Forwarded from ፩ ሃይማኖት
❖ መልካም አዲስ አመት አትበሉን!!!!!!!
@And_Haymanot
የ ፳፻፲፩ (2011) ዓ.ም የመልካም ምኞት መግለጫ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ማኅበራዊ ሚዲያዎች 'መልካም አዲስ አመት' ሲሉ "መልካም አዲስ ገረድ' ማለታቸው መሆኑን ያውቃሉ......
♦ "አመት" ተብሎ በአልፋው "አ" ሲጻፍ ሴት አገልጋይ ገረድን ይገልጻል። ለምሳሌ፦ "ተፈሥሒ ኦ አመት ወእም ድንግል ወሰማይ ሰማያዌ..." /ውዳሴ ማርያም ዘረቡዕ/ ሲል ገረድ(ሴት አገልጋይ) ና እናት፤ ድንግልና ሰማይ ሆይ ደስ ይበልሽ ማለት ነው።
♦ "ዓመት" ሲሆን ዘመን ይሆናል። "...ርእሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ።..."/መልክአ ዮሐንስ መጥምቅ፤ ለሥእርተ ርእስከ(ለራስ ጸጉርህ)/ ሲል ደግሞ "የመጥቅዕና የአበቅቴ መጀመሪያ ርእሰ ዓመት ዮሐንስ ሆይ..." ማለት ነው።
✍ አመት የሚለው በብዙ ቁጥር አእማት ይሆናል። በዕብራይስጥ አማህ፤ በሱሪስት አምታ፤ በዐረብኛ ደግሞ አመት ይለዋል። ትርጓሜውም ሴት ባሪያ፤ ገረድ፤ ደንገጥር ማለት ነው። "...በወፍጮ እግር እስካለችው እስከ ባሪያይቱ..." ዘፀ.11፥5 የሚለውን ግዕዙ "አመት እንተ ትነብር ዲበ ማሕረጽ።" ይለዋል። በዚህ አገባብ አማርኛው "ባሪያይቱ" የሚለውን ግዕዙ "አመት" ይላታል።
✔ ወንዶች ባሪያዎችን "አግብርት" ሲላቸው ሴቶች ባሪያዎችን ደግሞ "አእማት" ይላቸዋል። [ዘፍ.32፥5 ግዕዙን ንባብ ተመልከት]
♦ ዓመት የሚለው ደግሞ በብዙ ቁጥር "ዓመታት" ሲባል ዘመን፥ ዘመናት፥ ብዙ ቀን፥ የዕለታት ድምር ማለት ነው። "በባቢሎን ንጉሥ በብልጣሶር በመጀመሪያው ዓመት" ዳን.7፥1 የሚለውን ግዕዙ "በቀዳሚ ዓመተ መንግሥቱ።" ይለዋል። "የዕድሜህም ቁጥር ብዙ ነውና፥" ኢዮ.38፥21 የሚለውን ግዕዙ "ኊልቆ ዓመታቲከ፥" ይለዋል።
✍ ስለሆነም አንድ ሰው 'እንኳን ለአዲሱ አመት አደረሰን' ሲል 'እንኳን ለአዲሷ ገረድ አደረሰን' አለ ማለት ነው። ይኼ ደሞ ጸያፍ ነው።
♦ "እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰን" ሲል "እንኳን ለአዲሱ ዘመን አደረሰን ማለቱ ነው። ይኸውም የተገባ ነው።
✔ መልካም ምኞታችሁን የገለጻችሁ መስሏችሁ 'መልካም አዲስ አመት' አትበሉን!!!!!
በዲ/ን ቴዎድሮስ ዘለቀ

ፍቅሯ ቢጸናብኝ !
* ተወዳጆች ሆይ ! ቅዱስ ኤፍሬም ሲመጸውት ዘወትር
በእመቤታችን ስም ነበር "ምነው ሌሎቹን ንቋቸው ዘንግቷቸው
ነውን"? ቢባል ... ዘንግቶ ንቆስ አይደለም የእሷ ፍቅር ቢጸናበት
ነው እንጂ ! ብለው ሊቃውንቱ መስክረውለታል! ጠቢቡ ሲራክ
"ብዙ ሰዎች ወዳጅ ይሁኑህ ነገር ግን ከብዙዎቹ አንዱ ምክርህን
የምትገልጥለት ይሁን " ሲራክ 6;6 እንዳለው ሁሉም ቅዱሳን
ወዳጅህ ይሁኑ ከሁሉ ግን የማን ፍቅር ጸናብህ? ለቅዱስ
ኤፍሬም እመቤታችን ወላዲተ አሞላክ;ለነቢዩ ኤልሳዕ ነቢዩ
ኤልያስ ፡ ለአፎምያ ቅ/ሚካኤል፡ ለአቡነ ቄርሎስ ቅዱስ ሚናስ፡
ለቅ/አትናቴዎስ አባ እንጦንስ፡ ፍቅር ጸንቶባቸው ነበር
አርአያቸውንም ተከትለዋል ! ወዳጄ አንተ የማን ፍቅር ጸናብህ?
የእመብርሃን? የአቡነ ተክለ ሃይማኖት? የአቡነ ገ/መንፈስ
ቅዱስ? የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ? የቅዱስ ጊዮርጊስ?
የወንጌላዊው ዮሐንስ? የየቱ ፍቅር ጸናብህ? ከጸናብህ ከቅዱሱ
ምን ተማርክ? ወር ጠብቀህ ትዘክረዋለህ? ምክንያቱም
ለወዳጆችህ ልደት እየታደምክ ደስታቸውን እየተካፈልክ የቅዱሱን
በዓል እንዴት አትሳተፍም? ለወዳጅህ ሠርጉን እያደመቅክ
እንዴት የእመብርሃንን የአቡዬን የተክልዬን የቅ/አርሴማን በዓል
ማክበር ማድመቅ ለምን ተሳነህ? ፍቅሩ ለጸናብህ ቅዱስ፡ ቀኑን
አስበህ ትጸልያለህ? ድርሳኑን መልኩን ታደርሳለህ? የዚያ ቅዱስ
ስብዕናና ቅድስና ሕይወት ባንተ ውስጥ እንዲሰራ ምን ያህል
ራስህን አዘጋጀከው? ተወዳጆች ለእኔ ግን የእመብርሀን ፍቅሯ
ጸንቶብኛል፡ የእናትነቷ መዳፍ የሳተው ልቡናዬን ሲያቀናው
ችግሬንም ስታቀለው ልመናዋም የሐጥያቴን ነዶ ሰንደው ፍቅሯ
አብዝቶ በልቤ ነደደ ! ሙሴ ስለ ሮቤል "ሮቤል አይሙትብኝ
እፈልገዋለሁ" ካለው በላይ ድንግል ስለእኔና ስለልጆቿ "ተክለ
አብን እሻዋለሁ ፍቅረ ማርያምን እወደዋለሁ ሰይፈ ሚካኤልን
እለመነዋለሁ ተክለ ማርያምም አይነቀልብኝ ብላ ስትለመን
ስትማልድ ፍቅሯ ጸናብኝ ! ፍቅሯን ያሳድርባችሁ!
(ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ)

፩ ሃይማኖት
Photo
እኛ ግን እያከበርን እናመሰግናቸዋለን። ይኼን ፎቶ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሰዎች በብዛት እየተቀባበሉት ነው ፎቶውንም ሪፖርተር ላይ የሚሰራ አንድ መደዴ "ጋዜጠኛ" ለፌስቡክ ስላቅና መዘባበቻ ብሎ ያነሳው ፎቶ ነበር፤ ባይሳካለትም። እውነታው ግን ሰውየው የቤተክርስቲያን የጥበቃ ሠራተኛ ሲሆኑ
በፈረቃ ሰአታቸው እየተጠቀሙ ከመንገደኛ ምጽዋት ይሰበስቡና
በሰውኛ ለሚጠብቋት ቤተክርስቲያን ሕንጻ ማደሻ ያስገባሉ። ሙሉ ታሪኩ ባጭሩ ይኼ ነው። ያለ ስማቸው ስም እየሰጠን ቤተ ክርስቲያንን በአቅማቸው የሚረዱትን ባንገፋቸው መልካም ነው፡፡

✝እግዚአብሔርን የሚወድ እና በእግዚአብሔር የሚወደድ #መንፈሳዊ_ሰው ሁልጊዜ ደስተኛ ነው ። በምንም ሁኔታ ይሁን በምንም እግዚአብሔር በእርግጠኝነት እንደሚሰራለት ይሰማዋል በእርሱም ስራ ይደሰታል ። በእርግጥም እግዚአብሔር ሥራውን ባናየውም እንኳ ይሠራል ። ሥራውን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ልናየው እንችላለን በዚህም እንደሰታለን ። ይህን ደስታችንም ማንም አይወስድብንም ። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች የሚደሰቱት በስጦታዎቹ ብቻ ሳይሆን በራሱ በጌታም ነው ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ አባታችን ሆይ ካላቹ በኋላ እመቤታችን
ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው
ስለዚህ መፀለይ የለበትም ለሚሉን ሁሉ፡፡
እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን የተወደደች
እናታችንን እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን እንጠራታለን
እንዲህም እንላለን፦
እመቤታችን ንፅህት ቅድስት ድንግል
(ማቴ1:23) ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2) በመልአኩ በቅድስ
ገብሬል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28) በሀሳብሽ
ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2 ንፅህት )በስጋሽም ድንግል ነሽ
(ማቴ1:23) (ህዝ44:2) ያሸናፊ የልኡል እግዚአብሔር እናት ሆይ
(ሉቃ1:35)ሰላምታ ላንች ይገባሻል ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ
አንች የተባረክሽ ነሽ (ሉቃ1:28 ናሉቃ1:32) የማህፀንሽ ፍሬ
የተባረከ ነው (ሉቃ1:32) ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ
ይበልሽ ልኡል እግዚአብሄር ካንች ጋር ነውና(ሉቃ1:28-30)
ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን ከመዳህኒታችን ከኢየሱስ
ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን በ1ቆሮ5:20 በፅድቅ
ስራ የኖሩት ይለምኑ ዘንድ ተሰጥቷቸዋልናሃጢአታችንም
ያስተሰርይ ዘንድ ለዘላለሙ አሜን።
እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን ሊተቹ የሚነሱትን
እግዚአብሄር ልቦና ይስጣቸው፡፡
ኦርቶዶክስ መልሥ አላት
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመሥቀሉ ክቡር
ለሌሎች ሼር ማድረጎን አይዘንጉ

ታቦትና ኢየሱስ ክርስቶስ
@And_Haymanot
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታቦታት ላይ የተጻፈው ምንድር ነው? ተብለው ቢጠየቁ መልስዎ ምን ይሆን? ‹ዐሥርቱ ትእዛዛት ተጽፈዋል› ካሉ መልስዎ ትክክል አይደለም፡፡ ትክክለኛውን መልስ ከመመልከታችን በፊት ጥቂት ነገሮች ስለ ታቦት እንመልከት፡፡ ብዙ ጊዜ ስለ ታቦት አስፈላጊነት በሚሠጡ ማብራሪያዎች ላይ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው ስለ ብሉይ ኪዳን ታቦት የሚናገሩ ጥቅሶችን በመጥቀስ በመሆኑ ምክንያት ስለ ታቦት የሚነሡ ጥያቄዎች እንዳያቋርጡ ያደረገ ይመስላል፡፡ ስለዚህ በዚህች አጭር ጽሑፍ ‹ነገርን ከሥሩ› የሚለውን አካሔድ ሳንከተል በቀጥታ ስለ ሐዲስ ኪዳን ታቦት ብቻ እንመለከታለን፡፡
ታቦት በሐዲስ ኪዳን ለምን ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጌታችን በመጨረሻዋ ምሽት ሐሙስ ምሥጢረ ቁርባንን ባስተማረ ጊዜ ያደረገውን እናስታውስ፡፡ ጌታችን ሐዋርያቱ በተሰበሰቡበት ‹‹እንጀራውን አንሥቶ ባረከ ቆርሶም ሠጣቸው እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው አለ፡፡ ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነ እንካችሁ ጠጡ ይህ ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው አለ›› (ማቴ. 26፡26) ጌታችን አስቀድሞ ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ብሎ በትምህርት የመሠረተውን ምሥጢረ ቁርባን በተግባር ለሐዋርያቱ በዚህ መልኩ አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ. 6፡56) ሐዋርያቱም ከጌታችን ዕርገት በኋላ ወንጌልን እየሰበኩ ‹‹እንጀራውን በመቁረስ ይተጉ ነበር›› (ሐዋ.2፡42) ቅዱስ ጳውሎስም ‹‹ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ ደግሞ አሳልፌ ሠጥቻችኋለሁ›› በማለት ሥጋ ወደሙን እንዴት መቀበል እንደሚገባና ‹ሳይገባው የሚቀበል የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ›› እንዳለበት በማስተማር የቁርባንን ሥርዓት ደነገገ፡፡ (1ቆሮ. 11፡23-30)
