የኡስታዝ አቡ ሀይደር ትምህርቶች ስብስብ
17.3K subscribers
304 photos
106 videos
47 files
800 links
ኡስታዝ አቡ ሀይደር በፌስቡክ ያስተማራቸው የኦዲዮ የጹሁፍ እና የቪዲዮ ትምህርቶች ተሰባስበው የሚገኙበት ቻናል ነው።
Download Telegram
LOVE IN ISLAM - PART 1 - Brotherly Love
ፍቅር በኢስላም ክፍል 1
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
http://goo.gl/Y07b9t

Join us➤ t.me/abuhyder
LOVE IN ISLAM - Part 2 - What Allah Likes & Dislikes
ፍቅር በኢስላም ክፍል 2
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
http://goo.gl/fJd8fm

Join us➤ t.me/abuhyder
አላህ #ከዘረኝነት_ይጠብቀን

ዘረኝነት:– የራስን ቋንቋ፣ ባህልና ስርአት ማክበር፣ ቀጣይነት እንዲኖረውና እንዳይጠፋ መንከባከብ፣ ማንነትንም በዘርና በቋንቋ መግለፅ አይደለም!!።

ዘረኝነት:– የራስን ቋንቋ፣ ባህልና ስርአት: ከሌላው ዘርና ቋንቋ፣ ባህልና ስርአት: ከፍ አድርጎ መመልከት፣ የሌላውን ማንቋሸሽና አሳንሶ ማየት፣ ዕውቅና አለመስጠትና ዝቅ አድርጎ መመልከት ነው!!።

ዘረኝነት:– ራስን ከሌላው ለየት አድርጎ መመልከት፣ ለራሱ የሚገባውን ነገረረ ለሌሎቹ የማይገባ ነገር አድርጎ ማሰብ፣ በሌሎች ላይ ግዳጅ የሆነውን ነገር እኔን አይመለከተኝም ብሎ ማሰብ፣ አብሮነትን በመጠየፍ ለብቻ መመገብና ለብቻ መኖር ይገባኛል ማለት፣ በህይወት ተደሳች መሆን እኔ ብቻ ነኝ የሚገባኝ ማለት፣ የራሱን ዕልቅናና ክብር በሌሎች ውርደትና ዝቅተኝነት ላይ መገንባትን፣ የራስን ሀብትና ብልፅግና በሌሎች ድህነት ላይ መገንባትን፣ ሰላምና መረጋጋትን በሌሎች ረብሽና ወከባ ላይ መመስረትን፣ የራስን ህይወት በሌሎች ሞትና መስዋእትነት ላይ ማቆምን ማሰብ ነው!።

وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ

(ሱረቱ አል-ሩም - 22)
ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡

يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَاكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَاكُمْ شُعُوبًا وَقَبَائِلَ لِتَعَارَفُوا ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ

(ሱረቱ አል-ሁጁራት - 13)
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡

"ሁላችሁም ከአደም ናችሁ። አደም ደግሞ ከዐፈር ነው" ነቢዩ ሙሐመድ

"ዐረብ የኾነው ዐረብ ባልኾነው ላይ አላህን በመፍራት ካልሆነ በቀር ብልጫ የለውም" ነቢዩ ሙሐመድ

"እሷ (ዘረኝነት) ጥንብ ናትና ተዏት" ነቢዩ ሙሐመድ

"ክፉ ስራው ወደ ኋላ የጎተተው: ዘሩ ወደፊት አያስቀድመውም" ነቢዩ ሙሐመድ

"ወደ ዘሩ (በዳይም ቢሆን ለማገዝ) የተጣራ፣ ለዘሩ ሲል (በባጢልም ቢሆን) የተጋደለ፣ ለዘሩ ብሎ (ያለ አግባብ) የሞተ ሰው ከኛ አይደለም" ነቢዩ ሙሐመድ
Join us➤ t.me/abuhyder
13. "አልሙተከቢር" (ኩሩ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አልሙተከቢር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ኩራተኛ፡ የኩራት ባለቤት ማለት ነው፡፡ አላህ የሻውን ሰሪ፡ የፈለገውን አድራጊ፡ ፍጹም የበላይ አሸናፊ፡ ስልጣኑ ያልተገደበ ጌታ በመሆኑ "አልሙተከቢር" ይባላል፡፡ የፈለገውን እንደፈለገው ማድረግ ይችላል፡፡ ማንም ቢሆን ለምን? ብሎ ፈቃዱን መቃወም የሚችል ኃይል የለም፡፡ ኩራት በጌታ አላህ ባሕሪ ውስጥ የክብርና የምሉእነት መገለጫ ሲሆን፡ በፍጡር ላይ ግን የበታችነትና የውድቀት ምክንያት ነው፡፡ የጠጣውን ውሃ ከሰዓታት በኋላ ሽንት ሆኖ እንዳይወጣ መቆጣጠር ያልቻለ፤ የበላው ምግብ ከሰዓታት በኋላ ቆሻሻ ሆኖ እንዳይወጣ መቆጣጠር የማይችል አካል እንዴት ሆኖ ይኮራል? እኮ እንዴት? ጌታ አላህ ግን በራሱ የተብቃቃ ኩሩ የሆነ ጌታ ስለሆነ፡ ከመልካም ስራ እንኳ በኢኽላስ የተሰራውን እንጂ ሪያእ (እዩልኝ ስሙልኝ) የተቀላቀለበትን አይቀበልም፡-
አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፈው ሐዲሥ ላይ የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ፡- "አላህ (በሐዲሡል ቁድሲይ ላይ) እንዲህ ይላል፡- እኔ ከተጋሪዎችና ከሚያጋሩብኝም ነገር የተብቃቃሁ ነኝ፡፡ በኔ ላይ ሌላን አካል አጋርቶ አንድን ስራ የሰራ ሰው (በስራው) ማጋራቱንም ሰውየውንም (ወዳጋራብኝ ሰው) እተወዋለሁ" (ሙስሊም)፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አልሙተከቢር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ነው የመጣው፡-
" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23
"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. ጌታችን አላህ "አልሙተከቢር" ስለሆን ኩራት የርሱ መለኮታዊ ባሕሪ መሆኑን እንረዳለን፡-
" وَلَهُ الْكِبْرِيَاءُ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة الجاثية 37
"ኩራትም በሰማያትም በምድርም ለርሱ ብቻ ነው፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።" (ሱረቱል ጃሢያህ 37)፡፡
2. ማንም ሰው ሊኮራ እንደማይገባና ይህንንም የሚፈጽም በዱንያ ውርደት በአኼራ ቅጣት እንደሚገጥመው እንረዳለን፡-
" الَّذِينَ يُجَادِلُونَ فِي آيَاتِ اللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَانٍ أَتَاهُمْ كَبُرَ مَقْتًا عِنْدَ اللَّهِ وَعِنْدَ الَّذِينَ آمَنُوا كَذَلِكَ يَطْبَعُ اللَّهُ عَلَى كُلِّ قَلْبِ مُتَكَبِّرٍ جَبَّارٍ " سورة غافر 35
"እነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር፣ በአላህ ታምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ፣ በጣም ተለቀ፤ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል።" (ሱረቱ-ጋፊር 35)፡፡
" وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ تَرَى الَّذِينَ كَذَبُوا عَلَى اللَّهِ وُجُوهُهُمْ مُسْوَدَّةٌ أَلَيْسَ فِي جَهَنَّمَ مَثْوًى لِلْمُتَكَبِّرِينَ " سورة الزمر 60
"በትንሣኤ ቀንም፣ እነዚያን በአላህ ላይ የዋሹትን፣ ፊቶቻቸው የጠቆሩ ሆነው ታያቸዋለህ፤ በገሀነም ውስጥ ለትዕቢተኞች መኖሪያ የለምን?" (ሱረቱ-ዙመር 60)፡፡
" ادْخُلُوا أَبْوَابَ جَهَنَّمَ خَالِدِينَ فِيهَا فَبِئْسَ مَثْوَى الْمُتَكَبِّرِينَ " سورة غافر 76
"የጀሀነምን በርሮች፣ በውስጧ ዘውታሪዎች ስትሆኑ ግቡ (ይባላሉ)፤ የትዕቢተኞችም መኖሪያ (ጀሀነም) ምን ትከፋ!" (ሱረቱ ጋፊር 76)፡፡
" وَيَوْمَ يُعْرَضُ الَّذِينَ كَفَرُوا عَلَى النَّارِ أَذْهَبْتُمْ طَيِّبَاتِكُمْ فِي حَيَاتِكُمُ الدُّنْيَا وَاسْتَمْتَعْتُمْ بِهَا فَالْيَوْمَ تُجْزَوْنَ عَذَابَ الْهُونِ بِمَا كُنْتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ فِي الْأَرْضِ بِغَيْرِ الْحَقِّ وَبِمَا كُنْتُمْ تَفْسُقُونَ " سورة الأحقاف 20
"እነዚያም የካዱት በእሳት ላይ በሚጋፈጡ ቀም ጣፋጮቻችሁን በአነስተኛይቱ ሕይወታችሁ አሳልፋችሁ በርሷም ተጣቀማችሁ ስለዚህ በምድር ላይ ያለ አግባብ ትኮሩ በነበራችሁትና ታምጡ በነበራችሁት ዛሬ የውርደትን ቅጣት ትመነዳላችሁ (ይባላል)።" (ሱረቱል አሕቃፍ 20)፡፡
እንድንኮራስ የሚያደርገን ምን አለንና? በመሬት ላይ ብንጓዝ የኛን ምልክት እንኳ ላዩዋ ላይ የማናሳርፍ፡ ብንዘል ደግሞ ተራራ የማንደርስ ነን፡-
" وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا إِنَّكَ لَنْ تَخْرِقَ الْأَرْضَ وَلَنْ تَبْلُغَ الْجِبَالَ طُولًا " سورة الإسراء 37
"በምድርም ላይ የተንበጣረርክ ሆነህ አትኺድ፤ አንተ ፈጽሞ ምድርን አትሰረጉድምና፣ በርዝመትም ፈጽሞ ጋራዎችን አትደርስምና።" (ሱረቱል ኢስራእ 37)፡፡
" وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ " سورة لقمان 18
"ጉንጭህንም (በኩራት) ከሰዎች አታዙር፤ በምድርም ላይ ተንጠብርረህ አትኺድ፤ አላህ ተንበጥራሪን፣ ጉረኛን ሁሉ አይወድምና።" (ሱረቱ ሉቅማን 18)፡፡
عن عمرو بن شعيب عن أبيه عن جده عن النبي صلى الله عليه وسلم قال " يحشر المتكبرون يوم القيامة أمثال الذر في صور الرجال يغشاهم الذل من كل مكان فيساقون إلى سجن في جهنم يسمى بولس تعلوهم نار الأنيار يسقون من عصارة أهل النار طينة الخبال " رواه الترمذي. قال أبو عيسى هذا حديث حسن صحيح.
አምሩ ኢብኑ ሹዐይብ ከአባቱ፡ አባቱ ደግሞ ከአያቱ፡ አያቱ ከነቢያችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰምቶ እንዳስተላለፈልን እንዲህ አሉ፡- "ኩራተኞች የቂያም እለት እንደ ቀይ ጉንዳን አናሳ ሁነው ይቀሰቀሳሉ፡፡ ውርደት ከየ-አቅጣጫው ይከባቸዋል፡፡ ቡለስ ወደተባለው ጀሐነም እስር ቤት ይነዳሉ…." (ቲርሚዚይ)፡፡
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ مَسْعُودٍ عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ " لا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ مَنْ كَانَ فِي قَلْبِهِ مِثْقَالُ ذَرَّةٍ مِنْ كِبْرٍ قَالَ رَجُلٌ إِنَّ الرَّجُلَ يُحِبُّ أَنْ يَكُونَ ثَوْبُهُ حَسَنًا وَنَعْلُهُ حَسَنَةً قَالَ إِنَّ اللَّهَ جَمِيلٌ يُحِبُّ الْجَمَالَ الْكِبْرُ بَطَرُ الْحَقِّ وَغَمْطُ النَّاسِ" رواه مسلم .
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን ደግሞ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "በልቡ ላይ የጎመን ዘር ፍሬ ያህል ኩራት ያለበት ሰው ጀነት አይገባም፡፡ አንድ ሰውም መልክተኛውን፡- ሰውየው ልብሱና ጫማው ጥሩ እንዲሆንለት ይፈልጋል (ይሄ ኩራት ነውን?) ሲል፡- እሳቸውም፡- አላህ ውብ ጌታ ነው ውበትንም ይወዳል፡፡ ኩራት ግን ሐቅን አለመቀበልና ሰውን በንቀት መመልከት ነው" በማለት መለሱለት (ሙስሊም)፡፡
3. አላህንም ስንገዛው በመተናነስና በመዋረድ ስሜት ዝቅ ብለን፡ ከኩራት ርቀን መሆን እንዳለበት እንማራለን፡-
" إِنَّ الَّذِينَ عِنْدَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ " سورة الأعراف 206
"እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፤ ያወድሱታልም፤ ለርሱም ብቻ ይሰግዳሉ።" (ሱረቱል አዕራፍ 206)፡፡
" وَلِلَّهِ يَسْجُدُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَمَا فِي الْأَرْضِ مِنْ دَابَّةٍ وَالْمَلَائِكَةُ وَهُمْ لَا يَسْتَكْبِرُونَ " سورة النحل 49
"ለአላህም በሰማያት ያለው ከተንቀሳቃሻም በምድር ያለው ሁሉ መላክትም ይሰግዳሉ፤ እነርሱም አይኮሩም።" (ሱረቱ-ነሕል 49)፡፡
" وَلَهُ مَنْ فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَمَنْ عِنْدَهُ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَلَا يَسْتَحْسِرُونَ " سورة الأنبياء 19
"በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉም የርሱ ነው፤ እርሱ ዘንድ ያሉትም (መላእክት) እርሱን ከመገዛት አይኮሩም፤ አይሰለቹምም።" (ሱረቱል አንቢያእ 19)፡፡
" وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ " سورة غافر 60
"ጌታችሁም አለ፦ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና፤ እነዚያም እኔን ከመገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ሆነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ።" (ሱረቱ ጋፊር 60)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
14. "አል-ዐዚዝ" (አሸናፊ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ዐዚዝ" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉም፡- አሸናፊና የላቀ ማለት ነው፡፡ አላህ በነገሮቹ ሁሉ የበላይ አሸናፊ ነው፡-
" وَقَالَ الَّذِي اشْتَرَاهُ مِنْ مِصْرَ لِامْرَأَتِهِ أَكْرِمِي مَثْوَاهُ عَسَى أَنْ يَنْفَعَنَا أَوْ نَتَّخِذَهُ وَلَدًا وَكَذَلِكَ مَكَّنَّا لِيُوسُفَ فِي الْأَرْضِ وَلِنُعَلِّمَهُ مِنْ تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ وَاللَّهُ غَالِبٌ عَلَى أَمْرِهِ وَلَكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ " سورةِ يُوسُف 21
