የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.2K subscribers
306 photos
106 videos
47 files
801 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
Audio
"ከቂያማህ ምልክቶች ከፊሎቹ"
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/2miKdRQ

Join us➤ t.me/abuhyder
አላህን የመፍራት ጥቅም!

በአቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) የአላህ ውዳሴና ሰላም የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለኾኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

ባለፈው ትምሕርታችን ላይ አላህን በመፍራትና ፍጡራንን በመፍራት መሐል ስላለው ልዩነት የተወሰነ ነገር ተመልክተን ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ አላህን በየትም ስፍራ ፈርቶ መገኘት ዱንያዊና አኼራዊ ጥቅሞቹን በተወሰኑ መልኩ መዳሰስ ስላለብን በአላህ ፈቃድ እሱን እንመለከታለን፡፡ መልካም ንባብ፡-

ሀ. ዱንያዊ ጥቅሞቹ፡-

1. በቁርኣን መመራትን፡- አላህን የሚፈራ ሰው ቁርኣን ይመራዋል፡- "ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመኾኑ) ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡2)፡፡

2. የጌታችን አብሮነትን፡- አላህን የሚፈራ ሰው አላህ በእርዳታውና በጥበቃው ከርሱ ጋር ይሆናል፡- "…አላህንም ፍሩ አላህ ከሚፈሩት ጋር መኾኑንም ዕወቁ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡194)፡፡
"አላህ ከነዚያ ከሚፈሩትና ከነዚያም እነሱ መልካም ሠሪዎች ከሆኑት ጋር ነውና።" (ሱረቱ-ነሕል 16፡128)::
"…አጋሪዎችንም በአንድ ላይ ሆነው እንደሚዋጉዋቸሁ በአንድ ላይ ሆናችሁ ተጋደሉዋቸው፤ አላህም ከሚፈሩት ጋር መሆኑን ዕወቁ።" (ሱረቱ-ተውባህ 9፡36)፡፡
"እላንተ ያመናችሁ ሆይ! እነዚያን በአቅራቢያችሁ ያሉትን ከሐዲዎች ተዋጉ፤ ከናንተም ብርታትን ያግኙ፤ አላህም ከሚጠነቀቁት ጋር መሆኑን ዕወቁ።" (ሱረቱ-ተውባህ 9፡123)፡፡

3. የእውቀት እድገትን፡- አላህን የሚፈራ ሰው አላህ ጠቃሚ እውቀትን ይለግሰዋል፡- "…አላህንም ፍሩ፡፡ አላህም ያሳውቃችኋል፡፡ አላህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡282)፡፡

4. የአላህን ውዴታ፡- አላህ እንዲወድህ ከፈለክ እሱን ፍራው፡- "…በቃል ኪዳኑ የሞላና የተጠነቀቀ ሰዉ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳል።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 3፡76)፡፡
"ከአጋሪዎቹ እነዚያ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸዉና ከዚያም ምንም ያላጎደሉባችሁ በናንተ ላይም አንድንም ያልረዱባችሁ ሲቀሩ፤ (እነዚህን) ቃል ኪዳናቸዉን እስከ ጊዚያታቸዉ (መጨረሻ) ሙሉላቸዉ፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።" (ሱረቱ-ተውባህ 9፡4)፡፡
"ለአጋሪዎቹ አላህ ዘንድና እመልክተኛው ዘንድ ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል? እነዚያ በተከበረዉ መስጊድ ዘንድ ኪዳን የተገባችኋቸዉ ብቻ ሲቀሩ (እነዚህ) በኪዳናቸዉ ለናንተ ቀጥ እስካሉላቸሁ ድረስ ለነርሱም ቀጥ በሉላቸዉ፤ አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና።" (ሱረቱ-ተውባህ 9፡7)፡፡

