የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
የእሙ ልጅ

የአባቶቻቸውን የነ አፄ አምደ ፅዩንን ፈለግ ተከትለው 21 መሰጂዶችን አቃጥለዋል። ሙስሊሞችን አፈናቅለዋል፣ በቦንብ ሳይቀር ገድለዋል። ከተወለዱበት መንደር ንብረታቸውን ቀምተው አባረዋል፣ ዘርፈዋል፣ አቃጥለዋል። ይሄን ሁሉ ተግባር እየፈፀሙም በአደባባይ ጨፍረዋል። ይህ የሽፍታ ባህሪ ነው። ሸፍታነት ደግሞ የመሀይምነት፣ ኃላ ቀርነትና እርኩስና ድምር ስብዕና ነው። ይህን እንደ ማለዳ ፀሀይ አደባባይ የወጣ ያደፈ ሰብዕናቸውን ለመሸፈን ብዙ ተፍጨርጭረዋል፣ እየተፍጨረጨሩም ነው። የዲያቆን ዳንዔል ክብሪት መግለጫ፣ የአማራ ማሰሚዲያና አሰራ ቲቪ ዘገባና ዶክመንታሪዎች፣ የሀሳዊ ኢትዬጲያኒሰቶች ሀተታዎች፣ የአማራ ምሁራን ማህበር መግለጫ፣ የዘመድኩን ቀረርቶ ወዘተ ሁሉም ያደፈ ሰብዕናቸውንና የሽፍታ ተግባራቸውን ለመሸፈን ያለሙ ነበሩ። አልተሳካላቸውም እንጂ። እንደ ተራራ የገዘፈ ወንጀል በብጣቂ ጨርቅ አይሸፈንምና።

በአሁኑ ሠዐት የክልሉ መሰተዳደር፣ ማሰሚዲያ፣ ባለስልጣናት፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ደብተራዎች በሙሉ በህብረት እየሰሩ ያሉት የሽፍታ ተግባራቸውን መሸፈንና አጀንዳ የማሰቀየር ጥረት ነው። በዚህም

1) በተለያዩ አካባቢ በተደረጉ ሰለፎች የሚያዙ መፈክሮችን በማጉላት ሙስሊሙን ለማሸማቀቅ መሞከር

2) መሰጂዱን ለመሰራትና ገንዘብ ማሰባሰብ የሚል ዘመቻ በማከናወን አሳፋሪውን ተግባር ማረሳሳት

3) ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት በማድረስ አጀንዳውን ማሰቀየር

4) የነሱ ተላላኪ የሆኑ አድር ባይ ሙስሊሞችን በመጠቀም የመቻቻል ሰበካዎችን ማጧጧፍ

5) በፌዴራል መጅሊስ ውስጥ ያሉ ለሙስሊሙ ደንታ የሌላቸው እንደ ቃሲም ታጁዲን ያሉ አካላትን በመጠቀም ፌዴራል መጅሊሱ እንዲለሳለስና ተቃውሞዎች እንዲቆሙ ጥሪ እንዲያሰተላልፍ ማድረግ።

6) ተጠርጣሪዎቹ ተያዙ የሚል የሀሰት ዜና ማሰራጨት
.
.
.
.

ይህ አጀንዳ የማሰቀየርና ሽፍታነታቸውን የመሸፈን ጥራት የሚሳካው ግን እኛ ከተዘናጋን ብቻና ብቻ ነው። ሰለዚህም በተለያዩ ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶችና ሌሎች የዚህ የሽፍታ ተግባር ተባባሪዎች በሚፅፏቸው ፅሁፎች ሰር አጀንዳችንን በኮሜንት ማሰፈር፣ በገፆቻችን ላይ ከዚህ አጀንዳ ውጪ ትኩረት አለመሰጠት፣ ተቃውሞዋችንን አጠናክረን መቀጠል፣ ፎቶዎቹንና ቪዲዬዎቹን ደጋግመን መለጠፍ ያሰፈልጋል። የተቃጠለውን ማሰራት፣ የተጎዱትን መካስ የክልሉ መንግሰት ኃላፊነት በመሆኑ በማንኛውም የገንዘብ መዋጮ ላይ አለመሳተፍ። ከመጅሊስ የሚመጡ መግለጫዎችን በጥንቃቄ መከታተል ያሰፈልጋል።
USTAZ ABU HYDER Offical Page
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
Photo
ምንም የተለየ ሚስጥር የለውም!!

የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ–ሰላም) ስም እንኳን 25 ጊዜ 250 ጊዜ ቢጠራም: ከሰብአዊ ፍጡርት ወደ አምላክነት፣ ከመርየም ልጅነት ወደ አላህ ልጅነት አያሻግረውምና!!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

" نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ أَحْسَنَ الْقَصَصِ بِمَا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ هَذَا الْقُرْآنَ وَإِنْ كُنْتَ مِنْ قَبْلِهِ لَمِنَ الْغَافِلِينَ " سورة يوسف 3
"እኛ ይህንን ቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን በጣም መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሃለን፡፡ እነሆ ከእርሱ በፊት (ካለፉት ሕዝቦች ታሪክ) በእርግጥ ከዘንጊዎቹ ነበርክ፡፡" (ሱረቱ ዩሱፍ 12፡3)፡፡

በዚህና መሰል የቅዱስ ቁርኣን አንቀጾች መሠረት፡- ጌታ አላህ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከቀደምት የነቢያትና የሕዝቦቻቸው ታሪክ ውስጥ፡ ለእምነታችን ጠቃሚና አርአያ የሚሆነውን በሳቸው በኩል እንደሚተርክልን መግለጹን እንመለከታለን፡፡ አያይዞም ይህ የነቢያት ዜና ‹‹በጣም መልካም ዜና›› (አሕሰኑል-ቀሶስ) መኾኑን ይገልጽልናል፡፡ ምክንያቱም በነቢያት ሥም የተጻፉ፣ የአምላክ ቃል በሚል ሽፋን የሰው ድርሰት የኾኑ የሀሰት መጽሐፍቶች አሉና!፡፡ ቅዱስ ቁርኣን ግን ቃሉም ሆነ መልእክቱ የአላህ እንጂ፡ የመላእክት ወይም የነቢያት ወይንም የጸሐፍት አይደለምና፡ በውስጡ ያሉት ታሪኮች ሁሉ ፍጹም እውነት ናቸው፡፡ ሌሎች ‹መለኮታዊ› መጽሐፍት የተባሉት በጠቅላላ በሱ ይመዘናሉ እንጂ፡ እሱ በማንም መጽሐፍት አይመዘንም፡፡

በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ እንደ ሙሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሰፊ ምእራፍ (ሱራ) እና ሰፊ ትረካን አግኝቶ፡ ታሪኩ በስፋት የተወሳ አንድም ነቢይም ኾነ ረሱል የለም፡፡ የሙሳን ያህል ሥሙ በተደጋጋሚ የተጠቀሰም አንድም ነቢይ የለም!፡፡ ሙሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሥሙ ብቻ 136 ጊዜ በአላህ ቃል ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሥሙ ከተጠራበት 5 እጥፍ በላይ ማለት ነው!፡፡ የዒሳ ሥም 25 ጊዜ ነውና በአላህ ቃል ውስጥ የተጠቀሰው!፡፡

ታዲያ ክርስቲያን ወገኖቻችን ለምን ይኾን የዒሳን 25 ጊዜ በሥም መጠቀስ፡ ከነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) 5 ጊዜ ከተጠቀሰው ሥማቸው ጋር ማነጻጸር የሚፈልጉት? ምን ዓላማስ አንግቦ ይኾን? ጥያቄው ከዚህ በፊት በተለያዩ ወንድሞች በሰፊው ምላሽ የተሰጠበት ቢኾንም፡ እነሱ ግን እንደ በቀቀን ባገኙት አጋጣሚ ደጋግሞ ከማንሳት አልተቆጠቡምና እኛም ምላሹን ከመስጠት ልንቦዝን አይገባንም፡፡ ሀሳቡን ለመረዳትም እንዲያመች፡ እንዲሁም የወገኖቻችን ሀሳብ ምንም ውሀ መቋጠር እንደማይችል ለማሳየት ቀለል ባለ መንገድ ምላሹ ቀጥሎ ይቀርባል፡፡ መልካም ንባብ፡-

1ኛ/ የሥም ተደጋግሞ መጠቀስ ልይዩ ምስጢር ቢኖረው ኖሮ፡ ለውድድር መቅረብ የነበረበት፡ በሥም ብዛት ከፍተኛውን ስፍራ የያዘው ነቢዩላህ ሙሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ነበር እንጂ፡ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) አልነበረም፡፡ ጉዳዩ ግን ሰብአዊ ፍጡር የኾነውን ዒሳን፡ ከነቢይነትና ከባርነት በማላቀቅ፡ የአምላክ ልጅና አምላክ እንደሆነ ለማሳየት፡ ከነቢያት የተለየ አድርጎ የማቅረብ ከንቱ ሙከራን የያዘ ተልእኮ በመኾኑ ነው፡፡ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሥም ደግሞ አምስት ጊዜ ብቻ በመጠቀሱ፡ 25 ጊዜ ሥሙ ከተጠቀሰው ነቢይ በደረጃ ያንሳሉ የሚል እሳቸውን ዝቅ አድርጎ ለመመልከት የሚስችል ሀሳብንም ያዘለ ነው፡፡ ግን ደረጃና ክብር መች በሥም ብዛት መጠቀስ ሆነና?