@And_Haymanot
ልብ እንበል የክርስቶስ ሥጋና ደም መሠጠቱን የሚያምን አንድ ክርስቲያን ይህ የከበረ ሥጋና ደም እንደ ተራ ማዕድ በየቦታው ፣ በየጠረጴዛው ሊቀርብ ይችላል ብሎ ለማሰብ እጅግ ይከብደዋል፡፡ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ዘመነ ሰማዕታት አልፎ ስደትዋ እስካበቃበት ዘመን ድረስ በሒደት እየተሻሻለ በመጣ የቤተ መቅደስ ሥርዓት የሐዲስ ኪዳኑን መሥዋዕት በክብር ለመሠዋትና ለምእመናን ለማቀበል በቅታለች፡፡ የበግና የፍየል ደም ይሠዋ በነበረበት የኦሪት ዘመን እንኳን ለብቻው ትልቅ መሠዊያ ተዘጋጅቶ ፣ መሠዊያው ተቀድሶ ሰው በማይገባበት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በክብር ተቀምጦ ነበር፡፡ በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉት አሮንና ልጆቹም የተለየ ልብስ ለብሰው የበጉን ደም በመሠዊያው ዙሪያ ባለው ቀርነ ምሥዋዕ (የመሠዊያ ቀንድ) ላይ እየቀቡ ሥርዓቱን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ለበግና ለፍየል መሥዋዕት ይህ ሁሉ ክብር ከተሠጠ እንደ በግ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበው የእግዚአብሔር በግ ፣ እንደ ሊቀ ካህናትነቱ እጁን በመስቀል ላይ ዘርግቶ የተሠዋውና ሥጋና ደሙን እንካችሁ ብሉ ብሎ የሠጠን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርብበት መሠዊያ ምንኛ የከበረ ይሆን?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሥጋ ወደሙ ‹መሠዊያ› የምትለው ታቦት በቅርጽም ፣ በአገልግሎትም ፣ በክብርም በኦሪት እግዚአብሔር ለሙሴ ከሠጠው ታቦት ጋር አንድ አይደለም፡፡ የቀደመው ታቦት በአራት ካህናት የሚያዝ በውስጡ ጽላት የሚቀመጥበት ሲሆን የአሁኑ ታቦት ግን የጽላት ቅርጽ ያለው ጽሌ (ሰሌዳ) ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሐዲስ ኪዳኑን ታቦት በሦስት ስያሜ ትጠራዋለች - የቃልኪዳኑ ታቦት ፣ ጽላት እና መሠዊያ ብላ፡፡ የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር ስላደረገው ስለ ቀድሞ ቃልኪዳን ሳይሆን ‹‹ሥጋዬን የሚበላ ደሜን የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው›› ተብሎ ስለተሠጠው እና ‹‹ስለብዙዎች የኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰው የሐዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› ብሎ ጌታችን ስለ ሠጠን አዲሱ ኪዳን ነው፡፡ (ማቴ. 26፡26-30) የቃልኪዳኑ ታቦት የሚባለው በሥጋ ወደሙ ስለተሠጠን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ታቦት መባሉ ደግሞ እግዚአብሔር በረድኤት የሚያድርበት ፣ በሥጋ ወደሙ ደግሞ በአካል የሚገለጥበት ዙፋን ስለሆነ ነው፡፡
ጽላት (ሰሌዳ) የሚባለው ዐሠርቱ ትእዛዛት ተጽፈውበት አይደለም፡፡ የሕግ ሁሉ ፈጻሚ የሆነው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የከበረ ስሙ በታቦቱ ላይ ስለተጻፈ ነው፡፡ (ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን /ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ/ ፣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ/)
አንዳንድ ሰዎች ‹‹የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከኦሪቱ ጋር አይመሳሰልም!›› ብለው እንደ ትልቅ መከራከሪያ ሲያውጁ ማየት እጅግ ያስገርማል፡፡ አንዴ ‹ኦሪታዊት ነሽ› አንድ ጊዜ ደግሞ ‹‹ለምን እንደ ኦሪቱ አልሆንሽም›› ብሎ ንትርክ ግራ ያጋባል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ "የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው ከእንግዲህ አይሹትም ፣ አይደረግምም" የሚለውን በመጥቀስ የሐዲስ ኪዳነ ታቦትን ይቃወማሉ። ቃሉ የተነገረው ለእስራኤል ቤት ሲሆን እስራኤላውያን በእርግጥም የቃልኪዳኑ ታቦት ብለው አይሹትም። በኦሪት ከእስራኤል ጋር ያደረገው ቃልኪዳን በአዲስ ኪዳን ተተክቷል። ይህ ከሐዲስ ኪዳን መሠዊያ ጋር የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ "አዎ እስራኤል አይሹትም" ብለን እንመልሳለን።
የአሁኑ ታቦት የኦሪቱን ያልመሰለው አሁን ያለነው ሐዲስ ኪዳን ላይ ስለሆነና የታቦቱ አገልግሎት የተለየ ስለሆነ ነው፡፡ የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት ከቀድሞው አንድ ታቦት ተለይቶ በቁጥር የበዛውም ለብዙዎች መድረስ ያለበት የክርስቶስ ሥጋና ደም የሚፈተትበት መሠዊያ ስለሆነ ነው፡፡ መድኃኒት ቤት የሚበዛው መድኃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ሲበዙም አይደል? ታቦት የበዛው በታቦቱ የሚሠዋው መሥዋዕት ለብዙዎች ስለ ኃጢአት ይቅርታ የሚፈስሰውና ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻው ያለሱ ሕይወት የላችሁም የተባልነው ሥጋና ደሙ ለኃጢአት በሽተኞች ስለሚያስፈልገን ነው::
