የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
304 photos
106 videos
47 files
800 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
يَانِ مَثَلًا أَفَلَا تَذَكَّرُونَ " سورة هود 24-23
"እነዚያ ያመኑትና በጎ ሥራዎችን የሠሩት ወደ ጌታቸውም የተዋረዱት፣ እነዚያ የገነት ሰዎች ናቸው፤ እነሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው። የሁለቱ ክፍሎች (የከሐዲዎችና የምዕመናን) ምሳሌ እንደ ዕውርና እንደ ደንቆሮ እንደሚያይና እንደሚሰማም ብጤ ነው፤ በምሳሌ ይተካከላሉን? አትገሠጹምን?" (ሱረቱ ሁድ 23-24)፡፡
" قُلْ مَنْ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ قُلْ أَفَاتَّخَذْتُمْ مِنْ دُونِهِ أَوْلِيَاءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنْفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الْأَعْمَى وَالْبَصِيرُ أَمْ هَلْ تَسْتَوِي الظُّلُمَاتُ وَالنُّورُ أَمْ جَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ خَلَقُوا كَخَلْقِهِ فَتَشَابَهَ الْخَلْقُ عَلَيْهِمْ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ " سورة الرعد 16
"የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው? በላቸው፤ አላህ ነው በል፤ ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከርሱ ሌላ ያዛችሁን? በላቸው፤ ዕውርና የሚያይ ይተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አደረጉለትና ፍጥረቱ በነሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን? በል፤ አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው በል።" (ሱረቱ-ረዕድ 16)፡፡
አምላካችን አላህ ሆይ! በኛ በባሮችህ ላይ የሚወርደውን የጠላት ዱላ ተመልካች ጌታ ነህና አንተው እርዳን፡፡ በተመልካችነትህ ይሁንብህ ድረስልን፡፡ በመስሚያችንም፣ በማያችንም የምንጠቀም አድርገን፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
Allahin Lemin Inamelkalen
Ustaz Abu Heyder
አላህን ለምን እናመልካለን
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ

Join us➤ t.me/abuhyder
10. "አል-ሐቅ" (ፍጹም እውነት)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ሐቅ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፍጹም እውነት የሆነ ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ መኖሩ የተረጋገጠ፡ በግምትና በምናብ ያልሰፈረ እውነት በመሆኑ "አል-ሐቅ" ይባላል፡፡ ጌታ አላህ በባሕሪያቱ እውነተኛ አምላክ በመሆኑ "አል-ሐቅ" ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታ አላህ ንግግሩ ፍጹም እውነት በመሆኑ "አል-ሐቅ" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ሐቅ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አስር ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ ለናሙና ያህል፡-
"ثُمَّ رُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ أَلَا لَهُ الْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ الْحَاسِبِينَ " سورة الأنعام 62
"ከዚያም እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 62)፡፡
"فَذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمُ الْحَقُّ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ فَأَنَّى تُصْرَفُونَ " سورة يونس 32
"እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ" (ሱረቱ ዩኑስ 32)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አላህ መኖሩ የተረጋገጠ መሆኑ፡- የፈጣሪ አምላካችን አላህ መኖር ምናባዊ ሳይሆን ፍጹም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ የሱ መኖር scientifical truth ወይም Historical truth ሳይሆን Universal truth (ተፈጥሮአዊ እውነታ) ነው፡፡ የአላህን መኖር ለማረጋገጥ የከርሰ ምድር ጥናት ወይም የጠፈር ምርምር ወይም የታሪክ ማረጋገጫ አያስፈልግም፡፡ ማንም ሰው በተፈጥሮው ያለ-ምንም ሃይማኖታዊ ተጽእኖ አምኖ የሚቀበለውና የሚያድግበት እውነት ነው፡፡ ስለሆነም ጌታ አላህ "አል-ሐቅ" ተብሎ ይጠራል፡-
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنْ كُنْتُمْ فِي رَيْبٍ مِنَ الْبَعْثِ فَإِنَّا خَلَقْنَاكُمْ مِنْ تُرَابٍ ثُمَّ مِنْ نُطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ مِنْ مُضْغَةٍ مُخَلَّقَةٍ وَغَيْرِ مُخَلَّقَةٍ لِنُبَيِّنَ لَكُمْ وَنُقِرُّ فِي الْأَرْحَامِ مَا نَشَاءُ إِلَى أَجَلٍ مُسَمًّى ثُمَّ نُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوا أَشُدَّكُمْ وَمِنْكُمْ مَنْ يُتَوَفَّى وَمِنْكُمْ مَنْ يُرَدُّ إِلَى أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْلَا يَعْلَمَ مِنْ بَعْدِ عِلْمٍ شَيْئًا وَتَرَى الْأَرْضَ هَامِدَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ وَأَنْبَتَتْ مِنْ كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ * ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِ الْمَوْتَى وَأَنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الحج 6-5
"እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ)፤ እኛም ከዐፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ፣ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤ የምንሻውንም፣ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ፣ በማህጸን ዉስጥ እናረጋዋለን ከዚያም ሕጻን ሆናችሁ እናወጣችኋለን። ከዚያም ሙሉ ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፣ (እናሳድጋችኋለን)፤ ከናንተም የሚሞት ሰው አለ፤ ከናንተም ከዕውቀት በኋላ፣ ምንንም እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፤ ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ፤ በስዋም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ፣ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም፤ ውበት ካለው ቦታ ሁሉ ታበቅላለችም። ይህ፣ አላህ እርሱ #መኖሩ-የተረጋገጠ፤ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 5-6)፡፡
"ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ هُوَ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة الحج 62
"ይህ አላህ እርሱ #እውነት በመሆኑ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር እርሱ ፍጹም ውሽት በመሆኑ አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 62)፡፡
"يَوْمَئِذٍ يُوَفِّيهِمُ اللَّهُ دِينَهُمُ الْحَقَّ وَيَعْلَمُونَ أَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ الْمُبِينُ " سورة النور 25
"በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይመላላቸዋል አላህም እርሱ #መኖሩ-የተረጋገጠ (ሁሉን ነገር) ገላጭ መሆኑን ያውቃሉ።" (ሱረቱ-ኑር 25)፡፡
"ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة لقمان 30
"ይህ፣ አላህ እርሱ #እውነት፣ ከርሱም ሌላ የሚገዙት (ጣዖት)ውሸት በመሆኑና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመኾኑ ነው።" (ሱረቱ ሉቅማን 30)፡፡
2. ንግግሩ እውነት መሆኑን፡- እውነተኛው አምላክ አላህ የሚናገረውም እውነትን ብቻ ነው፡፡ ውሸት እሱ ዘንድ በፍጹም የለም አይታሰብምም፡፡ በንግግርም ከርሱ የበለጠ እውነተኛ የለም፡-
"اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا " سورة النساء 87
"አላህ ከርሱ በስተቀር አምላክ የለም፤ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 87)፡፡
"وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا وَعْدَ اللَّهِ حَقًّا وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا " سورة النساء 122
"እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሠሩ፣ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ እናገባዋቸዋለን፤ አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው። በንገገርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማን ነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 122)፡፡
"وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَيَوْمَ يَقُولُ كُنْ فَيَكُونُ قَوْلُهُ الْحَقُّ وَلَهُ الْمُلْكُ يَوْمَ يُنْفَخُ فِي الصُّورِ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ " سورة الأنعام 73
"እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ #እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 73)፡፡
"وَلَا تَنْفَعُ الشَّفَاعَةُ عِنْدَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ حَتَّى إِذَا فُزِّعَ عَنْ قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ قَالُوا الْحَقَّ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة سبأ 23
"ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ፣ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፤ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠም ጊዜ (ተማላጆቹ) ጌታችሁ ምን አለ? ይላሉ፤ (አማላጆቹ) #እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው ይላሉ።" (ሱረቱ ሰበእ 23)፡፡
3. መጽሐፍቱ እውነት መሆናቸውን፡- ከጌታ አላህ ዘንድ ለሰው ልጆች መመሪያ ይሆኑ ዘንድ የተወረዱት መለኮታዊ መጽሐፍት በእውነት የተሞሉ ሆነው ነው የወረዱት፡፡ የመጽሐፍቱ ባለቤት እውነተኛ ነውና፡-
"كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنْذِرِينَ وَأَنْزَلَ مَعَهُمُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ فِيمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ..." سورة البقرة 213
"ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)፡፡ አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡ ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ #በእውነት አወረደ…" (ሱረቱል በቀራህ 213)፡፡
"أُولَئِكَ الَّذِينَ اشْتَرَوُا الضَّلَالَةَ بِالْهُدَى وَالْعَذَابَ بِالْمَغْفِرَةِ فَمَا أَصْبَرَهُمْ عَلَى النَّارِ * ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ نَزَّلَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ وَإِنَّ الَّذِينَ اخْتَلَفُوا فِي الْكِتَابِ لَفِي شِقَاقٍ بَعِيدٍ " سورة البقرة 176-175
"እነዚያ ጥመትን በቅንነት ቅጣትንም በምሕረት የገዙ ናቸው፡፡ በእሳት ላይም ምን ታጋሽ አደረጋቸው! ይህ (ቅጣት) አላህ መጽሐፍን #በእውነት ያወረደ በመኾኑ ምክንያት (እና በርሱ በመካዳቸው) ነው፡፡ እነዚያም በመጽሐፉ የተለያዩት (ከእውነት) በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ ናቸው" (ሱረቱል በቀራህ 175-176)፡፡
"نَزَّلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ مُصَدِّقًا لِمَا بَيْنَ يَدَيْهِ وَأَنْزَلَ التَّوْرَاةَ وَالْإِنْجِيلَ " سورة آل عمران 3
"ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን መጽሐፉን (ቁርአንን) ባንተ ላይ ከፋፍሎ #በዉነት አወረደ። ተዉራትንና ኢንጅልንም አውርዷል።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 3)፡፡
4. ንግስናው እውነት መሆኑን፡- አላህ የዩኒቨርሱ አስተናባሪና ብቸኛ ተቆጣጣሪ በመሆኑ እውነተኛ ንጉስ ተብሎ ያጠራል፡፡ የሌላው ምድራዊ ንግስና በግዜና በቦታ የተገደበ ስለሆነ ይጠፋል፡፡ ፍጹም እውነተኛ ንጉስ እሱ ብቻ ነው፡-
"فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ وَلَا تَعْجَلْ بِالْقُرْآنِ مِنْ قَبْلِ أَنْ يُقْضَى إِلَيْكَ وَحْيُهُ وَقُلْ رَبِّ زِدْنِي عِلْمًا " سورة طه 114
"እውነተኛው ንጉስ አላህም (ከሃዲዎች ከሚሉት) ላቀ ወደ አንተ መወረዱም ከመፈጸሙ በፊት በማንበብ አትቸኩል፤ ጌታዬ ሆይ! ዕውቀትንም ጨምርልኝ በል።" (ሱረቱ ጣሀ 114)፡፡
"أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ * فَتَعَالَى اللَّهُ الْمَلِكُ الْحَقُّ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ رَبُّ الْعَرْشِ الْكَرِيمِ " سورة المؤمنون 116-115
"«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን) የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ የሚያምረው ዐርሽ ጌታ ነው፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 115-116)፡፡
"وَيَوْمَ تَشَقَّقُ السَّمَاءُ بِالْغَمَامِ وَنُزِّلَ الْمَلَائِكَةُ تَنْزِيلًا * الْمُلْكُ يَوْمَئِذٍ الْحَقُّ لِلرَّحْمَنِ وَكَانَ يَوْمًا عَلَى الْكَافِرِينَ عَسِيرًا " سورة الفرقان 26-25
"በሰማይም በደመና የምትቀደድበትንና መላእክትም መወረድን የሚወርዱበትን ቀን (አስታውስ)። እውነተኛው ንግሥና በዚያ ቀን ለአልረሕማን ብቻ ነው፤ በከሐዲዎችም ላይ አስቸጋሪ ቀን ነው።" (ሱረቱል ፉርቃን 25-26)፡፡
5. ነቢያችንም የእውነት ነቢይ መሆናቸውን፡- ነቢዩ ሙሐመድ(ዐለይሂ ሶላቱ ወስ-ሰላም) ከእውነተኛው አምላክ ከአላህ ዘንድ የተላኩ በመሆናቸው፡ የሳቸውም ነቢይነት የእውነት መሆኑን እንረዳለን፡-
"إِنَّا أَرْسَلْنَاكَ بِالْحَقِّ بَشِيرًا وَنَذِيرًا وَلَا تُسْأَلُ عَنْ أَصْحَابِ الْجَحِيمِ " سورة البقرة 119
"እኛ አብሳሪና አስፈራሪ ኾነህ #በውነት ላክንህ፡፡ ከእሳትም ጓዶች አትጠየቅም፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 119)፡፡
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْ جَاءَكُمُ الرَّسُولُ بِالْحَقِّ مِنْ رَبِّكُمْ فَآمِنُوا خَيْرًا لَكُمْ وَإِنْ تَكْفُرُوا فَإِنَّ لِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَكَانَ اللَّهُ عَلِيمًا حَكِيمًا " سورة النساء 170
"እላንተ ሰዎች ሆይ! መልክተኛው #እውነትን ከጌታችሁ አመጣላችሁ እመኑም ለናንተ የተሻለ (ይሆናል) ብትክዱም አትጎዱትም፤ በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የአላህ ነውና፤ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 170)፡፡
" إِنَّهُمْ كَانُوا إِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ يَسْتَكْبِرُونَ * وَيَقُولُونَ أَئِنَّا لَتَارِكُو آلِهَتِنَا لِشَاعِرٍ مَجْنُونٍ * بَلْ جَاءَ بِالْحَقِّ وَصَدَّقَ الْمُرْسَلِينَ " سورة الصافات 37-35
"እነርሱ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም በተባሉ ጊዜ ይኮሩ በነሩ። እኛ ለዕብድ ባለቅኔ ብለን አማልክቶቻችንን የምንተዉ ነን? ይሉም ነበር። አይደለም እዉነቱን (ሃይማኖት) አመጣ። መልክተኞቹንም እዉነተኛነታቸዉን አረጋገጠ።" (ሱረቱ-ሷፍፋት 35-37)፡፡
6. ኢስላም እውነት መሆኑ፡- አላህ ለሰዎች የወደደው ብቸኛው ሃይማኖት ኢስላም ምንጩ ከሱ ዘንድ የመጣ በመሆኑ እውነተኛ ሃይማኖት ነው፡-
"هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَى وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ " سورة التوبة 33
"እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛዉን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነዉ።" (ሱረቱ-ተውባህ 33)፡፡
"هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَى وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَكَفَى بِاللَّهِ شَهِيدًا " سورة الفتح 28
"እርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በውነተኛ ሃይማኖት፣ በውነተኛ ሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው።" (ሱረቱል ፈትሕ 28)፡፡
"هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَى وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ " سورة الصف 9
"እርሱ ያ አጋፋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ (መጽሐፍ
) በውነተኛው ሃይማኖትም (በኢስላም) ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው።" (ሱረቱ-ሶፍ 9)፡፡
7. ፍርዱ እውነት ነው፡- እውነተኛው አምላክ አላህ በባሪያዎቹ ላይ በዚህ ምድርም ሆነ በመጪው ዓለም የሚፈርደው ፍርድ ምንም አይነት አድሎ የሌለበት ፍጹም እውነት ነው፡-
"قَدِ افْتَرَيْنَا عَلَى اللَّهِ كَذِبًا إِنْ عُدْنَا فِي مِلَّتِكُمْ بَعْدَ إِذْ نَجَّانَا اللَّهُ مِنْهَا وَمَا يَكُونُ لَنَا أَنْ نَعُودَ فِيهَا إِلَّا أَنْ يَشَاءَ اللَّهُ رَبُّنَا وَسِعَ رَبُّنَا كُلَّ شَيْءٍ عِلْمًا عَلَى اللَّهِ تَوَكَّلْنَا رَبَّنَا افْتَحْ بَيْنَنَا وَبَيْنَ قَوْمِنَا بِالْحَقِّ وَأَنْتَ خَيْرُ الْفَاتِحِينَ " سورة الأعراف 89
"አላህ ከርሷ ካአዳነን በኋላ ወደ ሃይማኖታችሁ ብንመለስ በአላህ ላይ በእርግጥ ውሸትን ቀጠፍን፤ አላህ ጌታችን ካልሻም በስተቀር ለኛ ወደርሷ ልንመለስ አይገባንም፤ ጌታችን እውቀቱ ሁሉን ነገር ሰፋ በአላህ ላይ ተጠጋን፤ ጌታችን ሆይ! በኛና በወገኖቻችን መካከል በውነት ፍረድ፤ አንተም ከፈራጆቹ ሁሉ በላጭ ነህ (አለ)።" (ሱረቱል አዕራፍ 89)፡፡
"قَالَ رَبِّ احْكُمْ بِالْحَقِّ وَرَبُّنَا الرَّحْمَنُ الْمُسْتَعَانُ عَلَى مَا تَصِفُونَ " سورة الأنبياء 112
"ጌታዬ ሆይ በውነት ፍረድ፤ ጌታችንም እጅግ በጣም ርኅሩኅ፤ በምትሉት ነገር ላይ፤ መታገዣ ነው፤ አለ።" (ሱረቱል አንቢያእ 112)፡፡
" قُلْ يَجْمَعُ بَيْنَنَا رَبُّنَا ثُمَّ يَفْتَحُ بَيْنَنَا بِالْحَقِّ وَهُوَ الْفَتَّاحُ الْعَلِيمُ " سورة سبأ 26
"ጌታችን በመካከላችን ይሰበስባል፤ ከዚያም በመካከላችን በውነት ይፈርዳል፤ እርሱም በትክክል ፈራጁ ዐዋቂው ነው በላቸው።" (ሱረቱ ሰበእ 26)፡፡
8. እውነተኛ ጌታ መሆኑን፡- አላህ የባሮቹን ጉዳይ የሚያስተናብር፡ ከጥፋት የሚያድን ረዳት በመሆኑ እውነተኛ ጌታ ይባላል፡-
"وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً حَتَّى إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ * ثُمَّ رُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ أَلَا لَهُ الْحُكْمُ وَهُوَ أَسْرَعُ الْحَاسِبِينَ " سورة الأنعام 62-61
"እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸነፊ ነው፡፡ በናንተም ላይ ጠባቂዎችን (መላእክት) ይልካል፡፡ አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ (የሞት) መልእክተኞቻችን እነርሱ (ትእዛዛትን) የማያጓድሉ ሲኾኑ ይገድሉታል፡፡ ከዚያም እውነተኛ ወደ ኾነው ጌታቸው ወደ አላህ ይመለሳሉ፡፡ ንቁ! ፍርዱ ለእርሱ ብቻ ነው፡፡ እርሱም ከተቆጣጣሪዎች ሁሉ ይበልጥ ፈጣን ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 61-62)፡፡
"هُنَالِكَ تَبْلُو كُلُّ نَفْسٍ مَا أَسْلَفَتْ وَرُدُّوا إِلَى اللَّهِ مَوْلَاهُمُ الْحَقِّ وَضَلَّ عَنْهُمْ مَا كَانُوا يَفْتَرُونَ " سورة يونس 30
"በዚያ ቀን ነፍስ ሁሉ ያሳለፈችውን ሥራ ታውቃለች፡፡ (አጋሪዎች) ወደ አላህም እውነተኛ ወደ ሆነው ጌታቸው ይመለሳሉ፡፡ ከእነሱም ይቀጣጥፉት የነበሩት ነገር ይጠፋቸዋል፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 30)፡፡
" فَذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمُ الْحَقُّ فَمَاذَا بَعْدَ الْحَقِّ إِلَّا الضَّلَالُ فَأَنَّى تُصْرَفُونَ " سورة يونس 32
"እርሱ እውነተኛ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ከእውነትም በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ ምን አለ (ከውነት) እንዴት ትዞራላችሁ" (ሱረቱ ዩኑስ 32)፡፡
"هُنَالِكَ الْوَلَايَةُ لِلَّهِ الْحَقِّ هُوَ خَيْرٌ ثَوَابًا وَخَيْرٌ عُقْبًا " سورة الكهف 44
"እዚያ ዘንድ (በትንሣኤ ቀን) ስልጣኑ እውነተኛ ለሆነው አላህ ብቻ ነው፤ እርሱ በመመንዳት የበለጠ ፍጻሜንም በማሳመር የበለጠ ነው" (ሱረቱል ከህፍ 44)፡፡
9. የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው፡- ሙታን ሁሉ ከመቃብራቸው ተቀስቅሰው ለፍርድ እንደሚቀርቡ ጌታችን የቀጠረው ቀጠሮም እውነት ነው፡-
"وَقَالَ الشَّيْطَانُ لَمَّا قُضِيَ الْأَمْرُ إِنَّ اللَّهَ وَعَدَكُمْ وَعْدَ الْحَقِّ وَوَعَدْتُكُمْ فَأَخْلَفْتُكُمْ وَمَا كَانَ لِيَ عَلَيْكُمْ مِنْ سُلْطَانٍ إِلَّا أَنْ دَعَوْتُكُمْ فَاسْتَجَبْتُمْ لِي فَلَا تَلُومُونِي وَلُومُوا أَنْفُسَكُمْ مَا أَنَا بِمُصْرِخِكُمْ وَمَا أَنْتُمْ بِمُصْرِخِيَّ إِنِّي كَفَرْتُ بِمَا أَشْرَكْتُمُونِ مِنْ قَبْلُ إِنَّ الظَّالِمِينَ لَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ " سورة إبراهيم 22
"ነገሩም በተፈጸመ ጊዜ፣ ሰይጣን ይላቸዋል፦ አላህ እውነተኛውን ቃል ኪዳን ገባላችሁ፤ ቃል ኪዳንም ገባሁላችሁ፤ አፈረስኩባችሁም፣ ለኔም በናንተ ላይ ምንም ሥልጣን አልነበረኝም ግን ጠራኋችሁ፤ ለኔም ታዘዛችሁ ስለዚህ አትውቀሱኝ፤ ነፍሶቻችሁንም ውቀሱ እኔ የምረዳችሁ አይደለሁም፤ እናንተም የምትረዱኝ አይደላችሁም፤ እኔ ከአሁን በፊት ለአላህ ተጋሪ በአደረጋችሁት ነገር ካድኩ፤ በዳዮቹ ለነርሱ በእርግጥ አሳማሚ ቅጣት አልላቸው።" (ሱረቱ ኢብራሒም 22)፡፡
"وَاقْتَرَبَ الْوَعْدُ الْحَقُّ فَإِذَا هِيَ شَاخِصَةٌ أَبْصَارُ الَّذِينَ كَفَرُوا يَا وَيْلَنَا قَدْ كُنَّا فِي غَفْلَةٍ مِنْ هَذَا بَلْ كُنَّا ظَالِمِينَ " سورة الأنبياء 97
"እውነተኛውም ቀጠሮ በቀረበ ጊዜ፣ ያን ጊዜ እነሆ የነዚያ የካዱት ሰዎች ዓይኖች ይፈጥጣሉ፤ ዋ ጥፋታችን! ከዚህ (ቀን) በእርግጥ በዝንጋቴ ላይ ነበርን፤ በውነትም በዳዮች ነበርን፤ (ይላሉ)።" (ሱረቱል አንቢያእ 97)፡፡
10. እውነት ከውሸት ይልቃል፡- እውነት በመጣ ጊዜ ውሸት ይደበቃል፡፡ መውጪያ ቀዳዳ ያጣል፡ ደግሞም ይወገዳል፡-
"وَقُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَزَهَقَ الْبَاطِلُ إِنَّ الْبَاطِلَ كَانَ زَهُوقًا " سورة الإسراء 81
"በልም፦እውነት መጣ፣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፣" (ሱረቱል ኢስራእ 81)፡፡
"قُلْ جَاءَ الْحَقُّ وَمَا يُبْدِئُ الْبَاطِلُ وَمَا يُعِيدُ " سورة الأحزاب 49
እውነቱ መጣ፤ ውሸትም መነሻም መድረሻም የለውም (ተወገደ) በላቸው።" (ሱረቱል አሕዛብ 49)፡፡
አምላካችን አላህ ሆይ! እውነትን እውነት አድርገህ አሳየን እንድንከተለውም ተውፊቅህ (እገዛህ) አይለየን ውሸትን ውሸትነቱን ግለጽልን እንድንርቀውም አድርገን
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
Allah The All Knowing
አላህ ሁሉን ዐዋቂ ነው!
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
http://goo.gl/LqaEKW

