የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
304 photos
106 videos
47 files
800 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
ኢስላማዊ ሰላምታና ስርአቱ!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን(አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

1ኛ/ ከጌታ አላህ መለኮታዊ ሥሞች ውስጥ አንዱ "አስ-ሰላም" የሚለው ነው፡፡ ትርጉሙም የሰላም ባለቤት እንዲሁም ከነውር (ከእንከን) የጸዳ ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ የሰላም ምንጭ በመኾኑ ‹‹አስ-ሰላም›› ይባላል፡፡ ለአማኝ ባሪያዎቹ ሰላምን የሚለግስ እሱ ብቻ ነውና፡፡ ጌታ አላህ የሰላም ባለቤት በመኾኑ ወደ ሰላም ሀገር (ጀነት) ይጣራል፡፡ ለአማኝ ባሪያዎቹም የሰላምን ሀገር አዘጋጅቶላቸዋል፡፡
"እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ #የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኀያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡" (ሱረቱል ሐሽር 59፡23)፡፡
"አላህም ወደ #ሰላም አገር ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 10፡25)፡፡
"ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ #የሰላም አገር አላቸው፡፡ እርሱም (ጌታህ) ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ረዳታቸው ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 6፡127)፡፡
ሠውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሶላታቸውን ሲያጠናቅቁ፡ ሶስት ጊዜ ‹አስተግፊሩላህ› ከዛም ‹‹አልላሁመ አንተ-ስ-ሰላም፣ ወሚንከ-ስ-ሰላም፣ ተባረክተ ዘል-ጀላሊ ወል-ኢክራም›› ይሉ ነበር" (ሙስሊም 1362)፡፡ ትርጉሙም፡- አምላኬ ሆይ! አንተ ራስህ ሰላም ነህ! ሰላምም የሚገኘው ካንተው ዘንድ ነው፡፡ የእልቅናና የክብር ባለቤት የኾንከው ክብርህ ከፍ አለ (ላቀ) ማለት ነው፡፡

2ኛ/ ‹‹አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ›› ማለት፡- የአላህ ሰላም፣ እዝነቱና በረከቱ በናንተ ላይ ይስፈን ማለት ነው፡፡ በሰላምታ ወቅት አንዱ ለሌላው የአላህን ሰላምና እዝነት እንዲሁም በረከት እንዲሰፍንበት ከመመኘት የበለጠ ምንም አይነት ሰላምታ የለም፡፡ የሰላምታዎች ሁሉ ቁንጮ፣ ዓለም-አቀፋዊ የሰላምታ መግባቢያ የኾነ ነገር ቢኖር ይኸው ‹‹አሰላሙ-ዐለይኩም›› የሚለው ሰላምታ ብቻ ነው፡፡

3ኛ/ ‹‹አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ›› የሚለው ኢስላማዊ ሰላምታ፡ ከመጀመሪያው አባታችን ከአደም (ዐለይሂ-ሰላም) ዘመን ጀምሮ የነበረ ሰላምታ ነው፡፡ ጌታ አላህ አደምን (ዐለይሂ-ሰላም) ከፈጠረው በኋላ መላእክት ዘንድ በመሄድ ሰላምታን ያቀርብላቸው ዘንድ፡ እነሱም የሚመልሱለትን ምላሽ እንዲሰማና ይህም የሱና የዘሮቹ የመከባበሪያ ሰላምታ እንደሚኾን በመንገር አዘዘው፡፡ እሱም ‹‹አሰላሙ-ዐለይኩም›› በማለት ሰላምታን አቀረበላቸው፡፡ እነሱም ‹‹አስ-ሰላሙ ዐለይከ ወራሕመቱላህ›› በማለት ጨምረው መለሱለት፡፡ (ቡኻሪይ 6227፣ ሙስሊም 7342)፡፡
ይህ ኢስላማዊ የመከባበሪያ ሰላምታ በዚህ ምድር ብቻ ሳይኾን፡ በመጪው ዓለም በአኼራ የጀነት ሰዎች የመከባበሪያ ሰላምታ ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 10፡10)፡፡
"እነዚያም ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በጌታቸው ፈቃድ እንዲገቡ ይደረጋሉ፡፡ በውስጣቸው መከባበሪያቸው ሰላም (ለእናንተ ይኹን መባባል) ነው፡፡" (ሱረቱ ኢብራሂም 14፡23)፡፡