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እንዲህ ሲሉ ያብራራሉ ‹‹የኦሪት ጽላት እግዚአብሔር በደመና ተከናንቦ ሙሴንና አሮንን የሚያነጋግርበት ለእስራኤል ብቻ በረድኤት የሚገለጥበት ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ግን (የሐዲስ ኪዳኑ ታቦት) የአምላክ ሥጋና ደም የሚፈተትበት (ጌታችን) ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው ሥጋዬን ብሉ ደሜን ጠጡ እያለ ያመኑትን የሚጠራበት የምሕረት ምሥዋዕ (መሠዊያ) ነው፡፡ ክብርና ስግደትም የሚደረግለት ለዚህ ነው፡፡›› (የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ 109)
በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት በታቦታቱ ሁሉ ላይ የተጻፈው ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚለው የመድኃኔዓለም ክርስቶስ ስም ነው፡፡ ከስሙ ጋር ደግሞ በሁሉም ታቦታት ላይ የሚከተለው ጥቅስ በግእዝ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ከመ ለስሙ ለኢየሱስ ክርስቶስ ይስግድ ኲሉ ብርክ ዘበሰማያት ወዘበምድር›› ‹‹ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ›› የሚል ነው፡፡ (ፊልጵ. 2፡10) በታቦቱ ፊት የሚሰግድ ሰው ለምን እንደሚሰግድ በታቦቱ ላይ የሚጻፈው ይህ ጥቅስ ያስረዳናል፡፡ ምክንያቱ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ስም ይሰግዱ ዘንድ›› ስለሚገባ ነው፡፡ የክርስቶስ ሥጋ እንደሚቆረስ ደሙ እንደሚፈስስ የሚያምን ሰው በዚህ መሠዊያ ፊት በፍርሃት ለክርስቶስ ይሰግዳል፡፡ ሥጋ ወደሙን ‹‹ተራ መታሰቢያ ብቻ ነው›› የሚል ሰው ግን በመሠዊያው ፊት እንዲሰግድና መሠዊያውን እንዲያ

ከብር አንጠብቅም፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በታቦቷ ጽፋ ክብር የምትሠጥ የሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስለሆንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡
የታቦቱ ሌላ መጠሪያ የመሠዊያ ታቦት (ታቦተ ምሥዋዕ) የሚል ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ መሠዊያ ‹‹መሠዊያ አለን በድንኳኒቱ የሚያገለግሉ ከእርሱ ሊበሉ መብት የላቸውም›› በማለት ስለ ሐዲስ ኪዳኑ መሠዊያ ይነግረናል፡፡ (ዕብ. 13፡10) ይህ መሠዊያ በኦሪት ድንኳን የሚያገለግሉ የአሮን ልጆች ከእርሱ ሊበሉ መብት የሌላቸው ለእኛ ክርስቲያኖች ብቻ በመሠዊያው ያለውን ሥጋና ደም እንድንበላ የተሠጠን ታቦተ ምሥዋዕ (Christian Alter) ነው፡፡
@And_Haymanot
የታቦትን የሐዲስ ኪዳን አገልግሎት ስንናገር የሚቃወሙ ሰዎች ከሚያነሡት ተደጋጋሚ ትችት ‹‹አንዱ ታቦት ያላት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት›› የሚል ነጥሎ የመምታት ጥረት ነው፡፡ በተለይም የግብፅ ቤተ ክርስቲያንን በመጥቀስ ‹‹ግብፆች ታቦት የላቸውም›› የሚል ንግግር ይዘወተራል፡፡ ለዚህ ጉዳይ እኛ መልስ ከምንሠጥ የራሳቸው የግብፃውያንን ምላሽ ብቻ ማስቀመጥ ይቀልለናል፡፡ ግብፃውያን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ጋር አቻ የሆኑ ሁለት ንዋያተ ቅድሳት አሏት፡፡ አንደኛው የመሠዊያው ጽላት (ሰሌዳ) /Alter Board/ ሲሆን ሁለተኛው ታቦት /Ark/ ነው፡፡
ቄስ ታድሮስ ማላቲ የተባሉት የቤተ ክርስቲያኒቱ እውቅ ጸሐፊ ‹‹Church The House of God›› በተሰኘው መጽሐፋቸው ላይ ስለ የመሠዊያው ሠሌዳ (Alter Board) አሠራር ሲናገሩ ‹‹ይህ የመሠዊያ ጽላት አንድ መስቀል ወይም ብዙ መስቀሎች ይሳሉበታል ፤ አልፋና ኦሜጋ ተብሎ ይጻፍበታል ፤ ከዚያም መዝ. 86፡1 ላይ ያለው መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው የሚለው የመዝሙረ ዳዊት ቃል ይጻፍበታል፡፡›› ይሉና ስለ አሠራሩ ሲናገሩ ‹‹የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መሠዊያው ስለሚሠራበት ቁስ የተደነገገ ሕግ የላትም ፤ እስከ አራተኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ከእንጨት ብቻ ይሠራ ነበር፡፡ ከዕብነ በረድና ከድንጋይም ሊቀረጽ ይችላል፡፡›› ይህንን ካሉ በኋላም እግረ መንገዳቸውን ስለ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታቦተ ምሥዋዕ ሲናገሩ ‹‹ከእንጨት የሚሠራ ታቦተ ምሥዋዕ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መሥጠቱን ቀጥሏል›› (Wooden Alters continue in use in the Ethiopian Church at the present time) ብለው ያጠቃልላሉ፡፡
ይህ ስለ መሠዊያ እንጂ ስለ ታቦት አይናገርም፡፡ ስለ ታቦት ደግሞ እኚሁ ጸሐፊና በቤተ ክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ ድረ ገጾች ላይ የሚከተለው ተጽፎአል፡፡ ‹‹In the middle of the Alter, there is a wooden box, called in Coptic 'pi totc' which means 'a seat' or 'a throne', and is used as a Chalice-Stand. Usually it is cubicle in shape, about thirty centimetres high and twenty-five centimetres wide, the top is closed with high flaps. The beautiful carving is inlaid with ebony and ivory and is decorated with four small icons. It can be only the Lord in the last supper, St Mary, Archangel Michael, St. Mark and then the patron Saints.