Join us➤ t.me/abuhyder
ነገ ሙሐረም 1/ 1440 ነው!

የሂጅራ አቆጣጠር ታሪካዊ አጀማመር

በአቡ ሀይደር

በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን(አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡

1ኛ/ የቃላት ፍቺ፡- ሂጅራ ማለት፡- ቀጥታ ፍቺው ስደት ማለት ነው፡፡ ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ፡- ክህደት ከሰፈነት ሀገርና መንደር፡ አላህን በነጻነት ለማምለክና ህጉን ለመጠበቅ እምነትና መረጋጋት ወደሰፈነት ሀገር የሚደረግ እንቅስቃሴ (ቅዱስ ጉዞ) ማለት ነው፡፡

2ኛ/ የአላህ መልክተኛና የነቢያቶች ኹሉ መደምደሚያ የኾኑት፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በተወለዱባት በመካ ከተማ፡ እድሜያቸው ዐርባ በሞላ ጊዜ፡ ከዓለማቱ ጌታ ከአላህ ዘንድ ለዓለማት ህዝቦች ነቢይና መልክተኛ ኾነው ተመረጡ፡፡ ተወልደው ባደጉባት የመካ ከተማ ላይ ለአሥራ ሶስት ዓመታት የአላህን መልእክት ለሕዝባቸው፡ የሚደርስባቸውን መከራና ስቃይ በመቋቋም በታማኝነት አድርሰዋል፡፡ በመጨረሻም ከሕዝባቸው በኩል መከራውና ስቃዩ እየበረታባቸው ሲሄድ፡ በጌታ አላህ ትእዛዝ፡ ትውልድ ሀገራቸውን ለቀው፡ ወደ የሥሪብ (የአሁኗ መዲነቱል-ሙነወራህ) ቅዱስ ጉዞ እንዲያደርጉ ትእዛዝ መጣላቸው፡፡ ይህ ቅዱስ ጉዞ ‹‹ሂጅረቱ-ረሱል›› በመባል ይታወቃል፡፡

3ኛ/ ይህን የሂጅራን ክስተት በመያዝ፡ ለሙስሊሞች ኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠር አድርጎ መያዝ የተጀመረው፡ ረሱል (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወደ መዲናህ ከተሰዱ ከአሥራ ስድስት/አሥራ ሰባት ዓመት በኋላ (ማለትም እሳቸው ከሞቱ ከስድስት/ሰባት ዓመት በኋላ) በዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) የኺላፋነት (ዘመነ-ንግሥና) ጊዜ ነው፡፡

4ኛ/ ኢማሙ-ሱሀይሊ (ረሒመሁላህ) ‹‹ረውዱል-ኡንፍ›› በተሰኘው ኪታባቸው ላይ እንደገለጹት፡ ሶሓቦች (ረዲየላሁ ዐንሁም) ይህን የሂጅራን ቀን የዘመን መቁጠሪያ አድርገው መጠቀምን የመረጡት እንዲህ ከሚለው የአላህ ቃል በመነሳት ነው፡-