4ኛ/ አንድ ሙስሊም በሌላው ሙስሊም ላይ ካለው ኢስላማዊ መብት አንዱ ‹ሰላምታ› ነው፡፡ ሙስሊሞች በተገናኙ ቁጥር ‹አሰላሙ ዐለይኩም› የሚለውን ኢስላማዊ ሰላምታ መለዋወጥ አለባቸው፡፡ ቅድሚያ ሰላምታውን መጀመሩ ሱንና ቢኾንም፡ ሰላምታ የቀረበለት ሰው ግን ምላሽ መስጠቱ ግዳጅ ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
"#በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ከእርሷ ይበልጥ ባማረ (ሰላምታ) አክብሩ፡፡ ወይም (እርሷኑ) መልሷት፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና፡፡" (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡86)፡፡
ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሙስሊም በሌላው ሙስሊም ላይ ስድስት መብቶች አሉት፡፡ ሶሓቦችም (ረዲየላሁ ዐንሁም) ‹‹ምንድናቸው እነዚህ መብቶች?›› ሲሉ፡ እሳቸውም፡- ‹‹ስታገኘው #ሰላምታን ልታቀርብለት፣ ሲጠራህ ጥርሪውን አክብረህ ልትገኝ፣ ምክርን ከፈለገ ልትመክረው፣ አስነጥሶ ጌታውን ካመሰገነ፡ የርሐሙከላህ ልትለው፣ ከታመመ ልትጎበኘው፣ ከሞተ ደግሞ ልትቀብረው›› በማለት መለሱላቸው" (ሙስሊም 5778)፡፡
ከዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "‹አስ-ሰላም› ከአላህ ሥሞች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ በምድር ላይ ሰዎች ይከባበሩበት ዘንድ አኖረው፡፡ እናንተም በመሀከላችሁ #ሰላም! በመባባል አሰራጩት፡፡ አንድ ሙስሊም በሰዎች በኩል ሲያልፍ፡ ኢስላማዊ ሰላምታን አቅርቦላቸው እነሱም ምላሽን ከሰጡት፡ እሱ ሰላምታውን ጀማሪ በመኾን ስላስታወሳቸው፡ በነሱ ላይ አንድ ብልጫ ይኖረዋል፡፡ እነሱ ምላሹን ባይሰጡት ደግሞ ከነሱ የተሸሉ ንጹሀን መላእክት ይመልሱለታልና" (ሙስነድ አል-በዝዛር 1771፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 3697፣ ሶሒሑ-ተርጊብ ወት-ተርሂብ 2705)፡፡
ከአቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "በመንገድ ላይ መቀመጥን አደራችሁ ተጠንቀቁ!፡፡ ሶሓቦችም (ረዲየላሁ ዐንሁም) ‹‹የምንጨዋወትበት መሰባሰቢያችን ነውና ከመቀመጥማ ምንም ቅሮት የለንም›› አሉ፡፡ መልክተኛውም፡- ‹‹መሰባሰብን እንጂ እምቢ ካላችሁማ፡ እንግዲያውስ የመንገድን ሐቅ ጠብቁ!›› አሏቸው፡፡ እነሱም ‹‹የመንገድ ሐቅ ምንድነው?›› ብለው ሲጠይቁ፡ የአላህ መልክተኛም፡- ‹‹አይናችሁን መስበር፣ ሰውን አለማስቸገር፣ #ሰላምታን መመለስ፣ እንቅፋት ነገርን ከመንገዱ ማስወገድ፣ ሰዎችን በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነው›› በማለት መለሱላቸው" (ቡኻሪይ 2465)፡፡

5ኛ/ ኢስላማዊ ሰላምታን መለዋወጥ፡ ለጀማሪውም ኾነ ለመላሹ ከአሥር ጀምሮ እስከ ሰላሳ ሐሰናት (አጅርን) ያስገኛል፡፡ በአላህ ቸርነት ጀነት ለመግባትም ሰበብ ይኾናል፡፡ በምቀኝነትና በጥላቻ በሽታ ለተጠቃ ሰውም ፍቱን መድኃኒት ይኾነዋል፡፡
ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-"ነፍሴ በእጁ በኾነችው ጌታ ይሁንብኝ! ጀነትን እስክታምኑ ድረስ አትገቡም!፣ እስካልተዋደዳችሁ ድረስም አታምኑም!፡፡ ከተገበራችሁት ሊያዋድዳችሁ የሚችል ነገርን አላመላክታችሁምን? በመሐከላችሁ #ሰላምታን አብዙ" (ሙስሊም 203፣ አቡ ዳዉድ 5195፣ ኢብኑ ማጀህ 71፣ ቲርሚዚይ 2699፣ ሶሒሕ ኢብኑ-ሒብባን 236)፡፡
ከዐብዱላህ ኢብኑ-ሰላም (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ አለ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መዲና እንደገቡ መጀመሪያ የተናገሩት ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! #ሰላምታን አብዙ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት ተነስታችሁ ስገዱ፣ ጀነትን በ