"ያም ከምስር የገዛው ሰው ለሚስቱ፦ መኖሪያውን አክብሪ፤ ሊጠቅመን ወይም ልጅ አድርገን ልንይዘው ይከጀላልና፤ አላት፤ እንደዚሁም ለዩሱፍ (ገዥ ልናደርገውና) የሕልሞችንም ፍች፣ ልናስተምረው በምድር ላይ አስመቸነው፤ አላህም በነገሩ ላይ አሸናፊ ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም።" (ሱረቱ ዩሱፍ 21)፡፡
" إِنَّ الَّذِينَ يُحَادُّونَ اللَّهَ وَرَسُولَهُ أُولَئِكَ فِي الْأَذَلِّينَ * كَتَبَ اللَّهُ لَأَغْلِبَنَّ أَنَا وَرُسُلِي إِنَّ اللَّهَ قَوِيٌّ عَزِيزٌ " سورة المجالة 21-20
"እነዚያ አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩት እነዚያ በጣም በወራዶቹ ውስጥ ናቸው።አላህ ፦ እኔ በእርግጥ አሸንፋለሁ፤ መልክተኞቼም (ያሸንፋሉ ሲል)፤ ጽፏል። አላህ ብርቱ አሸናፊ ነውና።" (ሱረቱል ሙጃደላህ 20-21)፡፡
አሸናፊነት የጌታችን ባሕሪ ነው፡-
" الَّذِينَ يَتَّخِذُونَ الْكَافِرِينَ أَوْلِيَاءَ مِنْ دُونِ الْمُؤْمِنِينَ أَيَبْتَغُونَ عِنْدَهُمُ الْعِزَّةَ فَإِنَّ الْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا " سورة النساء 139
"እነዚያ ከምእመናን ሌላ ከሐዲዎችን ወዳጆች አድርገው የሚይዙ፣ እነሱ ዘንድ ልቅናን ይፈልጋሉን? ልቅናም ሁሉ ለአላህ ብቻ ነው።" (ሱረቱ-ኒሳእ 139)፡፡
" وَلَا يَحْزُنْكَ قَوْلُهُمْ إِنَّ الْعِزَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا هُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ " سورة يونس 65
"ንግግራቸውም አያሳዝንህ፡፡ ኀይል ሁሉ በሙሉ የአላህ ብቻ ነውና፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 65)፡፡
" مَنْ كَانَ يُرِيدُ الْعِزَّةَ فَلِلَّهِ الْعِزَّةُ جَمِيعًا إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ الطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّالِحُ يَرْفَعُهُ وَالَّذِينَ يَمْكُرُونَ السَّيِّئَاتِ لَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ وَمَكْرُ أُولَئِكَ هُوَ يَبُورُ " سورة فاطر 10
"ማሸነፍን የሚፈልግ የሆነ ሰው፣ አሸናፊነት ለአላህ ብቻ ነው፤ (እርሱን በመግገዛት ይፈልገው)፤ መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል፤ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፤ እነዚያም መጥፎ ሥራዎችን የሚዶልቱ፣ ለነሱ ብርቱ ቅጣት አላቸው፤ የነዚያም ተንኮል እርሱ ይጠፋል።" (ሱረቱ ፋጢር 10)፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ዐዚዝ" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ 92 ጊዜ ተጠቅሷል፡፡
" هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة آل عمران 6
"እርሱ ያ በማሕፀኖች ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነዉ። ከርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤ አሸናፊዉ ጥበበኛዉ ነዉ።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 6)፡፡
" وَالشَّمْسُ تَجْرِي لِمُسْتَقَرٍّ لَهَا ذَلِكَ تَقْدِيرُ الْعَزِيزِ الْعَلِيمِ " سورة يس 38
"ፀሐይም ለርሷ ወደሆነው መርጊያ ትሮጣለች ይህ የአሸናፊው የዐዋቂው አምላክ ውሳኔ ነው።" (ሱረቱ ያሲን 38)፡፡
" بِنَصْرِ اللَّهِ يَنْصُرُ مَنْ يَشَاءُ وَهُوَ الْعَزِيزُ الرَّحِيمُ " سورة الروم 5
"በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ) የሚሻውን ሰው ይረዳል፥ እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው።" (ሱረቱ-ሩም 5)፡፡
ሐ. ከዚህ መለኮታዊ ስም የምንማረው፡-
1. አላህ የእልቅና ባለቤት መሆኑን፡-
" سُبْحَانَ رَبِّكَ رَبِّ الْعِزَّةِ عَمَّا يَصِفُونَ " سورة الصافات 180
"የማሸነፍ ጌታ የሆነው ጌታህ ከሚሉት ሁሉ ጠራ" (ሱረቱ-ሷፍፋት 180)፡፡
2. አማኝ ባሪያዎቹን እንደሚያልቅ፡- በሱ አምላክነት አምነው በትእዛዙ የተመሩ ምእመናን ባሮቹን በከሀዲያን ላይ አሸናፊ ያደርጋቸዋል፡፡ ልቅናንም ይለግሳቸዋል፡፡
" يَقُولُونَ لَئِنْ رَجَعْنَا إِلَى الْمَدِينَةِ لَيُخْرِجَنَّ الْأَعَزُّ مِنْهَا الْأَذَلَّ وَلِلَّهِ الْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَكِنَّ الْمُنَافِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ " سورة المنافقون 8
"ወደ መዲና ብንመለስ አሸናፊው ወራዳውን በእርግጥ ከርሷ ያወጣል ይላሉ፤ አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና፣ ለምእምናን ነው፤ ግን መናፍቆች አያውቁም።" (ሱረቱል ሙናፊቁን 8)፡፡
" قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَنْ تَشَاءُ وَتَنْزِعُ الْمُلْكَ مِمَّنْ تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَنْ تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَنْ تَشَاءُ بِيَدِكَ الْخَيْرُ إِنَّكَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة آل عمران 26
"(ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- የንግሥና ባለቤት የሆንክ አላህ ሆይ! ለምትሻዉ ሰዉ ንግሥናን ትሰጣለህ፤ ከምትሻዉም ሰዉ ንግስናን ትገፍፋለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታልቃለህ፤ የምትሻዉንም ሰዉ ታዋርዳለህ። መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና።" (ሱረቱ አለ-ዒምራን 26)፡፡
3. በዚህ ስም አላህን መለመን እንደሚቻል፡-
" رَبَّنَا وَابْعَثْ فِيهِمْ رَسُولًا مِنْهُمْ يَتْلُو عَلَيْهِمْ آيَاتِكَ وَيُعَلِّمُهُمُ الْكِتَابَ وَالْحِكْمَةَ وَيُزَكِّيهِمْ إِنَّكَ أَنْتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ " سورة البقرة 129
"«ጌታችን ሆይ! በውስጣቸውም ከነሱው የኾነን መልክተኛ በነርሱ ላይ አንቀጾችህን የሚያነብላቸውን መጽሐፍንና ጥበብንም የሚያስተምራቸውን (ከክህደት) የሚያጠራቸውንም ላክ፤ አንተ አሸናፊው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» " (ሱረቱል በቀራህ 129)፡፡
4. ቅዱስ ቁርኣን የአሸናፊው አላህ ቃል በመሆኑ፡ ከፊቱም ሆነ ከኋላው ውሸት ሊቀርበው የማይችል አሸናፊ አድርጎታል፡-
" إِنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا بِالذِّكْرِ لَمَّا جَاءَهُمْ وَإِنَّهُ لَكِتَابٌ عَزِيزٌ * لَا يَأْتِيهِ الْبَاطِلُ مِنْ بَيْنِ يَدَيْهِ وَلَا مِنْ خَلْفِهِ تَنْزِيلٌ مِنْ حَكِيمٍ حَمِيدٍ " سورة فصلت 42-41
"እነዚያ በቁርአን፣ እርሱ አሸናፊ መጽሐፍ ሲሆን፣ በመጣላቸው ጊዜ የካዱት (ጠፊዎች ናቸው)።ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነውጌታ የተወረደ ነው።" (ሱረቱ ፉሲለት 41-42)፡፡
15. "አል-ጀባር"
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ጀባር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ኃያልና ጠጋኝ ማለት ነው፡፡ ሁሉም ነገር በኃያልነቱ ስር የተንበረከከ በመሆኑ አላህ "አል-ጀባር" ይባላል፡፡ ዳካማዎችን ጉልበት በመለገስ የሚጠግን፣ የተሰበረ ልብን ተስፋ በመሙላት የሚጠግን፣ ድኃን በማብቃቃት የሚጠግን፣ ህመምተኞችን በመፈወስ የሚጠግን፣አማኞችን በሚደርሰባቸው ሙሲባ (መከራ) ጽናትን በመለገስ የሚጠግን በመሆኑ አላህ "አል-ጀባር" ይባላል፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ጀባር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቅሷል፡-
" هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ " سورة الحشر 23
"እርሱ አላህ ነው፤ ያ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፤ ከጉድለት ሁሉ የጠራው፣ የሰላም ባለቤቱ ጸጥታን ሰጪው ባሮቹን ጠባቂው አሸናፊው፣ ኀያሉ ኩሩው ነው። አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ።" (ሱረቱል ሐሽር 23)፡፡
አላህ ኃያልና የባሮቹን ድክመት ጠጋኝ ጌታ በመሆኑ አንድ ሙስሊም በሩኩእና በሱጁድ ላይ ሲሆን ተከታዩን ዱዓ ያደርጋል፡- "ሱብሓነ ዚል-ጀበሩቲ ወል-መለኩቲ ወል-ኪብሪያኢ ወል-ዐዘማህ" (አቡ ዳዉድ 873፣ ነሳኢይ 1131፣ አሕመድ 23980)፡፡ ትርጉሙም፡- (የኃያልነት፣ የግዛት፣ የኩራትና የታላቅነት ባለቤት የሆነው አላህ ከጉድለት ሁሉ ጠራ) ማለት ነው፡፡
እንዲሁም በሁለቱ ሱጁዶች መሓል ሲቀመጥ እንዲህ ይላል፡- "አላሁምመ-ኢግፊር ሊ፣ ወርሐምኒ፣ ወጅቡርኒ፣ ወህዲኒ፣ ወርዙቅኒ" (ቲርሚዚይ)፡፡ ትርጉሙም፡- (አላህ ሆይ! ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፣ እዘንልኝም፣ ጠግነኝም፣ ቅኑን ጎዳና ምራኝ፣ ሲሳይንም ለግሰኝ) ማለት ነው፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምህርት፡-
1. መተናነስ እንደሚገባን፡- ፍጹም ኃያልነት የጌታ አላህ ብቻ በመሆኑ በምድር ላይ ማንም በማንም ላይ የበላይ መሆንን ከፈለገ አላህ ያዋርደዋል፡፡ የሐቅንም መንገድ እንዳይቀበል ልቡ ይታሸጋል፡-
" الَّذِينَ يُجَادِلُونَ فِي آيَاتِ اللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَانٍ أَتَاهُمْ كَبُرَ مَقْتًا عِنْدَ اللَّهِ وَعِنْدَ الَّذِينَ آمَنُوا كَذَلِكَ يَطْبَعُ اللَّهُ عَلَى كُلِّ قَلْبِ مُتَكَبِّرٍ جَبَّارٍ " سورة غافر 35
"እነዚያ፤ የመጣላቸው አስረጅ ሳይኖር፣ በአላህ ታምራቶች የሚከራከሩ (ክርክራቸው) አላህ ዘንድና እነዚያም አመኑት ዘንድ መጠላቱ፣ በጣም ተለቀ፤ እንደዚሁ አላህ በኩሩ ጨካኝ (ሰው) ልብ ሁሉ ላይ ያትማል።" (ሱረቱ ጋፊር 35)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
እምነት_ምንድን_ነው_ክፍል_1_ኡስታዝ_አቡ_ሀይደር.mp3
23.7 MB
እምነት ምንድን ነው ክፍል 1
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
http://goo.gl/AgKeWg