It is called 'the Throne' for it represents the presence of the Crucified Lord. Its name also corresponds to the 'Ark of the Old Testament', for it contained the Tablets of Law written with the finger of God to declare God's covenant with man. The new Ark now contains the true Blood of Christ, as the New covenant, that fulfils the Law and the prophets.›› (‹‹ከመሠዊያው መካከል የሚቀመጥ የእንጨት ሳጥን ሲኖር ይህ በኮፕት ቲቶት ተብሎ የሚሠራ ሲሆን ትርጉሙም ‹መንበር› ወይም ዙፋን ማለት ነው፡፡ ጽዋው የሚቆመውም በዚህ ላይ ነው፡፡ ቅርጹ ክበባዊ ሲሆን 13/25 ሴንቲሜትር ነው፡፡ ከላይ በጨርቅ ይሸፈናል፡፡ በጥቁርና ነጭ ኽብረ ቀለማት ያጌጠ ሲሆን አራት ሥዕላት በዙሪያው ይደረጋሉ፡፡ ሥዕላቱ የጌታችን ጸሎተ ሐሙስ ሥዕል የእመቤታችን ፣ የቅዱስ ሚካኤልና የሚታሰበው ቅዱስ ሥዕላት ናቸው፡፡
@And_Haymanot
‹ዙፋን› ተብሎ የሚጠራው የተሰቀለው ጌታ እንደሚያድርበት በማሰብ ነው፡፡ ይህ ስያሜም ‹ከብሉይ ኪዳኑ ታቦት› ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡ ያ ታቦት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን የተጻፈባቸው የሕግ ጽላት ያሉበት ነበር፡፡ አሁን ያለው አዲሱ ታቦት ግን እውነተኛውን የክርስቶስ ደም የያዘ ሲሆን ክርስቶስም ሕግንና ነቢያትን ፈጽሞ አዲሱን ኪዳን የሠጠን ነው፡፡››) http://www.stmarkdc.org/coptic-sanctuary ይህ ማብራሪያ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን ታቦት ከሠጡት ማብራሪያ ጋር ምንም አይለያይም፡፡ ይህን እንደ ማሳያ ጠቀስን እንጂ ታቦቱ ዑደት ባለማድረጉ እና በሥርዓቱ ይለያያል እንጂ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሥጋ ወደሙ መሠዊያ ነው ብላ ከምታከብረው ታቦት ጋር በክብርና በአገልግሎት አቻ የሆኑ በቅብዐ ሜሮን የሚከብሩና በመንበር የሚቀመጡ ንዋያተ ቅድሳት በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡
ባለንበት ዘመን በሥጋ ወደሙ እውነተኛነት ከማያምኑ ሰዎች ጋር ስለ መሠዊያው አስፈላጊነት በመከራከር ብዙ ጊዜ ሲባክን ይታያል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተጻፈበትን ታቦት ‹ጣዖት› ነው የሚሉ ‹ክርስቲያኖች› እያየን እንደነቃለን፡፡ ‹‹ጉልበት ሁሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይንበርከክ›› ተብሎ የተጻፈበት ‹ጣዖት› እንዴት ይኖራል? ‹‹አልፋና ኦሜጋ›› የሚል ጣዖት አለ? ወንጌል በላዩ ላይ የተቀመጠበት ፣ በቅብዐ ሜሮን የከበረ ፣ ሥጋ ወደሙ የሚፈተትበት ታቦት እንዴት ጣዖት ተብሎ ይጠራል? አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ተብሎ በሥላሴ ስም የሚቀደስበትን ታቦት ባዕድ አምልኮ ለማለት መድፈር እንዴት ያስደነግጣል፡፡
@And_Haymanot
አንዳንዶች ‹ታቦት ተሰርቆ ተሸጠ› የሚሉ ዜናዎችን በማራገብ ታቦቱ ኃይል የለውም ሊሉን ይሞክራሉ፡፡ እንኳን የክርስቶስ ስም የተጻፈበት ታቦት ቀርቶ ራሱ ክርስቶስ በሠላሳ ብር ተሸጦ ከሊቶስጥራ እስከ ቀራንዮ እየተተፋበት ፣ እየተደበደበ ተጎትቶ ተሰቅሎ የለምን? ክብር ይግባውና ኃይል የለውም ሊባል ይችላል? ‹‹ታቦቱን ገልጠን እናሳያለን›› ብለው እየፎከሩ ቤተ ክርስቲያንን ያዋረዱ የሚመስላቸው ፣ በታቦቱ እግዚአብሔርን የምታመልከውን ቤተ ክርስቲያን ታቦት ታመልካለች ብለው ያላለችውን በግድ ብላለች ብለው ድርቅ የሚሉ ሰዎች ስናይ ከማዘን ውጪ ምን እንላለን? ቤተ ክርስቲያን ታቦትን የምትሸፍነው ስለሚሠዋበት የጌታችን ሥጋና ደም ክብር እንጂ ቢገለጥ የምታፍርበት ነገር ኖሮ አይደለም፡፡ ቢገለጥ የሚታየው የመድኃኔዓለም ክርስቶስና የቅዱሳኑ ስም ነው፡፡ ጌታዋ ዕርቃኑን በመሰቀሉ ያላፈረች ቤተ ክርስቲያን ስሙ በተጻፈበት ታቦት አታፍርም!