5. "አስ-ሰላም"
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
ሀ. ትርጉሙ፡-
"አስ-ሰላም" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- የሰላም ባለቤት፤ ነውር አልባ የሚል ነው፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አስ-ሰላም" የሚለው ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-
" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23
"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ #የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት
1. እርሱ አላህ የሰላም ባለቤት መሆኑን፡- ጌታችን "አስ-ሰላም" በመሆኑ ሰላም የሚገኘው ከሱ ዘንድ ብቻ ነው፡፡
" تَحِيَّتُهُمْ يَوْمَ يَلْقَوْنَهُ سَلَامٌ وَأَعَدَّ لَهُمْ أَجْرًا كَرِيمًا " سورة الأحزاب 44
"በሚገናኙት ቀን መከባበሪያቸው ሰላም በመባባል ነው፤ ለነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል።" (ሱረቱል አሕዛብ 44)፡፡
" سَلَامٌ قَوْلًا مِنْ رَبٍّ رَحِيمٍ " سورة يس 58
"(ለነሱም) አዛኝ ከሆነው ጌታ ቃል በቃል ሰላምታ አላቸው።" (ሱረቱ ያሲን 58)፡፡ ሶላታችንን ሰግደን ስናጠናቅቅ ከሶስት ጊዜ "አስተግፊሩላህ" በኋላ የምንለው ዚክርም ይህን ያመላክታል፡-
عَنْ ثَوْبَانَ، قَالَ: كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، إِذَا انْصَرَفَ مِنْ صَلَاتِهِ اسْتَغْفَرَ ثَلَاثًا وَقَالَ: «اللهُمَّ أَنْتَ السَّلَامُ وَمِنْكَ السَّلَامُ، تَبَارَكْتَ ذَا الْجَلَالِ وَالْإِكْرَامِ» مسلم.
ከሠውባን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው፡- የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሶላታቸውን እንዳጠናቀቁ ፡- "አስተግፊሩላህ (አላህ ሆይ ይቅርታህን እጠይቃለሁ) ሶስት ጊዜ፡ ከዛም፡- አላሁምመ አንተ-ሰላም (አላህ ሆይ! አንተ ሰላም ነህ!) ወሚንከ-ሰላም (ሰላምም የሚገኘው ካንተው ነው)… ይሉ ነበር" (ሙስሊም)፡፡
2. አማኞች ሰላምን እንደሚያገኙ፡- ጌታችን አላህ "አስ-ሰላም" በመሆኑ በሱ ላመኑ ባሪያዎቹ ውስታዊና ውጫዊ ሰላም ያጎናጽፋቸዋል፡፡
" فَأْتِيَاهُ فَقُولَا إِنَّا رَسُولَا رَبِّكَ فَأَرْسِلْ مَعَنَا بَنِي إِسْرَائِيلَ وَلَا تُعَذِّبْهُمْ قَدْ جِئْنَاكَ بِآيَةٍ مِنْ رَبِّكَ وَالسَّلَامُ عَلَى مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَى " طه 47
"ወደርሱም ኺዱ፤ በሉትም፦ እኛ የጌታህ መልክተኞች ነን፤ የእስራኤልንም ልጆች፣ ከኛ ጋር ልቀቅ፤ አታሰቃያቸውም፤ ከጌታህ በሆነው ታምር በእርግጥ መጥተንሃልና፤ #ሰላምም ቀጥታን በተከተለ ሰው ላይ ይሁን።" (ሱረቱ ጣሀ 47)፡፡
" قُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ وَسَلَامٌ عَلَى عِبَادِهِ الَّذِينَ اصْطَفَى آللَّهُ خَيْرٌ أَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة النمل 59
"(ሙሐመድ ሆይ) በል «ምስጋና ለአላህ ይግባው፡፡ በእነዚያም በመረጣቸው ባሮቹ ላይ #ሰላም ይውረድ፡፡ አላህ በላጭ ነውን ወይስ ያ የሚያጋሩት (ጣዖት)፡፡" (ሱረቱ-ነምል 59)፡፡