" لَا تَقُمْ فِيهِ أَبَدًا لَمَسْجِدٌ أُسِّسَ عَلَى التَّقْوَى مِنْ أَوَّلِ يَوْمٍ أَحَقُّ أَنْ تَقُومَ فِيهِ فِيهِ رِجَالٌ يُحِبُّونَ أَنْ يَتَطَهَّرُوا وَاللَّهُ يُحِبُّ الْمُطَّهِّرِينَ " سورة التوبة 108
"በእርሱ ውስጥ በፍጹም አትስገድ፡፡ ከመጀመሪያ ቀን ይዞ በአላህ ፍራቻ ላይ የተመሠረተው (የቁባ) መስጊድ በውስጡ ልትሰግድበት ይልቅ የተገባው ነው፡፡ በእሱ ውስጥ መጥራራትን የሚወዱ ወንዶች አልሉ፡፡ አላህም ተጥራሪዎችን ይወዳል፡፡" (ሱረቱ-ተውባህ 9፡108)፡፡

በዚህ አንቀጽ ውስጥ ‹‹ከመጀመሪያ ቀን›› የሚል ቃል አልለ፡፡ በሁሉም ዘንድ እንደሚታወቀው፡ በአንጻራዊነት ካልኾነ በስተቀር፡ በልቁ የመጀመሪያ ቀን ተብሎ የሚጠራ ነገር የለም፡፡ (ከሱ በፊትም ሌሎች ቀናት ስለሚኖሩ ማለት ነው)፡፡ በዚህ አንቀጽ ላይ ግን ‹‹የመጀመሪያ ቀን›› የሚለው የተጠቀሰው፡ ኢስላም በግልጽ ይፋ የወጣበት፡ አላህን በነጻነት ያለ-ምንም ስጋት መዲናህ በሚገኘው መስጂድ ቁባእ ውስጥ ማምለክ ስለተቻለበት፡ እንዲሁም መስጂድ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለተገነባበት፡ ይህን ቀን የመጀመሪያ ብሎ ሰየመው፡፡ በዛው መልኩ ሶሓቦችም በስምምነት ከዚህ ጊዜ በመነሳት የዘመን አቆጣጠርንም ጀመሩ ማለት ነው፡፡ (አር-ረውዱል ኡንፍ 4/255)፡፡ (በመክተበቱ-ሻሚላህ ላይ ደግሞ 2/331 ይመልከቱ)፡፡

5ኛ/ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ የሂጅራን ታሪካዊ አጀማመር ምክንያት ሲገልጹ እንዲህ ይላሉ፡- ኢስላማዊ የዘመን አቆጣጠርን ከምን እንጀምር? ለሚለው ሀሳብ፡ አራት ዋና ዋና የተስማሙባቸው ምክንያቶች ቀርበው ነበር፡፡ እነሱም፡- የነቢዩ ሙሐመድን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የልደት ቀን፣ ነቢይ ኾነው የተመረጡበትን ቀን፣ ወደ የሥሪብ (የአሁኗ መዲና) ያደረጉትን የስደት ቀን እና የሞቱበትን ቀን፡፡ ከዛም የሂጅራ(ስደት) ቀን ይሁን! የሚለው በላጭ ሀሳብ ሆኖ ተገኘ፡፡ ምክንያቱም፡- የልደታቸውና ነቢይ ኾነው የተመረጡበትን ቀን በተመለከተ፡ በኢስላም ሊቃውንት ዘንድ መቼ ነበር ቀኑ? የሚለው ኺላፍ (የሃሳብ ልዩነት) ያለበት በመኾኑ፡ ከክርክር የሚወገድ ሀሳብ አይሆንም ማለት ነው፡፡ የሞቱበት ቀን ደግሞ እንዳይኾን፡ ቀኑን ማስታወሱ በራሱ ሐዘንን ያወርሳል በማለት ተዉት፡፡ ስለዚህ የቀረው ሂጅራህ ያደረጉበት ቀን ኾነ ማለት ነው፡፡

6ኛ/ የአላህ መልክተኛ ወደ የሥሪብ (ወዲናህ) የገቡት በሶስተኛው ወር በረቢዑል-አወል ነበር፡፡ ታዲያ የዓመቱ አቆጣጠር ለምን ከሙሐረም ተጀመረ? ለሚለው የተሰጠው ምላሽ፡- ለሂጅራ ስደት ሀሳቡና ውሳኔው ተላልፎ የነበረው በወርኃ ሙሐረም ነበር፡፡ ምክንያቱም ይህ በይዓህ (ቃል-መጋባት) የተከናወነው፡ በዙል-ሒጃህ (ከሙሐረም በፊት ያለው ወር) ላይ ነበር፡፡ ከበይዓው በኋላ የቀጣዩ ወር (የሙሐረም) ጨረቃ ብቅ አለ፡፡ በሙሐረም ወርም የስደቱ ውሳኔ ተከናወነ፡፡ ስለዚህም የዓመቱ አቆጣጠር ጅማሬ ከዚህ ወር እንዲሆን ተወሰነ ማለት ነው፡፡ (ወላሁ አዕለም)፡፡

ኢብኑ ሐጀር (ረሒመሁላህ) በኪታባቸው ‹‹ፈትሑል-ባሪይ›› ላይ እንደገለጹት፡- አባ ሙሳ አል-አሽዐሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ለዑመር ኢብኑል-ኸጥጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ከአንተ ዘንድ ዘመኑ ያልተጻፈበት (ያልተገለጸበት) መጽሐፍ እየመጣልን ነው ሲለው፡ ዑመርም ሰዎችን ሰበሰበና በጉዳዩ ዙሪያ አማከራቸው፡፡ ከፊሎቹ፡- እሳቸው ነቢይ ሆነው በተመረጡበት ቀን ይሁን ሲሉ፡ ከፊሉ ደግሞ፡- በሂጅራው ቀን ይሁን አሉ፡፡ ዑመርም ረዲየላሁ ዐንሁ፡ ሂጅራህ እውነትን ከሐሰት የለየች ቀን በመሆኗ በሷ ዘመንን ቁጠሩ! አለ፡፡ ይህም አሥራ ሰባተኛው ዓመት ላይ ነበር፡፡ እነሱም በሂጅራው ቀን መሆኑን ከተስማሙ በኋላ፡ ከፊሎቹ የወሩ መጀመሪያ ረመዷን ይሁን ሲሉ፡ ዑመርም፡- ሙሐረም ነው መሆን ያለበት፡፡ እሱ (ሙሐረም) ሰዎች የሐጅ ስርኣታቸውን ፈጽመው የሚመለሱበት ነውና አለ፡፡ ከዚያም በሙሐረም የመጀመሪያ ወርነት ተስማሙ፡፡ (ፈትሑል-ባሪይ፡ 7/268)፡፡ በሌሎች ዘገባዎችም፡ ይህ የሂጅራህ ቀን፡ የዘመን መቁጠሪያ ጅማሬ እንዲሆን ሐሳብ ያቀረበው ሶሓቢዩ ዐሊይ ኢብኑ አቢ-ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ ነው፡፡ ዑመርም ረዲየላሁ አንሁ ይህን ሀሳብ ተቀበለው የሚልም አልለ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