2ኛ/ በአላህ ቃል ውስጥ ታሪካቸው ከተወሱት ቀደምት የአላህ ነቢያት ውስጥ ሥማቸው ከ25 ጊዜ በላይ ተደጋግሞ የተወሳ አልለ፡፡ ይህ ማለት በነዚህ ወገኖቻችን ግንዛቤ መሠረት እነዚህ ነቢያት ደግሞ በክብርና በደረጃ ከመርየም ልጅ ይበልጣሉ ማለት ነው፡፡ አንዱን በሰፈርንበት ሚዛን ሌላውንም መስፈር ግድ ይለናልና!፡፡ የሙሳ (136)፣ የኢብራሂም (69)፣ የኑሕ (50) የዩሱፍ እና ሉጥ ሥም (27) ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለምን እነዚህን ነቢያት ዘንግተው ወደ ዒሳ መሄድ ፈለጉ? ለምን ከነሱስ ጋር ዒሳን ማወዳደር አልፈለጉም? ጉዳዩ በኢስላም ላይ የተከፈተ ዘመቻ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ የነቢዩ ሙሐመድን ክብር ዝቅ ለማድረግና የመርየምን ልጅ ከደረጃው በላይ ለመስቀል የሚደረግ መፍጨርጨር እንጂ ሌላ አይደለም!፡፡

3ኛ/ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) ሥሙ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 25 ጊዜ መጠቀሱ ምንም ምስጢር የለውም፡፡ እንግዳ ነገርም አይደለም፡፡ ባይሆን በተጠቀሰባቸው 25 ቦታዎች ላይ ከሥሙ ጋር ተያይዞ ስለ-ማንነቱ ምን መልእክት ለማስተላለፍ ተፈለገ? ብሎ ጥያቄ ማንሳቱ ብልህነት ነው፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ በተጠቀሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ላይ ለማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት፡-

ሀ/ እሱም እንደሌሎች መልክተኛ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ለመግለጽ!፡- ይህ አንዱ እና ዋናው ነጥብ ነው፡፡ የመርየም ልጅ ዒሳ ከሱ በፊት እንዳለፉት መልክተኞች የኾነ መልክተኛ እንጂ ሌላ አይደለም!፡፡ ምግብንም ተመጋቢ ነበር፡፡ የበላው ነገር ከሰአታት በኋላ ከሰውነቱ ማውጣቱና ማስወገዱም ግዳጁ ነው፡፡ ከተፈጥሮ ህግ ሊወጣ አይችልምና!፡፡ ይህ ደግሞ ሰብአዊ ፍጡር መኾኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"የመርየም ልጅ አልመሲሕ ከበፊቱ መልክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ እናቱም በጣም እውነተኛ ናት፡፡ (ሁለቱም) ምግብን የሚበሉ ነበሩ፤ አንቀጾችን ለነርሱ (ለከሓዲዎች) እንዴት እንደምናብራራ ተመልከት ከዚያም (ከእውነት) እንዴት እንደሚመለሱ ተመልከት፡፡" (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡75)፡፡

ለ/ አምላክ እንዳልሆነና ነኝ ማለትም እንደማይገባው ለማስረዳት፡- ዒሳን (ዐለይሂ-ሰላም) ከሰብአዊ ፍጡርነቱ በማውጣት መለኮታዊ ባሕሪን ማላበስ ፍጹም ክህደት ነው፡፡ የቂያም ቀንም ለጀሀነም እሳት የሚዳርግ ታላቅ ኃጢአት ነው፡፡ በመኾኑም እሱ አምላክ አለመኾኑን ለማስተማር ሥሙና ታሪኩ ተወሳ፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"እነዚያ «አላህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ነው» ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ አልመሲህም አለ፡- «የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታዬንና ጌታችሁን አላህን ተገዙ፡፡» እነሆ! በአላህ የሚያጋራ ሰው አላህ በርሱ ላይ ገነትን በእርግጥ እርም አደረገ፡፡ መኖሪያውም እሳት ናት፡፡ ለበዳዮችም ምንም ረዳቶች የሏቸውም፡፡" (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡72)፡፡

ሐ/ የአላህ ባሪያ እንጂ ልጁ እንዳልሆነ ለመግለጽ፡- ፍጥረታት በጠቅላላ የአላህ ባሪያ ናቸው (ሱረቱ መርየም 19፡93)፡፡ የመርየምን ልጅ ከዚህ ባርነት ሊያስወጣው የሚችል ምንም ማንነት የለውም፡፡ እሱም ቢሆን የአላህ ባሪያ በመሆኑ በፍጹም አይጠየፍም፡፡ ስለዚህ የአላህ ባሪይ እንጂ ልጁ ተብሎ እንደማይጠራ ለማስረዳት ተጠቀሰ፡፡ ጌታ አላህ እንዲህ ይላል፡-

"አልመሲሕ (ኢየሱስ) ለአላህ ባሪያ ከመኾን ፈጽሞ አይጠየፍም፡፡ ቀራቢዎች የኾኑት መላእክትም (አይጠየፉም)፡፡ እርሱን ከመገዛት የሚጠየፍና የሚኮራም ሰው (አላህ) ሁሉንም ወደ እርሱ በእርግጥ
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
Photo
ይሰበስባቸዋል፡፡ እነዚያማ ያመኑት መልካሞችንም የሠሩት ምንዳዎቻቸውን ይሞላላቸዋል፡፡ ከችሮታውም ይጨምርላቸዋል፡፡ እነዚያን የተጠየፉትንና የኮሩትንማ አሳማሚን ቅጣት ይቀጣቸዋል፡፡ ከአላህም ሌላ ለእነሱ ዝምድንና ረዳትን አያገኙም፡፡" (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡171-172)፡፡

"እርሱ በርሱ ላይ የለገስንለት ለእስራኤለም ልጆች ተዓምር ያደረግነው የኾነ ባሪያ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡" (ሱረቱ-ዙኽሩፍ 43፡59)፡፡

መ/ መጽሐፍና ተአምራት እንደተሰጠው ለመግለጽ፡- የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) እንደቀደሙት የአላህ መልክተኞች እሱም መልክተኛ በመሆኑ መጽሐፍ (ኢንጂል) ተሰጥቶታል፡፡ ቀደምት ነቢያት ተአምራት እንደተሰጣቸው ለሱም ተአምራት የማድረግ ችሎታ ተሰጥቶታል፡፡ ማንኛውም የአላህ መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ በቀር በገዛ ፈቃዱ ተአምርን ማድረግም ሆነ ማምጣት አይችልም (ሱረቱ-ረዕድ 13፡38)፡፡

"ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክትኞችን አስከታተልን፡፡ የመርየምን ልጅ ዒሳንም ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው፡፡ በቅዱሱ መንፈስም አበረታነው፡፡ ነፍሶቻችሁ በማትወደው ነገር መልክተኛ በመጣላችሁ ቁጥር (ከመከተል) ትኮራላችሁን? ከፊሉን አስተባበላችሁ፤ ከፊሉንም ትገድላላችሁ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡87)፡፡

ይህ ነው እውነታው!፡፡ የቁርኣኑ ዋና ዓላማ፡- በመርየም ልጅ ላይ ወሰን በማለፍ የተሳሳቱትን ሁለት ጠርዘኛ ቡድኖች በመገሰጽ፡ ትክክለኛ ማንነቱን ደግሞ በማብራራትና በመግለጽ ሚዛናዊነትን ማሳየት ነው!፡፡ አንደኛው ጠርዘኛ ቡድን፡ አላህ ከሰጠው የነቢይነትና የመልክተኝነት ሚና፡ ደረጃውን ዝቅ በማድረግና ክብሩን በማሳነስ፡ በሀሰተኝነትና በደጋሚነት ሲወነጅለው፣ እንዲሁም ከድንግል በተአምር መወለዱን ጥያቄ ውስጥ በመክተት የዝሙት ልጅ ብሎ ሲከሰው እናያለን (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡156፣ አል ማኢዳህ 5፡110፣ አል-ሶፍ 61፡6)፡፡

ሌላኛው ጠርዘኛ ቡድን ደግሞ፡ አላህ ከሰጠው የነቢይነትና የመልክተኝነት ሚና በላይ፡ ደረጃውን ከፍ በማድረግና ክብሩን በማላቅ፡ እሱን ጌታና አምላክ አድርጎ መያዝ፣ እንዲሁም ያለ አባት ከድንግል ብቻ መወለዱን በማንሳት የአምላክ ልጅ እንደሆነ አድርጎ መስበኩ ነው፡፡

ሁለቱም አመለካከቶች በስህተት ላይ ያሉ መሆናቸውን ለመግለጽ፡ እውነታውም የመርየም ልጅ ዒሳ (ዐለይሂ-ሰላም) የአላህ መልክተኛና ባሪያው፡ ከመርየም በይኹን ቃሉ የፈጠረው ፍጥረቱ መሆኑን ለማስረዳት፡ በሱ ላይ ወሰን ያለፉ የእምነት ግሩፖችም ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲመለሱ ለመርዳት የዒሳ ማንነት በሥሙ 25 ጊዜ፣ በኩንያው 23 ጊዜ፣ በለቀቡ (ቅጽል ሥሙ) 11 ጊዜ ተጠራ፡፡ ሌላ ምንም ስውር ምስጢር የለውም፡፡

4ኛ/ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስንመለስ ደግሞ፡- የሳቸው ሥም በአላህ ቃል ውስጥ አምስት ጊዜ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ ለምን እንደ ዒሳ 25 ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ አልተወሱም? የሚል ጥያቄ ከተነሳም፡ መልሳችን የሚሆነው፡-

ሀ/ ቅዱስ ቁርኣኑ ራሱ ይወርድ የነበረው በሳቸው ልብ ላይ ነው፡፡ የሚያናግረውም እሳቸውን ነው፡፡ እንደነ ዒሳና ሙሳ በታሪክ ኖረው ያለፉ ነቢይ ሳይሆኑ፡ በዘመኑ የነበሩ ሕያው ነቢይ ነበሩና፡ የሳቸውን ሥም ደጋግሞ መጥቀሱ ምንም አስፈላጊነት አልነበረውም፡፡ እነደቀደሙት ነቢያት ‹‹እንዲህ ነበሩ›› እየተባለ ሊወራላቸው የሚችለው፡ ምድራዊ ተልእኮዋቸውን ፈጽመው፡ ወደ ዘላለማዊው ዓለም ቢሻገሩ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ ከሳቸው መሞት በኋላ በተጻፉት የሲራ መጻሕፍት ላይ ነው የሚገኘው፡፡

