የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
እንዲህ ከተዛተባቸው አላህ ይጠብቀን
በአቡ ሀይደር
#አስሩ የተዛተባቸው ሰዎች
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኛ በሆነው፡፡
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
"ወይል" የሚለው የዐረብኛ ቃል ትርጉሙ፡- የቅጣት ቃል፣ የማስጠንቀቂያ ዛቻ ነው፡፡ እንዲሁም በጀሀነም ውስጥ የሚገኝ የሸለቆ ስም ነው፡፡ በጥቅሉ በአማርኛው የቅዱስ ቁርኣን ትርጉም ውስጥ ‹‹ወየውላቸው›› በሚል ትርጉም ሰፍሯል፡፡ ለአመጸኞች የተዛተባቸው መለኮታዊ ማስፈራሪያ ነው፡፡ ዛሬ አላህ ፈቃዱ ከሆነ በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ የመጣባቸውን ቦታዎች እንመለከታለን፡-
1. መጽሐፉን ለሚቀይሩ፡-
ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት(ተውራት፣ዘቡር፣ኢንጂል…) ምንጫቸው ከአላህ ዘንድ የመጡ፡ የአላህ ቃል ሁነው ሳለ፡ መጽሐፉ የወረደላቸው የእነዚያ ነቢያት ህዝቦች(አይሁዶች) ግን ስሜታቸውን በመከተል የአላህን መጽሐፍ አሽቀንጥረው ከጀርባቸው ኋላ ወረወሩት(አል-በቀራህ 101፣ አሊ-ዒምራን 187)፡፡ ያም አልበቃ ብሎ እጃቸውን በመጽሐፉ ላይ በማስገባት በውስጡ የነበረውን ከፊል በማውጣት፡ ሌላ ከመጽሐፉ ያልሆኑ አዳዲስ ቃላትን በመጨመር፡ እውነቱን ከሀሰት ደባልቀው፡- ይኸው ከአላህ ዘንድ የመጣላችሁ መጽሐፍ! ብለው ህዝቡን አደናገሩ፡፡ አላህም ይህን ለሚሰሩ ሰዎች (ወየውላቸው ‹‹ወይሉን ለሁም››) በማለት ዛተባቸው፡-
" فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ يَكْتُبُونَ الْكِتَابَ بِأَيْدِيهِمْ ثُمَّ يَقُولُونَ هَذَا مِنْ عِنْدِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا فَوَيْلٌ لَهُمْ مِمَّا كَتَبَتْ أَيْدِيهِمْ وَوَيْلٌ لَهُمْ مِمَّا يَكْسِبُونَ " سورة البقرة 79
"ለነዚያም መጽሐፉን በእጆቻቸው ለሚጽፉና ከዚያም በርሱ ጥቂትን ዋጋ ሊገዙበት «ይህ ከአላህ ዘንድ ነው» ለሚሉ ወዮላቸው፡፡ ለነርሱም ከዚያ እጆቻቸው ከጻፉት ወዮላቸው፡፡ ለነሱም ከዚያ ከሚያፈሩት (ኃጢኣት) ወዮላቸው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 79)፡፡
- ከዚህ የምንወስደው ትምሕርት፡-
ሀ. ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት አላህ ሊጠብቃቸው ቃል ስላልገባላቸው፡ በምትኩ መጽሐፉ የተሰጣቸው ነቢያትና ተከታዮቻቸው እንዲጠብቁ በመደረጉ(አል-ማኢዳህ 44) በጊዜ ሂደት መበረዛቸውን እንረዳለን፡፡
ለ. በመጽሐፉ ላይ እጃቸውን በማስገባት ቃላትን ከስፍራው የቀየሩ ሰዎች አላህ ዘንድ አሳማሚ ቅጣት እንደሚያገኛቸው ከተዛተባቸው፡ ዛሬም ቅዱስ ቁርኣንን ምንም ቃላቱን መቀየር እንኳ ባይቻልም( አላህ ሊጠብቀው ቃል ስለ-ገባለት አል ሒጅር 9) መልእክቱን ግን ሲተረጉሙ እያዛቡ ከእውነታው ውጪ የሆነ መልእክት በማስተላለፍ ሰውን ግራ የሚያጋቡ እና ኡማውን መከፋፈል የሚሹ ለሆኑት ይኸው ዛቻ የሚመለከታቸው መሆኑን እንረዳለን፡፡
2. ለከሀዲያን፡-
በአላህና በመልክተኛው በማመን እንዲሁም መልካም ስራዎችን በማስከተል፡ ዘለቄታዊ የሆነውን የመጨረሻውን ዓለም ጀነትን መፈለግ ሲገባቸው፡ የዱንያ ህይወትን ከአኼራ መርጠው፡ አላህ በላካቸው መልክተኞች ያስተባበሉትን ከሀዲያን ቅጣት እንደሚጠብቃቸው በመግለጽ ‹‹ወየውላችሁ!›› ተብለዋል፡-
" اللَّهِ الَّذِي لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ وَوَيْلٌ لِلْكَافِرِينَ مِنْ عَذَابٍ شَدِيدٍ * الَّذِينَ يَسْتَحِبُّونَ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا عَلَى الْآخِرَةِ وَيَصُدُّونَ عَنْ سَبِيلِ اللَّهِ وَيَبْغُونَهَا عِوَجًا أُولَئِكَ فِي ضَلَالٍ بَعِيدٍ " سورة إبراهيم 3-2
"አላህ ያ በሰማያት ያለው በምድርም ያለው ሁሉ የርሱ ብቻ የሆነ ነው፤ ለከሐዲዎችም ከብርቱ ቅጣት ወዮላቸው። እነዚያ የቅርቢቱን ሕይወት ከመጨረሻይቱ ሕይወት ይበልጥ የሚወዱ፤ ከአላህም መንገድ የሚያግዱ፤ መጥመሟንም የሚፈልጉዋት ናቸው፤ እነዚያ በሩቅ ስሕተት ውስጥ ናቸው።" (ሱረቱ ኢብራሂም 2-3)፡፡
" وَمَا خَلَقْنَا السَّمَاءَ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا بَاطِلًا ذَلِكَ ظَنُّ الَّذِينَ كَفَرُوا فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنَ النَّارِ " سورة ص 27
"ሰማይንና ምድርን በመካከላቸውም ያለውን ሁሉ ለከንቱ አልፈጠርንም፡፡ ይህ የእነዚያ የካዱት ሰዎች ጥርጣሬ ነው፡፡ ለእነዚያም ለካዱት ሰዎች ከእሳት ወዮላቸው!" (ሱረቱ ሷድ 27)፡፡
- ከዚህ የምንማረው፡-
ሀ. በአላህና በመልክተኞቹ ምንም ሳናስተባብልና ሳንወላውል በትክክል ማመን እንዳለብንና ይህ እምነትም ከእሳት ቅጣት ሊያድነን እንደሚችል እንማራለን፡፡
ሀ. የዱንያ ሕይወት በጣም አጭርና ለመጥፋት የተቃረበች በመሆኗ፡ ዘለቄታዊ ከሆነውና ከማይጠፋው የአኼራ ሕይወት በምንም አይነት መልኩ ልናስበልጣት እንደማይገባ እንማራለን፡፡
3. በዒሳ ጉዳይ የተለያዩትን፡-
የመርየም ልጅ ዒሳ(ዐለይሂ ሰላም) የአላህ ባሪያና መልክተኛው ብቻ ሆኖ ሳለ (አል-ማኢዳህ 75)፡ ክርስቲያኖች ግን በሱ ጉዳይ እርስ በርስ በመቃረን የተለያየ አመለካከት በመያዝ(አንዱ የአላህ ልጅ ነው፣ ሌላው ደግሞ እራሱ አላህ ነው፣ ሌሎቹ ደግሞ ከሶስቱ አንዱ ነው…) በማለት አሕዛቦች ሆነው ከመስመር የወጡትን ወየውላቸው ይላቸዋል፡-
" مَا كَانَ لِلَّهِ أَنْ يَتَّخِذَ مِنْ وَلَدٍ سُبْحَانَهُ إِذَا قَضَى أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُنْ فَيَكُونُ * وَإِنَّ اللَّهَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ هَذَا صِرَاطٌ مُسْتَقِيمٌ * فَاخْتَلَفَ الْأَحْزَابُ مِنْ بَيْنِهِمْ فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ كَفَرُوا مِنْ مَشْهَدِ يَوْمٍ عَظِيمٍ " سورة مريم 37-35
"ለአላህ ልጅን መያዝ አይገባዉም፤ (ከጉድለት ሁሉ) ጠራ፤ ነገርን በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለዉ ኹን ነዉ ውዲያዉም ይኾናል። (ዒሳ አለ) ፦ አላህም ጌታዬ ጌታችሁም ነዉና ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው። ከመካከላቸዉም አሕዛቦቹ በርሱ ነገር ተለያዩ ለነዚያም ለካዱት ሰዎች፣ ከታላቁ ቀን መጋፈጥ ወዮላቸዉ።" (ሱረቱ መርየም 35-37)፡፡
" وَلَمَّا جَاءَ عِيسَى بِالْبَيِّنَاتِ قَالَ قَدْ جِئْتُكُمْ بِالْحِكْمَةِ وَلِأُبَيِّنَ لَكُمْ بَعْضَ الَّذِي تَخْتَلِفُونَ فِيهِ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ * إِنَّ اللَّهَ هُوَ رَبِّي وَرَبُّكُمْ فَاعْبُدُوهُ هَذَا صِرَاطٌ مُسْتَقِيمٌ * فَاخْتَلَفَ الْأَحْزَابُ مِنْ بَيْنِهِمْ فَوَيْلٌ لِلَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْ عَذَابِ يَوْمٍ أَلِيمٍ " سورة الزخرف 65-63
"ዒሳ በታምራቶች በመጣ ጊዜም አላቸው፦ በእርግጥ በጥበብ መጣኋችሁ፤ የዚያንም በርሱ የምትለያዩበትን ከፊሉን ለናንተ ላብራራላች