Join us➤ t.me/abuhyder
ለምን ሴቶች በጀሀነም በዙ?
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ውዳሴና ሰላም፡ የሰላም አለቃና መምህር ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ ይሁን፡፡ ድልና የበላይነት ሐቅን ለማንገስና ሀሰትን ለማርከስ፡ በደልን አጥፎቶ ፍትህን ለማስፈን ዕውቀታቸውን፣ ንብረታቸውን፣ ጉልበታቸውን፣ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን መስዋእት በማድረግ ለሚታገሉት ይሁን፡፡
عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، خَرَجَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فِي أَضْحًى أَوْ فِطْرٍ إِلَى المُصَلَّى، ثُمَّ انْصَرَفَ، فَوَعَظَ النَّاسَ، وَأَمَرَهُمْ بِالصَّدَقَةِ، فَقَالَ: «أَيُّهَا النَّاسُ، تَصَدَّقُوا»، فَمَرَّ عَلَى النِّسَاءِ، فَقَالَ: «يَا مَعْشَرَ النِّسَاءِ، تَصَدَّقْنَ، فَإِنِّي رَأَيْتُكُنَّ أَكْثَرَ أَهْلِ النَّارِ» فَقُلْنَ: وَبِمَ ذَلِكَ يَا رَسُولَ اللَّهِ؟ قَالَ: «تُكْثِرْنَ اللَّعْنَ، وَتَكْفُرْنَ العَشِيرَ، …» رواه البخاري ومسلم.
አቢ ሰዒድ አል-ኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በዒደል አድሓ (ዒደል ፊጥር) ወደ መስገጃው ስፍራ ሄዱ፡፡ ከዛም ወደ ህዝቡ በመዞር ሰዎችን መከሯቸው፡፡ ሶደቃንም (ልገሳ) እንዲያወጡ አዘዟቸው፡፡ እንዲህም አሉ፡- ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! ሶደቃን አብዙ››፡፡ በሴቶች በኩልም አለፉና፡- ‹‹እናንተ ሴቶች ሆይ! ሶደቃን አብዙ፡፡ እኔ ከጀሀነም ሰዎች አብዛኛዎቹ ሆናችሁ አይቻችኋለሁና›› አሉ፡፡ ሴቶቹም፡- ‹‹አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! ይህ የሆነው በምን ምክንያት ነው?›› ብለው ጠየቁ፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹እርግማንን ታበዛላችሁ፣ የባለቤታችሁን ውለታ ትክዳላችሁ...›› አሉ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
ይህንን ነቢያዊ ሐዲሥ መሰረት በማድረግ አንዳንድ ክርስቲያን ወገኖች፡ በእስልምና አብዛኞቹ መስሊም ሴቶች ጀሀነም እንደሚገቡ ይታመናል በማለት የተሳሳተ ምልክታ ይዘው ሌላውንም ለማሳሳት ይሞክራሉ፡፡ ጭራሹኑ የሴቶችን የመዳን ተስፋ ያደበዝዘዋልም ሲሉ ይከሳሉ፡፡ ከኛ ሙስሊሞች ደግሞ የሚጠበቀው አገነዛዘቡ የተበደለውን ሐዲሥ የተቃና ማድረግ ስለሆነ፡ እውነትን ለሚፈልግ ሰው ይኸው ትክክለኛውን ማብራሪያ እንካችሁ ብለናል፡-
1ኛ. በሐዲሡ ላይ የተቀመጠው ኃይለ ቃል ‹‹ሴቶች›› የሚል እንጂ ‹ሙስሊም ሴቶች› የሚል እንዳልሆነ ልብ ይበሉ፡፡ ‹‹ሴት›› ከተባለ የአደምን ዘሮች፡ የሐዋእን ልጆች በጠቅላላ የሚመለከት እንጂ፡ ሙስሊሞችን ብቻ የሚመለከት አይደለም፡፡ የመጀመሪያው ስህተት እሱ ነውና፡፡ በሌላም ሐዲሥ ላይ እንደተነገረው፡- ‹‹እኔ እሳትን ተመለከትሁ፡፡ አብዝኃኛው ነዋሪዎቿ ሴቶች ናቸው›› ይላል እንጂ ‹ሙስሊም ሴቶች› አይልም፡፡
2ኛ. ምክንያቱስ ምንድነው? ብለንም ከጠየቅን፡ መልስ የሚሆነው፡- ከላይ በሐዲሡ ላይ እንደተገለጸው ሁለት የኃጢአት ባሕሪዎች እነሱ ላይ ጎልቶ መታየቱ ነው፡፡ እሱም፡- ‹‹እርግማንን ማብዛት›› እና ‹‹የባልን ውለታ መካድ›› ናቸው፡፡ ሴት ሆና መፈጠሯ አይደለም ችግር ያመጣባት፡፡ ሙስሊም መሆኗ አይደለም እንቅፋት የሆነባት፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ኃጢአት ላይ መዘፈቋ እንጂ!፡፡
ይህንን ስራ ‹እርግማንና ውለታ መካድ› ወንዱም ሊሰራው ይችላል፡፡ የሴቶች የግል መለያቸው አይደለም፡፡ ሆኖም በብዛት ጎልቶ የሚታየው እነሱ ላይ ነውና፡፡
አንድ ሚስት ባለቤቷ ለብዙ ጊዜያት መልካም ሲውልላት ቆይቶ አንድ ቀን እሷን የሚጎዳ ነገር ቢፈጽም፡- እስከ-ዛሬ ምን አድርገህልኝ ታውቃለህ? በማለት ያለፉ ጣፋጭ ዘመናትን ትክዳቸዋለች (አላህ በእዝነቱ የጠበቃት ስትቀር)፡፡
3ኛ. ታዲያ መፍትሄው ምንድነው ምንድነው? ብለን ጥያቄ ማንሳቱ አግባብነት አለው፡፡ ነቢዩ ሙሐመድም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህንን ለሴቶች የተናገሩት፡ ለነሱ ከነፍሳቸው በላይ በማዘን ከወዲሁ እንዲጠነቀቁ እንጂ፡ ተስፋ ለማስቆረጥ አይደለም፡፡ ደካማ ጎኑ የተነገረው ሰው አስተዋይ ከሆነ፡ ድክመቱን ለመሸፈን ይጥራል እንጂ ተስፋ አይቆርጥም፡፡ በዚህ ሐዲሥ ላይ ደግሞ ችግሩ ብቻ ሳይሆን የተወሳው መፍትሄውም ጭምር ነው፡፡ መፍትሄውም፡- ሶደቃን አብዙ ብለዋል፡፡ አዎ! ሶደቃ ኃጢአትን ያጠፋልና፡፡
ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ(ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደነገረን የአላህ መልክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "…ሶደቃህ ውሀ እሳትን እንደሚያጠፋው ኃጢአትን ያጠፋል…" (ሶሒሑ ተርጊብ ወት-ተርሒብ 866)፡፡
ደግሞም እህቶች ሆይ! ባለቤቶቻችሁን በውለታቸው አመስጋኝ ሚስቶች ሁኑ፡፡ ከመራገምም እራሳችሁን ጠብቁ፡፡ ሐዲሡ፡- ‹ሙስሊም ተሳዳቢም ተራጋሚም አይደለም› ይላልና፡፡
አላህን የምትፈራ ሙስሊም ሴት እራሷን ከነዚህ ሁለት መጥፎ ባሕሪያት ማራቅና ማግለል ትችላለች፡፡ እሱም፡- ሃይማኖቷን በአግባቡ በመማር፣ እንዲሁም ጥሩ አርአያ መሆን ከሚችሉ እህቶቿ ጋር ወዳጅነትን በመመስረት፡፡ ስለዚህ ሐዲሡ ተስፋ አስቆራጭ ሳይሆን ከወዲሁ ጥንቃቄ በማድረግ የተነገራችሁን ነገር በማስተዋል እንድትፈጽሙ ለናንተ በማሰብና በመጨነቅ የተሰጠ ነቢያዊ ትምህርት ነው፡፡ (ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለሏህ)፡፡