" وَسَلَامٌ عَلَى الْمُرْسَلِينَ * وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ " سورة الصافات 182-181
"በመልክተኞቹም ላይ #ሰላም ይኹን፤ ምስጋናም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይሁን" (ሱረቱ-ሷፍፋት 181-182)፡፡
3. ጀነት ለመግባት ሰበብ መሆኑን፡- ጌታችን አላህ "አስ-ሰላም" በመሆኑ በዚህ ምድር ላይ እኛ አማኝ ባሪያዎቹ ሰላምታን ማብዛት እንዳለብን ተነግሮናል፡፡ ይህንን የሚያደርግም ጀነት እንደሚገባ ተገልጾአል፡፡ ቀጣዩ ሐዲስም ይሐን ይጠቁማል፡-
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَا تَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ حَتَّى تُؤْمِنُوا، وَلَا تُؤْمِنُوا حَتَّى تَحَابُّوا، أَوَلَا أَدُلُّكُمْ عَلَى شَيْءٍ إِذَا فَعَلْتُمُوهُ تَحَابَبْتُمْ؟ أَفْشُوا السَّلَامَ بَيْنَكُمْ» مسلم.
ከአቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈው ሐዲሥ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "እስካላመናችሁ ድረስ ጀነትን አትገቡም፣ እስካልተዋደዳችሁ ድረስ አታምኑም፣ ከሰራችሁት ሊያዋድዳችሁ የሚችልን ነገር ላመላክታችሁን? #ሰላምታን በመሐከላችሁ አብዙ" (ሙስሊም)፡፡
በዚህም ምክንያት አንድ ሙስሊም ሌላኛውን ሙስሊም ባገኘው ጊዜ ‹ኢስላማዊ ሰላምታ› እንዲሰጠው ታዝዞአል፡፡
አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገሩን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሙስሊም በሙስሊሙ ላይ ስድስት መብቶች አሉት፡፡ ሶሐቦችም (ረዲየላሁ ዐንሁም) ፡- ‹‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምንድናቸው እነሱ?›› ብለው ሲጠይቁ፡ እሳቸውም፡- ሲያገኘው (አሰላሙ ዐለይኩም..) በማለት ሰላምታ ሊሰጠው…››በማለት መለሱ" (ሙስሊም 2162)፡፡
"እነዚያም በተአምራታችን የሚያምኑት (ወደ አንተ) በመጡ ጊዜ «ሰላም በእናንተ ላይ ይኹን፡፡ ጌታችሁ በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ እነሆ ከእናንተ ውስጥ በስሕተት ክፉን ሥራ የሠራ ሰው ከዚያም ከእርሱ በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ እርሱ (አላህ) መሓሪ አዛኝ ነው» በላቸው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 54)፡፡
4. ወደ ሰላም የሚመራ ጌታ መሆኑን፡- ጌታችን አላህ "አስ-ሰላም" በመሆኑ አማኝ ባሪያዎቹን በዚህ ዱንያ የሰላም መንገድ የሚመራ፡ በአኼራ ደግሞ የሰላም ሀገር ወደሆነችው ጀነት የሚጣራ አምላክ መሆኑን እንረዳለን፡-
"አላህ ውዴታውን የተከተሉትን ሰዎች #የሰላምን መንገዶች በርሱ ይመራቸዋል። በፈቃዱም ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል። ወደ ቀጥተኛም መንገድ ይመራቸዋል።" (ሱረቱል ማኢዳህ 16)፡፡
"አላህም ወደ #ሰላም አገር ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 25)፡፡
"ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ #የሰላም አገር አላቸው፡፡ እርሱም (ጌታህ) ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ረዳታቸው ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 127)፡፡
5. የመላእክት አቀባበል መሆኑ፡- አምላካችን አላህ "አስ-ሰላም" የሆነ አምላክ በመሆኑ፡ ነጌ በቂያም ዕለት አማኝ ባሪያዎቹን ወደ ጀነት ሲያስገባቸው መላእክት በየደጃፉ ሆነው የእንኳን ደህና መጣችሁ! ብ