5. ነገሮች ገር ይሆናሉ፡- በልቡ አላህን የሚፈራ ሰው ነገሮች ይገሩለታል፡፡ ሁኔታዎቹን ሁሉ አላህ ያቀልለታል፡- "አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል።" (ሱረቱ-ጦላቅ 65፡4)፡፡
"የሰጠ ሰውማ ጌታውን የፈራም፤በመልካሚቱም (እምነት) ያረጋገጠ፤ለገሪቱ ሥራ እናዘጋጀዋለን።" (ሱረቱ-ለይል 92፡5-7)፡፡

6. ሲሳይን ያሰፋል፡- አላህን የሚፈራ ሰው ከጭንቅ መውጫ ቀዳዳ ያበጅለታል፡፡ ካላሰበው በኩል ይረዘቃል፡- "…አላህንም የሚፈራ ሰው ለርሱ መውጫን ያደርግለታል።ከማያስበው በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል፤ በአላህም ላይ የሚጠጋ ሰው እርሱ በቂው ነው፤ አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው፤ አላህ ለነገሩ ሁሉ የተወሰነ ጊዜን በእርግጥ አርጓል።" (ሱረቱ-ጦላቅ 65፡2-3)፡፡
"የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ፣ በነርሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፤ ግን አስተባበሉ፤ ይሰሩት በነበሩትም ኃጢአት ያዝናቸው።" (ሱረቱል አዕራፍ 7፡96)፡፡

7. የአላህን ወዳጅነት ይጎናጸፋል፡- አላህ ለሚፈሩት ባሪያዎቹ ወዳጃቸው ነው፡- "ንቁ! የአላህ ወዳጆች በእነሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡(እነሱም) እነዚያ ያመኑትና ይፈሩት የነበሩ ናቸው፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 10፡62-63)፡፡
"እነርሱ ከአላህ (ቅጣት) ምንንም ከአንተ አይገፈትሩልህምና፤ በደለኞችም ከፊላቸው የከፊሉ ረዳቶች ናቸው፤ አላህም የጥንቁቆች ረዳት ነው።" (ሱረቱል ጃሢያህ 45፡19)፡፡

8. ሐቅን ከባጢል የመለያ ልቦና፡- አላህን የሚፈራ ሰው እውነትን ከሀሰት የሚለይበት ልቦናን አላህ ይለግሰዋል፡፡ በሐቅ ላይ የሚሄድበትንም ብርሐን ይለገሳል፡- "እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ብትፈሩ የእውነት መለያ ብርሃን ያደርግላችኋል፤ ክፉ ስራዎቻችሁንም ከናንተ ላይ ያብስላችኋል፤ ለናንተም ይምራችኋል፤ አላህ የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው" (ሱረቱል አንፋል 8፡29)፡፡
"እላንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ በመልክተኛውም እመኑ፤ ከችሮታው ሁለትን ክፍሎች ይሰጣችኋልና፤ ለናንተም በርሱ የምትኼዱበት የሆነ ብርሃንን ያደርግላችኋል፤ ለናንተም ይምራል፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነው።" (ሱረቱል ሐዲድ 57፡28)፡፡

9. የኃጢአት ስርየት፡- አላህን መፍራት ወንጀልን ያስምራል ኃጢአትን ያሰርዛል፡-
"ይህ የአላህ ፍርድ ነው። ወደናንተም አወረደው፤ አላህንም የሚፈራ ሰው ኅጢአቶቹን ከርሱ ያሰርይለታል፣ ምንዳንም ለሱ ያተልቅለታል።" (ሱረቱ-ጦላቅ 65፡5)፡፡
"የመጽሐፉም ባለቤቶች ባመኑና (ከክሕደትም) በተጠነቀቁ ኖሮ ከእነሱ ኃጢያቶቻቸውን በእርግጥ ባበስንና የመጠቀሚያ ገነቶችንም በእርግጥ ባገባናቸው ነበር።" (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡65)፡፡

10. ስራን ማበጀት፡- አላህን የሚፈራ ሰው፡ አላህ ስራውን ያቃናለታል፡- "እላንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ፤ ትክክለኛውንም ንግግር ተናገሩ።ሥራዎቻችሁን ለናንተ ያበጅላችኋልና፥ ኀጢአቶቻችሁንም ለናንተ ይምርላችኋል፤ አላህና መልክተኛውን የሚተዘዝም ሰው፥ በእርግጥ ታላቅን ዕድል አገኘ።" (ሱረቱል አሕዛብ 33፡70-71)፡፡

11. የሥራ ተቀባይነትን፡- አላህን የምንፈራ ከሆነ አላህ ስራችንን ይቀበለናል፡- "አላህ የሚቀበለው እኮ ከጥንቁቆቹ ብቻ ነው አለ።" (ሱረቱል ማኢዳህ 5፡27)፡፡

ለ. አኼራዊ ጥቅሞቹ፡-

1. አላህ ዘንድ የተከበረ ነው፡- አላህን የሚፈራ ሰው ከሌሎች ሁሉ በልጦ አላህ ዘንድ በላጭ ይሆናል፡- "እናንተ ሰዎች ሆይ እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፤ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፤ አላህ ዘንድ በላጫችሁ፣ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፤ አላህ ግልጽን ዐዋቂ፣ ውስጥንም ዐዋቂ ነው።" (ሱረቱል ሑጁራት 49፡13)፡፡

2. ከሲራጥ አደጋ መትረፍን፡- ከጸጉር የቀጠነና ከሰይፍ የሰላ የሆነውን በጀሐነም ጀርባ ላይ የተዘረጋውን የሲራጥ ድልድይ አላህን ፈሪዎች ያልፉታል፡- "ከእናንተም ወደ እርሷ ወራጅ እንጂ አንድም የለም፤ (መዉረዱም) ጌታህ የፈረደዉ ግዴታ ነዉ።ከዚያም እነዚያን የተጠነቀቁትን እናድናለን፤ አመጠኞቹንም የተንበረከኩ ኾነዉ በዉስጧ እንተዋቸዋለን።" (ሱረቱ መርየም 19፡63)፡፡

3. ጀነትን መውረስን፡- አላህ ለሚፈሩት ባርያዎቹ ጀነትን ሊያወርስ ቃል ገባላቸው፡- "ይህች ያቺ ከባሮቻቸን ጥንቁቆች ለኾኑት፣ የምናወርሳት ገነት ናት።" (ሱረቱ መርየም 19፡71-72)፡፡
"ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ሆነች ገነት፥ አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡133)፡፡
4. በጀነት የተዋቡ ክፍሎችን፡- ይህ አላህን የመፍራት ውጤት ነው፡- "ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለነርሱ ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የሆኑ አሏቸው፤ (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፤ አላህ ቃሉን አያፈርስም።" (ሱረቱ-ዙመር 39፡20)፡፡

5. ከከሀዲያን በላይ መሆንን፡- በዱንያ ላይ በእምነታቸው ሰበብ ሲያላግጡባቸው የነበሩ ከሀዲያን በተራቸው አማኞች ነገ ከነሱ በላይ በመሆን ይስቁባቸዋል፡- "ለእነዚያ ለካዱት ከእነዚያ ካመኑት የሚሳለቁ ሲኾኑ ቅርቢቱ ሕይወት ተሸለመችላችው፡፡ እነዚያም የተጠነቀቁት በትንሣኤ ቀን ከበላያቸው ናቸው፡፡ አላህም ለሚሻው ሰው ያለ ግምት ይሰጣል፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡212)፡፡

6. የተመኘኸውን ማግኘት፡- ጸጋዋ በማይቋረጠው ጀነት ውስጥ አላህን ፈሪዎች የሚመኙትን ሁሉ የሚያገኙ ናቸው፡- "(እርሷም) የሚገቡዋትና በሥርዋ ወንዞች የሚፈሱባት ስትሆን የመኖሪያ አትክልቶች ናት፤ ለነሱም በውስጧ የሚሹት ሁሉ አላቸው፤ እንደዚሁ አላህ ጥንቁቆችን ይመነዳል።" (ሱረቱ-ነሕል 16፡31)፡፡
"ጥንቁቆቹ በጥላዎችና በምንጮች ውስጥ ናቸው።ከሚከጅሉትም ሁሉ በፍራፍሬዎች ውስጥ ናቸው። ትሠሩት በነበራችሁት ዋጋ የምትደሰቱ ሆናችሁ ብሉ ጠጡም፤ (ይባላሉ)።" (ሱረቱል ሙርሰላት 77፡41-43)፡፡

7. ፍጻሜው የነሱ ነው፡- "ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፤ በርሷም ላይ ዘውትር፤ ሲሳይን አንጠይቅህም፤ እኛ እንሰጥሃለን መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት።" (ሱረቱ ጣሀ 20፡132)፡፡
"ሙሳ ለሰዎቹ ፦ ለአላህ ተገዙ ታገሱም፤ ምድር ለአላህ ናትና፤ ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል፤ ምስጉንዋም ፍጻሜ ለጥንቁቆቹ ናት አላቸው።" (ሱረቱል አዕራፍ 7፡128)፡፡
"ይህቺ ከሩቅ ወሬዎች ናት፤ ወደ አንተ እናወርዳታለን፤ አንተም ሕዝቦችህም ከዚህ በፊት የምታውቋት አልነበራችሁም፤ ታገሥም፤ ምስጉን የሆነችው ፍጻሜ ለሚጠነቀቁት ናትና።" (ሱረቱ ሁድ 11፡49)፡፡
"ይህች የመጨረሻይቱ አገር ለእነዚያ በምድር ውስጥ ኩራትንና ማመፅን ለማይፈልጉት እናደርጋታለን፡፡ ምስጉኒቱም መጨረሻ ለጥንቁቆቹ ናት፡፡" (ሱረቱል ቀሶስ 28፡83)፡፡

Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
Yemenafiqan Behari
Ustaz Abu Heyder
"የምናፍቃን ባህሪይ"
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
https://bit.ly/2kzKnUi

Join us➤ t.me/abuhyder
ግሩፑ ተከፍቷል!!

ሼር ሼር ሼር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

"ትድኑ ዘንድ መልካም ነገርን ሥሩ" (ሱረቱ ኑር 24:77)

"መልካም ሥራዎች ኃጢአትን ያስወግዳሉ" (ሱረቱ ሁድ 11:114)

"ለአላህ ብሎ የእርግብ እንቁላል መጣያ የሚሆን ስፍራ እንኳ ቢሆን መስጂድን የገነባ ሰው፣ አላህ በጀነት ቤትን ይገነባለታል" ሐዲሡን ሸሪፍ

በአላህ እገዛና ፈቃድ በገጠራማው የሀገራችን ክፍሎች የመሥጂድ ግንባታ ተጀምሮ በገንዘብ እጥረት ሰበብ ሳይጠናቀቁ የተቋረጡ መስጂዶችን በወንድምና እሕቶች ትብብር ለማስጨረስ እኔ አቡ ሐይደር፣ ኡስታዝ አቡ ዩስራና፣ ኡስታዝ የሕያ ኢብኑ ኑሕ ኃላፊነቱን በመውሰድ ጀምረነዋል።

እናንተም ይህን የቴሌግራም ግሩፕ በመቀላቀል የኸይር ሥራው ተሳታፊ ይሁኑ።

የመስጅድ ስራ ፕሮጀክት ✧ አቡ ሀይደር - የሕያ - አቡ ዩስራ
https://tttttt.me/Mesjidabuhyder
#SHARE #SHARE #SHARE

አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላህ

በጅምር የቀሩ መስጂዶችን ለማስጨረስ በሚል ሀሳብ ሶስት የኢስላም ወንድማሞች የጀመርነውን ፕሮጀት ለማገዝ የምትፈልጉ ወንድሞች/እሕቶች ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጨማሪ፣ የዳሸንና የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት መክፈታችንን በደስታ እንገልፅላችኋለን።

በተጨማሪም ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እንጂ ኦሮሚያ ህብረት ባንክ በሚል አካውንት የለንም።
#SHARE #SHARE #SHARE

አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላህ

በጅምር የቀሩ መስጂዶችን ለማስጨረስ በሚል ሀሳብ ሶስት የኢስላም ወንድማሞች የጀመርነውን ፕሮጀት ለማገዝ የምትፈልጉ ወንድሞች/እሕቶች ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጨማሪ፣ የዳሸንና የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት መክፈታችንን በደስታ እንገልፅላችኋለን።


SADIK MOHAMMED AHMED
OROMIA INTERNATIONAL BANK
1330004700001
0911 10 32 31

SADIK MOHAMMED AHMED
COMMERCIAL BANK OF ETHIOPIA
1000298991245
0911 10 32 31

SADIK MOHAMMED AHMED
DASHEN BANK
2900714650011
0911 10 32 31

በተጨማሪም ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እንጂ ኦሮሚያ ህብረት ባንክ በሚል አካውንት የለንም።
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ pinned «#SHARE #SHARE #SHARE አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላህ በጅምር የቀሩ መስጂዶችን ለማስጨረስ በሚል ሀሳብ ሶስት የኢስላም ወንድማሞች የጀመርነውን ፕሮጀት ለማገዝ የምትፈልጉ ወንድሞች/እሕቶች ከኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ በተጨማሪ፣ የዳሸንና የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አካውንት መክፈታችንን በደስታ እንገልፅላችኋለን። SADIK MOHAMMED AHMED OROMIA INTERNATIONAL BANK…»
Audio
🎤አጭር መልዕክት🎤

መስጂድን በመገንባት ዙሪያ

ከኡስታዝ አቡ ሐይደር
በኡስታዝ አቡ ሀይደር፣ በወንድም የሕያ ኢብኑ ኑህና በወንድም አቡ ዩስራ አማካኝነት የተጀመረው የመስጅድ ስራ ፕሮጀክት እንቅስቃሴው እንደቀጠለ ነው። በዚህ ሳምንት ደግሞ በባለፈው ቆርቆሮ የለበሱ ቦታዎችን ምንጣፍ ከማንጠፍ ጀምሮ ለተጨማሪ መስጅዶች ቆርቆሮ የማልበስ ስራዎች እየተካሔዱ ይገኛሉ። በቦታውም ኡስታዝ አቡ ሀይደር በመገኘት ለማህበረሰቡ ዳዕዋ ያደረገ ሲሆን የፕሮግራሙን ሙሉ ቪዲዬ ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል።

ስራችን በአላህ ﷻ ፍቃድ ይቀጥላል..!

ኑ ተባብረን ወገኖቻችንን ከኩፍር እንታደግ

ስራው ላይ አሻራዎትን ለማሳረፍ በሚከተለው ሊንክ ይቀላቀሉ ....

t.me/Mesjidabuhyder

____

ተጨማሪ ንጽጽራዊ ትምህርቶችን ለመከታተል

❐ በዩቲዩብ - http://bit.ly/2ZPzYTI

❐ በቴሌግራም t.me/yahya5

❐ በድረ ገጽ- www.ethio-islamic.org
👍1
Audio
🎙 አዲስና ወሳኝ መልዕክት🎙

ከኡስታዝ አቡ ሐይደር
Audio
"ቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት በአላህ ቃል ውስጥ"
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join us➤ t.me/abuhyder
👍1
የመዳኛ_ሰበቦች_ምንድን_ናቸው_በኢስላም.m4a
14.2 MB
"የመዳኛ ሰበቦች ምንድን ናቸው በኢስላም"

☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join us➤ t.me/abuhyder
Audio
"ኢስላም እና ዘረኝነት"
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Join us➤ t.me/abuhyder
What is Quran
የቅዱስ ቁርኣን ምንነት!
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
http://goo.gl/W2wrsZ

Join us➤ t.me/abuhyder
2👍1