የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
Audio
ረቢዑል አወል እና ረሱል ﷺ ወሳኝ ሙሐደራ
☞በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/2C8ENxj

Join us➤ t.me/abuhyder
እናንተ ሙስሊሞች በክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ካላመናችሁ፣ ትንሳኤ መኖሩን እንዴት አረጋገጣችሁ?

ለ "አንድ አምላክ አብ አለን" ጥያቄ ምላሽ

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡

ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ(ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡

" وَاتَّقُوا يَوْمًا تُرْجَعُونَ فِيهِ إِلَى اللَّهِ ثُمَّ تُوَفَّى كُلُّ نَفْسٍ مَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ " سورة البقرة 281
"በእርሱም ውስጥ ወደ አላህ የምትመለሱበትንና ከዚያም እነርሱ የማይበደሉ ሲሆኑ ነፍስ ሁሉ የሠራችውን ሥራ የምትሞላበትን ቀን ተጠንቀቁ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 281)፡፡

በመጨረሻው ዓለም (በአኼራ) መኖር ማመን፡ በኢስላም ከስድስቱ የእምነት ማእዘናት ውስጥ አንድ ማእዘን ነው፡፡ በገይብ (ከስሜት ህዋስ የራቀ ነገር) ማመን ከሚባሉት ውስጥም ይካተታል፡፡ በዚህ ምድር ላይ መልካም ሰዎችና መልካም ተግባራትም እንዲኖሩ የሚያደርገው የዚሁ ቀን (አኼራ) መኖር ነው፡፡ እኛ ሙስሊሞች በአይናችን ባየነውና በእጃችን በዳሰስነው፡ እንዲሁም በጆሮአችን በሰማነው ነገር ብቻ አይደለም የምናምነው፡፡ ከስሜት ህዋሳቶቻችን ውጪ በሆኑ፣ በምርምር ብዛትም ሊደረስባቸው በማይችሉ ነገራትም የቅዱስ ቁርኣንና የነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱንና በመከተል እናምናለን፡፡ ምክንያቱም በሰው ቁጥጥርና እይታ ውስጥ ከገባው የዓለም ክፍል ይልቅ ገና ያልገባውና በአይን ያልታየ፡ ከቁጥጥራችን ውጪ የሆነው የዓለም ክፍል በእጅጉ ይበልጣልና፡፡ ሆኖም አምነን የምንቀበለው የዓለሙ ፈጣሪና አስገኚ የሆነው አላህ በቅዱስ ቁርኣኑ እና በነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ሱንና አማካኝነት በተነገረንና በደረሰን ዕውቀት መሰረት ነው፡፡
ለዛሬ የማስተላልፍላችሁ መልእክት፡- ከሞት በኋላ ዳግም መቀስቀስና ህይወት መኖሩን፣ የሞተ ሰው ሁሉ ከመቃብር ድጋሚ ነፍስ ተዘርቶበት የሚቀሰቀስ መሆኑን ለማሳመን ቅዱስ ቁርኣን ከተጠቀመባቸው መንገዶች መሐከል የተወሰነውን ነው፡፡
ምክንያቱም ማን ሄዶ አየው? የሚል ጥያቄ ኢ-አማንያን ዘንድ የሚነሳ ስለሆነ፡ እኛም ምላሽ ለመስጠት ይረዳን ዘንድ ከወዲሁ እንድንዘጋጅ ነው፡፡

በፍጹም እርግጠኝነት፡ እንዲሁም በጌታዬ ስም በመማል ልነግራችሁ የምችለው ነገር ቢኖር፡- ከሞት በኋላ ህይወት መኖሩን ለማሳመን፡ ቅዱስ ቁርኣን ያቀረባቸውን አሳማኝ ነጥቦችና የተጠቀማቸውን ስልቶች፡ ከኢስላም ውጪ ባሉ ሃይማኖች መጽሐፍ ውስጥ አንድ ላይ ቢደመሩ እንኳ፡ የቁርኣኑን ሩብ ያህል ሊገልጹ እንደማይችሉ ነው፡፡

እስኪ እንዲህ እርግጠኛ የሚያደርገን ቅዱስ ቁርኣን እንዴት ቢያስተምር ነው? የሚለውን ለማየት፡ ወደ ቁርኣኑ ጎራ እንበልና ከማእዱ እንቋደስ፡-

1. የመጀመሪያው አፈጣጠራችን፡-

በብዙ የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾች ውስጥ ሰዎች ከሞት በኋላ ዳግም ህይወት እንዳለ እና እንደሚቀሰቀሱ ለመግለጽ የመጀመሪያውን አፈጣጠራቸውን እንደ ማስረጃ ይጠቀማል፡፡ ትላንት ከሌለንበት ዓለም ምንም ሳይቸግረውና ሳይከብደው፡ ከፈሳሽ ውሀ ከ(sperm cell) በሶስት ጨለማዎች ውስጥ (በሆድ፣ በማህጸንና በእንግዴ ልጅ) የፈጠረንና ያስገኘን አላህ፡ ዛሬ ካለንበት መቃብር ውስጥ ዳግም ነፍስን በመዝራት ለመቀስቀስ ምንም ሊከብደው እንደማይችል በመግለጽ ያስረዳል፡፡ የሌለን ነገር በማስገኘት መፍጠር የቻለ አላህ፡ እንዴት ያለን ነገር ነፍስ በመዝራት መመለስ ያቅተዋል? እያለን ነው፡፡ ቀጣዮቹን ቁርኣናዊ አንቀጾች እንመልከታቸው፡-
" وَقَالُوا أَإِذَا كُنَّا عِظَامًا وَرُفَاتًا أَإِنَّا لَمَبْعُوثُونَ خَلْقًا جَدِيدًا * قُلْ كُونُوا حِجَارَةً أَوْ حَدِيدًا * أَوْ خَلْقًا مِمَّا يَكْبُرُ فِي صُدُورِكُمْ فَسَيَقُولُونَ مَنْ يُعِيدُنَا قُلِ الَّذِي فَطَرَكُمْ أَوَّلَ مَرَّةٍ فَسَيُنْغِضُونَ إِلَيْكَ رُءُوسَهُمْ وَيَقُولُونَ مَتَى هُوَ قُلْ عَسَى أَنْ يَكُونَ قَرِيبًا * يَوْمَ يَدْعُوكُمْ فَتَسْتَجِيبُونَ بِحَمْدِهِ وَتَظُنُّونَ إِنْ لَبِثْتُمْ إِلَّا قَلِيلًا " سورة الإسراء 52-49
"አሉም፦ እንዴት አጥንቶችና ብስብሶች በሆን ጊዜ እኛ አዲስ ፍጥረት ሆነን በእርግጥ ተንቀሳቃሾች ነን? በላቸው፦ደንጊያዎችን ወይም ብረትን ሁኑ፤ ወይም በልቦቻችሁ ውስጥ የሚተልቅን ፍጥረት (ሁኑ መቀስቀሳችሁ አይቀርም)፡፡ የሚመልሰንም ማነው? ይላሉ፤ ያ በመጀመሪያ ጊዜ የፈጠራችሁ ነው በላቸው፤ ወደ አንተም ራሶቻቸውን ይነቀንቃሉ እርሱም መቼ ነው ይላሉ፤ (እርሱ) ቅርብ ሊሆነን ይቻላል በላቸው። (እርሱም) የሚጠራችሁና (አላህን) አመስጋኞቹ ሆናችሁ ጥሪውን የምትቀበሉበት ጥቂትንም (ቀኖች) እንጂ ያልቆያችሁ መሆናችሁን የምትጠራጠሩበት ቀን ነው (በላቸው)።" (ሱረቱል ኢስራእ 49-52)፡፡
" أَوَلَمْ يَرَ الْإِنْسَانُ أَنَّا خَلَقْنَاهُ مِنْ نُطْفَةٍ فَإِذَا هُوَ خَصِيمٌ مُبِينٌ * وَضَرَبَ لَنَا مَثَلًا وَنَسِيَ خَلْقَهُ قَالَ مَنْ يُحْيِ الْعِظَامَ وَهِيَ رَمِيمٌ * قُلْ يُحْيِيهَا الَّذِي أَنْشَأَهَا أَوَّلَ مَرَّةٍ وَهُوَ بِكُلِّ خَلْقٍ عَلِيمٌ " سورة يس 79-77
"ሰውየው እኛ ከፍቶት ጠብታ የፈጠርነው መሆናችን አላወቀምን? ወዲያውም እርሱ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይሆናልን? ለኛም ምሳሌን አደረገልን፤ መፈጠሩንም ረሳ አጥንቶችን እነርሱ የበሰበሱ ሲሆኑ ሕያው የሚያደርጋቸው ማነው? አለ። ያ በመጀመሪያ ጊዜ (ከኢምንት) ያስገኛት ሕያው ያደርጋታል፤ እርሱም በፍጡሩ ሁሉ (ሁነታ) ዐዋቂ ነው በለው።" (ሱረቱ ያሲን 77-79)፡፡
" أَيَحْسَبُ الْإِنْسَانُ أَنْ يُتْرَكَ سُدًى * أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِنْ مَنِيٍّ يُمْنَى * ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّى * فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنْثَى * أَلَيْسَ ذَلِكَ بِقَادِرٍ عَلَى أَنْ يُحْيِيَ الْمَوْتَى " سورة القيامة 40-36
"ሰው ስድ ሆኖ መትተውን ይጠረጥራልን? የሚፈሰስ የሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? ከዚያም የረጋ ደም ሆነ፤ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፤ አስተካከለውም። ከርሱም ሁለት ዓይነቶችን፣ ወንድና ሴትን አደረገ። ይህ (ጌታ) ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ አይደለምን?" (ሱረቱል ቂያማህ 36-40)፡፡
2. ሙታንን ህያው በማድረግ፡-

