Forwarded from 🇳 🇺 🇷 🇦
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጠቃሚ የፊቂህ ትምህርቶች
ክፍል 19
በዑስታዝ አቡሐይደር
ክፍል 19
በዑስታዝ አቡሐይደር
❤48👍11🥰1😁1
እንኳን ለ 1,446ኛው የዒዱል ፊጥር በዓል አላህ በሰላም አደረሳችሁ!
ጌታ አላ ህ ዒዱን የደስታ የምስጋናና የዚክር ያድርግልን
ዒዱኩም ሙባረክ!! ተቀበለሏሁ ሚንና ወሚንኩም
ጌታ አላ ህ ዒዱን የደስታ የምስጋናና የዚክር ያድርግልን
ዒዱኩም ሙባረክ!! ተቀበለሏሁ ሚንና ወሚንኩም
❤95👍38🥰13
ዐሹራእ ደረሰ
በአቡ ሀይደር
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን፡፡(አል-ፋቲሓ 2) ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
#ዐሹራእ ምንድነው?
ዐሹራእ ማለት (የሙሐረም ወር) አስረኛው ቀን ማለት ነው፡፡ አሁን ያለንበት ወር ሙሐረም አንደኛው ወር ተብሎ ይጠራል፡፡
#ይህ ወር ክብር ያለው ወር ነው
አቢ ሁረይራህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ከነቢያችን(ዐለይሂ ሶላቱ-ወስ-ሰላም) እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- "ከረመዷን ቀጥሎ ከጾሞች ሁሉ በላጩ የአላህ ወር የሆነው ሙሐረም ነው" (ሙስሊም 2812)፡፡
ከሙሐረም ወር ውስጥ ደግሞ አስረኛው የዐሹራእ ቀን በላጭ ቀን ነው፡፡
#ለምን ይጾማል?
ዐብደላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና ሲገቡ አይሁዶችን በዐሹራእ ቀን ሲጾሙ አገኟቸው፡፡ ይህን ቀን የምትጾሙት ለምንድነው? ብለው ሲጠይቋቸው፡ እነሱም፡- ይህ ታላቅ ቀን ነው! አላህ ሙሳንና ተከታዮቹን ከፊርዐውንና ሰራዊቱ በማዳን እነሱን በባሕር ያሰጠመበት ቀን ስለሆነ ሙሳም ለአላህ ምስጋናን ለማድረስ ጾሞታል እኛም እንጾመዋለን ብለው መለሱ፡፡ የአላህ መልክተኛውም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ፡- ለሙሳ (ወዳጅነት) ከናንተ ይልቅ እኛ የቀረብንና የተገባን ሰዎች ነን እኮ! በማለት እሳቸውም ጾሙት ሶሓባዎቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ" (ሙስሊም 2714)፡፡
ከዛ በፊት ግን በመካ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐሹራእን ይጾሙ ነበር ነገር ግን ማንንም አላዘዙም፡፡
#ጥቅሙስ ምንድነው?
አቢ ቀታዳህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዐረፋ ቀን ጾም አላህ ዘንድ ያለፈውንና የሚመጣውን (የሁለት) ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአቶችን ያስምራል፣ የዐሹራእ ቀን ጾም ደግሞ ያለፈውን አንድ ዓመት (ትናንሽ) ኃጢአት ያስምራል" (ሙስሊም 1976)፡፡
ዐብደላህ ኢብኑ ዐባስ(ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ አለ፡- የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የዐሹራእን ቀን የጾሙና ሶሓቦቻቸውን ያዘዙ ጊዜ፡- "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህን ቀን እኮ አይሁዶችና ክርስቲያኖች ያከብሩታል ሲሏቸው፡ እሳቸውም፡- በቀጣዩ ዓመት አላህ ካደረሰን ዘጠነኛውን ቀን እንጾማለን አሉ፡፡" (ሙስሊም 2722)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ "ከ(ዐሹራእ) ቀን ከፊቱ ወይም ከኋላው አንድን ቀን ጹሙ" ብለዋል (አሕመድ የዘገቡት)፡፡
ያ ዓመት ሳይደርስ የአላህ መልክተኛ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ የኢስላም ሊቃውንትም ከዚህ ሐዲሥ በመነሳት የሁዳዎችን ላለመመሳሰል ዘጠነኛውንም ቀን ጨምሮ መጾም ነቢያዊ ሱንና መሆኑን ገለጹ፡፡
#መጾሙ ዋጂብ ነው ወይስ ሱንና?
የዐሹራእን ቀን መጾም ሑክሙ ሱንና ነው፡፡ በሒጅራ 2ኛው ዓመት የመጀመሪያው ወር ሙሐረም ላይ ስለነበር የተደነገገው የረመዷን ጾም እስኪደነገግ ድረስ ዋጂብ ነበር፡፡ ከ7 ወር በኋላ ግን በሒጅራ 2ኛው ዓመት 8ኛው ወር ሻዕባን ላይ የረመዷን ጾም ግዳጅነት ሲደነገግ፡ ዐሹራእ ግዳጅነቱ ተሰረዘ፡፡ ይህን በተመለከተ ቀጣዩ ሐዲሥ እንዲህ ይላል፡-
እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ አለች፡- "የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ረመዷን ሳይደነገግ በፊት ዐሹራእን ይጾሙ ነበር፡፡ ካዕባም የሚሸፈንበት ቀን ነበር፡፡ አላህ ረመዷንን በደነገገበት ጊዜ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- የፈለገ ሰው (ዐሹራእን) ይጹመው ለመጾም ያልፈለገ ደግሞ ይተወው" (ቡኻሪይ 1489)፡፡
#መቼ እንጀምር?
የሙሐረም አስረኛው ቀን(ዐሹራእ) የፊታችን ቅዳሜ ነው የሚውለው፡፡ ስለዚህ አላህ ወፍቆት ይህን ዐሹራእን መጾም የፈለገ ከአራቱ መንገዶች አንዱን መርጦ ይጹም፡-
ሀ. ቅዳሜን ብቻ፡- 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ዋናው ዐሹራእ ተብሎ የሚጠራውም ይህ ቀንነው፡፡
ለ. ጁምዓና ቅዳሜን ፡- 9ኛውንና 10ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም በላጭ ነው፡፡
ሐ. ከ ጁምዓ-እሁድ ፡- 9ኛ፣10ኛና 11ኛውን ቀን ማለት ነው፡፡ ይህ ከሁሉም በላጩ ነው፡፡
መ. ቅዳሜና እሁድ፡- 10ኛውና 11ኛውን ቀን መጾም ማለት ነው፡፡ ይህም ሱንና ነው
አላህ ይወፍቀን፡፡
#ስምንቱ የፆም ቀናት
አላህ ፆምን ያገራለትና የወፈቀው ሰው ደግሞ ከፈለገ በተከታታይ ለስምንት ቀናት መፆም ይችላል፡፡ እንዴት ካሉም፡-
ሀሙስ፡- ይህ 8 ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡
ከጁምዓ-እሁድ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐመረም 9ኛ 10ኛና 11ኛ ቀናት ስለሆኑ፡ ከዐሹራእ ፆም ጋር በተያያዘ መልኩ ይፆማሉ ማለት ነው፡
ሰኞ፡- ይህ 12ኛው ቀን በራሱ የሱንና ፆም ቀን በመሆኑ ይፆማል ማለት ነው፡፡
ማክሰኞ -ሀሙስ ፡- እነዚህ ሶስት ቀናት የሙሐረም 13ኛ 14ኛና 15ኛ ቀናት ናቸው፡፡ አያሙል-ቢድ በመባልም ይጠራሉ፡፡ የወሩን ሶስት ቀናት በነዚህ ቀናት መፆም በላጭ ነው፡፡
Click and Like ➤➤ http://fb.com/Ustaz.Abuhyder

❤86👍17🥰5🍓5💯1😇1
አስቸኳይ የህክምና እርዳታ
ልጅ ረያን አብዱልከሪም አሊዪ AML የሚባል አጣዳፊ የደም ካንሰር ህክምና ታክሞ በማገገም ላይ እያለ ድጋሜ ያገረሸበት በመሆኑ የመቅኒ ቅያሬ ህክምና ለመዳን ብቸኛ አማራጭ መንገድ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም ይህ ህክምና ሀገር ውስጥ የሌለ በመሆኑ ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ ህክምናውን እንዲከታተል በሜዲካል ቦርድ ተወስኗል :: በመሆኑ የምትችሉትን ድጋፍ እንድታደርጉ ጥሪ ቤተሰቦቹ ጥሪ ያቀርባሉ::
ድጋፍ ለማድረግ የጎፈንድሚ ሊንክ
https://gofund.me/5dc21ab6
አካውንት Abdulkerim Aliyi Haji
Comertial bank of ethiopia 1000440849036
Awash Bank 01320157558300
Absinia 34482357
Oromia Coporative 1075100075079

💔21❤6