ታቦተ ጽዮን
@And_Haymanot
✞ የእግዚአብሔር ታቦት የገባበት ስፍራ ቅዱስ ነው 2ኛ ዜና 8፥11 ✞
✍ መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች ጥንታውያን መዛግብት እንደሚሉት የቃል ኪዳኑ ታቦት በሚንቀለቀል ብርሃኑና እሳቱ በነቀርሳማ እባጭና በለምጽ የመምታት፣ የማቃጠል፣ ተራሮችን ወደሜዳማነት የመለወጥ፣ ወንዞችን የማድረቅ፣ ታላላቅ ሠራዊቶችን የመደምሰስ፣ ከተማዎችን የማፈራረስ ኃይል አለው።
✔ እነዚህ ምንጮች አክለውም ታቦተ ህጉ የአይሁዶች የእምነት መሰረት እንደሆነና ንጉሥ ሰሎሞንም የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ያሰራው ይህንኑ ታቦት በክብር ለማኖር አስቦ እንደሆነ ይገልጻሉ ይሁንና ከክርስቶስ ልደት በፊት ከአንድ ሺህና ስድስት መቶ አመታት መካከል በነበረው ጊዜ ይህ እጅግ ድንቅና ተአምራዊ ታቦት የትና ወዴት እንደሄደ ሳይታወቅ በመሰወሩ ጉዳዩ ለብዙ ሺህ ዓመታት እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቷል ማስረጃዎች እንደሚጠቁሙት በ587 ዓመተ ዓለም የናቡከደነጾር ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ባቃጠላት ጊዜ ታቦቱ በቦታው አልነበረም በጦርነቱ የተማረኩ እስራኤላውያን ከባቢሎን ወደሀገራቸው ኢየሩሳሌም በ538 ዓመተ ዓለም ተመልሰው ሁለተኛውን ቤተ መቅደስም በሠሩበት ወቅትም ታቦቱ በዚያ አልነበረም ይህም ቀደም ሲል ታቦቱ በባቢሎናውያን አለመዘረፉን ያረጋግጣል።
♦ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቻርድ ኤሊየት ፍሬድማን በ1987 ይህን ጉዳይ አስመልክተው ሲጽፉ "የታቦቱ መጥፋት ከመጽሐፍ ቅዱስ አስደናቂ ምሥጢሮች እንደ አንዱ ይቆጠራል" ብለዋል።
❖ "ታቦቱ ወደሌላ ቦታ ስለመወሰዱ፣ ስለመውደሙ (መቃጠሉ) ወይም መደበቁ የተጻፈ ነገር የለም ከዚህ በኃላ ታቦቱ ጠፋ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለም አናውቅም ወይም የት እንዳለ ማንም አያውቅም የሚሉ አስተያየቶች እንኳን አልተጻፉም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዓለም ካሉ ነገሮች ሁሉ ትልቅ ሥፍራ የተሰጠው ክቡር ዕቃ፣ እንደዋዛ ይጠፋል"። [ ግራሃም ሐንኩክ፦ "The sign and the Seal" ወይም "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ" ገጽ 4 ትርጉም፦በጌታቸው ተስፋዬ ጎጂ]
☞ #የታቦተ_ጽዮን_መኖሪያ_ኢትዮጵያ
✍ ታቦተ ጽዮንን ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ይዞ የመጣው ልዑል ምኒልክ ይባላል ምኒልክ ማለት "የብልህ ሰው ልጅ" ማለት ነው እናቱ ንግስተ ሳባ የጠቢቡ ሰሎሞንን ጥበብ ለማየት ወደ ኢየሩሳሌም በሄደችበት ወቅት ኢየሩሳሌም ውስጥ ከጠቢቡ ሰሎሞን ብትፀንሰውም ማርገዟን እንዳወቀች ወደሀገሯ ተመልሳ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የወለደችው ሃያ ዓመቱ ሲሞላ ምኒልክ ከኢትዮጵያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ከአባቱ ቤተ መንግስት እንደደረሰም የክብር አቀባበል ተደረገለት ይሁንና ለአንድ አመት ያህል ከቆየ በኃላ የእስራኤል ታላላቅ ሰዎች ንጉሱ ሰሎሞን ምኒልክን ከእኛ የበለጠ ያቀርበዋል፣ ይወደዋል በሚል በምቀኝነት ተነሳሱበት ወደሀገሩ ይመለስ ዘንድም አጥብቀው ጠየቁ ንጉሱ ሰሎሞንም የቀረበለትን አቤቱታ ካዳመጠ በኃላ ምኒልክ ወደሀገሩ የሚመለሰው የእስራኤል ታላላቅ ሰዎች የበኩር ልጆች ሁሉ በአጃቢነት አብረውት ወደ ኢትዮጵያ የሚሄዱ ከሆነ ብቻ መሆኑን ገለጸላቸው።
❖ በዚህም ተስማሙ ከነዚህም መካከል ከምኒልክ ጋር አብረውት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት መካከል የሊቀ ካህናቱ ሳዶቅ የበኩር ልጅ አዛርያስም ይገኝበታል የቃል ኪዳኑን ታቦት ከቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ደብቆ ያወጣውም እርሱ ነበር ምኒልክ ታቦቱ በድብቅ ወጥቶ ከእርሱ ጋር መምጣቱን ያወቀው ከኢየሩሳሌም ብዙ ርቆ ከተጓዘ በኃላ ነበር ስለሁኔታውም እንደነገሩት ድርጊቱ የተፈጸመው በእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ተገንዝቦ ታቦተ ህጉ ከእነርሱ ጋር መሆን እንዳለበት አምኖ ተቀበለ በዚህ ሁኔታ ነበር ታቦተ ህጉ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው።
✍ በአጠቃላይ ስለ ታቦተ ጽዮን አስር ዓመታት የፈጀ ምርምርና ጥናት በማድረግ የሚታወቀው ግራሃም ሐንኩክ የተባለ እንግሊዛዊ ጸሐፊ "The sign and the Seal" ወይም "ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ" በሚለው መጽሐፉ ገጽ 245 ላይ የታቦተ ጽዮን መኖሪያ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መሆኗን አክሱም ጽዮን ቤተ መቅደስ ሆኖ ሲመሰክር፦ "...ከሲና ተራራ ግርጌ በወርቅ የተሰራው፥ በበረሃ የተጓዘውና የዮርዳኖስን ወንዝ የተሻገረው፥ ወደ ተስፊዪቱ ምድር ለመግባት እስራኤላውያን ያደረጉትን ትግል በድል ያጠናቀቀላቸው፥ በንጉሥ ዳዊት ዘመነ መንግስት ወደ እስራኤል የተወሰደው፥ በ955 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ አካባቢ በንጉሥ ሰሎሞን በተሰራው ቤተ መቅደስ ተቀምጦ የነበረው ይህ የቃል ኪዳን ታቦት ነው..." በማለት ነበር የደመደመው።
☞ ማሳሰቢያ፦ ከላይ የተጠቀሱት የዘመን አቆጣጠር በሙሉ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ነው።
✞ የእናታችን የአክሱም ጽዮን ረድኤት፣ በረከትንና ምልጃ አይለየን!!!! አሜን!!! ✞
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
ከወቅታዊ መረጃ ጋር
የሚቀርቡበት፡፡
°ለተሃድሶዎች መልስ የሚሰጥበት°
👉"፩ ሃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡

ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እውነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፣ እውነተኛ ትህትናስ ትሩፋት መስራት ነው፡፡
🍃ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🍃
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ
🍃ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🍃
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ
ኢየሱስ_ከአዳም_ዘር_ዉጪ_ነዉ_የተወለደዉ!_ለፓስተር_ዳዊት_ድፍረትና_ስህተት_የተሰጠ_ምላሽ_@And_Haymanot.mkv
55.9 MB
"ኢየሱስ ከአዳም ዘር ዉጪ ነዉ የተወለደዉ!" ለፓስተር ዳዊት ድፍረትና ስህተት የተሰጠ ምላሽ
@And_Haymanot
@And_Haymanot
ውርጃ
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስተምሮ
@And_Haymanot
ምድሪቱ (የሴቲቱ ማኅፀን) ዘር ከዘራንባት በኃላ ፍሬ እንዳታፈራ የምናደርገው ስለ ምንድን ነው? ውርጃን የምናካሒደው ስለ ምንድን ነው? እናንተ ዘማውያን ሆይ! ዝሙት መፈጸማችሁ ሳይበቃ ሰውን መግደል ትጨምሩበታላችሁን? እንግዲህ ስካር እንደ ምን ሴተኛ አዳሪን እንደሚያደርግ፣ ሴተኛ አዳሪነትም ዘማዊ፣ ዝሙትም እንደ ምን ነፍሰ ገዳይ እንደሚያደርግ ታስተውላላችሁን?