ሌላው ሰዎች ከሞቱ በኋላ ዳግም እንደሚቀሰቀሱ ለማረጋገጥ ቅዱስ ቁርኣን የሚጠቀመው ማስረጃ፡ አላህ በነቢያት በኩል ማስረጃ ይሆናቸው ዘንድ፡ ከዚህ በፊት ሞተው የነበሩ ሰዎችን ህያው ማድረጉን በመጥቀስ ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎችን ከሞቱበት ዓለም አላህ ዳግም ህያው አድርጓቸዋል፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
ሀ. 70ዎቹ የሙሳ ሰዎች፡- ሙሳ ከጌታው ጋር የነበረውን የአርባ ቀን ቀጠሮ ጨርሶ ሲመለስ፡ እነዚህ ሰዎች፡- ሙሳ ሆይ ከጌታዬ ጋር ቀጠሮ አለኝ እያልህ እንደፈለግህ አናግረኸውና አይተኸው ትመጣለህ፡፡ እኛም እንዳንተ ጌታህን ካላየነው አናምንልህም! ባሉና ባመጹ ጊዜ የተከሰተው ይህ ነበር፡-
" وَإِذْ قُلْتُمْ يَا مُوسَى لَنْ نُؤْمِنَ لَكَ حَتَّى نَرَى اللَّهَ جَهْرَةً فَأَخَذَتْكُمُ الصَّاعِقَةُ وَأَنْتُمْ تَنْظُرُونَ * ثُمَّ بَعَثْنَاكُمْ مِنْ بَعْدِ مَوْتِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ " سورة البقرة 56-55
"«ሙሳ ሆይ! አላህን በግልጽ እስከምናይ ድረስ ላንተ በፍጹም አናምንልህም» ባላችሁም ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ እናንተም እየተመለከታችሁ መብረቅ ያዘቻችሁ፡፡ ከዚያም ታመሰግኑ ዘንድ ከሞታችሁ በኋላ አስነሳናችሁ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 55-56)፡፡
ለ. የኢብራሂም ወፎች፡- አላህ ሙታንን ከመቃብራቸው እንደሚያስነሳ የሚያውቀውና የሚያምነው ነቢ ኢብራሂም (ዐለይሂ ሰላም)፡ አሁን ደግሞ ከዕውቀት ወደ ማየት መሸጋገርን ፈልጎ፡ ጌታውን ሙታንን እንዴት እንደሚያስነሳ እንዲያሳየው ተማጸነ፡፡ ምላሹም እንዲህ ተሰጠው፡-
" وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّ أَرِنِي كَيْفَ تُحْيِ الْمَوْتَى قَالَ أَوَلَمْ تُؤْمِنْ قَالَ بَلَى وَلَكِنْ لِيَطْمَئِنَّ قَلْبِي قَالَ فَخُذْ أَرْبَعَةً مِنَ الطَّيْرِ فَصُرْهُنَّ إِلَيْكَ ثُمَّ اجْعَلْ عَلَى كُلِّ جَبَلٍ مِنْهُنَّ جُزْءًا ثُمَّ ادْعُهُنَّ يَأْتِينَكَ سَعْيًا وَاعْلَمْ أَنَّ اللَّهَ عَزِيزٌ حَكِيمٌ " سورة البقرة 260
"ኢብራሂምም «ጌታዬ ሆይ! ሙታንን እንዴት ሕያው እንደምታደርግ አሳየኝ» ባለ ጊዜ (አስታውስ፡፡) አላህ ፡- «አላመንክምን» አለው፡፡ «አይደለም (አምኛለሁ)፤ ግን ልቤ እንዲረጋ» ነው አለ፡፡ (አላህም)፡- «ከበራሪዎች (ከወፎች) አራትን ያዝ፡፡ ወደ አንተም ሰብስባቸው፡፡ (ቆራርጣቸውም)፤ ከዚያም በየኮረብታው ሁሉ ላይ ከነርሱ ቁራጭን አድርግ፡፡ ከዚያም ጥራቸው፤ ፈጥነው ይመጡሃልና፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ መኾኑን ዕወቅ» አለው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 260)፡፡
ሐ. የዑዘይር አህያና ሰውነቱ፡- የአላህ መልካም ባሪያ የነበረው ዑዘይር (ዐለይሂ-ሰላም) በአንዲት መንደር ሲያልፍ፡ መንደሪቷ ፈራርሳ፡ ቤቶቿ ወድመው፡ አረንጓዴዎቿ ረግፈው ምድር ከውሀ እጦት ተሰነጣጥቃ (ሞታ) ባያት ጊዜ፡ በመገረም፡- አሁን አላህ ይህችን መንደር ከሞተች በኋላ እንዴት ነው ህያው የሚያደርጋት! አለ፡፡ አላህም ሁሉን ቻይነቱን በራሱ ሊያሳየው ስለፈለገ ገደለው፡፡ መቶ ዓመትም አቆይቶ ቀሰቀሰው፡፡ ለዑዘይር የአንድ ቀን ቆይታ ቢመስለውም የቆየው ለመቶ ዓመት ያህል ነበር፡፡ አላህ እሱን መጀመሪያ ህያው ካደረገው በኋላ አህያይቱንም እንዴት እንደሚያስነሳት፡ አጥንቶቿንና ስጋዎቿን እንዴት ወደነበረበት እንደሚመልሳት እንዲመለከት አደረገው፡፡ ይዞት የነበረውንም ስንቅ በዚህ የመቶ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምንም እንዳልተለወጠ ተመልከት አለው፡፡ በዚህ መልክ አላህ ሁሉን ቻይ ጌታ መሆኑን በተግባር አሳየው፡፡ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
" أَوْ كَالَّذِي مَرَّ عَلَى قَرْيَةٍ وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَى عُرُوشِهَا قَالَ أَنَّى يُحْيِي هَذِهِ اللَّهُ بَعْدَ مَوْتِهَا فَأَمَاتَهُ اللَّهُ مِائَةَ عَامٍ ثُمَّ بَعَثَهُ قَالَ كَمْ لَبِثْتَ قَالَ لَبِثْتُ يَوْمًا أَوْ بَعْضَ يَوْمٍ قَالَ بَلْ لَبِثْتَ مِائَةَ عَامٍ فَانْظُرْ إِلَى طَعَامِكَ وَشَرَابِكَ لَمْ يَتَسَنَّهْ وَانْظُرْ إِلَى حِمَارِكَ وَلِنَجْعَلَكَ آيَةً لِلنَّاسِ وَانْظُرْ إِلَى الْعِظَامِ كَيْفَ نُنْشِزُهَا ثُمَّ نَكْسُوهَا لَحْمًا فَلَمَّا تَبَيَّنَ لَهُ قَالَ أَعْلَمُ أَنَّ اللَّهَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة البقرة 259
"ወይም ያንን በከተማ ላይ እርሷ በጣራዎችዋ ላይ የወደቀች ስትኾን ያለፈውን ሰው ብጤ (አላየህምን)፡- «ይህችን (ከተማ) ከሞተች በኋላ አላህ እንዴት ሕያው ያደርጋታል» አለ፡፡ አላህም ገደለው መቶ ዓመትን (አቆየውም)፡፡ ከዚያም አስነሳው፡- «ምን ያህል ቆየህ» አለው፡፡ «አንድ ቀን ወይም የቀንን ከፊል ቆየሁ» አለ፡፡ «አይደለም መቶን ዓመት ቆየህ፡፡ ወደ ምግብህና ወደ መጠጥህም ያልተለወጠ ሲኾን ተመልከት፡፡ ወደ አህያህም ተመልከት፡፡ ለሰዎችም አስረጅ እናደርግህ ዘንድ (ይህንን ሠራን)፡፡ ወደ ዐፅሞቹም እንዴት እንደምናስነሳት ከዚያም ሥጋን እንደምናለብሳት ተመልከት» አለው፡፡ ለርሱም (በማየት) በተገለጸለት ጊዜ፡- «አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መኾኑን ዐውቃለሁ» አለ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 259)፡፡
እዚህ ላይ ዑዘይር የቆየው ለመቶ ዓመት ሁኖ ሳለ፡ ጌታው በጠየቀው ጊዜ ግን ቀንን ወይም የቀንን ከፊል ቆየሁ ለምን አለ? የሚለው ላይ ከአንድ ተፍሲር ላይ ያገኘሁት ማብራሪያ እንዲህ ይላል፡-
‹‹አላህ ዑዘይርን የገደለው የቀኑ መጀመሪያ ሰዓት አካባቢ ነበር፡፡ ከመቶ ዓመት በኋላ ሲቀሰቅሰው ደግሞ ጸሀይ መጥለቂያ ሰዓት አካባቢ ስለሆነ፡ ዑዘይር ማወቅ የሚችለው ነገር ቅድም ጸሀይ ወጥታ እንደነበርና አሁን ደግሞ ልትጠልቅ መቃረቧን ነው፡፡ በዚህ መሀል የቆየባቸውን ቀናቶች በፍጹም አያውቅም፡፡ ስለዚህም እኔ የቆየሁት ቀንን ወይም የቀንን ከፊል ነው በማለት ተናገረ፡፡›› (ዛዱል ሙሲር ፊ-ዒልሚ ተፍሲር፡ ዐብዱራሕማን አል-ጀውዚይ)፡፡