ለ/ ጌታ አላህ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በቀጥታ በመጥራት አናግሯቸዋል፡፡ ሲጠራቸው የነበረው ግን ‹‹ያ አዩኸ-ረሱሉ፣ ያ አዩኸ-ነቢዩ›› (አንተ መልክተኛ ሆይ! አንተ ነቢይ ሆይ!) በማለት ከአላህ ዘንድ በተመረጡበትና በተሰጣቸው የክብር ሥም ነው (አል-ማኢዳህ 5፡41፣ 5፡67፣ አል-አንፋል 8፡64፣ አል-አሕዛብ 33፡45)፡፡ አንድም ስፍራ ላይ ‹‹ሙሐመድ ሆይ!›› የሚል ጥርሪን ባዘለ መልኩ ሲያናግራቸው አናገኝም፡፡ ይህ የሚያሳያው እሳቸው ከቀደምት ነቢያት የበለጠ ክብርና ደረጃ ያላቸው መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም እኛም የሳቸው ተከታይ የሆንን ሙስሊሞች እሳቸውን በስማቸው ብቻ መጥራትን አላህ ከለከለን፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"በመካከላችሁ የመልክተኛውን ጥሪ ከፊላችሁ ከፊሉን እንደ መጥራት አታድርጉት፡፡ ከእናንተ ውስጥ እነዚያን እየተከለሉ በመስለክለክ የሚወጡትን አላህ በእርግጥ ያውቃቸዋል፡፡ እነዚያም ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ እንዳትደርስባቸው ወይም አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ፡፡" (ሱረቱ-ኑር 24፡63)፡


ሐ/ የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ክቡር ሥም የሆነው ‹‹ሙሐመድ›› እና ‹‹አሕመድ›› በአላህ ቃል ውስጥ አራት ጊዜና አንድ ጊዜ በጥቅሉ አምስት ጊዜ ተጠቀሶአል፡፡ በነዚህ ቦታዎችም ላይ ለማስተላለፍ የተፈለገው መልእክት፡- እሳቸው እነደቀደሙት ነቢያትና መልክተኞች ሰው የሆኑ ነቢይና መልክተኛ በመሆናቸው ዘላለማዊ ሕያው አይደሉምና ሊሞቱ እንደሚችሉ በመግለጽ፡ በሳቸው ሞት ሰበብ ማንም ከእምነት ማፈግፈግ እንደሌለበት በማስተማር ለመገሰጽ (አሊ-ዒምራን 3፡164)፣ እሳቸው ላልወለዷቸው ልጆች አባት ተብለው እንደማይጠሩና የአላህ መልክተኛና የነቢያት መደምደሚያ መሆናቸውን ለመግለጽ (አል-አሕዛብ 33፡40፣ አል-ፈትሕ 48፡29)፣ የሳቸውን ነቢይነት አምኖ የተቀበለ ሰው የኃጢአት ስርየትን እንደሚያገኝ ለማስተማር (ሱረቱ ሙሐመድ 47፡2)፡፡ እንዲሁም በመርየም ልጅ በዒሳ የተበሰሩ (ትንቢት የተነገረላቸው ነቢይ) መሆናቸውን ለማሳየት ነው (አል-ሶፍ 61፡6)፡፡

5ኛ/ እኛ እንደ ሙስሊምነታችን የመርየም ልጅ ዒሳም ሆነ ነቢዩ ሙሐመድ (ዐለይሂማ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) የአላህ ነቢይ እና መልክተኛ መሆናቸውን አምነናል፡፡ የሁለቱን ብቻ ሳይሆን በነቢያትና በመልክተኞች በጠቅላላ አምነናል (አል-በቀራህ 2፡285)፡፡ የእምነታችንም አንድ አካል ነው፡፡ (አል-በቀራህ 2፡177)፡፡ እናንተ ግን የነቢዩ ሙሐመድን ነቢይነት አምናችሁ ካልተቀበላችሁ፡ ለምን በሥም ብዛት የተጠቀሰውን በመፈለግ ማወዳደርን መረጣችሁ? ነቢይ መሆናቸውን አምናችሁ ካልተቀበላችሁ ሥማቸው አርባ ጊዜ ተጠቀሰ ወይም አራት ጊዜ ለናንተ ምን ይፈይድላችኋል? ለዚህ ነው ሙግታችሁ ውሀ የማያነሳ ከንቱ ሀሳብ ያልነው፡፡ ወገኖቻችን በእሳት ላይ ነው ያላችሁት፡፡ በዕድሜያችሁ አትቀልዱ፡፡ በፍጹማዊ አንድነቱ ሶስትነት የሌለበት፣ በአምላካዊ ማንነቱ ሰዋዊነት ያልተቀላቀለበት፣ በፍጹም ሕያውነቱ ሞትና እንቅልፍ የማይከተለው፣ በእኔነት እራሱን የሚገልጥ፣ በአንተነት የሚጠራና የሚለመን፣ በእሱነት ለሰዎች የሚሰበክ፣ በእኛት ሥራዎቹን የሚያሳይ፣ በእነሱነት ፈጽሞ የማይጠራ የኾነውን አንዱንና እውነተኛውን አምላካችንን አላህ ታመልኩ ዘንድ በአክብሮት ጥሪ እናቀርብላችኋለን፡፡ አላህ ወደ ሐቅ ይምራችሁ!

"የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! በእኛና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ (እርሷም) አላህን እንጅ ሌላን ላንገዛ፣ በርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጎ ላይይዝ ነው፤ በላቸው፡፡ እምቢ ቢሉም፡- እኛ ሙስሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፡፡" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡64)፡፡

ይቀጥላል….
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
ከንዲህ አይነቱ ከንቱ ምኞት አላህ ይጠብቀን
በአቡ ሀይደር
#ዘጠኙ ከንቱ ምኞቶች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
ምኞት የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ባሕሪ ነው፡፡ የወደደውንና ያሰበውን ነገር ለማግኘት ይመኛል፡፡ በመሆኑም በኢስላም ምኞት አልተከለከለም፡፡ የሚከለከለው ምኞታችን እውን እንዲሆን የሚያግዙ ነገሮችን ከመስራት ችላ ብለን፡ ካለንበት ቦታ ሳንንቀሳቀስ: ራሳችንን ለመቀየር ጥረት ሳናደርግ ያሰብነውን ለመሆንና ለማግኘት መመኘት ነው፡፡
ዛሬ የምናየው ‹‹ከንቱ ምኞት›› የተሰኘው ርእስ፡- ጊዜያቸው ካለፈ በኋላ የምንመኛቸው፡ መሆን በሚቻልበት ዘመን መሆን እየተቻለ፡ በስንፍናና በአልባሌ ነገር ተዘናግተን አሳልፈን ካጠፋነው በኋላ፡ ምነው ሰርቼ በነበር ብሎ መመኘት ነው፡፡ ጊዜው ካለፈ በኋላ ዳግም ላይመለስ፣ የጸጸቱ ብዛት ማስተዛዘኛ ላይደረግለት ሰው በከንቱ የሚመኛቸው በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የተጠቀሱ 9 ምኞቶች አሉ፡፡ እነሱም፡-
1. ምነው ከአማኞች ጋር በነበርኩ!
" يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا خُذُوا حِذْرَكُمْ فَانْفِرُوا ثُبَاتٍ أَوِ انْفِرُوا جَمِيعًا * وَإِنَّ مِنْكُمْ لَمَنْ لَيُبَطِّئَنَّ فَإِنْ أَصَابَتْكُمْ مُصِيبَةٌ قَالَ قَدْ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيَّ إِذْ لَمْ أَكُنْ مَعَهُمْ شَهِيدًا * وَلَئِنْ أَصَابَكُمْ فَضْلٌ مِنَ اللَّهِ لَيَقُولَنَّ كَأَنْ لَمْ تَكُنْ بَيْنَكُمْ وَبَيْنَهُ مَوَدَّةٌ يَا لَيْتَنِي كُنْتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًا " سورة النساء 73-71
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጥንቃቄያችሁን ያዙ። ክፍልፍልም ጓድ ሆናችሁ (ለዘመቻ) ውጡ፤ ወይም ተሰብስባችሁ ውጡ። ከናንተም ውስጥ በእርግጥ (ከዘመቻ) ወደ ኋላ የሚንጓደድ ሰው አለ፤ አደጋም ብታገኛችሁ ከነሱ ጋር ተጣጅ ባልሆንኩ ጊዜ አላህ በእኔ ላይ በእርግጥ ለገሰልኝ ይላል። ከአላህም የሆነ ችሮታ ቢያገኛችሁ፣ በናንተና በርሱ መካከል ፍቅር እንዳልነበረች ሁሉ፣ ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በኾንኩ ወይ ምኞቴ! ይላል።" (ሱረቱ-ኒሳእ 71-73)፡፡
- የኢስላምን ዳር ድንበር ለማስጠበቅና የአማኞችን የነጻነት አምልኮ ለማስከበር ጠላትን መታገል ግድ ሆኖ ሳለ፡ ለህይወቱና ለንብረቱ በመሳሳት ከትግል ወደ ኋላ የቀረ ሰው፡ አማኞች በአላህ እርዳታ ድልን የተጎናጸፉ ጊዜ፡ እሱ ግን ውስጡ በቁጭት የተሞላ ሆኖ፡- ‹‹ምነው እኔም ከነሱ ጋር በነበርኩና የድሉም ባለቤት በሆንኩ!›› ማለቱ የማይቀር ነው፡፡ ግን ከንቱ ምኞት ነው፡፡ በወቅቱ አብሯቸው ከመሆን ማን ከለከለውና!!፡፡ በመሆኑም ዛሬውኑ ከዱዓ ጀምሮ አቅሙ የቻለውን በማድረግ ለኢስላም የበኩሉን ግዳጅ ይወጣ፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡
2. ምነው ወደ ዱንያ በተመለስን!
" وَلَوْ تَرَى إِذْ وُقِفُوا عَلَى النَّارِ فَقَالُوا يَا لَيْتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِآيَاتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ " سورة الأنعام 27
"በእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን ከምእምናንም በኾንን ዋ ምኞታችን! ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር)፡፡" (ሱረቱል አንዓም 27)፡፡
- በምድረ ዓለም እያሉ ለጀነት ብቁ የሚያደርጋቸውን የተስተካከለ እምነትና መልካም ስራዎችን በመስራት በአላህ ራሕመት ከጀነት ሰዎች ለመሆን ዕድሉ የሰፋ ሆኖ ሳለ፡ ያንን ሳይጠቀሙበት ጊዜውን በከንቱና በመጥፎ አሳልፈው ነጌ የእሳት መሆናቸውን ሲያረጋግጡ፡- ‹‹ምነው አንዴ ወደ ዱንያ ተመልሰን አማኝና መልካም ሰሪ ሆነን በመጣን!›› ብሎ መመኘት ከንቱ የሆነ ምኞት ነው፡፡
እናም አሁንም ጊዜው አለንና ወደ ቀብር ዓለም ከመግባታችን በፊት፡ ለቀብርና ለዘለቄታው ዓለም (አኼራ) የሚጠቅመንን መልካም ስራ በመስራት ላይ እንበርታ እንጠናከር፡፡ በተለይም፡- በ5 ወቅት የፈርድ ሶላቶች፣ በዱዓእ፣ በዚክር፣ በወላጅ ሐቅና በመሳሰሉት፡፡
3. ምነው በጌታዬ ባላጋራሁ!
" وَأُحِيطَ بِثَمَرِهِ فَأَصْبَحَ يُقَلِّبُ كَفَّيْهِ عَلَى مَا أَنْفَقَ فِيهَا وَهِيَ خَاوِيَةٌ عَلَى عُرُوشِهَا وَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُشْرِكْ بِرَبِّي أَحَدًا " سورة الكهف 42
"ሀብቱም ተጠፋ፤ እርሷ በዳሶችዋ ላይ የወደቀች ሆና በርሷ ባወጣው ገንዘብ ላይ (እየተጸጸተ) መዳፎቹን የሚያገላብጥና ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድንም ባላጋራሁ የሚል ሆነ።" (ሱረቱል ከህፍ 42)፡፡
- አላህ በሰጠው ሃብትና ንብረት ጌታውን እያመሰገነ መልካም ሊሰራበት ሲገባው፡ በትእቢቱና በክህደቱ ሰበብ አላህ የሰጠውን ሃብት ተመልሶ የወሰደበትና ያጠፋበት ጊዜ፡- ‹‹ምነው በጌታዬ ባላጋራሁ ኖሮ!›› ብሎ ቢመኝ የማይሆን ከንቱ ምኞት ነው፡፡ በመሆኑም፡- አላህ በሰጠን ንብረት የሚገባውን ሶደቃ በመስጠት፡ አላህን ሊያስቆጣ ከሚችል ተግባርና ከኢስራፍ (ማባከን) በመጠንቀቅ፡ አኼራችንን እናሳምርበት፡፡
4. ምነው እሱን ጓደኛ ባላደረኩ!
" وَيَوْمَ يَعَضُّ الظَّالِمُ عَلَى يَدَيْهِ يَقُولُ يَا لَيْتَنِي اتَّخَذْتُ مَعَ الرَّسُولِ سَبِيلًا * يَا وَيْلَتَى لَيْتَنِي لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًا * لَقَدْ أَضَلَّنِي عَنِ الذِّكْرِ بَعْدَ إِذْ جَاءَنِي وَكَانَ الشَّيْطَانُ لِلْإِنْسَانِ خَذُولًا " سورة الفرقان 29-27
"በዳይም፦ ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ ዋ ምኞቴ! እያለ (በጸጸት) ሁለት እጆቹን የሚነክስበትን ቀን (አስታውስ)።ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፤ (የእምነት ቃልን) ከመጣልኝ በኋላ ከማስታወስ በእርግጥ አሳሳተኝ፤ (ይላል)፤ ሰይጣንም ለሰው አጋላጭ ነው።" (ሱረቱል ፉርቃን 27-29)፡፡
- አላህ የላከለትን መልክተኛ ማመንና የሱን መንገድ ተከትሎ ከአማኞች ጋር መሆን እየቻለ፡ የክህደትን መንገድ መርጦ ከክፉ ጓደኞች ጋር ተወዳጅቶ መጨረሻውም ተበላሽቶ የሞተ ሰው፡ የትንሳኤ እለት የቅጣቲቱ ቃል ሲረጋገጥበት ጣቶቹን እየነከሰ፡- ‹‹ምነው መልክተኛውን በተከተልኩና ከነ-እንትና ጋር ጓደኝነትን ባልመሰረትኩ!›› እያለ ቢመኝና ቢቆጭ የማይሰራ ከንቱ ምኞት ከመሆን አይዘልም፡፡
ስለዚህም፡- ለአኼራ የሚጠቅመንን ጓደኛ እንምረጥ፡፡ ስናየው አኼራን የሚያስታውሰን፣ ስናጠፋ የሚገስጸንና የሚመክረን፣ ያላወቅነውን የሚያስተምረን፣ ኢማንና መልካም ስነ-ምግባር ያለው ወዳጅ እንፈልግ፡፡
5. ምነው ታዝዤ በነበር!
" إِنَّ اللَّهَ لَعَنَ الْكَافِرِينَ وَأَعَدَّ لَهُمْ سَعِيرًا * خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا لَا يَجِدُونَ وَلِيًّا وَلَا نَصِيرًا * يَوْمَ تُقَلَّبُ وُجُوهُهُمْ فِي النَّارِ يَقُولُونَ يَا لَيْتَنَا أَطَعْنَا اللَّهَ وَأَطَعْنَا الرَّسُولَا * وَقَالُوا رَبَّنَا إِنَّا أَطَعْنَا سَادَتَنَا وَكُبَرَاءَنَا فَأَضَلُّونَا السَّبِيلَا " سورة الأحزاب 67-64
"አላህ ከሐዲዎችን በእርግጥ ረግቸሟዋል፤ ለነርሱም የተጋጋመችን እሳት አዘጋጅቷል። በርሷ ውስጥ ዘለዓለም ዘውታሪዎች ሲሆኑ፤ ወዳጅም ረዳትም አያገኙም። ፊቶቻቸው በእሳት ውስጥ በሚገለባበጡ ቀን፥ ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን፥ መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ እያሉ ይጸጸታሉ፤ይላሉም ፦ ጌታችን ሆይ እኛ ጌቶቻችንንና ታላቆቻችንን ታዘዝን፤ መንገዱንም አሳሳቱን፤" (ሱረቱል አሕዛብ 64-67)፡፡
- ዛሬ በዱንያ አላህን በብቸኝነት እያመለኩ የተላከላቸውን መልክተኛ ደግሞ እየታዘዙ መኖርና ለአኼራ ስኬታማ መሆን ሲቻል፡ ከሀዲያንን ታዘው የጥመት መምህራንን ተከትለው ሲያበቁ የቂያም ዕለት፡- ‹‹ምነው መልክተኛውን ታዘን በነበር!›› ማለት ከንቱ ምኞት ነው፡፡
ይህ ዕጣ እኛም ላይ እንዳይደርስ፡ ቅድሚያ ታዛዥነትን ለአላህና ለመልክተኛው እናድርግ፡፡ ከነሱ ፈቃድና ትእዛዝ በፊት የነፍሲያችንንም ስሜት ቢሆን አናስቀድም፡፡ ወደ ሀሰት የሚጠሩ የጥመት መሪዎችንም እንራቃቸው፡፡
6. ምነው ተራርቀን በነበር!
" وَمَنْ يَعْشُ عَنْ ذِكْرِ الرَّحْمَنِ نُقَيِّضْ لَهُ شَيْطَانًا فَهُوَ لَهُ قَرِينٌ * وَإِنَّهُمْ لَيَصُدُّونَهُمْ عَنِ السَّبِيلِ وَيَحْسَبُونَ أَنَّهُمْ مُهْتَدُونَ * حَتَّى إِذَا جَاءَنَا قَالَ يَا لَيْتَ بَيْنِي وَبَيْنَكَ بُعْدَ الْمَشْرِقَيْنِ فَبِئْسَ الْقَرِينُ * وَلَنْ يَنْفَعَكُمُ الْيَوْمَ إِذْ ظَلَمْتُمْ أَنَّكُمْ فِي الْعَذَابِ مُشْتَرِكُونَ " سورة الزخروف 39-36
"ከአልረሕማን ግሣጼ (ከቁርአን) የሚደናበርም ሰው ለርሱ ሰይጣንን እናስጠጋለን፤ ስለዚህ እርሱ ለርሱ ቁራኛ ነው። እነርሱም (ተደናባሪዎቹ) ተመሪዎች መሆናቸውን የሚያስቡ ሲሆኑ እነርሱ (ሰይጣናት) ከቀጥተኛው መንገድ በእርግጥ ያግዷቸዋል። (በትንሣኤ) ወደኛ በመጣም ጊዜ (ቁራኛዬ ሆይ!) በኔና ባንተ መካከል የምሥራቅና የም ዕራብ ርቀት በኖረ ወይ ምኞቴ! ምን የከፋህ ቁራኛ ነህ ይላል። ስለ በደላችሁም ዛሬ እናንተ በቅጣት ተጋሪዎች መሆናችሁ አይጠቅማችሁም፤ (ይባላሉ)።" (ሱረቱ-ዙኽሩፍ 36-39)፡፡
- አላህን ከማውሳትና ከቅዱስ ቁርኣን የራቀ ሰው በምትኩ የሸይጧን ቁራኛ ይሾምበታል፡፡ ታዲያ የትንሳኤ ዕለትም ቁራኛውን፡- ‹‹አንተ ምንኛ የከፋህ ቁራኛ ነህ! ምነው መጀመሪያውኑ ተራርቀን በነበር›› ብሎ ቢመኝ ከንቱ ጸጸትና ምኞት ነው፡፡ ይህ እንዳይከሰት፡- አላህን ከማውሳትና ከማወደስ፡ እንዲሁም ቁርኣንን ከማንበብና ከማስተንተን እንዳንቦዝን እንዳንዘናጋ፡፡
7. ምነው ባልተሰጠኝ!
" وَأَمَّا مَنْ أُوتِيَ كِتَابَهُ بِشِمَالِهِ فَيَقُولُ يَا لَيْتَنِي لَمْ أُوتَ كِتَابِيَهْ * وَلَمْ أَدْرِ مَا حِسَابِيَهْ * يَا لَيْتَهَا كَانَتِ الْقَاضِيَةَ * مَا أَغْنَى عَنِّي مَالِيَهْ * هَلَكَ عَنِّي سُلْطَانِيَهْ " سورة الحاقة 29-25
"መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ ዋ ጥፋቴ ምነው ምጽሐፌን ባልተሰጠሁ ይላል። ምርመራየንም ምን እንደ ሆነ ባላወቅሁ። እርሷ (ሞት ሕይወቴን) ምነው ፈጻሚ በሆነች። ገንዘቤ ከኔ ምንንም አላብቃቃኝ (አልትጠቀመኝም)።ኅይሌ ከኔ ላይ ጠፋ (ይላል)።" (ሱረቱል ሓቅቃህ 25-29)፡፡
- የመልካም ስራ መዝገቡ እንዲያመዝንለት በእምነትና በበጎ ተግባር መሽቀዳደም እየታቸለ፡ በዝንጋቴ ላይ ሁኖ መጥፎ ስራው አመዝኖበት የስራ መጽሐፉ በግራው የተሰጠው ሰው፡- ‹‹ምነው ባልተሰጠኝ!›› የሚል ከንቱ ምኞትን ይመኛል፡፡ ከመልካም ፈገግታ ጀምሮ በኸይር ስራ ሚዛን ላይ ሊያመዝንልንና ሊጠቅመን የሚችልን ነገር ከመተግበር ወደ ኋላ አንበል፡፡
8. ምነው አፈር በሆንኩ!
" إِنَّا أَنْذَرْنَاكُمْ عَذَابًا قَرِيبًا يَوْمَ يَنْظُرُ الْمَرْءُ مَا قَدَّمَتْ يَدَاهُ وَيَقُولُ الْكَافِرُ يَا لَيْتَنِي كُنْتُ تُرَابًا " سورة النبأ 40
"እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሐዲውም ዋ ምኞቴ ምንነው ዐፈር በሆንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የሆነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ።" (ሱረቱ-ነበእ 40)፡፡
- እንሰሳቶችም ተቀስቅሰው ቀንድ የነበረው ከብት ቀንድ ያልነበረውን ወግቶ ከነበረ፡ አሁን በምትኩ ቀንድ ላልነበረው ቀንድ ይሰጥና ቀንድ የነበረውን ከብት እንደወጋው እንዲወጋው ተደርጎ ፍትሕ ይጠበቅና፡ ከዛም አፈር ሁኑ ሲባል፡ ከሀዲው የሰው ልጅ ደግም እሱ ጀሐነም እንጂ ሌላ እንደሌለው ሲያረጋግጥ፡- ‹‹ምነው እኔም አፈር ሆኜ በቀረሁ!›› በማለት የማይሆን ከንቱ ምኞት ይመኛል፡፡
9. ምነው ሰርቼ በነበር!
" وَجِيءَ يَوْمَئِذٍ بِجَهَنَّمَ يَوْمَئِذٍ يَتَذَكَّرُ الْإِنْسَانُ وَأَنَّى لَهُ الذِّكْرَى * يَقُولُ يَا لَيْتَنِي قَدَّمْتُ لِحَيَاتِي " سورة الفجر 24-23
"ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ፣ በዚያ ቀን ሰዉ (ጥፋቱን) ይገነዘባል። መገንዘቡም ለርሱ ከየቱ? ዋ እኔ! ምነዉ በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ ይላል።" (ሱረቱል ፈጅር 23-24)፡፡
ዛሬ በተሰጠን ረጅም እድሜ መልካም ስራ በመስራት ጊዜያችንን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት፡ የጸጸቱ ቀን ይመጣና፡- ‹‹ምነው መልካም ስራ ሰርቼ በነበር!›› በማለት ከንቱ የሆነ ምኞት የምናስብበት ቀን ይመጣል፡፡
አላህ በአኼራ ከንቱ ከሆነ ጸጸትና ምኞት ጠብቆ በዱንያ በትክክለኛ እምነትና በመልካም ስራ የምንገናኘው ያደርገን፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኡስታዝ አቡ ሐይደር ከልጁ ሐይደር ጋር ያስተላለፈው ወሳኝ መልዕክት
https://youtu.be/9nn7C4bYU9E
ታቦትን እንድናከብር የሚያዝ የቁርኣን ክፍል የለም! እዛው በፀበላችሁ!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

ወደ ኢስላም ብርሀን የሚጣሩና ከኢስላም ውጭ ያሉ የጨለማው ዓለም ተጓዦችን መንገድ እንዳንከተል የሚያስጠነቅቁ ሙስሊም ዳዒያን ትልቅ ለውጥ አምጥተዋል። ጀዛሁሙላሁ ኸይራ። ሙስሊሙ ኡምማ ከሌላው ሃይማኖት ተከታይ ጋር: ከአላህ ዘንድ ከመጣልን መመሪያ ጋር ባልተጋጨ መልኩ: በማኀበራዊ ኑሮ በጋራ በመተጋገዝ፣ የራሱን ሃይማኖት አስከብሮና የሌላውን አክብሮ እንዲኖር፣ በመከባበርና በመቻቻል ሽፋን ግን ከሌላው ሃይማኖት ተከታይ ጋር በሃይማኖታዊ ስርአትም ሆነ በዓላት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በፍፁም ተሳታፊ እንዳይሆን አበክረው መክረዋል። መከባበርና መቻቻል ሌላ፣ መመሳሰል ደግሞ ሌላ እንደሆነ መረጃን አጣቅሰው አብራርተዋል። የጥፋት ሰባኪያን ግን ይህ ሐቅ አልዋጥ አላቸው። እንደ ጨለማው ዘመን ሙስሊሙ ከኋላቸው ጭራ በመሆን ታቦት ሲወጣ አብሮ መከተልና መሸኘት፣ ለሃይማኖታዊ በዓላቸው የእንኳን አደረሳችሁ መልክት መጉረፍ እየመነመነ ሲመጣ: በነዚህ የኢስላም ዳዒያን ላይ ጥርሳቸውን ነከሱ። እነሱንም ከሌላው ሙስሊም ለመነጠልና በግል ለማጥቃት እንዲመቻቸው "ወሀቢይ" የሚለውን ስያሜ በግርድፉ በመዋስ በነሱ ላይ ለጠፉባቸው። እንደዛም ሆኖ አልተሳካላቸውም። አሁንም ወሀቢያ ተብሎ ከማይተቸው ሙስሊም ማኀበረሰብ እንደበፊቱ ለበዓላቸው ጭራና ተከታይ የሚሆን ማግኘት አልተቻላቸውም። ይህ አልሳካ ሲል ከጥፋት ሰባኪዎቻቸው አንዱ ወደ ቅዱስ ቁርኣን በመግባት: ቁርኣን ታቦትን አክብሩ ይላል! ዑስታዞችችሁ ግን ይህን እውነት ለዘመናት ከናንተ ደብቀውታል! እነሱ ግን ስድብና ጥላቻ ብቻ ነው የሚያስተምሯችሁ በማለት ቅጥፈቱን ተያይዞታል።

ስድብ ቤቱን ያውቃል። መነሻውም መድረሻውም ከናንተው ነው። ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የሙስሊምን ባሕሪ ሲገልፁ:– "ለይሰል ሙስሊሙ ሳብበን ወላ ለዕዓናህ" [ሙስሊም ተሳዳቢም ተራጋሚም አትደለም!] በማለት መላበስ ያለብንን ስነ–ምግባር ገልፀዋል። የእምዬን እከክ ወደ አብዬ ልክክ ማድረግ የሚቀናቸው የጥፋት ሰባኪያን ግን የዋሁ ተከታያቸው የኢስላም ብርሀን እንዳይደርሰውና ባለበት ጨለማ ፀንቶ እንዲጓዝ ጉድጓዱን እየማሱለት ነው። አላህ ይድረስላቸው።

ይህ የጥፋት ሰባኪ ሙስሊሞች ታቦትን ያከብሩ ዘንድ ቁርኣን ያዛቸዋል በማለት ተከታዩን ጥቅስ በአግባቡ ሳይረዳው ለማቅረብ ሞክሯል:–

وَقَالَ لَهُمْ نَبِيُّهُمْ إِنَّ آيَةَ مُلْكِهِ أَن يَأْتِيَكُمُ التَّابُوتُ فِيهِ سَكِينَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَبَقِيَّةٌ مِّمَّا تَرَكَ آلُ مُوسَىٰ وَآلُ هَارُونَ تَحْمِلُهُ الْمَلَائِكَةُ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَةً لَّكُمْ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ

[ አል-በቀራህ - 248 ]
ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «የንግሥናው ምልክት ከጌታችሁ የኾነ እርጋታ የሙሳ ቤተሰብና የሃሩን ቤተሰብ ከተውትም ቅርስ በውስጡ ያለበት መላእክት የሚሸከሙት ኾኖ ሳጥኑ ሊመጣላችሁ ነው፡፡ አማኞች ብትኾኑ በዚህ ለእናንተ እርግጠኛ ምልክት አልለ» አላቸው፡፡

ዕውን በዚህ አንቀፅ ውስጥ: እኛ ሙስሊሞች ታቦትን እናከብር ዘንድ የሚያስተምር ሀሳብ ይገኛልን? በፍፁም! ታዲያ የአንቀፁ መልእክት ምንድነው? ከተባለም:–

ከእስራኤላውያን ዝርያ የሆኑ የተወሰኑ ሹማምንቶች: በወቅቱ ወደተላከው ነቢያቸው (ሳሙዔል) ዘንድ በመምጣት: ጠላቶቻቸውን ይጋደሉ ዘንድ አንድን ንጉስ ይመርጥላቸው ዘንድ ጠየቁት። ነቢያቸውም:– አላህ ለናንተ ጣሉትን(ሳኦልን) ንጉሥ አድርጎ መርጦላችኋል ሲላቸው፣ እነሱም በመቃወም:– እኛ ከሱ ይልቅ ለንግስና የተገባን ሆነን ሳለ: እንዴት ለሱ በኛ ላይ ንግስና ይኖረዋል? ደግሞስ ከገንዘብም ብዙ ያልተሰጠው ሆኖ ሳለ! በማለት ተቃወሙት። ነቢያቸውም:– በናንተ ላይ ንጉስ ይሆን ዘንድ የመረጠው አላህ ነው። በተጨማሪም በዕውቀትም በአካልም ጥንካሬን ጨምሮለታል። አላህ ለፈለገው ሰው ንግስናን ይሰጣል በማለት መለሰላቸው። እነሱም:– ይህ ሰው በኛ ላይ ንጉስ ይሆን ዘንድ ከአላህ ዘንድ ለመመረጡ ምልክቱ ምንድነው? ብለው ሲጠይቁ: ነቢያቸው ሳሙዔልም:– ምልክቱማ በጠላታችሁ ተወስዶና ተዘርፎ የነበረው ታቡት (ሳጥን) ሊመለስላችሁ መሆኑ ነው። ታቡቱ ሲመለስ ደግሞ: መላእክት የተሸከሙት ሆኖ: በውስጡም የሙሳና የወንድሙ ሀሩን ቤተሰቦች የተዉት ቅርስ (የሙሳ ተአምረኛዋ በትር፣ የተውራት ህግ የተፃፈበት ተውራት ወዘተ) በውስጡ የሚገኝ መሆኑ ነው። የአላህ ቃል እንዲህ ይላል:–

"ከእስራኤል ልጆች ከሙሳ በኋላ ወደ ነበሩት ጭፍሮች ለነቢያቸው (ለሳሙኤል)፡- «ለእኛ ንጉሥን አስነሳልን በአላህ መንገድ እንዋጋለን፤» ባሉ ጊዜ አላየህምን? (አላወቅህምን?)፡-«መዋጋት ቢጻፍባችሁ አትዋጉም ይኾናል» አላቸው፡፡ «ከሀገሮቻችንና ከልጆቻችን የተባረርን ስንኾን በአላህ መንገድ የማንዋጋ ለእኛ ምን አለን?» አሉ፡፡ በእነርሱ ላይ መዋጋት በተጻፈባቸውም ጊዜ ከእነርሱ ጥቂቶች ሲቀሩ አፈገፈጉ፡፡ አላህም በዳዮቹን ዐዋቂ ነው፡፡ ነቢያቸውም ለእነርሱ፡- «አላህ ጧሉትን (ሳኦልን) ንጉሥ አድርጎ በእርግጥ ላከላችሁ» አላቸው፡፡ (እነርሱም)፡- «እኛ ከእርሱ ይልቅ በንግሥና ተገቢዎች ስንኾን ከሀብትም ስፋትን ያልተሰጠ ሲኾን ለእርሱ በኛ ላይ እንዴት ንግሥና ይኖረዋል?» አሉ፡፡ (ነቢያቸውም)፡-«አላህ በእናንተ ላይ መረጠው፡፡ በዕውቀትና በአካልም ስፋትን ጨመረለት፡፡ አላህም ንግሥናውን ለሚሻው ሰው ይሰጣል፡፡ አላህም ችሮታው ሰፊ ዐዋቂ ነው» አላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2:246–248)።

ይህ ነው የቁርኣኑ መልእክት! በጥንት ዘመን በእስራኤላውያን ዘንድ ለጣሉት(ሳኦል) ንግስና ትክክለኛነት ምልክት ይሆን ዘንድ የተነገረውን የታቡት ጉዳይ ለነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተከታዮች ታቦትን ያከብሩ ዘንድ ቁርኣን ያዛቸዋል ማለት ጭፍንንት ነው። እኛ ታቦታችሁን እንከተልና እንሸኝ ዘንድ እኛን ከማሳሰባችሁ በፊት: ለምን የናንተው የእምንት ወንድሞች የሆኑትን የክርስትና ቡድኖች ለምን አታሳስቧቸውም? የኛ የአዲስ ኪዳን ታቦታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው! የሚሉትን የፕሮቴስታንት አማኞችን እንዲያከብሩላችሁና ይከተሉትም ዘንድ ለምን አትመክሯቸውም? ምነው ዘላችሁ ወደኛ መጣችሁሳ?
ደግሞስ አክብሮትን ካመናችሁበት: አብሯችሁ ከሺህ አመት በላይ የኖረውን ሙስሊም ሳታከብሩ፣ የአምልኮ ቦታዎቹን እያቃጠላችሁ፣ ንብረታቸውን በማውደም እየጨፈራችሁና የደስታ መግለጫ እየሰጣችሁ፣ ዜግነቱንና የሀገር ባለቤትነቱን በመካድ እንግዳ የሚል ታፔላ እየለጠፋችሁለት፣ በዚህም ድርጊታችሁ ሳትፀፀቱ ጭራሹኑ የናንተን ታቦት እናከብር ዘንድ ትመክሩናላችሁ?? "ዕድሜ ሰጥቶት የሚኖር ብዙ ጉድ ያያል" በማለት ረሱል ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ነግረውን ነበር!

ቅድሚያ አክብሮት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከሙስሊሙ ተማሩ!!

Join us➤➤ t.me/abuhyder
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhayder
የመጸዳጃ ቤት ስርአት በኢስላም

በአቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ውዳሴና ሰላም የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለኾኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

1/ ኢስላም ለንጽህና ከፍተኛ ትኩረትን የሰጠ ሃይማኖት ነው፡፡ ከዛም አልፎ ንጽህናን የእምነቱ አንድ አካል አድርጎ ነው የሚቆጥረው፡፡ ከንጽህናዎች ሁሉ ቀዳሚው ደግሞ የልብ ንጽህና ነው፡፡ እሱም፡- ከጣኦት አምልኮ እርክሰት (ሺርክ)፣ ከአስመሳይነት (ኒፋቅ)፣ መልካም ሥራን ለታይታ ከመሥራት (ሪያእ)፣ በወንድምና እሕቶች ላይ ከመመቅኘት (ሒስድ)፣ በአማኞች ላይ ጥላቻን ከማሳደር (ቡግድ) እና ከመሳሰሉት የሸይጧን ተግባራት በእጅጉ ያስጠነቅቃል፡፡ የቂያም ቀንም አላህ ዘንድ የሚያድነው በዱንያ የሰበሰብናቸው ገንዘብና ልጆች ሳይኾኑ፡ ልበ-ሰላም ኾኖ የመጣ ሰው ብቻ መኾኑን አበክሮ ይናገራል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"በሚቀሰቀሱበት ቀንም አታዋርደኝ፡፡ ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፡፡ ወደ አላህ በንጹህ ልብ የመጣ ሰው ቢኾን እንጅ፡፡" (ሱረቱ-ሹዐራእ 26፡87-89)፡፡

"ገነትም አላህን ለፈሩት እሩቅ ባልኾነ ስፍራ ትቅቀረባለች፡፡ «ይህ ወደ አላህ ተመላሽና (ሕግጋቱን) ጠባቂ ለኾነ ሁሉ የተቀጠራችሁት ነው» (ይባላሉ)፡፡ «አልረሕማንን በሩቁ ኾኖ ለፈራና በንጹሕ ልብ ለመጣ» (ትቅቀረባለች)፡፡" (ሱረቱ ቃፍ 50፡31-33)፡፡

በዛው መልኩም፡ ከልብ ንጽህና ቀጥሎ ለአካላዊ ንጽህናም ትኩረትን በመስጠት፡ እራሳችንን ከነጃሳ፣ ከቆሻሻና መጥፎ ጠረን ካላቸው ነገራት እንድናርቅና፡ ከነዚህ ነጃሳ ከኾኑት ነገራት (ሰገራ፣ ሽንት፣ የወር አበባና የወሊድ ደም…) ሰውነታችን፣ ልብሳችንና የመስገጃ ስፍራችን ላይ እንዳያርፍ መጠንቀቅ፡ ካረፈም በውሀ ትጥበት ቦታውን ማጽዳት እንዳለብን ያሳስበናል፡፡

ከሰማያት በላይ ካለው አምላካችን አላህ ዘንድ ቁርኣን ወሕይ (መለኮታዊ ራእይ) ኾኖ ለልብ ንጽህና ፍቱን መድሃኒት በመኾን እንደወረደው፡ ካረገዙ ዳመናዎችም ውሀ (ዝናብ) ለውጪያዊ ነጃሳዎች (እርኩሰቶች) የንጽህና መሣሪያ በመኾን ወርዷል፡፡ የውሀ ጠቀሜታ ለመጠጥነት ወይንም ለእጽዋት እድገት ብቻ ሳይኾን፡ ነጃሳን ለማስወግድም በማገልገል የአምልኮ መሣሪያ ይኾናል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-

"…ውሃውንም በእርሱ ሊያጠራችሁ፣ የሰይጣንንም ጉትጎታ ከእናንተ ሊያስወግድላችሁ፣ ልቦቻችሁንም (በትዕግስት) ሊያጠነክርላችሁ፣ በእርሱም ጫማዎችን (በአሸዋው ላይ) ሊያደላድልላችሁ በእናንተ ላይ ከሰማይ ባወረደላችሁ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡" (ሱረቱል አንፋል 8፡11)፡፡

አቢ ማሊክ አል-አሽዐሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ንጽህና የኢማን አንድ ክፍል ነው…" (ሙስሊም 556)፡፡

2/ ኢስቲብራእ ማለት፡- ሽንትም ኾነ ሰገራ ከሰውነታችን ሙሉ በሙሉ ወጥቶ መጠናቀቁን እርግጠኛ መኾን ማለት ነው፡፡ ኢስቲንጃእ ማለት ደግሞ፡- ይህ ከሰውነታችን ቆሻሻ የወጣበትን ስፍራ (የብልትና የመቀመጫን ቀዳዳ) እና ቆሻሻው የነካውን ቦታ በውሀ ማጠብና ማጽዳት ማለት ነው፡፡ ኢስቲጅማር የሚባለው ደግሞ፡- ይህንን ቆሻሻ የወጣበትን እና የነካውን ስፍራ በውሀ ምትክ በትናንሽ ድንጋይና ድንጋይን በሚተኩ (እንደ ሶፍት ባሉ ነገራት) ቦታውን ከነጃሳ የማጽዳት ተግባር ማለት ነው፡፡

3/ ወደ መጸዳጃ ቤት በመግባት በውሀ ወይንም በድንጋይና ሶፍት ኢስቲንጃእና ኢስቲጅማር የማድረግ ስርአት ግዳጅ የሚኾነው፡ ከብልታችን ወይንም ከመቀመጫ ስፍራ ነጃሳ ነገር ከወጣ ብቻ ነው፡፡ ከዛ ውጭ አየር ቢያመልጠን (ብንፈሳ)፣ ወይንም ተኝተን ብንነሳ፣ ወይንም ብልትን በእጅ መዳፍ ብንነካ፡ ለነዚህ ተግባራት ዉዱእን መልሶ በማድረግ ብቻ መብቃቃት እንችላለን፡፡ መጸዳጃ ቤት መግባት የለብንም፡፡ ምክንያቱም እነሱ ዉዱእን ብቻ የሚፈቱ ናቸው እንጂ፡ ትጥበትን ግዳጅ የሚያደርጉ ወይንም የነኩትን ቦታ የሚነጅሱ አይደሉምና፡፡ ቢኾን ኖሮማ፡ አየር ያመለጠው ሰው፡ የውስጥ ሱርሪውንና የላይ ሱርሪውን ለማጠብ በተገደደ ነበር፡፡

4/ ከሶስት ባላነሱ ድንጋዮች ወይም ሶፍት ነጃሳ የወጣበትን ቦታ ከጠረገው: ከዚህ በኋላ ውሀን እንኳ ባይጠቀም: ድንጋዩ ወይም ሶፍቱ ያብቃቃዋል። ዋናው የሚፈለገው ነጃሳውን ከስፍራው ማስወገድ ነውና። ውሀውን በተጨማሪ መጠቀሙ ግን ተወዳጅ ነው። (ፈታዋ–ለጅነህ 5/125፣ መጅሙዕ ፈታዋ ኢብኑ ዑሠይሚን 4/112)።

5/ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ፡ ዝም ብሎ መግባት እንደሚቻለው ሁሉ፡ ዚክር አድርጎ መግባቱ ደግሞ፡ የበለጠ ተወዳጅ፣ አላህ ዘንድ አጅር የሚያስገኝ፣ በአላህ ፈቃድም ከሸይጧናት ልክፍት ሰበብ በመኾን የሚጠብቀን ነው፡፡ ዘይድ ኢብኑ አርቀም (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "እነዚህ ቆሻሻ የማራገፊያ ስፍራዎች (መጸዳጃ ቤቶች) ሸይጧናት ይጣዱባቸዋል፡፡ ስለዚህም ከናንተ አንዳችሁ፡ ጉዳዩን ለመፈጸም ወደ መጸዳጃ ቤት በመጣ ጊዜ ‹‹አዑዙ ቢላሂ ሚነል-ኹብሢ ወል-ኸባኢሥ›› ይበል" (አቡ ዳዉድ 6፣ ኢብኑ ማጀህ 296፣

ከአነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ፡ ‹‹አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ፡ ሚነል-ኹብሢ ወል-ኸባኢሥ›› ይሉ ነበር" (ቡኻሪይ 142፣ ሙስሊም 857፣ ኢብኑ ማጀህ 296፣ ቲርሚዚይ 6፣ ነሳኢይ 19)፡፡

ትርጉሙም፡- አምላኬ አላህ ሆይ! እኔ በዚህ ስፍራ የሚሰበቡ ከኾኑ ወንድና ሴት ሰይጣናት (አጋንንት) ልክፍት፡ በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው፡፡

6/ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ፡ ማንኛውንም እግር አስቀድሞ ማስገባት እንደሚቻለው ሁሉ፡ ግራ እግርን ቀድሞ ማስገባቱና በሱ መጀመሩ የተወደደና በላጭ የኾነ ተግባር ነው፡፡ ይህንንም ወደ መስጂድ መግባትንና መውጣትን የተመለከተውን ስርአት ቂያስ በማድረግ (በማነጻጸር) የቀረበ እይታ ነው፡፡ አንድ ሙስሊም ወደ አላህ ቤት ሲገባ በቀኝ እግር መጀመሩ፡ ሲወጣ ደግሞ በግራ መጀመሩ፡ የተወደደ የሱንና ተግባር እንደኾነው ሁሉ፡ የዛን ተቃራኒ ደግሞ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገባ በግራ እግሩ ቢጀምር፡ ሲወጣ ደግሞ በቀኝ እግሩ መጀመሩ መልካም ነው የሚል ነው፡፡ ከዛ ውጭ በሐዲሥ ላይ የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ፡ በየትኛው እግራቸው እንደሚጀምሩ በተግባር የታየ መረጃ የለም ይላሉ የኢስላም ሊቃውንቶች፡፡ (ኢብኑ ዑሠይሚን፡ አሽ-ሸርሑል ሙምቲዕ 1/108፣ ኢማሙ-ነወዊይ፡ ሸርሑ ሶሒሕ ሙስሊም 3/160)፡፡

እናታችን ሐፍሷህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ትላለች፡- "የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ቀኛቸውን ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ለመልበስ ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ግራቸውን ደግሞ ከዛ ውጭ ላለው ነገር ይጠቀሙበታል" (አቡ ዳዉድ 32)፡፡

7/ ወደ መጸዳጃ ቤት ሲገቡ፡ የአላህ ሥም ያለበትን ነገር፡ ወይም የቁርኣን አንቀጽ የተጻፈትን ነገር ከደጅ ማስቀመጡና ይዞ አለመግባቱ መልካምና የተወደደ ነው፡፡ (ኢብኑ ቁዳማህ፡ አል-ሙግኒይ 1/190)፡፡ ከላይ ፊት-ለፊት የማይታይ እና ከኪስ ስር በማድረግ የሚገባ ከኾነ ደግሞ እንደሚቻል ኢብኑ ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ይናገራሉ (ፈታዋ-አጥ–ጡሀራህ
👍1
109)፡፡ አሽ-ሸይኽ ኢብኑ ባዝም (ረሒመሁላህ) በበኩላቸው፡- ሰውየው ከደጅ ካስቀመጥኩት ይጠፋብኛል ብሎ ካልሰጋ በስተቀር፡ ከውጭ አስቀምጦ መግባቱ የተወደደ ነው፡፡ ይጠፋብኛል ብሎ ከፈራ ግን ይዞ መግባቱ ችግር የለውም ይላሉ፡፡ https://www.binbaz.org.sa/noor/7671

በተጨማሪም፡- በውስጡ ቁርኣን የተጫነን ማንኛውንም የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ይዞ ወደ መጸዳጃ ቤት መግባት ይችላል፡፡ በውስጡ በጆሮ ሊደመጥ የሚችል ቁርኣን ተጭኗል ተብሎ እራስን ማስቸገር የለም፡፡ አሽ-ሽይኽ ዐብዱላህ አል-ሙጥለቅ (ሐፊዘሁላህ) እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡-

ጠያቂው፡- ያ ሸይኽ! እኔ ወደ መጸዳጃ ቤት በውስጡ ቁርኣን የተጫነን ሞባይል በኪሴ ይዤ እገባለሁ፡፡ ይህ ይበቃልኛልን?
ሸይኹ፡- ምንም ችግር የለውም!
ጠያቂው፡- ግን እኮ በውስጡ ቁርኣን ተጭኗል?
ሸይኹ፡- ወንድሜ! ችግር የለውም አልኩህ እኮ! ቁርኣኑ እኮ በውስጥ ሜሞሪው ነው የተቀመጠው፡፡
ጠያቂው፡- ያ ሸይኽ! እና ቁርኣን የጫንኩበትን ሞባይል መጸዳጃ ቤት ይዤው መግባት እችላለሁ?
ሸይኹ፡- አንተ የተወሰነ የቁርኣን ሱራዎችን በአእምሮህ አልያዝክም?
ጠያቂው፡- አዎን ያ ሸይኽ! ብዙ የቁርኣን ሱራዎችን ይዣለሁ!፡፡
ሸይኹ፡- እንግዲያውስ መጸዳጃ ቤት መግባት በፈለግህ ጊዜ፡ ይህን ቁርኣን የሐፈዝክበትን ጭንቅላትህን ከደጅ አስቀምጠውና ግባ! ፡D

8/ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ኾኖ አላህን በአንደበት መዘከር የተጠላ ተግባር ነው፡፡ ስፍራው ቆሻሻን ማራገፊያና መጸዳጃ ቦታ በመኾኑ፡ ለአላህ ሥም ክብር ሲባል የአላህን ሥም በማንሳት በምላስ መዘከሩ የተጠላ መኾኑን ሊቃውንት ይገልጻሉ፡፡ አላህን በልብ መዘከሩ ግን አልተከለከለም፡፡ ደግሞም ልብ አላህን ልርሳው ብትል እንኳ ካፊር ካልኾነች በቀር አይቻላትምና፡፡ (ኢቡኑል-ሙንዚር፡ አል-አውሰጥ 1/341፣ ፈታዋ-ለጅነህ 5/93፣ ፈታዋ-ሸይኽ ኢብኑ ባዝ 5/408)፡፡

በዛው መልኩ፡ መጸዳጃ ቤቱን እያጸዱ ጊዜያቸውን በአግባቡ ለመጠቀም፡ ቁርኣንን ወይም አዝካሮችን ለማዳመጥ የሚፈልጉ ሰዎችን በተመለከተ አሽ-ሸይኽ ሷሊሕ አል-ሙነጂድ እንዲህ ይላሉ፡- ገላችንን ስንታጠብም ኾነ ቆሻሻችንን ስናራግፍ፡ እግረ መንገዱንም ቁርኣንን በአንደበታችን እስካልቀራነው ድረስ ከኤሌክትሮኒክስ መሣሪያ ላይ በማዳመጫ መስማቱ ችግር የለውም፡፡ ቁርኣኑን የሚቀራው መሣሪያ ግን ከመጸዳጃ ቤቱ ውጭ መኾን አለበት፡፡ ከሰለፍ ሊቃውንት የኾኑት ኢማም አቡ ሓቲም አር-ራዚ እና ልጃቸው ዐብዱ-ራህማንን (ራሕመቱላሂ ዐለይሂማ) በተመለከተ የተዘገበልን ታሪክም ሀሳቡን ያጠናክርልናል፡፡ ዐብዱ-ራህማን ስለ አባቱ ሲናገር፡- ‹‹አባቴ እየተመገበ እኔ ሐዲሥን አነብለት፣ እየተጓዘም ሳለ፣ ሽንት ቤትም ሲገባ፣ የኾነ ነገር ፈልጎ ወደቤትም ሲገባ አነብለት ነበር›› በማለት ለጊዜ የነበራቸውን ጉጉት ይገልጻል፡፡ (ኢማሙ-ዘሀቢይ፡ ሲየር አዕላም አን-ኑበላእ 13/251)፡፡ የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚህ አያትም አል-መጅድ ኢብኑ ተይሚያህ (ረሒመሁላህ) መጸዳጃ ቤት በሚገቡ ወቅት፡ በጊዜው ለመጠቀም በማለት ልጃቸውን ድምጹን ከፍ አድርጎ ያነብላቸው ዘንድ ያዙት ነበር (ኢብኑል ቀይዪም፡ ረውደቱል-ሙሒብቢን 65)፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
https://islamqa.info/ar/78370

9/ በመጸዳጃ ወቅት፡ ፊታችንንም ኾነ ጀርባችንንም ወደ ቂብላ ማዞር የለብንም፡፡ ለቂብላ ቀኝ ወይንም ግራ እጃችንን በመስጠት መጸዳዳት ይጠበቅብናል፡፡ በተለይ የመጸዳጃ ስፍራው ምንም አይነት ግርዶሽ የሌለው ሜዳ ከኾነ፡ ለቂብላህ ፊትንም ኾነ ጀርባን መስጠት ክልክል እንደኾነ የኢስላም ሊቃውንት ይገልጻሉ፡፡ ቀጣዩንም ሐደሥ እንደማስረጃነት ያቀርባሉ፡-

ከአቢ አዩብ አል-አንሷሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፡- "ከናንተ አንዳችሁ ወደ መጸዳጃ ስፍራ ቆሻሻውን ሊያራግፍ ከመጣ፡ ወደ ቂብላህ ፊታችሁንም ኾነ ጀርባዎቻችሁን አታዙሩ…" (ቡኻሪይ 394፣ ቲርሚዚይ 8)፡፡

የመጸዳጃው ስፍራ በአጥር የተከለለ ከኾነ ግን፡ ወደ ቂብላህ መዞሩም ኾነ ጀርባ መስጠቱ ችግር የለውም የሚሉ ብዙ ሊቃውንት አልሉ፡፡ እነዚህ ሊቃውንት ቲርሚዚይ የዘገበውን፡ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) የአላህ መልክተኛን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በእናታችን ሐፍሷ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ቤት በታጠረ መጸዳጃ ክፍል ጀርባቸውን ለከዕባ ሰጥተው ሲጸዳዱ እንደተመለከተ የተናገረውን በመግለጽ፡ በተገነባ ቤት ውስጥ ወደ ቂብላ መዞሩ ችግር የለውም ይላሉ (ቲርሚዚይ 11)፡፡ በተጨማሪም ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተናገረው፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሽንት ወቅት ወደ ቂብላህ ፊታችንንም ኾነ ጀርባዎቻችንን እንዳናዞር ከለከሉ፡፡ ከመሞታቸው አንድ አመት በፊት ግን ፊታቸውን ወደ ቂብላህ ሲያዞሩ ተመለከትኳቸው" ይላል (አቡ ዳዉድ 13፣ ኢብኑ ማጀህ 325፣ ቲርሚዚይ 9)፡፡ ኢብኑ ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) በበኩላቸው፡ በታጠረ መጸዳጃ ቤት ፊትን ሳይኾን ጀርባን መስጠቱ ችግር የለውም ይላሉ ወላሁ አዕለም፡፡

10/ በመጸዳጃ ቤት ውስጥ ኾነው ሲጸዳዱ፡ ቁጭ ብለውና ተቀምጠው መጸዳዳቱ የተወደደ ሱንና ተግባር ነው፡፡ ከመኾኑም ጋር ቆሞ መሽናት ከፈለጉ ግን ሽንቱ ተፈናጥሮ ልብስንና ሰውነትን እንዳይነጅስ እስከተጠነቀቁ ድረስ ይቻላል ክልክል አይደለም፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ላይ በተዘገበው ሐዲሥ መሠረትም የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቆመው እንደሸኑ ተጠቅሷል (ቡኻሪይ 224፣ ሙስሊም 647፣ አቡ ዳዉድ 23፣ ኢብኑ ማጀህ 306፣ ነሳኢይ 18)፡፡

11/ በመጸዳዳት ወቅት ብልትን፣ ቆሻሻ መውጫን በግራ እጅ ማጠቡና ማጽዳቱ የተወደደ ሱንና ተግባር ነው፡፡ በቀኝ እጅ መጠቀሙ ደግሞ የተጠላ ነው፡፡ ይህን በተመለከተ የተነገረ ሐዲሥ አልለ፡፡

አቢ ቀታዳህ ከአባቱ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በመስማት እንዳስተላለፈልን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ከናንተ አንዳችሁ በሚሸና ጊዜ፡ ብልቱን በቀኝ እጁ አይንካ፣ በቀኝ እጁም ኢስቲንጃእ አያድርግ…" (ቡኻሪይ 154፣ ኢብኑ ማጀህ 310)፡፡

ሰልማኑል ፋሪሲይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- "የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፡ በሽንትም ኾነ በሰገራ ወቅት ለቂብላ ፊታችንንም ኾነ ጀርባችንን እንዳንሰጥ፣ በቀኝ እጃችንም ኢስቲንጃእ እንዳናደርግ ከለከሉን…" (አቡ ዳዉድ 7፣ ቲርሚዚይ 16፣ ነሳኢይ 41)፡፡

12/ በአሁን ዘመን የተገነቡ አብዛኞቹ መኖሪያ ቤቶች፡ ለዉዱእ የሚሆን ብቸኛ ስፍራ የላቸውም፡፡ የገላ መታጠቢያውና መጸዳጃ ቤቱ በአንድ ላይ በአንድ ክፍል ውስጥ የተገነባ በመኾኑ፡ እዛው መጸዳጃ ክፍል ውስጥ ዉዱእ ለማድረግ እንገደዳለን፡፡ ከዉዱእ በፊት ደግሞ ‹‹ቢስሚላህ›› በማለት መጀመሩ፡ የተወደደ የሱንና ተግባር በመኾኑ፡ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ኾኖ በዉዱእ ወቅት የአላህን ሥም ማንሳቱ እንዴት ነው? የሚል ጥያቄን ያስነሳል፡፡ ለዚህ ጥያቄ፡- አሽ-ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) የሰጡት ምላሽ፡- ኢማሙ አሕመድ (ረሒመሁላህ) ሰውየው በመጸዳጃ ቤት ኾኖ በሚያስነጥስበት ወቅት፡ በምላሱ ሳይሆን በልቡ ለአላህ ምሥጋናን ያቅርብ የሚለውን በመጥቀስ፡ በዉዱእ ወቅትም ሰውየው ‹‹ቢስሚላህ››ን በልቡ ይበል የሚል ነው፡፡ (አሽ-ሸርሑል ሙምቲዕ 1/105)፡፡

ኢብኑ ባዝ (ደግሞ)፡- በዛው መጸዳጃ ቤት ዉዱእ ለማድረግ ከተገደደ፡ በዉዱእ ወቅት ‹‹ቢስሚላህ›› ብሎ ቢ
ናገርም ችግር የለውም፡፡ ምክንያቱም ‹‹ቢስሚላህ›› ብሎ ዉዱእን መጀመሩ፡ ከፊል ዑለማዎች ዘንድ ዋጂብ መኾኑ ስለተገለጸ፡ ዋጂቡን ለመፈጸም ሲል በስፍራው ማለቱ የተጠላውን ዚክር ይላል ማለት ነው ይላሉ፡፡ (ፈታዋ-ሸይኽ ኢብኑ ባዝ 10/28)፡፡ በተለይ ውዱእ ማድረጊያው ሰፍራ፡ ቆሻሻን ለማራገፍ ከምንቀመጥበት ስፍራ ትንሽም ቢኾን ራቅ ያለ በመኾኑ፡ ዚክሩ የተጠላው እዛው ቆሻሻን ማራገፊያ ስፍራው ላይ ስለኾነ: ከመታጠቢያው ስፍራ ስንነሳ ግን ‹‹ቢስሚላህ›› ብሎ መጀመሩ ችግር የለውም ወላሁ አዕለም፡፡ (https://islamqa.info/ar/23308)

13/ ሰዎች በሚተላለፉበት መንገድ እና ለማረፍ እንደጥላ በሚጠቀሙበት ስፍራ ከመጸዳዳት እንጠንቀቅ፡፡ ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "ሁለት ተራጋሚዎችን (ሰዎች እንዲረግሙት የሚያስደርግን ነገር) ተጠንቀቁ፡፡ ሶሓቦችም (ረዲየላሁ ዐንሁም) ማናቸው ሁለቱ ተራጋሚዎች? (ሰዎች እንዲረግሙት የሚያስደርገው) አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! በማለት ጠየቁ፡፡ እሳቸውም፡- ያ በሰዎች መተላለፊያ ወይንም በማረፊያ ጥላቸው ላይ የሚጸዳዳው ነው አሉ፡፡" (ሙስሊም 641)፡፡

14/ በመጨረሻም ከመጸዳጃ ቤት ሲወጡ፡ ቀኝ እግርን በማስቀደም መውጣት እና ‹‹ጉፍራነክ›› ማለትንም አይርሱ፡፡ (ሶሒሑ ቲርሚዚይ 9)።
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤➤ t.me/abuhyder
Audio
🛑ይድረስ! ለቄስ ቢንያም ቅጥፈት 🛑
➤ ምላሽ በኡስታዝ አቡ ሐይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/2vbVJmz

Join us➤ t.me/abuhyder
በዩቱብ ለመከታተል➤
https://youtu.be/tDQ-jM_LlPc
Audio
አላሁ አክበር! ጉዞው ወደ ኢስላም በአላህ ፍቃጅ ጁምዓ ወደ የፈጠሩበት እስልምና ለመጡ እንግዶች ኡስታዝ አቡ ሐይደር መልእክት አስተላለፈ

Join ust.me/abuhyder

በዩቱብ ለመከታተል➤
https://youtu.be/Q5COrXTAO_I
አጂብ አስተዋይነት!!
አንዱ ሷሊሕ ሲናገሩ:–
አላህን ለምኘው ከተሳካልኝና ከፈፀመልኝ አንዴ እደሰታለሁ። ከከለከለኝ ደግሞ አስር ጊዜ እደሰታለሁ አሉ። ለምን? ሲባሉ እሳቸውም:–
አላህን ለምኘው ካሳካልኝ እኔ የፈለግሁትን አገኘሁ ማለት ነው።
ካላሳካልኝ ደግሞ እሱ አልፈለገልኝም ማለት ነው። ከኔ ፍላጎት የጌታዬ ምርጫ አስር እጅ የተሻለ በመሆኑና የሱን ምርጫ ስለማስቀድም ደስታዬም እጥፍ ድርብ ይሆናል በማለት መለሱ።
አላህን ለምነን ባይሳካልን ወይ ከእኛ ዘንድ የጎደለ ነገር ኑሮ ነው: ካልሆነም አላህ በተሻለ ነገር ሊቀይርልን ፈቅዶ ነው እንጂ ጌታችን አላህ ዘንድ "NO!" የሚባል ነገር የለም።
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤➤ t.me/abuhyder
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ሙስሊሞች እንዴት ከኮረና ቫይረስ እራሳችንን እንጠብቅ" ወሳኝ መልዕክት በኡስታዝ አቡ ሐይደር #ሸር #ይደረግ👇👇👇
https://youtu.be/UDxSB6XQ5Lk
https://youtu.be/UDxSB6XQ5Lk