ይህን ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ምክንያቱም ይህን ሕፃን ከተወለደ በኃላ ከቤት አስወጥተን አይደለም ያባረርነው፤ እንዳይወለድ ከለከልነው እንጂ ወዮ! ስለምን የእግዚአብሔርን ስጦታ ታቃልላላችሁ? ስለምን ሕጉን ትተላለፋላችሁ? ስለምን ርጉም የሆነን ግብር እንደ በረከት ትቆጥሩታላችሁ? ስለምን እግዚአብሔር ሰውን ለመፍጠር ያዘጋጀውን መንገድ መግደያ ታደርጉታላችሁ? ስለምን ልጅን አቅፋ እንድትስም የተፈጠረችውን ሴት ነፍሰ ገዳይ እንድትሆን ታደርጓታላችሁ? እህቴ ሆይ! ፍቅረ ንዋይ ዐይንሽን አሳውሮት፣ ዳግመኛም በፍትወት ከሚመስሉሽ ጋር ዝሙትን ለመሥራት ስትዪ ፍምን በራስሽ ላይ አታከማቺ ወንድሜ ሆይ! ምንም እንኳን ይህን አሰቃቂ ግድያ የምትፈጽመው እርሷ ብትሆንም አንተም ከእርሷ ጋር ተባባሪ ነህ። ✞
ምንጭ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችው በገብረ እግዚአብሔር ኪደ ገፅ 53

#ወዳጄ ሆይ!!!
⛪የሚታገል ሰው ቢወድቅ አዲስ ነገር አይደለም፤ ወድቆ መቅረቱ ነው እንጂ፡፡ አንድ ቦክስ የሚጋጠም ሰውም ቢቆስል የሚያሳዝን ነገር አይደለም፤ የሚያሳዝነው ቁስሉን ችላ ያለው እንደ ኾነ ነው እንጂ፡፡ አንተም በመንፈሳዊ ሕይወትህ ብትወድቅ አይደንቅም፤ ለቅጽበትም የማይተኛልህ ጠላት አለህና፡፡ ነገር ግን ወድቀህ አትቅር፡፡
@And_Haynanot
🔔 አንድ ወታደር ጦር ሜዳ ሔዶ ቢቆስል ማንም ጤነኛ አእምሮ ያለው ሰው አይወቅሰውም፡፡ አንተም ጠላትህ ዲያብሎስ ቢያቆስልህ ማንም አይወቅስህም፡፡ መንፈሳዊ ተጋድሎ ውስጥ ነውና ያለኸው፡፡ የምትወቀሰው ለቁስልህ መድኃኒት ማድረግህን ችላ ያልህ እንደ ኾነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ከላይ የነገርኩህ ወታደር ከታከመ፥ ተመልሶ ወደ ጦር ሜዳ ይሔዳል፡፡ ጠላቱን ድል ሲያደርግም ሹመት ሽልማት ይሰጡታል፡፡ አንተም ከወደቅህበት ተነሥና ንስሐ የተባለ ሕክምናን ውሰድ፡፡ ከዚያም ጠላትህ ዲያብሎስን ድል አድርገህ ከክርስቶስ ዘንድ ሹመት ሽልማትን ተቀበል፡፡ ስለዚህ በርታ፡፡ በርታና ተነሥ ዘግይቻለሁ ብለህ በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ፤ አሁንም መጀመር ትችላለህና፡፡
✍ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
#ይህ ጽሑፍ ለሌሎች እህት ወንድሞቻችን እንዲደርስ👉 Share ያድርጉ...