መ. ሞትን የሸሹ ህዝቦች፡-

በድሮ ዘመን በበኒ ኢስራኢሎች ውስጥ ዳወርዳን በተባለች መንደር ውስጥ ነዋሪ የነበሩ ህዝቦች፡ ወረርሺኝ ሲከሰትባቸው ከሞት ለማምለጥ በማሰብ መንደራቸውን ለቀው ወደ ሌላ ከተማ ሲሸሹ አላህ በመለኮታዊ ትእዛዙ "ሙቱ" በማለት ገደላቸው፡፡ ኢብኑ ከሢር (ረሒመሁላህ) ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስን (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ዋቢ አድርገው እንደገለጹት ህዝቦቹ ወደ 4.000 ወይም 40.000 የሚደርሱ ናቸው፡፡ ታዲያም በነዚህ ሰዎች መንደር አንድ ነቢይ (ስሙ አልተነገረም) ሲያልፍ፡ ሁኔታውን አይቶ አላህን በመማጸን ዳግም ነፍስ እንዲዘሩ ከሞት እንዲነሱ ሆነዋል፡፡ ይህም የሚያመላክተው፡- የአላህን ችሮታ (ቸርነት) እንዲሁም ዳግም መቀስቀስ መኖሩን እና ከሞት ማንም ሊያመልጥ እንደማይችል ነው፡፡ ቀጣዩም አንቀጽ ይህን ይገልጻል፡-
" أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِينَ خَرَجُوا مِنْ دِيَارِهِمْ وَهُمْ أُلُوفٌ حَذَرَ الْمَوْتِ فَقَالَ لَهُمُ اللَّهُ مُوتُوا ثُمَّ
أَحْيَاهُمْ إِنَّ اللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى النَّاسِ وَلَكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ " سورة البقرة 243
"ወደ እነዚያ እነርሱ ብዙ ሺሕ ኾነው ሞትን ለመፍራት ከሀገሮቻቸው ወደ ወጡት ሰዎች ዕውቀትህ አልደረሰምን? አላህም ለነርሱ «ሙቱ» አላቸው፤ (ሞቱም)፡፡ ከዚያም ሕያው አደረጋቸው፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ባለችሮታ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 243)፡፡
ሠ. የአጎቱ ገዳይ ታሪክ፡- ጉዳዩ እንዲህ ነው፡፡ በበኒ ኢስራኢሎች ውስጥ አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህም ሰው ሐብታም ነበር፡፡ ዘር ግን አልነበረውም፡፡ የሚወርሰው አንድ የወንድሙ ልጅ አለ፡፡ ይህ ልጅ የአጎቱን ንብረት ቶሎ ለመውረስ በመጓጓት አጎቱን ይገድለውና በሌሊት ሬሳውን ተሸክሞ ሰው ቤት ደጃፍ ይጥለዋል፡፡ በነጋታውም የአጎቴ ገዳዮች በማለት ሬሳው የተጣለበትን ቤት ይከሳል፡፡ ሰይፍን አንግበው እስከመማዘዝም ደርሰው ነበር፡፡ ከመሀከላቸው አስተዋይና ዐዋቂዎች የነበሩትም፡- እርስ በርስ ከመፋጀታችሁ ይልቅ ለምን ነቢይ ወደሆነው ሙሳ ዘንድ በመሄድ የገዳዩን ማንነት እንዲነግራችሁ አታደርጉምን? ይሏቸዋል፡፡ እነሱም ወደ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዘንድ በመምጣት ጉዳዩን ይነግሩታል፡፡ እሱም ከአላህ ዘንድ በተነገረው መሰረት፡- ‹‹አላህ ላምን እረዱ!›› ብሏችኋል አላቸው፡፡ እነሱም፡- ‹‹እኛ ገዳይን ትነግረናለህ ብለን ወዳንተ ብንመጣ አንተ ትሳለቅብናለህን?›› ሲሉት፡ ሙሳም፡- ‹‹በመሳለቅ ከመሀይማን ጎራ ከመሆን በአላህ እጠበቃለሁ!›› አላቸው፡፡ ጉዳዩ የምር መሆኑን ሲረዱ፡ እንደታዘዙት ከከብቶቻቸው መሐል አንዲትን ላም ወስደው ማረድ ሲገባቸው፡ በለመደው ትእቢታቸው ‹‹ምን አይነት ላም እንደሆነች ጌታህን ጠይቅልን›› አሉት፡፡ እሱም፡- ‹‹ያላረጀችና ድንግልም(ጥጃ) ያልሆነች ናት›› ብሏል ጌታችሁ አላቸው፡፡ እነሱም አሁንም በትእቢት ‹‹መልኳስ?›› አሉ፡፡ እሱም ‹‹ዳልቻ መልክ ያላት ደማቅና ተመልካቾችን የምታስደስት›› ናት ተብላችኋል አላቸው፡፡ እነሱም በድጋሚ ‹‹ምን አይነት እንደሆነች ይብራራልንና አላህ ከፈቀደ እናርዳታለን ላሞች ሁሉ ተመሳስለውብናልና›› አሉ፡፡ ሙሳም፡- ‹‹እሷ ምድርን በማረስ ያልተገራች፡ አዝመራንም በማጠጣት ያልደከመች፡ ከነውር የጻዳችና ምንም አይነት ምልክት የሌለባት ናት›› ተብላችኋል ሲላቸው፡ እነሱም ‹‹አሁን በትክክል መጣህ!›› በማለት ለማረድ ያልፈለጉ ሆነው ገዳዩን ለማወቅ ግን አረዷት፡፡ ከዛም አላህ በሙሳ በኩል፡- ‹‹ሟችን ከታረደችው ላም ከፊል ስጋን ቁረጡና ምቱት!›› በማለት ትእዛዝን ሰጣቸው፡፡
እነሱም ያንን ሲፈጽሙ ሟች ተነሳና የገደለው የወንድሙ ልጅ መሆኑን ተናገረ፡፡ አላህ በዚህ አይነት መልኩ ያለአግባብ ለተከሰሱት ፍትሐዊ ዳኛ መሆኑን በማሳወቅ፣ የሙሳን ነቢይነት በማስረጃ በማጠናከር፡ የሱን ሁሉን ቻይነት በተግባር በማሳየት፡ ነጌም ከሞት በኋላ መቀስቀስ መኖሩን አመላከታቸው ማለት ነው፡፡ (ተፍሲር ኢብኑ ከሢር)፡፡ ይህ ታሪክ በተከታዮቹ ቁርኣናዊ አንቀጾች ውስጥ ይገኛል፡-
" وَإِذْ قَالَ مُوسَى لِقَوْمِهِ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَنْ تَذْبَحُوا بَقَرَةً قَالُوا أَتَتَّخِذُنَا هُزُوًا قَالَ أَعُوذُ بِاللَّهِ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْجَاهِلِينَ * قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّنْ لَنَا مَا هِيَ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَا فَارِضٌ وَلَا بِكْرٌ عَوَانٌ بَيْنَ ذَلِكَ فَافْعَلُوا مَا تُؤْمَرُونَ * قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّنْ لَنَا مَا لَوْنُهَا قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ صَفْرَاءُ فَاقِعٌ لَوْنُهَا تَسُرُّ النَّاظِرِينَ * قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّنْ لَنَا مَا هِيَ إِنَّ الْبَقَرَ تَشَابَهَ عَلَيْنَا وَإِنَّا إِنْ شَاءَ اللَّهُ لَمُهْتَدُونَ * قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَا ذَلُولٌ تُثِيرُ الْأَرْضَ وَلَا تَسْقِي الْحَرْثَ مُسَلَّمَةٌ لَا شِيَةَ فِيهَا قَالُوا الْآنَ جِئْتَ بِالْحَقِّ فَذَبَحُوهَا وَمَا كَادُوا يَفْعَلُونَ * وَإِذْ قَتَلْتُمْ نَفْسًا فَادَّارَأْتُمْ فِيهَا وَاللَّهُ مُخْرِجٌ مَا كُنْتُمْ تَكْتُمُونَ * فَقُلْنَا اضْرِبُوهُ بِبَعْضِهَا كَذَلِكَ يُحْيِ اللَّهُ الْمَوْتَى وَيُرِيكُمْ آيَاتِهِ لَعَلَّكُمْ تَعْقِلُونَ " سورة البقرة 73-67
"ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «አላህ ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል» ባለ ጊዜ (አስታወሱ)፡፡«መሳለቂያ አድርገህ ትይዘናለህን?» አሉት፡፡ «ከተሳላቂዎች ከመኾን በአላህ እጠበቃለሁ» አላቸው፡፡ «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች (ዕድሜዋን) ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ይላችኋል፤ የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡ «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ መልኳ ምን እንደኾነ ለኛ ይግለጽልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ መልኳ ደማቅ ተመልካቾችን የምታስደስት ዳለቻ ላም ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ «ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች ይግለጽልን፤ ከብቶች በኛ ላይ ተመሳሰሉብን፡፡ እኛም አላህ የሻ እንደኾነ በእርግጥ ተመሪዎች ነን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያልተገራች ምድርን (በማረስ) የማታስነሳ እርሻንም የማታጠጣ (ከነውር) የተጠበቀች ልዩ ምልክት የሌለባት ናት ይላችኋል» አላቸው፡፡ «አሁን በትክክል መጣህ» አሉ፤ ሊሠሩ ያልተቃረቡም ሲኾኑ አረዷት፡፡ ነፍስነም በገደላችሁና በርሷም (ገዳይ) በተከራከራችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ አላህም ትደብቁት የነበራችሁትን ሁሉ ገላጭ ነው፡፡ «(በድኑን) በከፊሏም ምቱት» አልን፤ እንደዚሁ አላህ ሙታንን ያስነሳል፤ ታውቁም ዘንድ ታምራቶችን ያሳያችኋል፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 67-73)፡፡
ረ. የዒሳ ተአምር፡- የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ ሰላም) ከአላህ ዘንድ ወደ በኒ ኢስራኢሎች መልክተኛ ሁኖ ሲላክ ከተሰጡት ተአምራት አንዱ ሙታንን በአላህ ፈቃድ መቀስቀስ ነበር፡፡ ይህም ለማኅበረሰቡ ዒሳ ነቢይነቱን እንዲመሰክሩና ከሞት በኋላም ዳግም መነሳት መኖሩን እንዲያውቁ ለማድረግ ነው፡፡ ቅዱስ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
" إِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ اذْكُرْ نِعْمَتِي عَلَيْكَ وَعَلَى وَالِدَتِكَ إِذْ أَيَّدْتُكَ بِرُوحِ الْقُدُسِ تُكَلِّمُ النَّاسَ فِي الْمَهْدِ وَكَهْلًا وَإِذْ عَلَّمْتُكَ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَالتَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ وَإِذْ تَخْلُقُ مِنَ الطِّينِ كَهَيْئَةِ الطَّيْرِ بِإِذْنِي فَتَنْفُخُ فِيهَا فَتَكُونُ طَيْرًا بِإِذْنِي وَتُبْرِئُ الْأَكْمَهَ وَالْأَبْرَصَ بِإِذْنِي وَإِذْ تُخْرِجُ الْمَوْتَى بِإِذْنِي وَإِذْ كَفَفْتُ بَنِي إِسْرَائِيلَ عَنْكَ إِذْ جِئْتَهُمْ بِالْبَيِّنَاتِ فَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا مِنْهُمْ إِنْ هَذَا إِلَّا سِحْرٌ مُبِينٌ " سورة المائدة 110
"አላህ በሚል ጊዜ (አስታውስ) ፦ የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ (የዋልኩላችሁን) ጸጋዬን አስታውስ፤ በሕጻንነትና በከፈኒሳነት (የበሰለ ሰው ሆነህ) ሰዎችን የምትናገር ስትሆን በቅዱስ መንፈስ (በጅብሪል) ባበረታሁህ ጊዜ ጽሕፈትንና ጥበብንም፣ ተውራትንና ኢንጂልንም፣ ባስተማርኩህ ጊዜ ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ብጤ በፈቃዴ በምትሠራና በውስጧ በምትነፋ፣ በፈቃዴም ወፍ በምትሆን ጊዜ፣ ዕውርም ሆኖ የተወለደንና ለምጻምንም በፈቃዴ በምታሽር ጊዜ፣ ሙታንንም በፈቃዴ (ከመቃብራቸው) በምታወጣ ጊዜ፣ የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣህባቸውና ከነሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ባሉ ጊዜ፣ (ሊገድሉህ ሲያስቡህ) ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ፣ (ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ)።" (ሱረቱል ማኢዳህ 110)፡፡
3. ትላቅ ፍጥረታትን በመጠቆም፡-

ሌላው አምላካችን አላህ ከሞት በኋላ ህይወት መኖሩን ለመግለጽ፡ ከመቃብር በታች ያሉ የበሰበሱ አጥንቶችን ዳግም ነፍስ በመዝራት ማስነሳት እንደማያቅተው ለማስረዳት የተጠቀመበት መንገድ ነው፡፡ እሱም፡- ከሰው በእጅጉ የሚበልጡ ግዙፍ ፍጥረታትን (ሰማይና ምድር) ሳይቸግረውና ሳያቅተው መፍጠርና ማስገኘት የቻለ አላህ፡ እንዴት ከ100 ኪሎ ግራም በላይ የማይመዝነውን ደቃቃ የሰው ልጅ ከመቃብር መቀስቀስ ይከብደዋል ተብሎ ይታሰባል? እያለን ነው፡፡ እስኪ እራሴን በነፍስ ወከፍ ከምድር ጋር ላነጻጽራት፡፡ ነፍሴ ሆይ! አንቺ ለምድር ስንት ስንተኛዋ ነሽ? ብዬም ልጠይቃት፡፡ ከመሬት 1/4 ሩብ በሚሆነው ክፍል ላይ ነው 7 ቢልየን የሚደርስ ህዝብ እየኖረ ያለው፡፡ እሱንም ያለምንም መሬት መጣበብ፡፡ ታዲያ እኔ ለ7 ቢልየኑ ህዝብ 1/7ቢለየነኛ ከሆንኩ፡ ለመሬት ስንት ስንተኛዋ ልሆን ነው፡፡ ታዲያ እኔን ነው አላህ ከመቃብር አይቀሰቅሰኝም ብዬ ከማመን የምኮራው? 100 ኪሎ ግራም የሚመዝን እቃን በጀርባው የተሸከመ ሰው፡ 25 ኪሎ ግራም ግን መሸከም ይከብደዋል ብሎ መናገር የጤና ነውን? ታዲያ ሰማያትንና ምድርን ያስገኘ አላህ፡ እኔን ማን ሆኜ ነው ከተኛሁበት መቃብር፡- ያ ዐብደላህ! ሰዓቱ ደርሷልና ውጣ ብሎ መቀስቀስ የሚከብደው? ቀጣዮቹ የቁርኣን አንቀጾች ይህንን ይገልጻሉ፡-
" أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ قَادِرٌ عَلَى أَنْ يَخْلُقَ مِثْلَهُمْ وَجَعَلَ لَهُمْ أَجَلًا لَا رَيْبَ فِيهِ فَأَبَى الظَّالِمُونَ إِلَّا كُفُورًا " سورة الإسراء 99
"ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ አላህ ብጤያቸውን በመፍጠር ላይ ቻይ መሆኑን በርሱ ጥርጣሬ የሌለበትንም ጊዜ (ለሞትም ለትንሣኤም) ለርሱ የተወሰነ መሆኑን አላወቁምን? በደለኞችም ከክሕደት በቀር እምቢ አሉ።" (ሱረቱል ኢስራእ 99)፡፡
" لَخَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَكْبَرُ مِنْ خَلْقِ النَّاسِ وَلَكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ " سورة غافر 57
"ሰማያትንና ምድርን መፍጠር፣ ሰዎችን ከመፍጠር ይልቅ ታላቅ ነው፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም።" (ሱረቱ ጋፊር 57)፡፡
" أَوَلَمْ يَرَوْا أَنَّ اللَّهَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلَمْ يَعْيَ بِخَلْقِهِنَّ بِقَادِرٍ عَلَى أَنْ يُحْيِيَ الْمَوْتَى بَلَى إِنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الأحقاف 33
"ያ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ እነርሱም በመፍጠሩ ያልደከመው አላህ ሙታንን ሕያው በማድረግ ላይ ቻይ መሆኑን አላስተዋሉምን? (በማስነሳት) ቻይ ነው እነርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና" (ሱረቱል አሕቃፍ 33)፡፡

4. ምድርን በመጠቆም፡-

ይህ ደግሞ አራተኛው መንገድ ነው፡፡ ጌታ አላህ በቅዱስ ቃሉ ላይ የመሬትን ሞትና ትንሳኤ ይጠቁመናል፡፡ ምድር ከዝናብ እጦት የተነሳ ተሰነጣጥቃ፡ ለምነቷ ጠፍቶ፡ አረንጓዴ እጽዋቶቿ ረግፈው ስትታይ መሬት ሞተች ማለት ነው፡፡ ከዛም በአላህ ቸርነት ዝናብ ሲወርድላት ወዲያውኑ መላወስ ትጀምራለች፡ ትነፋፋለች፡ ውበት ካለው የእጽዋት ጎሳ ሁሉ በያይነቱ ማብቀል ትጀምራለች፡ ስብራቷ(የተሰነጠቀው ክፍሏ) ይጠገናል፡፡ በዚህ አይነት መልኩ ምድርን ከሞተችበት ህያው ያደረገ አላህ፡ ሙታንንም ከመቃብራቸው በመቀስቀስ ቻይ ነው በማለት ያስረዳናል፡፡ ተከታዮቹን የቁርኣን አንቀጾች ያጢኗቸው፡-
" وَهُوَ الَّذِي يُرْسِلُ الرِّيَاحَ بُشْرًا بَيْنَ يَدَيْ رَحْمَتِهِ حَتَّى إِذَا أَقَلَّتْ سَحَابًا ثِقَالًا سُقْنَاهُ لِبَلَدٍ مَيِّتٍ فَأَنْزَلْنَا بِهِ الْمَاءَ فَأَخْرَجْنَا بِهِ مِنْ كُلِّ الثَّمَرَاتِ كَذَلِكَ نُخْرِجُ الْمَوْتَى لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ " سورة الأعراف 57
"እርሱም ያ ነፋሶችን ከችሮታው (ከዝናም) በፊት አብሳሪዎች አድርጎ የሚልክ ነው። ከብባዳዎችንም ደመናዎች በተሸከሙ ጊዜ ሙት ወደ ሆነ አገር እንነዳዋለን፤ በርሱም ውሃን እናወርዳለን፤ ከፍሬዎችም ሁሉ በርሱ እናወጣለን፤ እንደዚሁ ትገነዘቡ ዘንድ ሙታንን (ከመቃብር) እናወጣለን።" (ሱረቱል አዕራፍ 57)፡፡
"...وَتَرَى الْأَرْضَ هَامِدَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ وَأَنْبَتَتْ مِنْ كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ * ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِ الْمَوْتَى وَأَنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الحج 6-7
"…ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ፤ በስዋም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ፣ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም፤ ውበት ካለው ጎሳ ሁሉ ታበቅላለችም። ይህ፣ አላህ እርሱ መኖሩ የተረጋገጠ፤ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 5-6)፡፡
" وَاللَّهُ الَّذِي أَرْسَلَ الرِّيَاحَ فَتُثِيرُ سَحَابًا فَسُقْنَاهُ إِلَى بَلَدٍ مَيِّتٍ فَأَحْيَيْنَا بِهِ الْأَرْضَ بَعْدَ مَوْتِهَا كَذَلِكَ النُّشُورُ " سورة فاطر 9
"አላህም ያ ነፋሶችን የላከ ነው፤ ደመናዎችንም ትቀሰቅሳለች፤ ወደ ሙት (ድርቅ) አገርም እንነዳዋለን፤ በርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው እናደርጋታለን፤ ሙታንንም መቀስቀስ እንደዚሁ ነው።" (ሱረቱ ፋጢር 9)፡፡
" وَمِنْ آيَاتِهِ أَنَّكَ تَرَى الْأَرْضَ خَاشِعَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ إِنَّ الَّذِي أَحْيَاهَا لَمُحْيِ الْمَوْتَى إِنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة فصلت 39
"አንተ ምድርን ደረቅ ሆና ማየትህም ከምልክቶቹ ነው፤ በርሷም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ፣ (በቡቃያዎችዋ) ትላወሳለች፤ ትንነፋለችም፤ ያ ህያው ያደረጋት ጌታ በእርግጥ ሙታንን ሕያው አድራጊ ነው፤ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።" (ሱረቱ ፉሲለት 39)፡፡

5. እንቅልፍን በማስታወስ፡-

ጌታ አላህ ለባሪያዎቹ ከለገሳቸው ጸጋዎቹ መካከል አንዱ እንቅልፍ ነው፡፡ እንቅልፍ የሞት ታናሽ ወንድም በመባል ይታወቃል፡፡ የተኛ ሰው እንደ ሞተ ሰው በአጠገቡ የሚሰራውን አያውቅም፡ አያይም፡ አይሰማምና፡፡ ከሞተ ሰው የሚለየው ከሰዓታት በኋላ መነሳት መቻሉ ነው፡፡ ታዲያ በእንቅልፍ ሰበብ ሩሐችንን (መንፈሳችንን) በመውሰድ ለትንሹ ሞት የዳረገን አላህ፡ ሩሑን ሲመልስልን ደግሞ ከእንቅልፋችን ከነቃን፡ ነጌም ዋናውን ሞት እንድንሞት ከወሰነብን በኋላ፡ ለቂያም ቀን ደግሞ እንደሚቀሰቅሰን አመላካች ይሆናል ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ቁርኣን በጉዳዩ ላይ እንዲህ ይላል፡-

" وَهُوَ الَّذِي يَتَوَفَّاكُمْ بِاللَّيْلِ وَيَعْلَمُ مَا جَرَحْتُمْ بِالنَّهَارِ ثُمَّ يَبْعَث
ُكُمْ فِيهِ لِيُقْضَى أَجَلٌ مُسَمًّى ثُمَّ إِلَيْهِ مَرْجِعُكُمْ ثُمَّ يُنَبِّئُكُمْ بِمَا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ " سورة الأنعام 60
"እርሱም ያ በሌሊት የሚያስተኛችሁ በቀንም የሠራችሁትን ሁሉ የሚያውቅ ከዚያም የተወሰነው ጊዜ ይፈፀም ዘንድ በእርሱ (በቀን) ውስጥ የሚቀሰቅሳችሁ ነው፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እርሱ ነው፡፡ ከዚያም ትሠሩት የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል፡፡" (ሱረቱል አንዓም 60)፡፡
" اللَّهُ يَتَوَفَّى الْأَنْفُسَ حِينَ مَوْتِهَا وَالَّتِي لَمْ تَمُتْ فِي مَنَامِهَا فَيُمْسِكُ الَّتِي قَضَى عَلَيْهَا الْمَوْتَ وَيُرْسِلُ الْأُخْرَى إِلَى أَجَلٍ مُسَمًّى إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ " سورة الزمر 42
"አላህ ነፍሶችን በሞታቸው ጊዜ፣ ይወስዳል፤ ያችንም ያልሞተችውን በእንቅልፏ ጊዜ (ይወስዳታል)፤ ታዲያ ያችን ሞትን የፈረደባትን ይይዛታል፤ ሌላይቱንም እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ ይለቃታል፤ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች ምልክቶች አሉበት።" (ሱረቱ-ዙመር 42)፡፡
" وَكَذَلِكَ أَعْثَرْنَا عَلَيْهِمْ لِيَعْلَمُوا أَنَّ وَعْدَ اللَّهِ حَقٌّ وَأَنَّ السَّاعَةَ لَا رَيْبَ فِيهَا إِذْ يَتَنَازَعُونَ بَيْنَهُمْ أَمْرَهُمْ فَقَالُوا ابْنُوا عَلَيْهِمْ بُنْيَانًا رَبُّهُمْ أَعْلَمُ بِهِمْ قَالَ الَّذِينَ غَلَبُوا عَلَى أَمْرِهِمْ لَنَتَّخِذَنَّ عَلَيْهِمْ مَسْجِدًا " سورة الكهف 21
"እንደዚሁም፣ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ መሆኑን፥ ሰዓቲቱም በርሷ ጥርጣሬ የሌለ መሆኑን ያውቁ ዘንድ፥ በነርሱ ላይ (ሰዎችን) አሳወቅን፤ (አማኞቹና ከሐዲዎቹ) ነገራቸውን በመካከላቸው ሲከራከሩ (የሆነውን አስታውስ፤ ከሐዲዎቹ)፡- በነሱ ላይም ግንብን ገነቡ አሉ፤ ጌታቸው በነሱ ይበልጥ ዐዋቂ ነው፤ እነዚያ በነገራቸው ላይ ያሸነፉት፣ (ምእመናን) በነሱ ላይ በእርግጥ መስጊድን እንሰራለን አሉ።" (ሱረቱል ከህፍ 21)፡፡
በዚህ አንቀጽ ውስጥ የተወሱት የዋሻው ሰዎች (አስሐቡል-ከህፍ) በመባል የሚታወቁት ናቸው፡፡ በጌታቸው ያመኑ ጠንካራ ባሮች ነበሩ፡፡ እነዚህን ሰዎች ለ300(309) አመት አላህ ሩሐቸውን በመውሰድ በዋሻው ውስጥ በእንቅልፍ አቆይቷቸዋል፡፡ ነገር ግን አልሞቱም፡፡ ኋላም ላይ አላህ ከተኙበት ቀሰቀሳቸው፡፡ ሌሎች ሰዎችን በነዚህ ሰዎች መነሳት ምክንያት ከሞት መቀስቀስም ሊኖር እንደሚችል ትምህርት ይሆን ዘንድ አላህ ይህን አደረገ፡፡

6. ክፉዎችና ጥሩዎች እኩል አለመታየታቸው፡-

ሌላው ከሞት በኋላ ህይወት መኖሩን ለማሳመን ቅዱስ ቁርኣን የሚጠቀምበት መንገድ ነው፡፡ እሱም፡- በዚህ ምድር ላይ አማኝና መልካም ሰሪዎች እንዳሉ ሁሉ፡ ከሀዲና አመጸኞችም ሞልተዋል፡፡ ታዲያ አላህ በሱና በነቢያቱ አምነው ለህጉ ያደሩ መልካም ባሪያዎቹን፡ በሱና በነቢያቱ ክደው ከህጉ ካፈነገጡ መጥፎ ባሪያዎቹ ጋር በእኩል ያስቀምጣቸዋል ተብሎ ይታሰባልን? በፍጹም አይሆንም! የሚባል ከሆነም፡ ታዲያ መች ነው ሁሉም የስራውን ያህል ተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኘው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ግድ ነው፡፡ በዚህ ዱንያ እንዳንል፡ እንደውም ነገሮች ተቃራኒ በሆነ መልኩ እየተከሰቱ እያየን ነው፡፡ ማለትም መልካም የአላህ ባሪያዎች በግፍ እየተገደሉ፡ ደማቸው ያለ አግባብ እየፈሰሰ፡ ንብረታቸው በከንቱ እየተወረሰ፡ በሀገራቸው ሰላም አጥተው ለስደት እየተዳረጉ፣ በአንጻሩ ግን ከሀዲያን ከሰው በላይ ሁነው በአመጽና በወንጀል ተዘፍቀው፡ ግን ውጪያዊ ሰላም አግኝተው እየኖሩ ነው፡፡ ታዲያ አምላካችን አላህ ይህን ሁሉ እያየ፡ የፈለገውንም ማድረግ እየቻለ፡ ዝም ያለው ግን ለሁሉም ፍትሐዊ ፍርድ የሚሰጥበት ቀን ስለያዘላቸው ነው፡፡ የዛኔ በዳይም ተበዳይም ዋጋቸውን ያገኛሉ፡፡ ይህቺ ዱንያ ግን የፈተና ዓለም ነች፡፡ አላህ አማኞችን በፈተናው ሰበብ ኢማናቸውን የሚያጎለብትበት፡ ኃጢአታቸውን የሚያጥብበት እንዲሆን ፈቅዷል፡፡ ከሀዲያንን ደግሞ ዱንያ ጀነታቸው እንድትሆን ፈቅዷል፡፡ ስለዚህ ከሞት በኋላ ህይወት የለም ብሎ ማሰብ፡ የመልካም ሰዎችና የመጥፎ ሰዎች ፍጻሜ ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁሉም በሞት ያከትምለታል ወደሚል ድምዳሜ ያደርሳል፡፡ ጉዳዩ እንደዛ ከሆነ፡ ለምን ጥሩ መሆን አስፈለገ? ለምንስ የግል ፍላጎትንና ስሜትን በመርገጥ ለሌላው ቅድሚያ መስጠት አስፈለገ? በደለኞች የስራቸውን ዋጋ ካልተቀበሉ የአምላክስ ፍትሐዊነትና ጥበበኛነት ምኑ ላይ ነው? ቅዱስ ቁርኣን ግን አማኝና ከሀዲ በፍጹም አይስተካከሉም በማለት ያስረዳል፡-
" أَمْ حَسِبَ الَّذِينَ اجْتَرَحُوا السَّيِّئَاتِ أَنْ نَجْعَلَهُمْ كَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَوَاءً مَحْيَاهُمْ وَمَمَاتُهُمْ سَاءَ مَا يَحْكُمُونَ " سورة الجاثية 21
"እነዚያ ኀጢያቶችን የሠሩ፣ ሕይወታቸውም ሞታቸውም ትክክል ሲኾን፤ እንደነዚያ እንደ አመኑትና መልካሞችን እንደሠሩት ልናደርጋቸው ይጠረጥራሉን? (አይጠርጥሩ)፤ የሚፈርዱት ምንኛ ከፋ!" (ሱረቱል ጃሢያህ 21)፡፡
" إِنَّ لِلْمُتَّقِينَ عِنْدَ رَبِّهِمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ * أَفَنَجْعَلُ الْمُسْلِمِينَ كَالْمُجْرِمِينَ * مَا لَكُمْ كَيْفَ تَحْكُمُونَ * أَمْ لَكُمْ كِتَابٌ فِيهِ تَدْرُسُونَ " سورة القلم 37-34
"ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው። ሙስሊሞቹን እንደ ከሐዲዎች እናደርጋለን? ለናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ። በውነቱ ለናንተ በርሱ የምታጠኑበት መጽሐፍ አላችሁን?" (ሱረቱል ቀለም 34-37)፡፡
" أَفَمَنْ كَانَ مُؤْمِنًا كَمَنْ كَانَ فَاسِقًا لَا يَسْتَوُونَ * أَمَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ فَلَهُمْ جَنَّاتُ الْمَأْوَى نُزُلًا بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ * وَأَمَّا الَّذِينَ فَسَقُوا فَمَأْوَاهُمُ النَّارُ كُلَّمَا أَرَادُوا أَنْ يَخْرُجُوا مِنْهَا أُعِيدُوا فِيهَا وَقِيلَ لَهُمْ ذُوقُوا عَذَابَ النَّارِ الَّذِي كُنْتُمْ بِهِ تُكَذِّبُونَ " سورة السجدة 20-18
"አማኝ የኾነ ሰው አመጠኛ እንደሆነ ሰው ነውን? አይተካከሉም፡፡ እነዚያ ያመኑና መልካሞችን የሠሩማ፣ ለነሱ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መስተነግዶ ሲኾኑ መኖሪያ ገነቶች አሏቸው። እነዚያ ያምመጡትማ፤ መኖሪያቸው እሳት ናት፤ ከርሷ መውጣትን በፈለጉ ቁጥር በርሷ ውስጥ ይመለሳሉ፤ ለነርሱም ያንን በርሱ ታስተባብሉበት የነበራችሁትን የእሳት ቅጣት ቅመሱ ይባላሉ።" (ሱረቱ-ሰጅዳህ 18-20)፡፡
" وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاءَ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَاطِلًا ذَلِكَ ظَنُّ الَّذِينَ كَفَرُوا فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا م
ِنَ النَّارِ * أَمْ نَجْعَلُ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَالْمُفْسِدِينَ فِي الْأَرْضِ أَمْ نَجْعَلُ الْمُتَّقِينَ كَالْفُجَّارِ " سورة ص 28-27
"ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው! በእውነቱ እነዚያን ያመኑትንና መልካሞችን የሠሩትን በምድር ውስጥ እንደሚያጠፉት እናደርጋለን? ወይስ አላህን ፊረዎቹን እንደ ከሓዲዎቹ እናደርጋለን?" (ሱረቱ ሷድ 27-28)፡፡
" وَمَا يَسْتَوِي الْأَعْمَى وَالْبَصِيرُ وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ وَلَا الْمُسِيءُ قَلِيلًا مَا تَتَذَكَّرُونَ " سورة غافر 58
"ዕውርና የሚያይ፣ እነዚያም አምነው መልካሞችን የሠሩና መጥፎ ሠሪው አይተካከሉም፤ በጣም ጥቂትን ብቻ ትገሠጻላችሁ።" (ሱረቱ ጋፊር 58)፡፡
" وَنَضَعُ الْمَوَازِينَ الْقِسْطَ لِيَوْمِ الْقِيَامَةِ فَلَا تُظْلَمُ نَفْسٌ شَيْئًا وَإِنْ كَانَ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِنْ خَرْدَلٍ أَتَيْنَا بِهَا وَكَفَى بِنَا حَاسِبِينَ " سورة الأنبياء 47
"በትንሣኤም ቀን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን እናቆማለን፣ ማንኛይቱም ነፍስ ምንንም አትበደልም፤ (ሥራው) የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ቢሆንም እርሷን እናመጣታለን፤ ተቆጣጣሪዎችም በኛ በቃ።" (ሱረቱል አንቢያእ 47)፡፡

7. ጥርጣሬ የሌለበት መሆኑ፡-

ወደ አኼራ መጓዛችን፡ የመጨረሻው ቀን የተባለው መምጣቱ እንደማይቀር በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በተለያየ መልክ ተገልጾአል፡፡ ከነዚህም መካከል በአስር አንቀጾች ላይ "ጥርጥር የሌለው" ተብሎ መገለጹ አንዱ ነው፡፡ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
1. "ጌታችን ሆይ! አንተ (ለመምጣቱ) በርሱ ጥርጥር የሌለበት በሆነ ቀን ሰዉን ሁሉ ሰብሳቢ ነህ ምንጊዜም አላህ ቀጠሮን አያፈርስምና።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 9)፡፡
2. "በርሱ (መምጣት) ጥርጥር የሌለበት በሆነዉ ቀን በሰበሰብናቸዉና ነፍስ ሁሉ የሠራችዉን ሥራ በተሞላች ጊዜ እንዴት ይሆናሉ? እነርሱም አይበደሉም።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 25)፡፡
3. "አላህ ከርሱ በስተቀር አምላክ የለም፤ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ እውነተኛ ማነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 87)፡፡
4. "«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የማን ነው» በላቸው፡፡ (ሌላ መልስ የለምና) «የአላህ ነው» በል፡፡ «በነፍሱ ላይ እዝነትን ጻፈ፡፡ በትንሣኤ ቀን በእርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲኾን በእርግጥ ይሰበስባችኋል፡፡ እነዚያ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፤ እነርሱም አያምኑም፡፡" (ሱረቱል አንዓም 12)፡፡
5. "እንደዚሁም፣ የአላህ ቀጠሮ እርግጠኛ መሆኑን፥ ሰዓቲቱም በርሷ ጥርጣሬ የሌለ መሆኑን ያውቁ ዘንድ፥ በነርሱ ላይ (ሰዎችን) አሳወቅን፤ (አማኞቹና ከሐዲዎቹ) ነገራቸውን በመካከላቸው ሲከራከሩ (የሆነውን አስታውስ፤ ከሐዲዎቹ)፡- በነሱ ላይም ግንብን ገነቡ አሉ፤ ጌታቸው በነሱ ይበልጥ ዐዋቂ ነው፤ እነዚያ በነገራቸው ላይ ያሸነፉት፣ (ምእመናን) በነሱ ላይ በእርግጥ መስጊድን እንሰራለን አሉ።" (ሱረቱል ከህፍ 21)፡፡
6. "ሰዓቲቱም መጪ በርሷ ፈጽሞ ጥርጣሬ የሌለባት በመሆኗ፣ አላህም በመቃብሮች ዉስጥ ያለን ሁሉ፣ የሚቀሰቅስ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 7)፡፡
7. "ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፤ በርሷ ጥርጥር የለም፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም" (ሱረቱ ጋፊር 59)፡፡
8. "እንደዚሁም የከተሞች እናት የሆነችውን (የመካን ሰዎች)፣ በአካባቢዋ ያሉትንም ልታስፈራራ፣ የመሰብሰቢያውንም ቀን፣ በርሱ ጥርጣሬ የሌለበት ሲሆን ልታስጠነቅቅ ዐረብኛ የሆነን ቁርአን ወደአንተ አወረድን፤ (ከነሱም) ከፊሉ በገነት ውስጥ ከፊሉም በእሳት ውስጥ ነው።" (ሱረቱ-ሹራ 7)፡፡
9. "አላህ ሕያው ያደርጋችኋል፤ ከዚያም ያሞታችኋል፤ ከዚያም ወደ ትንሣኤ ቀን ይሰበስባችኋል፤ በርሱ ጥርጥር የለበትም፤ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም በላቸው።" (ሱረቱል ጃሢያህ 26)፡፡
10. "የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፤ ሰአቲቱም በርሷ (መምጣት) ጥርጥር የለም፤ በተባለ ጊዜም ሰዓቲቱ ምን እንደ ሆነች አናውቅም፤ መጠራጠርን የምንጠራጠር እንጅ ሌላ አይደለንም፤ እኛም አረጋጋጮች አይደለንም አላችሁ።" (ሱረቱል ጃሢያህ 32)፡፡
8. በመሐላ የጸና መሆኑ፡- ሌላው ከሞት በኋላ ዳግም መቀስቀስና መነሳት እንዳለ ቅዱስ ቁርኣን ያመላከተን ጉዳዩን በመሓላ አጥብቆ መናገሩ ነው፡፡ የሚማልበት ነገር ደግሞ ክብደት የሚሰጠው እንደሆነ ሁላችንም እናውቀዋለን፡፡ እንዲህ ይላል ቁርኣን፡-
" وَيَسْتَنْبِئُونَكَ أَحَقٌّ هُوَ قُلْ إِي وَرَبِّي إِنَّهُ لَحَقٌّ وَمَا أَنْتُمْ بِمُعْجِزِينَ " سورة يونس 53
"እርሱም(የመቀስቀሻው ቀን) «እውነት ነውን» (ሲሉ) ይጠይቁሃል፡፡ «አዎን፤ በጌታዬ እምላለሁ፤ እርሱ እውነት ነው፡፡ እናንተም አምላጮች አይደላችሁም፤» በላቸው፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 53)፡፡
" وَقَالَ الَّذِينَ كَفَرُوا لَا تَأْتِينَا السَّاعَةُ قُلْ بَلَى وَرَبِّي لَتَأْتِيَنَّكُمْ عَالِمِ الْغَيْبِ لَا يَعْزُبُ عَنْهُ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَلَا أَصْغَرُ مِنْ ذَلِكَ وَلَا أَكْبَرُ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُبِينٍ " سورة سبأ 3
"እነዚያ የካዱትም፣ ሰዓቲቱ አትመጣብንም አሉ፤ በላቸው ፡- አይደለም ሩቁን ሁሉ አዋቂ በሆነው ጌታዬ እምላለሁ፤ በእርግጥ ትመጣባችኋለች፤ የብናኝ ክብደት ያክል እንኳን በሰማይና በምድር ውስጥ ከርሱ አይርቅም፤ ከዚህ ያነሰም ሆነ የበለጠም የለም፣ በግልጹ መጽሐፍ ውስጥ የተመዘገበ ቢሆን እንጅ።" (ሱረቱ ሰበእ 3)፡፡
" زَعَمَ الَّذِينَ كَفَرُوا أَنْ لَنْ يُبْعَثُوا قُلْ بَلَى وَرَبِّي لَتُبْعَثُنَّ ثُمَّ لَتُنَبَّؤُنَّ بِمَا عَمِلْتُمْ وَذَلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ " سورة التغابن 7
"እነዝያ የካዱት በፍፁም የማይቀሰቀሱ መሆናቸውን አሰቡ፤ አይደለም! በጌታዬ እምላለሁ፤ በእርግጥ ትቀሰቀሳላችሁ፤ ከዝያም በሰራችሁት ሁሉ ትነገራላችሁ ይህም በአላህ ላይ ቀላል ነው፤ በላቸው።" (ሱረቱ-ተጋቡን 7)፡፡

ታዲያ የትኛው መጽሐፍ ነው እንደ ቅዱስ ቁርኣን ከሞት በኋላ ህይወት መኖሩን ለማስረዳት የሞከረው? መልሱን ሃይማኖት አለኝ ለሚል ሰው ሁሉ የተተወ የቤት ስራ ይሆናል፡፡ እኔም በዚሁ ላብቃ፡፡ ወሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
1👍1
Audio
የውዱእ መስፈርቶች
☞በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/37rcf0B

Join us➤ t.me/abuhyder
ከትችት መዳን አትችልም!!
ለምትሰራው ስራ ዓላማና ግብ ይኑርህ፡፡ ጽናትና ትግስትን ተላበስ፡፡ አላህን ፈሪ የሆነ ዓሊም አማካሪ ይኑርህ፡፡ ከዛ ውጪ ለሰዎች ተራ አሉባልታ ቦታ ሳትሰጥ ጉዞህን ቀጥል፡፡ ከትችት መቼም ቢሆን አትድንምና፡፡ ቀጣዩ ምሳሌም ይሄን ይበልጥ ያብራራው ይሆናል፡-
አባትና ልጅ አህያቸውን ለመሸጥ ወደ ገበያ እየነዱት ሲጓዙ መንገድ አላፊ ያገኛቸውና፡- እነዚህ ሰዎች ምን አይነት ቂሎች ናቸው! አህያቸውን ይዘው በእግራቸው ይደክማሉ! ብሎ አለፈ፡፡ እነሱም እውነት ይሆን እንዴ? በማለት ሁለቱም አህያው ላይ በመፈናጠጥ ይጋልቡታል፡፡
ጥቂት እንደተጓዙ ሌሎች አላፊዎች ደግሞ፡- ምን አይነት ጨካኞች ናቸው! ትንሽ እንኳ ለአህያው አያዝኑለትም! በማለት ይተቿቸዋል፡፡ እነሱም የሰዉን ትችት በመፍራት ልጅየው ይወርድና አባት ብቻ በመቀመጥ ይጓዛሉ፡፡
አሁንም ሌላ አላፊ ይገጥማቸውና፡- ልጁን በእግሩ እያደከመ እሱ በአህያው ተቀምጦ የሚሄድ ምን አይነት አባት ነው! በማለት አባትየውን ተቃወሙ፡፡ አባት ከአህያው ላይ ይወርድና ልጅ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡
አሁንም ትንሽ እንደተጓዙ ሌላ ሰው ደግሞ፡- አባቱን በእግር እያስኬደ እሱ በአህያ የሚቀመጥ አባቱን የማያከብር ምን አይነት ክፉ ልጅ ነው! ብለው ልጁን ክፉኛ ኮነኑት፡፡ ልጅም ከአህያው ይወርድና ሁለቱም አህያውን እየነዱ በእግር ይጓዛሉ፡፡
ሌላ ሰው ያገኛቸውና ደግሞ፡- እስኪ አሁን ይሄን አህያ እንዲህ በእግሩ እያደከሙት ወደ ገበያ ሲደርሱ ቆዳውን ብቻ ለመሸጥ ነው ወይስ ምኑን? በማለት አፌዘባቸው፡፡ አባትና ልጅም ምናልባት እንዳይሞትብን ብለው በመስጋት ሁለቱም አህያውን ይሸከሙትና መጓዝ ይጀምራሉ፡፡
ሌሎች መንገደኞች ይመለከቷቸውና፡- ጉድ! ጉድ! በዚህ ክፍለ ዘመን እንደነዚህ አይነት አህያ ተሸክሞ የሚሄድ ቂል አይተንም አናውቅም ! በማለት ተቿቸው፡፡ እነሱ ግን የሰዉ ትችት በዝቶባቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ጉዞዋቸውን ቀጠሉ፡፡
ሁላችንም የአኼራ ሰዎች ነን፡፡ ዓላማና ግባችን አኼራ ያለውን ቤታችንን በማሳመር ላይ ይሁን፡፡ እስክናገኘውም ድረስ ለሚደርሱብን መከራዎች ጽናትና ትግስት ይኑረን፡፡ ዓላማችን እንዲሳካና ቤቱን የመታ እንዲሆን የኢስላም ሊቃውንቶችን እናማክር፡፡ በተማርነው ነገር በመጽናት ሰዎች ለምን ተቹን ብለን ለሁሉም ቦታ አንስጥ፡፡ ከሰው ትችት መቼም ቢሆን መዳን አይቻልምና፡፡
ወቢላሂ ተውፊቅ
ምንጭ፡- الثقفة لكم ከሚለው የፌስ ቡክ ገጽ የተወሰደ፡፡

Join us➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhayder
እንዲህ ከተዛተባቸው አላህ ይጠብቀን
በአቡ ሀይደር
#አስሩ የተዛተባቸው ሰዎች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
"ወይል" የሚለው የዐረብኛ ቃል ትርጉሙ፡- የቅጣት ቃል፣ የማስጠንቀቂያ ዛቻ ነው፡፡ እንዲሁም በጀሀነም ውስጥ የሚገኝ የሸለቆ ስም ነው፡፡ በጥቅሉ በአማርኛው የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም ውስጥ ‹‹ወየውላቸው›› በሚል ትርጉም ሰፍሯል፡፡ ለአመጸኞች የተዛተባቸው መለኮታዊ ማስፈራሪያ ነው፡፡ ዛሬ አላህ ፈቃዱ ከሆነ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የመጣባቸውን ቦታዎች እንመለከታለን፡-
1. መጽሐፉን ለሚቀይሩ፡-
ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት(ተውራት፣ዘቡር፣ኢንጂል…) ምንጫቸው ከአላህ ዘንድ የመጡ፡ የአላህ ቃል ሁነው ሳለ፡ መጽሐፉ የወረደላቸው የእነዚያ ነቢያት ህዝቦች(አይሁዶች) ግን ስሜታቸውን በመከተል የአላህን መጽሐፍ አሽቀንጥረው ከጀርባቸው ኋላ ወረወሩት(አል-በቀራህ 101፣ አሊ-ዒምራን 187)፡፡ ያም አልበቃ ብሎ እጃቸውን በመጽሐፉ ላይ በማስገባት በውስጡ የነበረውን ከፊል በማውጣት፡ ሌላ ከመጽሐፉ ያልሆኑ አዳዲስ ቃላትን በመጨመር፡ እውነቱን ከሀሰት ደባልቀው፡- ይኸው ከአላህ ዘንድ የመጣላችሁ መጽሐፍ! ብለው ህዝቡን አደናገሩ፡፡ አላህም ይህን ለሚሰሩ ሰዎች (ወየውላቸው ‹‹ወይሉን ለሁም››) በማለት ዛተባቸው፡-
" فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَذَا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا فَوَيْلٌ لَهُمْ مِمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَهُمْ مِمَّا يَكْسِبُونَ " سورة البقرة 79
"ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 79)፡፡
- ከዚህ የምንወስደው ትምሕርት፡-
ሀ. ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት አላህ ሊጠብቃቸው ቃል ስላልገባላቸው፡ በምትኩ መጽሐፉ የተሰጣቸው ነቢያትና ተከታዮቻቸው እንዲጠብቁ በመደረጉ(አል-ማኢዳህ 44) በጊዜ ሂደት መበረዛቸውን እንረዳለን፡፡
ለ. በመጽሐፉ ላይ እጃቸውን በማስገባት ቃላትን ከስፍራው የቀየሩ ሰዎች አላህ ዘንድ አሳማሚ ቅጣት እንደሚያገኛቸው ከተዛተባቸው፡ ዛሬም ቅዱስ ቁርኣንን ምንም ቃላቱን መቀየር እንኳ ባይቻልም( አላህ ሊጠብቀው ቃል ስለ-ገባለት አል ሒጅር 9) መልእክቱን ግን ሲተረጉሙ እያዛቡ ከእውነታው ውጪ የሆነ መልእክት በማስተላለፍ ሰውን ግራ የሚያጋቡ እና ኡማውን መከፋፈል የሚሹ ለሆኑት ይኸው ዛቻ የሚመለከታቸው መሆኑን እንረዳለን፡፡
2. ለከሀዲያን፡-
በአላህና በመልክተኛው በማመን እንዲሁም መልካም ስራዎችን በማስከተል፡ ዘለቄታዊ የሆነውን የመጨረሻውን ዓለም ጀነትን መፈለግ ሲገባቸው፡ የዱንያ ህይወትን ከአኼራ መርጠው፡ አላህ በላካቸው መልክተኞች ያስተባበሉትን ከሀዲያን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በመግለጽ ‹‹ወየውላችሁ!›› ተብለዋል፡-
" اللَّهِ الَّذِي لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَوَيْلٌ لِلْكَافِرِينَ مِنْ عَذَابٍ شَدِيدٍ * الَّذِينَ يَسْتَحِبُّونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا عَلَى الْآخِرَةِ وَيَصُدُّونَ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا أُولَئِكَ فِي ضَلَالٍ بَعِيدٍ " سورة إبراهيم 3-2
"አላህ ያ በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ የሆነ ነው፤ ለከሐዲዎችም ከብርቱ ቅጣት ወዮላቸው። እነዚያ የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ሕይወት ይበልጥ የሚወዱ፤ ከአላህም መንገድ የሚያግዱ፤ መጥመሟንም የሚፈልጉዋት ናቸው፤ እነዚያ በሩቅ ስሕተት ውስጥ ናቸው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 2-3)፡፡
" وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاءَ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَاطِلًا ذَلِكَ ظَنُّ الَّذِينَ كَفَرُوا فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنَ النَّارِ " سورة ص 27
"ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው!" (ሱረቱ ሷድ 27)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. በአላህና በመልክተኞቹ ምንም ሳናስተባብልና ሳንወላውል በትክክል ማመን እንዳለብንና ይህ እምነትም ከእሳት ቅጣት ሊያድነን እንደሚችል እንማራለን፡፡
ሀ. የዱንያ ሕይወት በጣም አጭርና ለመጥፋት የተቃረበች በመሆኗ፡ ዘለቄታዊ ከሆነውና ከማይጠፋው የአኼራ ሕይወት በምንም አይነት መልኩ ልናስበልጣት እንደማይገባ እንማራለን፡፡
3. በዒሳ ጉዳይ የተለያዩትን፡-
የመርየም ልጅ ዒሳ(ዐለይሂ ሰላም) የአላህ ባሪያና መልክተኛው ብቻ ሆኖ ሳለ (አል-ማኢዳህ 75)፡ ክርስቲያኖች ግን በሱ ጉዳይ እርስ በርስ በመቃረን የተለያየ አመለካከት በመያዝ(አንዱ የአላህ ልጅ ነው፣ ሌላው ደግሞ እራሱ አላህ ነው፣ ሌሎቹ ደግሞ ከሶስቱ አንዱ ነው…) በማለት አሕዛቦች ሆነው ከመስመር የወጡትን ወየውላቸው ይላቸዋል፡-
" مَا كَانَ لِلَّهِ أَنْ يَتَّخِذَ مِنْ وَلَدٍ سُبْحَانَهُ إِذَا قَضَى أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُنْ فَيَكُونُ * وَإِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ هَذَا صِرَاطٌ مُسْتَقِيمٌ * فَاخْتَلَفَ الْأَحْزَابُ مِنْ بَيْنِهِمْ فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ مَشْهَدِ يَوْمٍ عَظِيمٍ " سورة مريم 37-35
"ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም፤ (ከጉድለት ሁሉ) ጠራ፤ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለዉ ኹን ነዉ ውዲያዉም ይኾናል። (ዒሳ አለ) ፦ አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነዉና ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው። ከመካከላቸዉም አሕዛቦቹ በርሱ ነገር ተለያዩ ለነዚያም ለካዱት ሰዎች፣ ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ወዮላቸዉ።" (ሱረቱ መርየም 35-37)፡፡
" وَلَمَّا جَاءَ عِيسَى بِالْبَيِّنَاتِ قَالَ قَدْ جِئْتُكُمْ بِالْحِكْمَةِ وَلِأُبَيِّنَ لَكُمْ بَعْضَ الَّذِي تَخْتَلِفُونَ فِيهِ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ * إِنَّ اللَّهَ هُوَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ هَذَا صِرَاطٌ مُسْتَقِيمٌ * فَاخْتَلَفَ الْأَحْزَابُ مِنْ بَيْنِهِمْ فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْ عَذَابِ يَوْمٍ أَلِيمٍ " سورة الزخرف 65-63
"ዒሳ በታምራቶች በመጣ ጊዜም አላቸው፦ በእርግጥ በጥበብ መጣኋችሁ፤ የዚያንም በርሱ የምትለያዩበትን ከፊሉን ለናንተ ላብራራላች
ሁ፣ (መጣሁ) አላህንም ፍሩ፤ ታዘዙኝም። አላህ ጌታየ ጌታችሁም ነውና ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው። ከመካከላቸውም አህዛቦቹ ተለያዩ፤ ለነዚያም ለበደሉት ከአሳማሚ ቀን ቅጣት ወዮላቸው።" (ሱረቱ-ዙኽሩፍ 63-65)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. የመርየም ልጅ ዒሳ(ዐለይሂ ሰላም) አላህ ከሰጠው የነቢይነትና የረሱልነት ደረጃ የዘለለ ሌላ ማንነት እንደሌለውና፡ በፍጥረታዊ ማንነቱም ቢሆን የአላህ ባሪያና የመርየም ልጅ እንጂ የአላህ ልጅ እንዳልሆነ እንረዳለን፡፡
ለ. በነቢያት ላይ ወሰን ማለፍ (ከተሰጣቸው ደረጃ በላይ ከፍ በማድረግ ወይም ከማእረጋቸው ዝቅ ማድረግ) እንደማይገባን እንማራለን፡፡
4. ውሸትን የሚቀጥፉ፡-
የአላህን እውነት ለመደበቅና ህዝብን ለማምታታት ለምድራዊ ጥቅማቸው ሲሉ እውነትን ደብቀው በአላህ ላይ ሀሰትን የሚቀጥፉ የሆኑ ሰዎች ከነጌው ቅጣት ወየውላችሁ ተብለዋል፡-
" فَتَوَلَّى فِرْعَوْنُ فَجَمَعَ كَيْدَهُ ثُمَّ أَتَى * قَالَ لَهُمْ مُوسَى وَيْلَكُمْ لَا تَفْتَرُوا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا فَيُسْحِتَكُمْ بِعَذَابٍ وَقَدْ خَابَ مَنِ افْتَرَى " سورة طه 61-60
"ፈርዖንም ዞረ፤ ተንኮሉንም ሰበሰበ፤ ከዚያም መጣ። ሙሳ ለነሱ አላቸው፦ ወዮላችሁ በአላህ ላይ ውሸትን አትቅጠፉ፤ በቅጣት ያጠፋችኋልና፤ የቀጠፈም ሰው በእርግጥ አፈረ።" (ሱረቱ ጣሀ 60-61)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. ለምድራዊ ጥቅም ሲባል በአላህ ዲን ላይ መዋሸት አደጋው እጅግ የከፋ ስለሆነ፡ ቅጣቱ ሳይመጣ በፊት ወደ እውነቱ መመለስ እንዳለብን ነው፡፡
5. ልበ ደረቆችን፡-
አላህ በማውሳት ልቦች ይረካሉ፡ ይረጥባሉ (አር-ረዕድ 28)፡፡ ሶላት አላህን ለማውሳት ይረዳል (ጣሀ 14)፡፡ አላህን ከማወደስና ከማውሳት እንዲሁም ሶላትን ከመስገድ ለዘነጉ ሰዎች ግን ወየውላቸው!
" أَفَمَنْ شَرَحَ اللَّهُ صَدْرَهُ لِلْإِسْلَامِ فَهُوَ عَلَى نُورٍ مِنْ رَبِّهِ فَوَيْلٌ لِلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمْ مِنْ ذِكْرِ اللَّهِ أُولَئِكَ فِي ضَلَالٍ مُبِينٍ " سورة الزمر 22
"አላህ ደረቱን ለእስልምና ያሰፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የሆነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸውም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው፤ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው።" (ሱረቱ-ዙመር 22)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. አላህን ማወደስና ዚክር ማብዛት የዘወትር ስራችን መሆን እንዳለበት ነው፡፡ በዚህ ጉዳይም ልንሳነፍ አይገባም፡፡
ለ. ሶላታችንም ላይ ጠንካራዎች በመሆን ሁሌም በዘውታሪነት ልንሰግድ እንደሚገባን ነው፡፡
6. በአላህ የሚጋሩትን፡-
ግዴታ የሆነባቸውንም ዘካ ሳያወጡ፡ በመጨረሻው ዓለምም መኖር አስተባብለው በጌታቸው ላይ ባላንጣን በማጀት፡ ለሱ ከሚገቡት መለኮታዊ ክብሮች ውስጥ (ጌትነትን ወይም አምልኮን) አንዳቸውንም ቢሆን ለፍጡር አሳልፎ በመስጠት የሚያጋሩ ለሆኑት ሙሽሪኮች ወየውላችሁ! ተብለዋል፡-
" قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِثْلُكُمْ يُوحَى إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَهُكُمْ إِلَهٌ وَاحِدٌ فَاسْتَقِيمُوا إِلَيْهِ وَاسْتَغْفِرُوهُ وَوَيْلٌ لِلْمُشْرِكِينَ * الَّذِينَ لَا يُؤْتُونَ الزَّكَاةَ وَهُمْ بِالْآخِرَةِ هُمْ كَافِرُونَ " سورة فصلت 7-6
"(እንዲህ) በላቸው፦ እኔ መሰላችሁ ሰው ብቻ ነኝ፤ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፤ ወደርሱም ቀጥ በሉ፤ ምሕረትንም ለምኑት ማለት፣ ወደኔ ይወርድልኛል። ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው። ለነዚያ ዘካን ለማይሰጡት እነሱም በመጨረሻይቱ ዓለም እነሱ ከሐዲዎች ለሆኑት (ወዮላቸው)።" (ሱረቱ ፉሲለት 6-7)፡፡
- ከዚህ የምንወስደው ትምሕርት፡-
ሀ. በአላህ ላይ ከማጋራት(ለሱ ብቻ የሚገባን የአምልኮ አይነትና መለኮታዊ ስልጣንን ለሌላ አሳልፎ መስጠት) መራቅ እንደሚገባንና ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ አምነን መቀበል እንዳለብን እንዲሁም አቅሙ ካለን ግዴታ የሆነውን ዘካን በአግባቡ ማውጣት እንዳለብን እንማራለን፡፡
7. ለአስተባባዮች፡-
ከሞት በኋላ ዳግም ሕይወት፡ ዳግም መቀስቀስ መኖሩን አምኖ መቀበል ከእምነት ማእዘናት አንድ ክፍል ነው (አል በቀራህ 177)፡፡ በምድራዊ ሕይወታችን ያሳለፍነው መልካምም ሆነ መጥፎ ስራ ሁሉ ዋጋ የምንቀበለው በዚያ ቀን ነው፡፡ ታዲያ በዚህ ቀን መምጣት የሚጠራጠርና የሚያስተባብል ለሆነ ሰው ወየውለት!
" وَيْلٌ يَوْمَئِذٍ لِلْمُكَذِّبِينَ * الَّذِينَ يُكَذِّبُونَ بِيَوْمِ الدِّينِ * وَمَا يُكَذِّبُ بِهِ إِلَّا كُلُّ مُعْتَدٍ أَثِيمٍ " سورة المطففين 12-10
"ለአስተባባዮች በዚያ ቀን ወዮላቸው። ለነዚያ በፍርዱ ቀን ለሚያስተባብሉት። በርሱም ወሰን አላፊ ኀጢአተኛ ሁሉ እንጂ ሌላ አያስተባብልም።" (ሱረቱል ሙጠፊፊን 10-12)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. ከሞት በኋላ ሕይወት መኖሩነረ አምነን መቀበል እንደሚገባን ነው፡፡
8. ለአጉዳዮች፡-
በንግዱ ዓለም ተሰማርተው ለራሳቸው ሲሸምቱና ሲገዙ በትክከል ሰፍረው እንዳይጎድልባቸው ተጠንቀው ሞልተው እየገዙ፡ እነሱ ደግሞ በችርቻሮ ለሌላው ማኅበረሰብ ሲያከፋፍሉና ሲሸጡ ለሚያጎድሉና ለሚያጭበረብሩ ሰዎች ወየውላቸው! ተብለዋል፡፡
" وَيْلٌ لِلْمُطَفِّفِينَ * الَّذِينَ إِذَا اكْتَالُوا عَلَى النَّاسِ يَسْتَوْفُونَ * وَإِذَا كَالُوهُمْ أَوْ وَزَنُوهُمْ يُخْسِرُونَ * أَلَا يَظُنُّ أُولَئِكَ أَنَّهُمْ مَبْعُوثُونَ " سورة المطففين 1-4
"ለሰላቢዎች ወዮላቸው፤ ለነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ፤ለነሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይንም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለሆኑት)።እነዚያ እነሱ ተቀስቃሾች መሆናቸውን አያውቁምን?" (ሱረቱል ሙጠፊፊን 1-4)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. በንግዱ ዓለም ተሰማርተን ከሆነ ማታለልና ሚዛን ማጉደል ታላቅ ኃጢአት እንደሆነና አላህ ዘንድም እንደሚያስጠይቀን ነው፡፡
ለ. ለሰዎች ስንሸጥና ስንመዝን(ስንሰፍር) በትክክለኛ ሚዛን መሆን እንዳለበት ነው፡፡ በተለይ ተከታዮቹ ሁለት አንቀጾች ይህን ግልጽ ያደርጉታል፡-
" وَأَوْفُوا الْكَيْلَ إِذَا كِلْتُمْ وَزِنُوا بِالْقِسْطَاسِ الْمُسْتَقِيمِ ذَلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا " سورة الإسراء 35
"በሰፈራችሁም ጊዜ ስፍርን ሙሉ፤ በትክክለኛው ሚዛንም መዝኑ፤ ይህ መልካም ነገር ነው፤ መጨረሻውም ያማረ ነው።" (ሱረቱል ኢስራእ 35)፡፡
" أَوْفُوا الْكَيْلَ وَلَا تَكُونُوا مِنَ الْمُخْسِرِينَ * وَزِنُوا بِالْقِسْطَاسِ الْمُسْتَقِيمِ * وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِينَ " سورة الشعراء 183-181
"ስፍርን ሙሉ፡፡ ከአጉዳዮቹም አትኹኑ፡፡ በትክክለኛ ሚዛንም መዝኑ፡፡ ሰዎችንም ነገሮቻቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ላይ አጥፊዎች
ኾናችሁ አታበላሹ፡፡" (ሱረቱ-ሹዐራእ 181-183)፡፡
9. ሐሜተኞችን፡-
የራሳቸውን ነውር ቅድሚያ በመመልከት ሊያጠሩና ሊሸፍኑ ሲገባቸው፡ የሰዎችን ነውር እየተከታተሉ ከመምከር ይልቅ ማማትና ማጋለጥ ለሚቀናቸው ሰዎች ወየውላቸው!
" وَيْلٌ لِكُلِّ هُمَزَةٍ لُمَزَةٍ " سورة الهمزة 1
"ለአሚተኛ ለዘላፊ ሁል ወዮለት።" (ሱረቱል ሁመዛህ 1)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. ሃሜት በዱንያ ክብርን የሚያጎድፍ ሰው ዘንድ ተአማኒነትን የሚያሳጣ፡ በአኼራ ደግሞ ለቅጣት የሚዳርግ መጥፎ ተግባር መሆኑን አውቀን ሰዎችን በስህተታቸው መምከር እንጂ ማማት እንደሌለብን ነው፡፡ አላሁመ ነጂና!
10. ለሰጋጆች፡-
እንደ አማኞች ሶላትን የሚሰግዱ ሆነው ነገር ግን ወቅቱን እያዘገዩ ያለ-ምክንያት ከሌላ ሶላት ጋር ደርበው የሚሰግዱ ወይንም አንዳንዴ ሶላታቸውን እያቋረጡ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለሆኑት ሰዎች ወየውላቸው!
" فَوَيْلٌ لِلْمُصَلِّينَ * الَّذِينَ هُمْ عَنْ صَلَاتِهِمْ سَاهُونَ * الَّذِينَ هُمْ يُرَاءُونَ * وَيَمْنَعُونَ الْمَاعُونَ " سورة الماعون 7-4
"ወዮላቸው ለሰጋጆች፤ለነዚያ እነሱ ከስግደታቸው ዘንጊዎች ለኾኑት፤ (ሰጋጆች)።ለነዚያ እነሱ ይውልኝ ባዮች ለኾኑት፤ የዕቃ ትውስትንም (ሰዎችን) የሚከለክሉ ለኾኑት (ወዮላቸው)።" (ሱረቱል ማዑን 4-7)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. ሶላትን ሳናቋርጥ ከወቅቱም ሳናዘገይ(ሌላ የሶላት ወቅት እስኪገባ ድረስ) በተመደበለት ሰዓት መስገድ እንደሚገባን ነው፡፡
ለ. በስራችን ላይ የሰዎችን እይታ ሳናስገባ ለአላህ ብቻ ብለን መስራት እንደሚገባን ነው፡፡
ሐ. የማይጎዳን እስከሆነ ድረስ ሰዎችን የእቃ ትውስታ ልንከለክላቸው እንደማይገባ ነው፡፡
አላህ በሰሙትና ባወቁት ከሚተገብሩ መልካም ባሮቹ ያድርገን፡፡
Join us➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Audio
🎙አዲስ ሙሐደራ🎙
"ቅዱስ ቁርአን ለኛ ምንድን ነው?"
☞በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/2qrXCJE

Join us➤ t.me/abuhyder
በጣም ይገርማል!!
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ከኢስላም ሊቃውንቶች አንዱ እንዲህ ተጠየቀ፡- የሙስሊሞችን ሁኔታ ዛሬ እንደሚታየው ስቃይና መከራ በዝቶ፣ ውርደትና እንግልት አይሎ እዚህ ደረጃ ያደረሰው ምንድነው?
ዓሊሙም ሲመልስ እንዲህ አለ፡- ስምንትን ከሶስት ያስበለጥን ጊዜ ነው አለ፡፡
ስምንት ምንድነው? ሶስትስ? በማለት ሲጠየቅ እንዲህ መለሰ፡-
እስኪ እንዲህ የሚለውን የአላህ ቃል እናንብበው፡-
"አባቶቻችሁና ወንዶች ልጆቻችሁ፣ ወንድሞቻችሁም፣ ሚስቶቻችሁም፣ ዘመዶቻችሁም፣ የሰበሰባችኋቸዉ ሀብቶችም፣ መክሰሩዋን የምትፈሩዋት ንግድም፣ የምትወዷቸው መኖሪያዎችም እናንተ ዘንድ ከአላህና ከመልክተኛዉ በርሱ መንገድም ከመታገል፣ ይበልጥ የተወደዱ እንደሆኑ፣ አላህ ትእዛዙን እስከሚያመጣ ድረስ ተጠባበቁ፣ በላቸው፤ አላህም አመጠኞች ሕዝቦችን አይመራም።" (ሱረቱ-ተውባህ 24)፡፡
1. አባቶቻችሁ
2. ልጆቻችሁ
3. ወንድሞቻችሁ
4. ሚስቶቻችሁ
5. ዘመዶቻችሁ
6. ሀብቶቻችሁ
7. ንግዶቻችሁ
8. መኖሪያ ቤቶቻችሁ
እነዚህ ስምንቱ
1. ከአላህ
2. ከመልክተኛው
3. በአላህ መንገድ ከመታገል በልጠው የተወደዱ ከሆነ ከውርደትና ከሽንፈት አንላቀቅም ነው፡፡
الثقافة لكم ከሚለው የፌስ ቡክ ፔጅ ላይ የተተረጎመ
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤ t.me/abuhyder
ክፍል ሁለት!!

አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ውድና የተከበራችሁ እሕቶቼና ወንድሞቼ!!

"ቅዱስ ቁርኣን ለኛ ምንድነው?" በሚል ርእስ ዛሬ ማታ በኢትዮ አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ በቢላል ሚዲያ በዪቲዩብ እና ፌስ ቡክ ገፅ ላይ የቀጥታ ትምሕርት ክፍል ሁለቱን ይዤላችሁ እቀርባለሁ ኢንሻአላህ።
ኡስታዝ አቡ ሀይደር

"ቅዱስ ቁርኣን ለኛ ምንድነው? #2" በኡስታዝ አቡ ሀይደር በቀጥታ LIVE ክፍል ሁለት በፌስቡክ ላይቭ ይከታተሉ


https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=541460459739244&id=378024948894679