4ኛ. ትልቁ ቁም ነገር እዚህ ጋር ነው፡፡ አንዲት ሙስሊም ሴት በኃጢአቷ ምክንያት አላህ በቀብር ቅጣት፣ ወይም በቂያም ቀን ጭንቀት፣ ወይም በነቢያችን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሸፋዐህ (ምልጃ) ያ ካልሆነም ከራሱ በመነጨ ራሕመት ልማርሽ ባይላትና በእሳት ሊቀጣት እንኳ ቢወስን፡ በእሳት ውስጥ ዘውታሪ አይደለችም አትሆንምም፡፡ የጥፋቷን ያህል ተቀጥታ ወደ ጀነት መመለሷ የማይቀር ነው፡፡ በጀሀነም መዘውተር የከሀዲያን እንጂ የሙስሊሞች አይደለምና፡፡ ጀነትን ከሙስሊም ውጪ ማንም አይገባትምና፡፡ ተከታዩ ሐዲሥ ይህን ይገልጻል፡-
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ: كُنَّا مَعَ النَّبِيِّ فِي قُبَّةٍ، فَقَالَ: «أَتَرْضَوْنَ أَنْ تَكُونُوا رُبُعَ أَهْلِ الجَنَّةِ» قُلْنَا: نَعَمْ، قَالَ: «أَتَرْضَوْنَ أَنْ تَكُونُوا ثُلُثَ أَهْلِ الجَنَّةِ» قُلْنَا: نَعَمْ، قَالَ: «أَتَرْضَوْنَ أَنْ تَكُونُوا شَطْرَ أَهْلِ الجَنَّةِ» قُلْنَا: نَعَمْ، قَالَ: «وَالَّذِي نَفْسُ مُحَمَّدٍ بِيَدِهِ، إِنِّي لَأَرْجُو أَنْ تَكُونُوا نِصْفَ أَهْلِ الجَنَّةِ، وَذَلِكَ أَنَّ الجَنَّةَ لاَ يَدْخُلُهَا إِلَّا نَفْسٌ مُسْلِمَةٌ،
ዐብዱላህ ኢብኒ መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላል፡- ከነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጋር (በሚና) ድንኳን ስር እያለን እንዲህ አሉን፡- ‹‹የጀነት ሰዎች ሩብ እናንተ ብትሆኑ ትወዳላችሁን?›› አዎን ! አልናቸው፡፡ በድጋሚ ‹‹የጀነት ሰዎች 1/3 እናንተ ብትሆኑ ትወዳላችሁን?›› ሲሉን፡ አዎን! አልናቸው፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ ‹‹የጀነት ሰዎች ግማሹ እናንተ ብትሆኑ ትወዳላችሁን?›› ሲሉን አዎን! አልናቸው፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹የኔ ነፍስ
በእጁ በሆነችው በአላህ እምላለሁ፡፡ እናንተ የጀነት ሰዎች ግማሹ እንደምትሆኑ ባለ ሙሉ ተሰፋ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ጀነትን ሙስሊም የሆነ ነፍስ እንጂ ሌላው አይገባትምና›› አሉ፡፡ (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡
5ኛ. እነዚህ ክርስቲያን ወገኖች እንደሚሉት ‹‹በጀሀነም ውስጥ ሴቶች በዝተው አየሁ›› የሚለው ሐዲሥ ፡ ሴቶችን ለተውበትና ለመልካም ስራ ከማነሳሳት ይልቅ ተስፋ የሚያስቆርጥ ከሆነ (አይደለም እንጂ)፡ ታዲያ በእናንተ መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የሐብታሞችን ገነት የመግባት ተስፋ የሚያሟጥጥ አነጋገርን ምን ልትሉት ነው?፡፡ አንድ ሐብታም ወደ መንግስተ ሰማያት መግባትን ፈልጎ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ በጠየቀው ጊዜ የኢየሱስ ምላሽ ምን እንደነበር ከመጽሐፉ እናንብብ፡-
‹‹እነሆም፥ አንድ ሰው ቀርቦ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ላድርግ? አለው። እርሱም። ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም የሆነ አንድ ነው፤ ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትእዛዛትን ጠብቅ አለው እርሱም። የትኞችን? አለው። ኢየሱስም። አትግደል፥ አታመንዝር፥ አትስረቅ፥ በሐሰት አትመስክር፥ አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።
ጐበዙም። ይህንማ ሁሉ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአለሁ፥ ደግሞስ የሚጐድለኝ ምንድር ነው? አለው። ኢየሱስም። ፍጹም ልትሆን ብትወድ፥ ሂድና ያለህን ሸጠህ ለድሆች ስጥ፥ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፥ መጥተህም ተከተለኝ አለው። ጐበዙም ይህን ቃል በሰማ ጊዜ ብዙ ንብረት ነበረውና እያዘነ ሄደ። ኢየሱስም ለደቀ መዛሙርቱ። እውነት እላችኋለሁ፥ ለባለጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ጭንቅ ነው። ዳግመኛም እላችኋለሁ፥ ባለጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢገባ ይቀላል አለ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው እጅግ ተገረሙና። እንኪያስ ማን ሊድን ይችላል? አሉ። ኢየሱስም እነርሱን ተመልክቶ። ይህ በሰው ዘንድ አይቻልም በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል አላቸው።›› (የማቴዎስ ወንጌል ምዕ 19 ቁ 16-26)፡፡
ስለዚህ ሐብታም ክርስቲያኖች የግመልን በመርፌ መግባት ተስፋ ያድርጉ ወይስ…?
6ኛ. በመጨረሻም እህቶቼ ሆይ! እነዚህን የጌታችሁን ምክር ስሙና በስራ ላይ አውሉት፡፡ መዳንን ከፈለጋችሁ፡፡
"ከወንድ ወይንም፣ ከሴት፣ እርሱ አማኝ ሆኖ ከበጎ ሥራዎች አንዳች የሚሠራም ሰው እነዚያ ገነትን ይገባሉ፤ በተምር ፍሬ ላይ ያለችን ነጥብ ያህል እንኳ አይበደሉም።" (ሱረቱ-ኒሳእ 124)፡፡
"ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፤ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።" (ሱረቱ-ነሕል 97)፡፡
"መጥፎን የሠራ ሰው፣ ብጤዋን እንጅ አይመነዳም፤ እርሱ መእምን ሆኖ ከወንድ ወይም ከሴት በጎን የሠራም ሰው፣ እነዚያ ገነትን ይገባሉ፤ በርሷ ውስጥ ያለ ቁጥጥር ይመገባሉ።" (ሱረቱ ጋፊር (ሙእሚን) 40)፡፡
አምላካችን አላህ ሆይ! በኢስላም ላይ ጽናትን፣ በሞት ጊዜ ሸሀደተይንን፣ በቀብር ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽን ወፍቀን፡፡ በራሕመትህ ከቂያም ቀን ንዳድ እና ከእሳትም ጠብቀን፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
እምነት ምንድነው ክፍል 2
ኡስታዝ አቡ ሀይደር
እምነት ምንድን ነው ክፍል 2
☞በኡስታዝ አቡ ሀይደር