7ኛ/ ቀኑን እንደ ዒድ መያዝ፡-

በዚህ አዲስ አመት ላይ የ‹‹እንኳን አደረሰህ›› የመልካም ምኞት መግለጫን፡ ሙስሊሙ ለሌላው ሙስሊም ወንድሙ መስጠቱ ይበቃል ወይስ አይበቃም? ለሚለው፡ ሁለት ወይም ሶስት የኢስላም ሊቃውንት ተጠይቀው የሰጡትን ምላሽ አቀርበዋለሁ፡-

ሀ/ ኢብኑ ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ)፡-

አንድ ሰው ወደ አንተ በመምጣት ‹‹እንኳን አደረሰህ!›› ካለህ፡ አንተም በዛው አምሳያ መልስለት፡፡ ግን አንተ በዚህ (የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ) ጀማሪ አትሁን፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የተሻለው ሀሳብ ይህ ነው፡፡ አንድ ሰው እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰህ! በማለት፡ የመልካም ምኞት መግለጫውን ቢሰጥህ፡ አንተም፡- አላህ አንተንም በመልካም ያበስርህ! ዓመቱንም የበረካና የመልካም ሥራ ዓመት ያድርገው በለው፡፡ ሆኖም አንተ ሰዎችን በዚህ ሰላምታ ጀማሪ አትሁን፡፡ እኔ ይህ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሰህ! ሰላምታ ከ
ሰለፎች ለመገኘቱ የማውቀው ነገር የለም፡፡ እንደውም ሰለፎች (ሶሓቦች) ሙሐረምን በዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ የኸሊፋነት ጊዜ እንጂ፡ ከዛ በፊት የዓመቱ መጀመሪያ አድርገው ይዘው እንደማያውቁ ዕወቁ፡፡ (ሊቃእ ባቡል-መፍቱሕ ጥያቄ ቁ 835)፡፡ የድምጽ ማስረጃ ለፈለገ ደግሞ https://ar.islamway.net/fatwa/3181

ለ/ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ)፡-

በየአዲስ ዓመቱ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት መለዋወጥ ከሰለፉ-ሷሊሕ የተገኘ መሰረት ያለው መኾኑን የምናውቀው ነገር የለም፡፡ ከቁርኣንም ሆነ ከሱንና ሸሪዓዊ መሠረት እንዳለውም የሚያሳይ ነገር አይታወቅም፡፡ ሆኖም፡ በእንኳን አደረሰህ ቀድሞ የጀመረህን ሰው፡ ላንተም እንኳን አደረሰህ! ብለህ መመለሱ ችግር የለውም፡፡ ቀድሞ የሰላምታው ጀማሪ መሆን ላይ ግን ምን መሠረት እንዳለው አላውቅም፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡ (የድምጽ ማስረጃ http://www.binbaz.org.sa/noor/1179

ጠቅለል ለማድረግ፡- የሂጅራን ዓመታዊ አቆጣጠር አስመልክቶ፡ የእንኳን አደረሳችሁ! መልእክት መለዋወጡ፡ ከሰለፎች ያልተገኘ፡ ኢስላማዊ መሠረት የሌለው ተግባር ነው፡፡ ሆኖም አንድ ሰው አንተን ቀድሞ ‹‹እንኳን ለሂጅራ አዲሡ ዓመት አደረሰህ!›› ቢልህ፡ ድርጊቱን አታውግዘው፡፡ ኃጢአት አልሰራምና የሚል ነው፡፤ ወላሁ አዕለም፡፡

ምንጭ፡- አቡ ዐብደላህ አዝ-ዘሀቢይ http://www.saaid.net/Doat/Althahabi/2.htm
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
What is Quran
የቅዱስ ቁርኣን ምንነት!
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
http://goo.gl/W2wrsZ

Join us➤ t.me/abuhyder
11. "አል-ሙሰዊር" (ቅርጽን ሰጪ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ሙሰዊር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ቅርጽን አሳማሪ፣ ሰዓሊና ቀራጭ የሚል ነው፡፡ ፈጣሪ አምላካችን አላህ ፍጥረታቱን እሱ ብቻ በሚፈልገው ቅርጽ ያበጀና ያዘጋጀ ነው፡፡ በመልክም ሆነ በቅርጽ፤ በይዘትም ሆነ በአይነት፡ የተለያዩ የሆኑ ድንቅ ስራዎቹን ገልጾአል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ ፍጹም ተመሳሳይ የሆኑ ሁለት ነገሮችን ማግኘት አይቻልም፡፡ ይህ የችሎታውን ወሰን-የለሽነት፣ የጥበቡን ጥልቀት፣ የዕውቀቱን ስፋት የሚገልጽ ነው፡፡ ከሰው፣ ከእንሰሳት፣ ከነፍሳት፣ ከእጽዋት፣ ከበራሪዎች እና ከመላእክት በቅርጽ የማይመሳሰሉ ስንትና ስንት ፍጥረታት አሉት፡፡
ለ. አመጣጡ፡- "አል-ሙሰዊር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-
" هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَى يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة الحشر 24
"እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ቅርጽን አሳማሪው ነው፤ ለርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፤ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለርሱ ያሞግሳል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱል ሐሽር 24)፡፡
ሐ. ከዚህ የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አላህ የፈለገውን ፍጥረት በፈለገው መልኩ መቅረጽ የሚችል ጌታ መሆኑን፡- መፍጠር የአምላካችን የአላህ መለኮታዊ ባሕሪው መሆኑን ካመንን፡ የፈጠረውን ፍጥረት ደግሞ ምን አይነት ቅርጽ መያዝ እንዳለበት መወሰንም የሱ መብትና ችሎታ ብቻ ነው ማለት ነው፡-
" هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة آل عمران 6
"እርሱ ያ በማሕፀኖች ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነዉ። ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 6)፡፡
" يَا أَيُّهَا الْإِنْسَانُ مَا غَرَّكَ بِرَبِّكَ الْكَرِيمِ * الَّذِي خَلَقَكَ فَسَوَّاكَ فَعَدَلَكَ * فِي أَيِّ صُورَةٍ مَا شَاءَ رَكَّبَكَ " سورة الإنفطار 8-6
"አንተ ሰው ሆይ በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ? በዚያ በፈጠረህ አካለ ሙሉም ባደረገህ፣ ባስተካከለህም። በማንኛውም በሻው ቅርጽ በገጣጠመህ (ጌታህ ምን አታለለህ?)።" (ሱረቱል ኢንፊጣር 6-8)፡፡
በሶላታችን ውስጥ በሱጁድ ስፍራ ላይ ሆነን ከምናደርጋቸው ዚክሮች አንዱ ይህንን የሚገልጽ ነው፡-
عن علي رضي الله عنه قال: أن رسول الله صلى الله عليه وسلم كان إذا سجد قال : " اللهمَّ لَكَ سَجَدْتُ ، وَبِكَ آمَنْتُ ، وَلَكَ أَسْلَمْتُ ، سَجَدَ وَجْهِي للذِي خَلَقَهُ وَصَوَّرَهُ ، وَشَقَّ سَمْعَهُ وَبَصَرَهُ ، تَبَارَكَ الله أَحْسَنُ الخَالِقِينَ " رواه مسلم.
ዐሊይ ኢብኑ-አቢ ጧሊብ(ረዲየላሁ ዐንሁ) ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡- "የአላህ መልክተኛ ሱጁድ ሲያደርጉ፡- ‹‹አላህ ሆይ! ላንተ ሰገድኩ፣ ባንተም አመንኩ፣ ላንተም ታዘዝኩ፣ ፊቴም ለዚያ ለፈጠረውና ቅርጽ ላስያዘው፣ መስሚያውንና መመልከቻውን ለከፈተለት ሰገደ፡፡ ከሰዓሊዎች ሁሉ በላጭና አሳማሪ የሆነው አለህ ክብሩ ላቀ" (ሙስሊም)፡፡
2. አላህ በፈለገው ቅርጽ የተሰራው ፍጥረት ደግሞ እጅጉኑ ያማረና የተዋበ፡ የማያስቀይምም መሆኑንም እንማራለን፡-
" اللَّهُ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ الْأَرْضَ قَرَارًا وَالسَّمَاءَ بِنَاءً وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ وَرَزَقَكُمْ مِنَ الطَّيِّبَاتِ ذَلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ فَتَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ " سورة الغافر 64
"አላህ ያ ምድርን መርጊያ ሰማይንም ጣሪያ ያደረገላችሁ ነው፤ የቀረጻችሁም ቅርጻችሁንም ያሳመረ፣ ከጣፋጮችም ሲሳዮች የሰጣችሁ ነው፤ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ።" (ሱረቱል ጋፊር 64)፡፡
" خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَصَوَّرَكُمْ فَأَحْسَنَ صُوَرَكُمْ وَإِلَيْهِ الْمَصِيرُ " سورة التغابن 3
"ሰማያትንና ምድርን በውነት ፈጠረ፤ ቀረፃችሁም ቅርፃችሁንም አሳመረ፤ መመለሻችሁም ወደርሱ ነው።" (ሱረቱ-ተጋቡን 3)፡፡
" ثُمَّ خَلَقْنَا النُّطْفَةَ عَلَقَةً فَخَلَقْنَا الْعَلَقَةَ مُضْغَةً فَخَلَقْنَا الْمُضْغَةَ عِظَامًا فَكَسَوْنَا الْعِظَامَ لَحْمًا ثُمَّ أَنْشَأْنَاهُ خَلْقًا آخَرَ فَتَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ " سورة المؤمنون 14
"ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን፡፡ የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን፡፡ ቁራጯንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን፡፡ አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው፡፡ ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው፡፡ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡" (ሱረቱል ሙእሚኑን 14)፡፡
" الَّذِي أَحْسَنَ كُلَّ شَيْءٍ خَلَقَهُ وَبَدَأَ خَلْقَ الْإِنْسَانِ مِنْ طِينٍ " سورة السجدة 7
"ያ የፈጠረውን ነገር ሁሉ ያሳመረው፣ የሰውንም ፍጥረት ከጭቃ የጀመረው፥ ነው።" (ሱረቱ-ሰጅዳህ 7)፡፡
" لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنْسَانَ فِي أَحْسَنِ تَقْوِيمٍ " سورة التين 4
"ሰውን በጣም በአማረ አቋም ላይ ፈጠርነው።" (ሱረቱ-ቲን 4)፡፡
3. ለሕያዋን ፍጥረታት ቅርጽን ማሳመር የአላህ ስራ ስለሆነ፡ ለኛ ሕይወት ያለውን (የሰውም ሆነ የእንሰሳት) ምስል መስራት፣ መቅረጽ እንደማይፈቀድልን እንማራለን፡፡ ምክንያቱም በውስጡ ሩሕን በመንፋት ሕይወትን መለገስ አንችልምና፡-
عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: " أشد الناس عذابا يوم القيامة رجل قتل نبيا ، أو قتله نبي أو رجل يضل الناس بغير علم ، أو مصور يصور التماثيل " رواه الطبراني وحسنه الشيخ الألباني.
ዐብደላህ ኢብኑ-መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሐዲሥ፡ የአላህ ነቢይ እንዲህ አሉ፡- "የቂያም ቀን ቅጣቱ እጅግ የሚበረታባቸው ሰዎች፡- ነቢይን የገደለ ወይም ነቢይ እሱን (በክህደቱ) የገደለው፣ ያለ እውቀት ሰዎችን ያጠመመ፣ (ህይወት ያላቸውን ነገሮች) አምሳል የሚቀርጽ ነው" (ጦበራኒ የዘገቡት፣ ሶሒሑል-ጃሚዕ 1000)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
Is death the outcome of a sin ?
🔵ሞት በኃጢአት ምክንያት የመጣ ነውን? ☞ በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
☞ http://goo.gl/i5wYxd

Join us ➤ http://tttttt.me/abuhyder
ኢስላም አና ዘረኝነት
አቡ ሀይደር
💧የትምህረቱ ርዕስ 💧

💥 ኢስላምና ዘረኝነት 💥

💨 የትምህርቱ አቅራቢ 💨

🎙🎙 ኡስታዝ አቡ ሀይደር


🎙 ሒዳያ ቲዩብ 💻
https://tttttt.me/hidayaislam
Recording Feb 10 2010 8 25 18 AM
ነቢያት ሁሉ ሙስሊም ነበሩ
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
☞ http://goo.gl/7I8BXy