✥┈┈ • ┈┈•┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈ • ┈┈┈••✥

ዋሽንት
በቤተክርስቲያን የምን ምሳሌ ነው❓
በቤተክርስቲያን የምን ምሳሌ ነው❓
Anonymous Quiz
40%
ሀ, የወንጌል ምሳሌ
22%
ለ, የኪዳነ ኖህ ምሳሌ
14%
ሐ, የሀይማኖት ምሳሌ
24%
መ, የእመቤታችን ምሳሌ
በብሉይ ኪዳን የመጀመሪያዋ የሴት ዘማርያት ምሳሌ ናት❓
Anonymous Quiz
17%
ሀ, ሣራ
21%
ለ, ራሄል
15%
ሐ, ማርያም እህተ አልአዛር
47%
መ, ማርያም እህተ ሙሴ
በቅዱሳን ሥዕላት አመጣጥ ታሪክ የመጀመሪያው ሥዕል ምንድን ነዉ❓
Anonymous Quiz
36%
ሀ, የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
19%
ለ, የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
23%
ሐ, የአዳም ና የሄዋን
22%
መ, የኪሩቤል
+ ኢየሱስ ሆይ ከሀገራችን ሒድልን +
ሰዎች ኢየሱስን በብዙ ምክንያት ለምነውታል:: "ማረኝ" "ዓይኔን አብራልኝ" "ልጄን ፈውስልኝ" "ሙት አስነሣልኝ" ብለው የጮኹ ብዙዎች ናቸው:: የጌርጌሴኖን ሰዎች ግን ጌታን በአንድ ላይ ተሰብስበው "ከሀገራቸው እንዲሔድላቸው ለመኑት" ማቴ. 8:34
"ኢየሱስ ሆይ ውጣልን ! : ኢየሱስ ሆይ ሒድልን : ኢየሱስ ሆይ አትድረስብን : ኢየሱስ ሆይ አትምጣብን ! " የሚል ድምፅ እያሰሙ ተረባረቡበት::
ውጣልን ያሰኛቸው ሁለት ጋኔን የያዛቸውን ሰዎች ከላያቸው አጋንንቱን አውጥቶ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡ በፈቀደ ጊዜ አጋንንቱ አሳማዎቹን ወደ ገደል እንዲገቡ ስላደረጉ ነበር:: ጌታችን አጋንንቱ ወደ አሳማ መንጋ እንዲገቡና ገደልም እንዲሰዱአቸው በመተዉ ትልቅ መልእክትን ለሰው ልጅ አስተላልፎ ነበር:: አጋንንቱ ወደ አሳማው ከመሔዳቸው በፊት ሁለት ሰዎች ላይ
ነበሩ:: እነዚያን ሰዎች ላይ ቢቆዩም ግን ሰዎቹን ወደ ገደል አልከተቱአቸውም:: ልክ አሳማዎቹ ላይ እንደሰፈሩ ግን ወደ ገደል ጨመሩአቸው:: ክርስቶስ በዚህ ያስረዳን "እኔ በቸርነቴ ባልከለክለው ሰይጣን በእያንዳንዳችሁ ላይ ያለው ዕቅድ በቅጽበት ወደ ገደል እስከ መጨመር የጨከነ ነው" የሚል
ነው:: ሰዎቹን ገደል እንዳይሰድ የከለከለው እሱ ነበር:: ዛሬም
እኛን ከአፋፉ ላይ ሆነን ወደ ገደል ያልወረድነው "ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው" በተጨማሪም ሰይጣንም እንኳን በሰው ልጅ ላይ ቀርቶ በአሳማ ላይ እንኳን እንደፈለገ የመስፈር ሥልጣን እንደሌለውም በዚህ ታሪክ ተረዳን::
የጌርጌሴኖን ሰዎች ግማሾቹ ጌታችንን ስለኃይሉ በትሕትና ፈርተውት ግማሾቹ ደግሞ በአሳማዎቹ መሞት ተበሳጭተው
ክርስቶስን ውጣልን አሉት:: ክርስቶስ የሰው ልጅ ከሚሰቃይ ጊዜያዊው ንብረት ቢጠፋ ይሻላል ብሎ ቅድሚያ ሲሠጥ ሰዎቹ ደግሞ ንብረታችን ከሚወድም ሁለቱ ሰዎች ጋኔን ቢጫወትባቸው
እንመርጣለን ብለው ውጣልን አሉት::
አሣማ ቆሻሻ እንስሳ ነው:: በግእዝ ሕሱም ሐሳማ ማለት አስቀያሚ ማለት ነው:: ቆሻሻ ወዳዱ ሰይጣን ወደ ማደሪያው ገብቶ ሕዝቡንም በጌታ ላይ አሳመፀ:: ሕዝቡም ኢየሱስ ሆይ
ሒድልን አሉት:: ጌታ ሆይ ከእኛ ጋር እደር ጌታ ሆይ ቶሎ ና ተብሎ ለሚዘመርለት
ጌታ ሒድልንን አዜሙለት:: አፍ አውጥተን አንበለው እንጂ እኛም ጌታችንን ብዙ ጊዜ "ሒድልን" ብለነው እናውቃለን:: ወዳጄ አንተስ “ክርስትና በአፍንጫዬ ይውጣ" ብለህ አታውቅም? ያም ባይሆን መንፈሳዊ ነገር ማሰብ ወይም መዝሙር መስማት የማትፈልግበት ቀን ወይም ቃሉን ማዳመጥ የምትሸሽበት ቀን የለም? ዛሬስ ይቅርብኝ ብለህ ከልብህ ሀገር
ኢየሱስን እንዲሔድልህ የለመንክበት ቀን : በቂም በቀል ልብህ ቆስሎ አኩርፈህ የይቅር ባዩን ጌታ ስሙን መስማት የጠላህበት ዕለት የለም?
ነጋዴው ከንግዱ ላይ ኢየሱስ ዘወር ቢልለት አይጠላም:: ኢየሱስ ከመጣ ገደል የሚጨምራቸው ብዙ ቆሻሻ ሥራዎች ያሉበት ሰው ጌታን ከሥራው ቦታ ዞር በልልኝ ይለዋል:: ሌብነት ማሟረት ጥንቆላ ዝሙት ሙስና የሚባሉ አሳማዎችን ገደል እንዳይገቡ ለመንከባከብ ስንል የናዝሬቱን መድኃኒት ዘወር በልልን ብለን የተማጸንን ብዙዎች ነን:: እንደፈለግን ለመኖር ከቆሸሸ አሳማ ጋር ለመዋል መርጠን በሀገራችን ላይ አጋንንት ሲጨፍሩ ሳያስከፋን የጌታችንን
መምጣት ግን ያልፈለግን ብዙዎች ነን:: ከእኛ መካከል እንደ አሳማ የከፋ ልማዱ እና ሱሱ ወደ ጥልቅ እንዳይወረወርበት
ፈርቶ የሚሸሽ ስንት አለ? የጌታችንን ቃል ለመስማት የማንፈልግ መንፈሳዊ ነገር ስንሰማ ጆሮአችንን የምንደፍን "ሒድልን
እባክህ" ብለን የምንለምን ስንቶች ነን::
ጌታ ሆይ ክፋትን መርጠን ከሀገራችን ሒድልን ከቀዬያችን ውጣልን ስላልንህ አትቀየመን:: በሽተኛ ሲነጫነጭ ክፉ
የሚያናግረው በሽታው ነው እንደሚባለው ክፉ የሚያናግረን
ኃጢአታችን ነውና አትቀየመን:: የኃጢአት ፍቅር እንደ አሣማ ፍቅር ከባድ ነው:: ሽታው ቢከረፋም እኛ ግን ለምደነዋልና
በቀላሉ መላቀቅ አቅቶናል:: አንተ ግን ሒድልን ብንልህም አትስማን:: አሳማ ኃጢአታችንን ከሚፈትኑን አጋንንት ጋር ወደ ጥልቁ ጣልልን:: ያን ጊዜ ነቢዩ
የተናገረው ቃል ይፈጸማል:-
"ተመልሶ ይምረናል፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል፥ ኃጢአታችንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል" ሚክ 7:19
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 20 2013 ዓ ም
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ!
#Share
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot