፩ ሃይማኖት
8.98K subscribers
246 photos
29 videos
21 files
96 links
ኦርቶዶክሳዊ ምላሾች
የሚቀርቡበት፡፡
👉"፩ ኃይማኖት"👈
@And_Haymanot
ቤተክርስቲያን ባህረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት
የገሀነም ደጆች አያናውጧትም
✞ እ...ና...ታ...ች...ን
#አ__ት__ታ__ደ__ስ__ም፡፡
@And_Haymanot
ኦርቶዶክስ መልስ አላት፡፡
ለአስተያየት
@And_Haymanot_bot

፩ ሃይማኖት ኤፌ 4፥5
Download Telegram
​​+++ምን ሰጡህ ይሁዳ+++


ሙትን ልታስነሳ ድውይን ልትፈውስ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ
ልታስር ልትፈታ በነፍስም በሥጋ
ሥልጣን ሰጥቶህ ነበር አልፋና ኦሜጋ

ምን ሰጡህ ይሁዳ አይሁድ ወገኖችህ
ለነርሱ አሳልፈህ ጌታህን የሰጠህ
ከሁሉ የሚበልጥ ሥልጣን ሰጥቶህ ሳለ
ብርን ለመቀበል ልብህ ተታለለ

ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ
እንዴት በመቃብር ሶሥት ቀን አደረ
አንተ የሰጠኸው አሳልፈህ ለሞት
ሞትን ድል አድርጎ ተነሳ በሰንበት
1
✟ክርስቶስ ተንስዓ ሙታን✟
✟አብይ ሀይል ወበስልጣን✟
✟አሰሮ ለሰይጣን✟
✟አግአዞ ለአዳም✟
✟ሰላም✟
✟እምይዜየሰ✟
✟ኮነ✟
✟ፍስሀ ወሰላም✟

"ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጉታላችሁ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም"ሉቃ፦24፥5

"እንደተናገረ ተነስቷልና በዚህ የለም የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ" ማቴ፦28፥6

እንኳን አደረሰን መልካም በዓል ለሁላችንም!!!
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ለምን አንጾምም?

ተወዳጆች ሆይ የተሃድሶ መናፍቃን በዓለ ሃምሳን ለምን አትፆሙም ሲሉ ይደመጣሉ ከዛም አልፎ በዓቢይ ጾም የጾማችሁትን ለማካካስ ነው በማለት ይተቻሉ ቅድስት ቤተክርስቲያናችንስ ምን ትላለች?

ጥያቄ:- በበዓለ ሃምሳ ለምን አንጾምም?
በፍትሐ ነገሥት ላይ እንዲህ የሚል ትዕዛዝ አለ፦ "ዳግመኛ በየሳምንቱ ዓርብ እና ረቡዕን መጾም ነው፡፡ በዓለ ሃምሳ፣ የልደት እና የጥምቀት በዓል የተባበሩባቸው ጊዜ ካልሆነ በቀር" /ዐንቀጽ 15:566/።

"የዓርብን እና የረቡዕን ጾም ግን ከልደት፣ ከጥምቀት እና ከበዓለ ሃምሳ በቀር ዘወትር ይጹሙ" /ዐንቀጽ
15:603/። የዐቢይ ጾምን ፍቺ ተከትሎ ለ50 ቀናት የማንጾምበት ምክንያት
ብዙ ጥልቅ ምሥጢር ያለው ሥርዓተ ሃይማኖት ነው። በምሳሌ ለማስረዳትም ፦ ከትንሣኤ በፊት ያለውን አንድ ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ብለን የምናስበው ዘመነ ኦሪት እንደሆነ በማሰብ ነው።
በዚኸ ሳምንት ከሌሎች ድርጊቶች በተጨማሪ መስቀል አንሳለምም። ይኸ የሆነበት ምክንያት በዘመነ ኦሪት መስቀል በክርስቶስ መለኮታዊ ደም ተባርኮ አልተሰጠም'ና ነው። ልክ
እንደዚሁ ከትንሣኤ ዕለት ጀምሮ አስከ በዓለ ጰራቂሊጦስ (አስከ የሐዋርያት ጾም መግቢያ ድረስ) ያሉት 50 ቀናት እንደ አንድ ቀን ነው የሚታዩት። ይህም ማለት ሰው ከትንሣኤ በኃላ ፍጹም
ያለ ድካም እንደሚኖር ለማስተማር ጾም እና የንስሐ ቀኖና አይሰጡም።
@And_Haymanot
@And_Haymanot
​​❝የኪዳነምህረት ተዓምር!❞

ይህ ተዓምር የሆነው በጎፋ መንበረ ጸሐይ ቅድስት ኪዳነምህረት ቤተክርስትያን ነው። ደብሯም ይህቺ በፎቶው ላይ የምታይዋት እጅግ ውቧ ቤተክርስትያን ናት። የሆነውም እንዲህ ነው፦ ይህች የተዋበችው የኪዳነምህረት ቤተክርስትያን የጣሪያ ቆርቆሮዋ ቀለም በጸሐይ ምክንያት ይለቅና ለማየት የሚያምር አልሆነም።
ይሄኔ የደብሯ አገልጋዮች ቀለም ለማስቀባት ወስነው ቀለም እስከ ጉልላቱ ጫፍ ወጥቶ የሚቀባ ባለሞያ ይፈልጋሉ። አንድ ምስኪን ሰው የቀለም ባለሞያ "ደሞ ለጌታዬ እናት
ለኪዳነምህረት......" አለና መቀባት ይጀምራል። እየቀባ ከላይ ከጉልላቱም ይደርሳል። በድንገት ከመሬት እስከ 20 ሜትር (በግምት) ከሚርቀው ጣርያ አንሸራቶት እየተንከባለለ ይወድቃል። ይሄኔ እዚያው ቤተክርስትያን የነበሩ አገልጋዮች እና ጥቂት ምዕመናን ተደናግጠው እየጮሁ ከወደቀበት መጥተው ይመለከቱታል። የለም አይንቀሳቀስ አይናገር አይጋገር። ትንፋሹ
ግን ነበር። ተሸክመውት ወደ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ። ሆስፒታል እንደደረሰ ሃኪሞች ይመረምሩታል። ከሰውየው የተጎዳ ምንም የሰውነት ክፍል ግን አልነበረም። በድንጋጤ ራሱን ስቶ
ብቻ ስለነበር ትንሽ እረፍት አድርጎ ተሸክመውት ከሄዱ አገልጋዮች እና ጥቂት ምዕመናን ጋር በእግሩ እየተራመደ
ተመለሰ። ይህን ያዩ ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ ለኪዳነምህረት ምስጋና እያደረሱ ተመለሱ።
©ንሽኩር ረቢና!
15/08/2012 ዓ.ም (ሐሙስ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
​​ የያረድ ዉብ ዜማ

የያረድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታየ ነሺ / 2/ 
በምን አንደበቴ እንደምን ባለ ቃል ማርያም ልበልሺ/ 2 

ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ 
ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ 
ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሺ 
ድንግል ሆይ እናተ አምሳያም የለሺ 
ማርያም ድንግል እረዳተ 
የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀተ 
ታምርሺን በአይነ አይቻለሁ 
ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ 
አዝ - - - 
የእግዚአብሀር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ 
የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ 
ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሺ 
ነገን ባላውቅ እነም ቢያስፈራኚ 
አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም 
በፊትሺም እንድቆም ለምስጋና 
ማርያም ልበልሽ በትህትና 
አዝ - - - 
ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም 
ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም 
አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር 
ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሺን ይናገር 
ጨለማው ከፊተ ተገፈፈ 
ማርያም በምልጃሽ ልበ አረፈ 
ከጎነ ነይ ስልሺ እጽናናለሁ 
እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ 
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ኃጥእ ነኝ ማለት ብቻ እውነተኛ ትህትና እንዳይደለ በእውነት እናገራለሁ፣ እውነተኛ ትህትናስ ትሩፋት መስራት ነው፡፡
🍃ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ🍃
@And_Haymanot
@AHati_Haymanot
መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።

1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።

ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።

የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።

ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
​​✞ ግንቦት ፩ እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከኢያቄምና ከሐና ስትወለድ የሆነውን ነገር ሐዋርያው ያዕቆብ የጻፈው ጥንታዊ መጽሐፍ ሲገልጽ፡፦
@And_Haymanot
"And Joachim(ኢያቄም) said: Now I know that the Lord has been gracious unto me, and has remitted all my sins . And he went down from the temple of the Lord justified,
and departed to his own house. And her months were fulfilled, and in the ninth month Anna(ሐና) brought forth. And she said to the midwife: What have I brought forth? And she said: A girl. And said Anna: My soul has been magnified this day. And she laid her down. And the days having been fulfilled, Anna was
purified, and gave the breast to the child, and called her name Mary." The Protoevangelium of James, 5
👉 @Konobyos
👉 @And_Haymanot
[ከእንጦጦ ሰማይ ስር]
(በመ/ሐ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ)
👉 ጸጥ ባለው ምሽት ነፋስ በበዛበት፤
ሰዎችም ቤታቸው ለዕረፍት በተኙበት፤
ድንቁን የአምላክ ሥራን በምሽት ለማየት፤
በእንጦጦ ተራራ ተገኘሁ በድንገት።

👉 ከዋክብት በሰማይ ያብረቀርቃሉ፤
ፕላኔት በጠፈር ደምቀው ይታያሉ፤
በአንድነት በመሆን የፈጣሪን ጥበብ ይመሰክራሉ።

👉 ቀደምት ኢትዮጵያውያን በዕውቀት የላቁ፤
በጠፈር ምርምር እየተራቀቁ፤
የሰማዩን ምስጢር ጠንቅቀው አወቁ፤
ያወቁትን ምስጢር ምንም ሳይደብቁ፤
በጽሑፍ አኑረው በጥበብ መጠቁ።

👉 ንግሥት ካሲዮፕያ ብትወድ ፈለክን፤
መሠየም ጀመረች ሕብረ ከዋክብትን።

👉 ሴፌውስ በአድናቆት እርሱም አስተውሎ፤
ከአንድሮሜዳ ጋር ፈጠነና ቶሎ፤
ያየውን አኖረ ለትውልዱ ብሎ።

👉 ቀደምቶች ያኖሩት የሰማይ ምስጢር፤
አስተዋይ እስኪኖር የሚመረምር፤
በክብር ይቀመጣል ዕውቀት እስኪከብር፤
በዕውቀት መራቀቅ ጊዜው እስኪጀምር።

👉 ቴሌስኮፑን ቶሎ በፍጥነት አቆምኩት፤
መመልከት ጀመርኩ ሰማዩን በትኩረት፤
የግዮኗ ኮከብ ሳይረስን አየኋት፤
የዐባይን ወንዝ መሙላት ቀደምት ያወቁባት።

👉 ኢዮብ የጠቀሰው የኦርዮን ኮከብ፤
ቀበቶውን አርጎ ውበትን በማበብ፤
ደምቆ እየታየ ተከቧል በክበብ።

👉 አይቼው ዞር ስል በሰሜኑ በኩል፤
ዝሁራ ቬነስ የጠፈር ዕንክብል፤
ደምቃ ትታይ ነበር በከዋክብት መሃል።

👉 ማዛሮትና ድብ እነኢዮብ ያይዋቸው፤
እነ ሔኖክ ቀድሞው የመረመሯቸው፤
የኢትዮጵያ ሊቆች የመዘገቧቸው፤
ይታያሉ በእውነት በደንብ ላጤናቸው።

👉 ደስ በሚል ምሽት የጨረቃም ድምቀት ተጨምሮበታል፤
ውስጧንም መመልከት በእጅጉ ያጓጓል።

👉 የጨረቃ ስሟ አንዴ አሶንያ ሌላ ጊዜ ቀመር፤
ብናሴና ኤራዕ ቢሉ ስሟን በማሽከርከር።

👉 ወርህም ዕብላም ቢሉ ደግሞም ሶልያና፤
ይህን ሁሉ ስሟን ጻፉት በብራና።

👉 አቅርቦ ቢያሳየኝ ቴሌስኮፑ ድንገት፤
እቺን ድንቅ ፍጥረት ለካስ ውብ ደማቅ ናት።

👉 ፈጣሪ ይመስገን እነዚህን ሁሉ በአንድነት ያስገኘ፤
ጥበብን የሚገልጽ በእውነት ለተመኘ።

👉 ከዚያ ከተመስጦው ደስ ከሚል ምሽት፤
የጠፈር ዕንቁዎች ደምቀው ካበሩበት፤
ዕውቀት ከሚያበዛው ደስ ከሚል ሌሊት፤
ጊዜው መሽቷልና ተነሣሁ በድንገት።

👉 ከተማ ደረስኩኝ የወሬ ማዕበል ወደ ሚጎርፍበት፤
ጫጫታና ሁከት ወደሰፈነበት፤
ጽሙና ዕርጋታ ከቶ የሌለበት፤
ተፈጥሮንም ማድነቅ የማይታሰብበት።

👉ቢሆንም!! አምላክ የእጅህ ሥራ በእጅጉ ይደንቃል፤
የዓለም ጫጫታን ከኅሊና ያጠፋል፤
አስተዋይ ልቡናን በደስታ ያራቅቃል፤
መንፈስን ልቡናን በፍቅር ያሞቃል፤
ሕሊናን መስጦ ወደ ላይ ያወጣል።
በመ/ሐ/ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ
(ግንቦት 4/ 2012 ዓ.ም. ከሌሊቱ 12:12 ተጻፈ)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"ሰይጣን የማይነካው ዕቃ "

በአንድ ሐገር ድንገት የአንድ" ጠንቋይ ዝና ከዳር ዳር ተሰማ ። ሰውዬው የማያሳየው ምትሐት የለም። አንበሳ ላለ አንበሳ፣ ነብር ላለ ነብር፣ የሞተ ዘመዴን ላለ የሞተ ዘመዱን፣ የጠፋብኝን ዕቃ
ከቤት ፈልገህ አምጣልኝ ላለ ዕቃውን ያመጣለታል። እንደሚታወቀው አጋንንት ከክብራቸው የተዋረዱ መላእክት ናቸው። መላእክት ደግሞ በፈለጉት ሁኔታ መገለጥ ይችላሉ። ይህ ጠንቋይ የሚሰጣቸውን ገጸ ባሕርይ ተቀብለው አንዴ አንበሳ፣ አንዴ ነብር፣ አንዴ ሰው እየሆኑ የሚተውኑት እንግዲህ አጋንንቱ ነበሩ። የበዚህ ጠንቋይ ዝና ወደ ንጉሱ ደረሰ። ንጉሱ ደግሞ ክርስቲያን
ቢሆንም ከመጸሐፍ ቅዱስ ይልቅ እንዲህ ያለ ተአምር እዚህ ቦታ ተፈጸመ ሲባል ለማየተት የሚሮጥ ሰው ነበር። ተአምር የሚወድ ሰው ደግሞ ክርስቲያንም ቢሆን ሰይጣን በሚሰራው ምትሐት
መታለሉ የማይቀር ነው። ስለዚህ ይህ ንጉስ የተማረውን መጽሐፍ ቅዱስ ዘንግቶ በጠንቋዩ ምትሐት አመነ።
ይህንን የሰሙ የንጉሱ ንስሐ አባት ነገሩን ሰምተው ወደ ቤተ መንግሥት ሲሮጡ ደረሱ። ሲደርሱ ንጉሡ ከቁም ነገር
አልቆጠራቸውም። እሱ የጠንቋይ ትርዒት ማየት ቀጠለ። "እስቲ አሁን ደግሞ እእእ ነጭ ፈረስ አምጣልኝ" ማለቱን ቀጠለ በነገሩ ያዘኑት "ኧረ ንጉሥ ሆይ ይተዉ፡ ይህ እኮ የሰይጣን ምትሐት ነው " ብለው ሊያስረዱት ሲሉ በቁጣ አስቆማቸው። ተአምር የሚከተል ሰው መቼስ ቢነግሩት አይሰማም። ጭራሽ
እንዲያው ለንስሐ አባቱ እንዲህ አላቸው። " የሰይጣን ስራ ነው አትበሉ፤ ቅናት ነው ይኼማ,,,, ይልቅ እርስዎም የሚፈልጉትን ነገር ይጠይቁት ያምጣልዎት!"አላቸው። ጠንቋዩ «የፈለጉትን ላምጣልውት,,,,,ምን ይፈልጋሉ,,,, " የሞተ ዘመድ አለዎት,,,,, ወይስ ከቤትዎ,,,, » አላቸው በኩራት። ካህኑ ውስጣቸው በመንፈሳዊ ቅናት ተቃጠለ። « እንግዲያውስ የፈለኩትን ማምጣት ከቻልህ ወደ ቤተ መቅደስ ሔደህ ልብሰ ተክህኖዬ ውስጥ መስቀል አለ እርሱን ይዘህልኝ ና » አሉት።
ይህን ግዜ ጠንቋዩ ገና ድግምቱን ሲጀምር አጋንንቱ እላዩ ላይ ሰፍረው ጣሉት። በካህኑ ፊት ወደቀ። ሰይጣን ምንም ነገር ማምጣት ይችል ይሆናል። መስቀሉን ግን ማምጣት አይችልም።
አባቶቻችን ሰይጣን እንኳን መስቀል ቀርቶ መስቀለኛ መንገድም
አይወድም ይላሉ።
የጌታችን ቅዱስ መስቀል ሆይ ቅዱስ ዳዊት እንዳለ «ብከ ንወግዖሙ ለኩሎሙ ጸርነ»
@And_Haymanot
«በአንተ ጠላቶቻችንን እንወጋቸዋለን!»
በዲ/ን ሔኖክ ሙላት
"ከሞት ባሻገር" የተወሰደ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"ዐረገ በስባት ዐረገ በልልታ"
እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል (በዓለ አርብዓ) በሠላም አደረሳችሁ።

በእልልታ አረገ አረገ በእልልታ 
ሞትን ድል አድረጎ የሠራዊት ጌታ /2 
አረገ አረገ በእልልታ 

ከጌታ ዓበይት በዓላት አንዱ ዕርገት ነው።
"ወረሲ ኀዋኅወ ቤተ ክርስቲያንከ ቅድስት ርኅዋተ ለነ በምሕረት ወአሚን"
"የቅድስት ቤተ ክርስቲያንህንም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት እንዲከፈቱ አድርግልን።"
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ምንፍቅና በቅዱስ ቃሉ ሲፋቅ!
#ስግደት_ለመላእክት
👉ኢያሱ ለመልአኩ ሰገደ
👉ዮሀንስ ስለምን አትስገድልኝ ተባለ?

@And_Haymanot

መናፍቃን የሚያነሱትን ጥያቄ ቀለል ባለ
መንገድ ስንመልስ!!
👉1. የእስራኤል መስፍን የሆነው ኢያሱ “የምታመልኩትን ዛሬ ምረጡ እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን” ብሎ
እንዳላለ !!መጽ.ኢያሱ 5ቁ13“……እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኘ አሁን መጥቻለሁ አለ. ኢያሱም ‘ወደ ምድር በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደና’ ጌታየ ለባሪያው
የሚነግረው ምንድር ነው አለው. የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ስፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን አውልቅ አለው” የምታመልኩትን ምረጡ ያለው ኢያሱ ለመልአኩ በስህተት ሰገደ ብለን አናምንም!!!ለመልአኩ በግንባሩ መደፋቱም መልአኩን ለማክበር እንጅ ለማምለክ እንዳልሆነ እናውቃለን!!!ዛሬም ኢያሱን ተከትለን እንዲሁ ስናደርግ አምላክን ከመልአክ ለይተን ነው!!!የአንዱን ላንዱ ሳንሰጥ፣ሳንቀላቅል!!

👉2. ወንጌላዊው ዮሐንስ፡በራእይ 19ቁ10 እና 22ቁ8 ….በመልአኩ እግር ፊት ሰገድኩለት እሱ ግን አትስገድልኝ፣ ሁለታችንም የእግዚአብሔር ባሪያዎች ነን አለኝ….የሚለውን ጥሬ ንባብ ለመላእክት ስግደት እንደማይገባ ለማሳየት መናፍቃን ያቀርባሉ!!!ተሳስተዋል!!
✔️(ሀ)ወንጌሉን፣መልእክታቱን፣ራእዩን የጻፈው ዮሐንስ ለመልአኩ የሰገደው ባለማወቅ ነው ማለት ይሄን ሁሉ የጻፈውን ዮሐንስ ለማን መስገድ እንዳለበት እንኩዋ የማያውቅ አዲስ ምእመን ማስመሰል ነው!!!ዮሐንስ የሰገደው መስገድ ስለሚገባው ነው!!!
✔️(ለ)መልአኩ አትስገድልኝ ያለው ስግደት የበላይና የበታች መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ዮሐንስ በክብር እደተስተካከለው አውቆ ነው!!!ለትህትና!!!
✔️(ሐ)መልአኩ በምእራፍ 19 ቁ 10 እንደተገለጸው ዮሐንስን አትስገድልኝ ቢለውም ዮሐንስ ግን በምእራፍ 22 ቁ 8’ም ዳግመኛ ለመልአኩ ሲሰግድ እናገኘዋለን!!ዮሐንስን ያህል የጌታ
ወዳጅ(ፍቁረ-እግዚእ) ተብሎ የተነገረለትና በጰራቅሊጦስ
መንፈስቅዱስ የወረደበት አባት ለመልአክ መስገድ ስህተት
መሆኑ ጠፍቶ፣ እየተነገረው ጭምር ከአንዴም ሁለቴ ሰገደ ማለት ቅድስናውን መጠራጠር ይሆናል!!!ስለሆነም መልአኩ
አትስገድልኝ ያለው ለትህትና ነው ስንል እናምናለን!!!

👉3. የሞቱ ቅዱሳን ከእኛ ጋር የሚያገናኛቸው ነገር የለም የምትሉ ሰዎች አላችሁ!!!እሺ ቅዱሳኑስ ይሁኑ ታዲያ መላእክት እኮ አይሞቱም!!!ስለታናናሾች የአብን ፊት ያያሉ እንጅ-በማቴ 18ቁ 10 እንደተጻፈው!በዘካርያስ 1 ቁ 13 የመልአኩ ምልጃ እንዲህ
ተጽፉዋል “አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ እነዚህ 70 አመት የተቆጣሀቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተማዎች የማትምራቸው እስከመቼ ነው አለው እግዚአብሔርም መልሶ ከእኔ ጋር ይነጋገር ለነበረው መልአክ በመልካምና በሚያጽናና ቃል ተናገረው” ታዲያ ሳንለምነው እንዲህ የሚማልድልን መልአክ ብንለምነውማ ምን ያህል ይማልድልን?ሰአሉ ለነ ሚካኤል ወገብርኤል እንበላቸውማ!!!

👉4.የሞቱ ቅዱሳን በክርስቶስ ህያው ስለሆኑ ከእኛ ጋር በመንፈስ
እንደሚገናኙ ደግሞ ይሄው!!!የሞቱ ቅዱሳን “እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነሱ እንደማያፍር” በዕብ 11 ቁ 16 ተጽፉዋል!!!የሞቱ ቅዱሳን አላዋቂዎች ሳይሆኑ ወደፍጹምነት የተሸጋገሩ ‘ፍጹማን’ መሆናቸው በዕብ 12 ቁ 22 ሰፍሮልናል!!! ጌታም ከአመታት በፊት በሞት የተለዩትን አብርሃምን፣ይስሀቅንና
ያዕቆብን ጠቅሶ “የህያዋን አምላክ ነኝ” ሲል በማቴ 22 ቁ 32 ገልጹዋል!!!ጌታችን በስጋ ስለሞተው አብርሃም በዮሀንስ 8 ቁ56 ሲናገር፡ “አብርሃም ቀኔን ያይ ዘንድ ሀሴትን አደረገ፤አየም ደስ አለው” ይላል!!!በአጸደ ነፍስ ያለው አብርሃም የጌታን ቀን አይቶ የተደሰተው በሰማይ ያሉ ቅዱሳን በምድር ካለነው ጋር ህብረት ስላላቸው ነው!! ዮሐንስ በራዕዩ ምዕራፍ 8 ቁ 3 “የዕጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚብሔር ፊት ወጣ” ይለናል!!መላእክት ጸሎታችንን ያሳርጋሉ!!!አእርጉ ጸሎተነ የምንላቸውም ለዚሁ ነው-እንደ ቅ/ያሬድ-እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ!!ሙሴስ በዘጸአት 32 ቁ 13 “በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ይስሀቅንና እስራኤልን አስብ” ብሎ በአጸደነፍስ ነፍስ ባሉ ቅዱሳን ስም ጌታውን ሲማጸን ከሞቱ ቅዱሳን ህብረት ስላለን አይደለምን?ነው እንጅ!!!

👉5. ይሄን ሁሉ ስንል ባለቤቱን ረስተን አይደለም!!!በቀጥታም እሱን ማረን እንለዋለን-እግዚኦ መሀረነ ክርስቶስ በምህላ- መሀረነ አብ በማስታኮት!!!ስማን፣ተማለደን፣ታረቀን እንለዋለን!!! ግን እንደሌሎቹ አማልደን አንለውም!!!ሌሎቹ የሚያማልደን ጌታ ነው እያሉ ቤዛነቱን እንደአማላጅነት ስለሚወስዱት ነው እኛ ቅዱሳንን አማልዱን ስንል አምላክ ያደረግናቸው የሚመስላቸው!!! አምላካችን አንድ ነው!!!የሃይማኖታችን መሰረትም እሱ-ለዚህም ነው ሰማይንና ምድርን በፈጠረ በአንድ አምላክ እናምናለን ስንል የሃይማኖት ጸሎታችንን የምንጀምረው!!!
ይቆየን
#ኦርቶዶክሳዊ_ምላሾች_እና_መረጃ_ብቻ_የሚቀርቡበት
👇👇👇
አንድ ሃይማኖት
`ተዋህዶ´´´
@And_Haymanot
JOIN
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~Share~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
~~~JoIN~~~
@And_Haymanot
@And_Haymanot
፩ ሃይማኖት
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መልስ አላት
@And_Haymanot
የአበው ሃይማኖት አትታደስም፡፡
``የተፈጠረ እንጂ ያልተወለደ``
(ቢመርም ጠጣው)

ውኃ ያላረጠበው የበረሃ ተጓዥ ጥምቀት ያላራሰው; ጣዖት የለበለበው ተፈጣሪ ግን ያልተወለደ; አባት ያለው ግን ልጅ
ያልሆነ የተፈጠረ እንጂ ያልተወለደ አሕዛብ! ጸሎተ ሃይማኖታችን ላይ 318ቱ ሊቃውንት ወልድ የተወለደ እንጂ ያተፈጠረ` ብለውታል! ተወዳጆች! እኛ ኦርቶዶክሳውያን ደግሞ ``የተወለድንም የተፈጠርንም እንባላለን` የተፈጠርን-
መባሉ በአርአያ ሥላሴ ስለተፈጠርን ሲሆን ፤``የተወለድንም መባሉ በጥምቀት ተወልደናልና ነው፡፡ ልዩ የሆኑት አሕዛብ መናፍቃን ግን የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ`` ናቸው፡፡
አሕዛብ/መናፍቃን ``የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ከተባለለት አምላክ ያልተወለዱ ሆነው ቢገኙ `የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ አሰኘባቸው፡፡ መፈጠርን አግኝተዋል የነፍስ መወለድን ግን አላገኙም፤በሥጋ ተወልደዋል ከጥምቀት የሚገኝ መንፈሰ ልደት
ግን አላገኛቸውም፤በምጥ ተወልደዋል ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ በረቂቅ አልተወለዱም፤ተስዕሎተ መልክ አግኝተዋል ተሥዕሎተ ሥላሴን ግን አላገኙም ፤አካለ ሥጋን አግኝተዋል በሜሮን ግን አልከበረም፤መብለ ሥጋን ይበላሉ ቁርባኑ ግን አላሻተታቸውም፤ይጠጣሉ ጠበል ግን አልዳበሳቸውም ፤በከበረው ቤት ኖረዋል የከበረች ቤ/ክ ውስጥ ግን አልኖሩም፤ዓለምን ሁሉ ያውቃሉ ቤ/ክን ግን አያውቋትም፤ቤ/ክን ይጠሏታል እርሷ ግን ሥራቸውን እንጂ እነሱን አትጠላቸውም እነዚህም… እንደ ኦሪቱ ያልተገዘሩ ቆላፎች ሸለፈት ጌጣቸው
አንባር ዝናራቸው የሆነ በሐዲስ ኪዳኑ
የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ`` አሕዛብ ናቸው! ለማያውቁት ይሰግዳሉ የሚያውቃቸው ግን በሌላ አምላክ
ቀይረውታል እሱም ያዝንባቸዋል!
በአርአያው ፈጥሯቸው ሳለ አርአያውን ለማያውቁት ይሰግዳሉ! ከነፍስ መንጺያ ጥምቀት ይልቅ የሥጋ መንጸትን ይሻሉ!
ከክርስቶስም ሥጋና ደም ይልቅ የክርስቲያች ደም ያጸድቃቸዋል! ስለዚህ ተፈጥረዋል ግን አልተወለዱም ! ለአባትነቱ ሲል ፈጥሯቸዋል አባትነቱን ግን አላመኑለትም ምክንያቱም አልተወለዱምና! ለጌትነቱ ፈጥሯቸዋል እነሱ ግን አገልጋይነቱን አልፈለጉም! ለንጉሥነቱ ፈጥሯቸዋል ግን ስላልተወለዱ ሕዝብ መሆንን አላገኙም! በውኃ ውስጥም አልፈው ሥላሴን አላገኙም! ለፍቅሩ የሰጣቸውን ለልጅነት የሚሆን ሰውነታቸውን ለአላዊው
ዲያብሎስ ገበሩት እርሱም ለማያውቁት መስገድን ለሚያውቁት መገዳደርን አስተማራቸው! በጥምቀት መወለድን ትተው በመፈጠር ብቻ ቆሙ!
ስለዚህ ያልተወለዱት በተወለዱት ላይ አመጹ! መኖራቸው አነደዳቸው አመጹባቸውም! መኖሪያዎቻቸውን አነደዱ ስፍራዎቻቸውን ተቀራመቱ በስፍራዎቻቸውም ይጠጋሉ መሬት
ይከባሉ ጽነትን ያደርጋሉ ይቆረቁራሉ ያሰፋሉ ያስተጋባሉም የጥምቀት ውኃ ባላበረደው ሰውነት ያመኑትን ይጻረራሉ !
የተወለዱት ግን ያያሉ ይታዘቡማል ይመረምራሉ ይማጸናሉ ! አይጠሉም ይወዳሉ ሰውን ያይደለ ክፉ ግብርን ይጸየፋሉ! ስለዚህም አሕዛብ ተፈጥረው ቆሙ መወለድን ግን አልፈለጉም!
አሕዛቡ የማመናቸው መሠረት የተወለዱት ባለመኖራቸው ላይ ሆነ፤መኖራቸውን የሚያረጋግጡት የተወለዱትአለመኖራቸውን
ቅድሚያ አረጋግጠው ነው! ቢቻል ስፍራዎቻቸውን ማጥፋት ባይቻል መውረስ ባይቻል ተጠግቶ ቁር-ብትና(ብርዳም ጎረቤት፤አንድም ቁርበታም የሆነ ጎረቤት) ሆኖ መገኘት ነው! የተወለዱት ግን እንደ ልጅ ይኖራሉ - ምክንያቱም አባት አላቸውና! እንደ ባርያ ይኖራሉ -ምክንያቱም ጌታ አላቸውና !
እንደ አገልጋይም ይኖራሉ-ምክንያቱም ንጉሥ አላቸውና! በአንድነት ይኖራሉ ምክንያቱም - አንድ አምላክ አላቸውና!
ከሁሉም አስቀድሞ ደግሞ ጌታቸውን በ40/80 ቀን በውኃ ውስጥ ሦስት አካል ሆኖ አግኝተውታል! አባ አባ ማለትን አስለምዶ አንደበታቸው ሲፈታ አባታችን ሆይ ማለትን አስለምዷቸዋል! እነዚያ አሕዛብ ግን ``አባታችን ሆይ አይሉም
ምክንያቱም አባት ሳላቸው ልጅ አልሆኑለትምና! ምክንያቱም
`
የተፈጠሩ እንጂ ያልተወለዱ ናቸውና!
By:- ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
“ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡ አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡”

© ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ፣ ገጽ 33
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
"12 የሆነው በምክንያት ነው"
# ቅዱሳን መላእክትን መታሰቢያቸውን መዘከራችን -በምክንያት
ነው
#ቅዱስ ሚካኤልን ማክበራችንም - በምክንያት ነው
#ቅዱስ ሚካኤል ዓይኑ ዘርግብ መባሉም - በምክንያት ነው
#ቅዱስ ሚካኤል እርዳን ማለታችን - በምክንያት ነው
# ቅዱስ ሚካኤል በ12 ማክበራችን - በምክንያት ነው
#ቅዱሳን መላእክትን መታሰቢያቸውን መዘከራችን -በምክንያት ነው...... በመጽሐፈ መሳፍንት የሶምሶን እናትና አባት መልአኩ ተገልጦ ልጅን እንደሚወልዱና እርሱም ናዝራዊ እንደሆነ በነገራቸው ጊዜ የሶምሶን አባት ማኑሄ ለመልአኩ " ማኑሄም የእግዚአብሔርን መልአክ ነገርህ በደረሰ ጊዜ መታሰቢያህን እንድናደርግ ስምህ
ማን ነው? አለው" (መጽሐፈ መሳፍንት 13:17) መልአኩም ስሜ ድንቅ
ነው ብሎታል፡፡ እንኳን በሐዲስ ኪዳን በብሉይ እንኳን መላእክት መታሰቢያቸው ይከበራል፡፡
*እስራኤላውያን ከቀሳፊው መልአክ የተረፋበትን ቀን " ይህም ቀን መታሰቢያ ይሁናችሁ፥ ለእግዚአብሔርም በዓል ታደርጉታላችሁ፤ለልጅ ልጃችሁ ሥርዓት ሆኖ ለዘላለም ታደርጉታላችሁ"(ኦ.ዘጸ
12:14) እስራኤላውያን ከቀሳፊው መልአክ የተረፋባትን ቀን
ካከበሩ እኛማ ቅ/አፎምያ በቅ/ሚካኤል መትረፏን ብናከብር እኛም የቅ/
ሚካኤንም ውለታ እንዴት አናከብር !! ጠቢቡም " የጻድቅ መታሰቢያ
ለበረከት ነው፤ የኅጥኣን ስም ግን ይጠፋል። ምሳሌ 10:7)
እውነት ነው የቅ/ሚካኤል መታሰቢያ ለበረከት ነው፡፡
#ቅዱስ ሚካኤል ዓይኑ ዘርግብ መባሉም - በምክንያት ነው
*ለቅ/ሚካኤል የሰውና እንስሳ ዓይነት ዓይን ኖሮት "ዓይኑ ዘርግብ "
የተባለ አይደለም፡፡ይልቁንም የሰው ዓይን የሚያየው ነጩ ያይደለ
ጥቁሩ (ብሌን) ነው፡፡ ርግብ ግን ዓይኗ የሚያየው ነጩም ጥቁሩም
ነው፡ እንዲሁ ቅ/ሚካኤል ሆይ አንተም ያለፈውንም የሚመጣውንም
ማየት ይቻልሀል (በጸጋ ተሰጥቶሀል) ስንል ነው፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ መልአኩ ነጫጭ ልብስ
የለበሱት ማናቸው ባለው ጊዜ ዮሐንስ ሲመልስ " እኔም ጌታ ሆይ፥ አንተ
ታውቃለህ አልሁት አለኝም እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፥ ልብሳቸውንም አጥበው በበጉ ደም አነጹ"ዮሐንስ ራእይ 7:14)
#ቅዱስ ሚካኤል በ12 ማክበራችን - በምክንያት ነው
*ቅ/ገብርኤል በ19 መታሰቡ በምክንያት እንደሆነው የቅ/ሚካኤልም
በ12 መሆኑ በምክንያት ነው፡፡ የቅ/ገብርኤል " መልአኩም መልሶ።
እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም
ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር "የሉቃስ ወንጌል
1:19 ........ ቁጥር "19" ይህ በምክንያት ነው፡፡ የቅ/ሚካኤል
" በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ
ሚካኤል ይነሣል " ትንቢተ ዳንኤል 12:1 ..... ምዕራፍ "12" ይህም በምክንያት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በዚህች ቀን
መታሰቢያውን እናደርጋለን ስሙንም ከፍከፍ እናደርጋለን ! ቅዱስ ሚካኤል
ያማልደን ዘንድ እንማጸነዋለን .... ምን ማማለድ ብቻ መልአክ አይደል
ደስ ያለውንም ያደርግልናል "እርሱም እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፤ አንተ ጌታዬ ንጉሥ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤
ደስም ያሰኘህን አድርግ " (መጽ.ሳሙ 19:27)
#ቅዱስ ሚካኤል ረዳትነቱንም ስንመሰክር በምክንያት ነው "
ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም" (ት.ዳን 10:21) .......እናም ከቅዱስ ሚካኤል በረከቱን ያድለን፡፡
(ኢዮብ ዘገነተ ጽጌ ሰኔ 12/2012)
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
ሐይማኖት አይወረስም?

@And_Haymanot

ተወዳጆች የተሃድሶ መናፍቃን ሃይማኖት አያስፈልግም፤አያድንም፤አይወረስም በማለት ብዙዎችን ለማደናገር ይሞክራሉ ከዚህ በፊት በስፋት የዳሰስነው ርዕሳችን ቢሆንም በውስጥ ለጠየቀን ወንድማችን እነሆ ብለናል

ሐይማኖት አይወረስም ላልከን እንዲህ የምናምነውንም እንመሠክራለን! > እንግዲያውስ ከኃይማኖት በላይ ሊያወርሱት እና ሊወርሱት የተገባ የከበረ ነገር በዚች አለም የለም። ሰው መልካም መልካሙን ነገር ለልጆቹ ያወርሳል ከመልካም ስጦታዎች ሁሉ የሚልቀውን የዘላለም ሕይወት የሚገኝበትን ሐይማኖት ከማውረስ የበለጠ ታላቅ ውርስ እንዳውም በጭራሽ አይገኝም።

ሰው በምድር ላይ ለልጆቹ የሚሆን ታላቅ መኖሪያ ቢያወርስ ነገር ግን የዘላለም ሕይወት የሚያገኙበትን ሐይማኖቱን ግን ባያወርስ ምን ይረባቸዋል! ??
ሁለት ነገርን አደፈረስክ! መጀመሪያ ሐይማኖት ሊወረስ የተፈቀደ መሆኑን ካድክ ሲቀጥል ደግሞ በገዛ ድምዳሜክ ገባህና ሐዋርያት ከሀድያን ናቸው አልክ! እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ።
አስቀድመህ በራስህ አላዋቂነት የደመደምከው ድምዳሜ ላይ የተመረጡትን ሁሉ አጋጭተሀል።
በመሰረቱ ሀይማኖት ለሰው ልጆች የተሰጠችው ልንጠብቃት እና ለትውልድም ልናወርሳት ነው።
አብርሃም አባታችን ለአይሁድም ሆነ ለሀዲስ ኪዳን ህዝቦች አባት ነው። ከህግ ለሆኑት የመገረዝ አባት ነበረ። ከእምነት ለሆንነው ደግሞ የእምነት አባት ነው። የፃድቅ አብርሃም
ሕይወት ለእኛ ምሳሌ ነው። አብርሃም እግዚአብሔር ን አመነ ፅድቅም ሆኖ ተቆጠረለት ነገር ግን ይህ ብቻ አልነበረም ጉዳዩ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም ትዛዝን ሲሰጠው ልጆችህ ቃል ኪዳኔን እንዲጠብቁ አድርግ በሚል ጠንካራ
ማሰሪያም ጭምር ነው። አብርሃምም በቤቱ ለተወለዱት ልጆች ሁሉ ይህን የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ገና በተወለዱ በ8 ቀናቸው ጀምሮ ይፈፅምላቸው ነበር። የእርሱን ሐይማኖት ለልጆቹ ገና በስምንት ቀን ጨቅላነታቸው እያሉ ጀምሮ እንዲቀበሉ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ስለሆነ ነው። ልጆችም በአባቶቻቸው
ሐይማኖት ተወስነው እንዲኖሩ ነው የጌታ ትእዛዝ። ስለዚህ ሐይማኖት ይወረሳል። ከሐይማኖት የበለጠ ለልጅ ሊያወርሱት የሚገባ መተኪያ የሌለው ውድ ነገርስ ከየት ይገኛል???
ዘፍጥረት 17
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘላለም ኪዳን አቆማለሁ፥
#ለአንተና_ከአንተ_በኋላ_ለዘርህ_አምላክ_እሆን_ዘንድ
⁸ በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ለዘላለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ አምላክም እሆናቸዋለሁ።
⁹ እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ አንተ ደግሞ ቃል ኪዳኔን ትጠብቃለህ፥ አንተ ከአንተም በኋላ ዘርህ በትውልዳቸው።
¹⁰ በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል የምትጠብቁት ቃል ኪዳኔ ይህ ነው፤ ከእናንተ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
¹¹ የቍልፈታችሁንም ሥጋ ትገረዛላችሁ፤ በእኔና በእናንተ
መካከል ላለውም ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናል።
¹² #የስምንት_ቀን_ልጅ_ይገረዝ ፤ በቤት የተወለደ ወይም ከዘራችሁ ያይደለ በብርም ከእንግዳ ሰው የተገዛ፥ ወንድ ሁሉ በትውልዳችሁ ይገረዝ።
¹³ በቤትህ የተወለደ በብርህም የተገዛ ፈጽሞ ይገረዝ። ቃል ኪዳኔም በሥጋችሁ የዘላለም ቃል ኪዳን ይሆናል።
¹⁴ የቍልፈቱን ሥጋ ያልተገረዘ ቈላፍ ሰው ሁሉ፥ ያች ነፍስ ከወገንዋ ተለይታ ትጥፋ፤ ቃል ኪዳኔን አፍርሳለችና።//

ሮሜ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ
አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው።
¹³ የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው
የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም።
¹⁴ ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል
የተስፋውም ቃል ተሽሮአል፤
¹⁵ ሕጉ መቅሠፍትን ያደርጋልና፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት መተላለፍ የለም።
¹⁶-¹⁷ ስለዚህ ከሕግ ብቻ ሳይሆን ከአብርሃም እምነት ደግሞ ለሆነ ለዘሩ ሁሉ የተስፋው ቃል እንዲጸና እንደ ጸጋ ይሆን ዘንድ በእምነት ነው፤ እርሱም፦ ለብዙ አሕዛብ አባት አደረግሁህ
ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ለሙታን ሕይወት በሚሰጥ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት በአምላክ ፊት #የሁላችን #አባት #ነው
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot
Forwarded from ፩ ሃይማኖት
አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።

1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።

ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።

የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።

ሰው ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@And_Haymanot
@And_Haymanot_bot