http://tttttt.me/abuhyder
የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
11. "አል-ሙሰዊር" (ቅርጽን ሰጪ) በአቡ ሀይደር በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡ ሀ. ትርጉም፡…
12. "አር-ረሒም" (በጣም አዛኝ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
በቁጥር አንድ ትምሕርታችን ላይ፡ ስለ አላህ መለኮታዊ ስሞች መማር ስንጀምር መጀመሪያ ያደረግነው ስም ‹‹አር-ረሕማን›› የሚለውን መለኮታዊ ስም ነበር፡፡ ዛሬ የምንመለከተው ደግሞ ‹‹አር-ረሒም›› የሚለውን መለኮታዊ ስም ነው፡፡
ሀ.ትርጓሜው
የዚህ መለኮታዊ ስም "አር-ረሒም" ትርጉም፡- እጅግ በጣም አዛኝ ማለት ነው፡፡ እዝነቱ ምእመናን ባሮቹንና በተውበት የሚመለሱትን ያካለለ ስም ነው፡፡
"አር-ረሒም" የሚለው ስም "አር-ራሕማን" ከሚለው ስም ጋር ያለውን ልዩነት ሊቃውንት ካስቀመጡት ነጥቦች ውስጥ ሁለቱን እንመልከት፡-
- "አር-ራሕማን" የሚለው ስም የሚያመለክተው የጌታችንን የህልውናው (የዛቱ) መጠሪያ ስም ሲሆን "አር-ረሒም" ደግሞ በስራና በተግባር የሚገለጸውን የባሕሪ ስም አመልካች ነው፡፡
- "አር-ራሕማን" የሚለው ስም በዚህ ዓለም ላይ ለፍጡራኑ በጠቅላላ ለሙስሊሙም ለካፊሩም አዛኝነቱን የሚያመላክት ስም ነው፡፡ ጸሐይ ቢወጣ፣ ዝናብ ቢዘንብ፣ ምድር ብታበቅል የሚዳረሰው ለሁሉም ነውና፡፡
"አር-ረሒም" ግን ለአማኞች ብቻ የሚገለጽ የራህመት አይነት ነው፡፡ ለዚህም እንደማስረጃነት የሚቀርበው ተከታዩ አንቀጽ ነው፡-
" هُوَ الَّذِي يُصَلِّي عَلَيْكُمْ وَمَلَائِكَتُهُ لِيُخْرِجَكُمْ مِنَ الظُّلُمَاتِ إِلَى النُّورِ وَكَانَ بِالْمُؤْمِنِينَ رَحِيمًا " سورة الأحزاب 43
"እነሱ ያ በናንተ ላይ እዝነትን የሚያወርድ ነው፤ መላእክቶችም ፥ ( እንደዚሁ ምሕረትን የሚለምኑላችሁ ናቸው) ፣ ከጨለማዎች ወደ ብርሃን ያመጣችሁ ዘንድ (ያዝንላችኋል)፤ #ለአማኞችም በጣም አዛኝ ነው።" ሱረቱል አሕዛብ 43
" يَوْمَ لا يُغْنِي مَوْلًى عَن مَّوْلًى شَيْئاً وَلا هُمْ يُنصَرُونَ * إِلا مَن رَّحِمَ اللهُ إِنَّهُ هُوَ العَزِيزُ الرَّحِيمُ " سورة الدخان 42-41
"ዘመድ ከዘመዱ ምንንም የማይጠቅምበት፣ እነሱም የማይርረዱበት ቀን ነው።አላህ ያዘነለት ብቻ ሲቀር፤ (እርሱስ ይርረዳል)፤ እርሱ አሸናፊው አዛኙ ነውና።" ሱረቱ-ዱኻን 41-42
ለ. አመጣጡ፡-
"አር-ረሒም" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 114 ጊዜ መጥቷል፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-
" وَإِذْ قَالَ مُوسَى لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ إِنَّكُمْ ظَلَمْتُمْ أَنْفُسَكُمْ بِاتِّخَاذِكُمُ الْعِجْلَ فَتُوبُوا إِلَى بَارِئِكُمْ فَاقْتُلُوا أَنْفُسَكُمْ ذَلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ عِنْدَ بَارِئِكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ إِنَّهُ هُوَ التَّوَّابُ الرَّحِيمُ " سورة البقرة 54
"ሙሳም ለሕዝቦቹ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! እናንተ ወይፈንን (አምላክ አድርጋችሁ) በመያዛችሁ ነፍሶቻችሁን በደላችሁ፡፡ ወደ ፈጣሪያችሁም ተመለሱ፤ ነፍሶቻችሁንም ግደሉ*** ይሃችሁ በፈጣሪያችሁ ዘንድ ለናንተ በላጭ ነው» ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእናንተም ላይ ጸጸትን በመቀበል ተመለሰላችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 54)
" وَلِلَّهِ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ يَغْفِرُ لِمَنْ يَشَاءُ وَيُعَذِّبُ مَنْ يَشَاءُ وَاللَّهُ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة آل عمران 129
"በሰማያት ያለዉ፣ በምድርም ያለዉ፣ ሁሉ፣ የአላህ ነዉ፤ ለሚሻዉ ሰዉ ይምራል፤ የሚሻዉንም ሰዉ ይቀጣል፤ አላህም መሐሪ አዛኝ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 129)፡፡
" فَمَنْ تَابَ مِنْ بَعْدِ ظُلْمِهِ وَأَصْلَحَ فَإِنَّ اللَّهَ يَتُوبُ عَلَيْهِ إِنَّ اللَّهَ غَفُورٌ رَحِيمٌ " سورة المائدة 39
"ከመበደሉም በኋላ የተጸጸተና ሥራውን ያሳመረ አላህ ጸጸቱን ከርሱ ይቀበለዋል፤ አላህ መሐሪ አዛኝ ነውና።" (ሱረቱል ማኢዳህ 39)፡፡
ሐ. የምንማረው ትምሕርት፡- "አር-ረሒም" ከሚለው መለኮታዊ ስም ብዙ ትምሕርት እናገኛለን፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
1. ጌታችን "አር-ረሒም" የሚል መለኮታዊ ስም እንዳለው እንረዳለን፡፡ አምነንም እንቀበላለን፡፡
" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ هُوَ الرَّحْمَنُ الرَّحِيمُ " سورة الحشر 22
"እርሱ አላህ ነው፤ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የሆነው፤ እርሱ እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ ነው።" (ሱረቱል ሐሽር 22)፡፡
2. በዚህ ስም እንድንለምነው፡- ጌታችን አላህን ስንለምነውና ስንማጸነው "ያ አላህ" እንደምንለው ሁሉ "ያ ረሒም" ብለንም መማጸንና መለመን እንችላለን፡፡
" قَالَ رَبِّ إِنِّي ظَلَمْتُ نَفْسِي فَاغْفِرْ لِي فَغَفَرَ لَهُ إِنَّهُ هُوَ الغَفُورُ الرَّحِيمُ " [القصص:16]
"«ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ለእኔም ማር አለ፡፡» ለእርሱም ምሕረት አደረገለት እርሱ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡" (ሱረቱል ቀሶስ 16)፡፡
3. ባሕሪውን መላበስን፡- ጌታችን አላህ በባሕሪውም ሆነ በስሞቹ ከፍጡራን ጋር አይመሳሰልም (አሽ-ሹራ 11)፡፡ ለፍጡሩ ባሪያው ግን ከማንነቱ ጋር ተስማሚ የሆነ ባሕሪ ለግሶታል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ እዝነት ነው፡፡ እርሱ ጌታችን "አር-ረሒም" ነውና ለባሪያውም እዝነትን ለገሰ፡፡ በተለይ ለነቢያችን የተለገሰው ባሕሪ ተጠቃሽ ነው፡፡ ተከታዮቹ አንቀጾች ይህን ይገልጻሉ፡-
" لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِنْ أَنْفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُمْ بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَحِيمٌ " سورة التوبة 128
"ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በርሱ ላይ ጥኑ የሆነ፣ በናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ርኅሩህ #አዛኝ የሆነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ።" (ሱረቱ-ተውባህ 128)፡፡
" وَمَا أَرْسَلْنَاكَ إِلَّا رَحْمَةً لِلْعَالَمِينَ " سورة الأنبياء 107
"(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም #እዝነት አድርገን እንጅ አልላክንህም።" (ሱረቱል አንቢያእ 107)፡፡
ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በአኼራ የአንተ ራሕመት አይለየን፡፡ አዛኝ ነህና እዘንልን፡፡ በራሕመትህም ጀነት ከሚገቡ መልካም ባሮችህ አድርገን
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us ➤➤ http://tttttt.me/abuhyder