅዱስ አውግስጢን "መናፍቃንን ስለ ጥርጥር ጥያቄያቸው ሁሉ እናመሰግናቸዋለን፤ የበለጠ እንድናጠና፣ በጥልቀት እንድንመራመር አድርገውናልና" እንዳለው የመናፍቃን መነሣት ለቤተ ክርስቲያን ትልቅ ጥቅም ነው ታላቁ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስም "ስራ የሞላበት ታላቅ በር ተከፍቶልኛል ተቃዋሚዎች ግን ብዙ ናቸው" ብሏል ዛሬም በእኛ ዘመን የእናት ጡት ነካሾች የተሃድሶ መናፍቃን የነገረ ሃይማኖት ጥያቄዎቻቸውን በማትታደስ ኦርቶዶክሳዊ ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ማጉረፍ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል ምንም እንኳን ጥያቄዎቹ የተለመዱ እና ከጥንት ጀምሮ ተመሳሳይነት ያላቸው ቢሆንም አዲስ ትውልድ በየጊዜው ይመጣልና በየጊዜው ኩላዊት ቤተ ክርስቲያናችን መልስ ስትሰጣቸው ቆይታለች ሃራጥቃውያኑ ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነታን ተረድተው በንሰኃ ከመመለስ ይልቅ አሁንም የኑፋቄ ጭቃቸውን ማቡካት ነው የመረጡት።

ወደድንም ጠላንም በአሁን ጊዜ የቅዱሳንን ሕይወት ተረድተን መጓዝ ካልቻልን ወንጌልን እንፈጽማለሁ ማለት ውሸት ነው በየዓውደ ምሕረቱ ላይ ከገድላት የሚጠቀሱ ተአምራት ታሪኮች መብዛት ይገባቸዋል ሁሉንም ነገር በጥቅስ ለማስደገፍ መሯሯጥ የእምነታችንን መላላት ያሳያል እንጂ የሃይማኖት ጥንካሬያችንን አያመላክትም የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሙሉ በሙሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቢሆንም ያልተመዘገቡ በርካታ ነገሮች አሉ "ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ" ተብሎ ተጽፏል" /ዮሐ 14፥12/ ኃላ የሚነሱ ቅዱሳን ጌታ ካደረገው ተአምር የበለጠ በክርስቶስ ስም እንደሚያደርጉ ተጽፏል /ዮሐ 14፥12/ በቅዱሳን ሕይወት የሚመሰገነው ክርስቶስ ነው ቅዱሳን ዐርባና ሃምሳ ዓመት በጾም ተወስነው እንዲቆዩ የሚያደርጋቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው ቅዱሳን ለእግዚአብሔር የተመቹ ድንቅ ተአምራት የተደረጉባቸው ናቸው "እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቆ ነው" ተብሎ ተጽፏል /መዝ 67፥35/ ቅዱሳንን መንቀፍ፣ አያማልድም ብሎ ክብራቸውን ማቃለልም ባለቤቱን ቃል ኪዳን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን መቃወም ነው።

እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ሰጥቶ ኃጥአንን ቢምር አንተ ምን ያበሳጭሃል? "ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ" ተብሎ ተጽፎ የለምን? /መዝ 88፥3/ ሰው ቢድን ለምን እንደ ሰይጣን ትቀናለህ? ክርስቶስን እስከመቼ ስታሳድድ ትኖራለህ? በቸርነቱ ሰው ይድን ዘንድ የዘረጋውን የማማለድ በረከት ለምን ትነቅፋለህ? "ባሪያዬ ኢዮብ ስለ እናንተ ይጸልያል" እንደተባለ፤ የባሪያዬ የተክለ ሃይማኖት ቃል ኪዳን የሌሎቹንም አልረሳም ቢል ምን ያበሳጭሃል? በቅዱሳኑ አድሮ የሰራ መንፈስ ቅዱስ ነው ቅዱሳንን መንቀፍና አለመቀበል መንፈስ ቅዱስን፤ ክርስቶስን አለመቀበል ነው በሐዋ.ሥራ 9፥4 ላይ ያለውን እስቲ በቅንነት እናንብበው " #ሳውል_ሳውል_ስለምን_ታሳድደኛለህ?" የተሰደዱት ሐዋርያት፣ ተናጋሪው ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር የሚሰደዱት ሐዋርያት ላይ ያደረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነበርና " #አንተ_የምታሳድደኝ_እኔ_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ነኝ" ብሎታል ስለዚህ ቅዱሳንና እግዚአብሔር አይነጣጠሉም።።።።።። ደግሞስ "የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል" ተብሎ የለምን? /መዝ 111፥6፣ ምሳ 10፥7/ ከዚህ አንጻር የድርሻችንን እየተወጣን እያንዳንዳችን ልንዘክራቸው የሚገቡንን ቅዱሳን በመያዝ ገድላቸውን በማንበብ፣ በመጸለይ፣ በስማቸው ነዳያንን እያበላን በእምነትና በቃል፣ በሥራን ልንመስላቸው ይገባል። /1ኛ ጢሞ 4፥12/

ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ በነቢዩ አድሮ እንደተናገረው ለመታሰቢያ፣ ለበረከት፣ ለፈውስ እንዲሆን የቅዱሳን ገድላቸው ተጽፏል መጠቀም የእውነተኛ ክርስቲያን ድርሻ ነው መጽሐፍስ "እግዚአብሔርንም ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መጽሐፍ በፊቱ ተጻፈ" ብሎ ትንቢት ተነግሮላቸዋል /ሚል 3፥16/ ገድላት ወንጌልን በተግባር የገለጡ የመንፈስ ቅዱስ ሥራዎች ናቸው ከዚህ ከማያልቀው የገድላት በረከት ለመሳተፍ ገድላትን እናንብብ፤ ቅዱሳንን እንዘክር አሁን በእውነት በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አማላጅነት ካልሆነ በቀር በዚህ ዘመን በሥራው የሚጸድቅ ይኖር ይሆን? ስለዚህ በዚህ ክፋት በሰለጠነበት ዘመን ወደ ቅዱሳኑ መጠጋት ይገባል ለዚህም የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን። አሜን።✞✞✞

☞ "አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና።" 2ኛ ጢሞ 3፥14 ✞✞✞

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት ተዋህዶ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
@And_Haymanot
✞_✞_✞