Mp3 ዳውሎድ ለማድረግ
http://goo.gl/AgKeWg

Join us➤ t.me/abuhyder
16-17 "አል-ቀሓር"፣"አል-ቃሒር" (የበላይ አሸናፊ)
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ቀሓር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉሙ፡- ፍጹም የበላይ አሸናፊ ማለት ነው፡፡ "አል-ቃሒር" ለሚለው መለኮታዊ ስም የsuperlative degree form ነው፡፡ ጌታ አላህ ምንም ነገር የማያቅተው የፈለገውን ማጥፋት የፈለገውን ማዳን ስለሚችል "አል-ቀሓር" ተብሎ ይጠራል፡-
" وَلَا يَحْسَبَنَّ الَّذِينَ كَفَرُوا سَبَقُوا إِنَّهُمْ لَا يُعْجِزُونَ " سورة الأنفال 59
"እነዚያም የካዱት (ከአላህ ቅጣት) ያመለጡ መሆናቸውን አያስቡ፤ እነሱ አያቅቱምና።" (ሱረቱል አንፋል 59)፡፡
" أَوَلَمْ يَسِيرُوا فِي الْأَرْضِ فَيَنْظُرُوا كَيْفَ كَانَ عَاقِبَةُ الَّذِينَ مِنْ قَبْلِهِمْ وَكَانُوا أَشَدَّ مِنْهُمْ قُوَّةً وَمَا كَانَ اللَّهُ لِيُعْجِزَهُ مِنْ شَيْءٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ إِنَّهُ كَانَ عَلِيمًا قَدِيرًا " سورة فاطر 44
"በምድር ላይ አይኼዱምና የነዚያን ከነርሱ በፊት የነበሩትን ሰዎች መጨረሻ እንዴት እንደነበረ አይመለከቱምን? ከነርሱም በኀይል የበረቱ ነበሩ፤ አላህም በሰማያትም ሆነ በምድር ውስጥ ምንም ነገር የሚያቅተው አይደለም፤ እርሱ ዐዋቂ ቻይ ነውና።" (ሱረቱ ፋጢር 44)፡፡
አመጸኞችን በቅጣት ለማጥፋት ከፈለገ የውሳኔ ቃሉ ተፈጻሚ ከመሆን የሚያግደው ምንም ነገር የለም፡፡ ህይወትና ሞት፣ ሀብትና ድህነት፣ ስልጣንና ሹመት በእጁ ነው፡፡ ለሚፈልገው በመስጠት ማክበር፡ ከሚፈልገው ላይ ደግሞ በመቀማት ማዋረድ ይችላል፡፡ምክንያቱም እሱ "አል-ቀሓር" ነውና፡-
" وَأَنَّهُ أَهْلَكَ عَادًا الْأُولَى * وَثَمُودَ فَمَا أَبْقَى * وَقَوْمَ نُوحٍ مِنْ قَبْلُ إِنَّهُمْ كَانُوا هُمْ أَظْلَمَ وَأَطْغَى * وَالْمُؤْتَفِكَةَ أَهْوَى * فَغَشَّاهَا مَا غَشَّى " سورة النجم 54-50
"እነሆ እርሱም የፊተኛይቱን ዓድ አጥፍቷል። ሠሙድንም፣ (አጥፍቷል)፤ አላስቀረምም። በፊትም የኑሕን ሕዝቦች (አጥፍቷል)፤ እነሱ በጣም በደለኞችና እጅግ የጠመሙ እነሱ ነበሩና። የተገለበጠችውን ከተማ ደፋ። ያለበሳትንም አለበሳት።" (ሱረቱ-ነጅም 50-54)፡፡
"أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِعَادٍ * إِرَمَ ذَاتِ الْعِمَادِ * الَّتِي لَمْ يُخْلَقْ مِثْلُهَا فِي الْبِلَادِ * وَثَمُودَ الَّذِينَ جَابُوا الصَّخْرَ بِالْوَادِ * وَفِرْعَوْنَ ذِي الْأَوْتَادِ * الَّذِينَ طَغَوْا فِي الْبِلَادِ * فَأَكْثَرُوا فِيهَا الْفَسَادَ * فَصَبَّ عَلَيْهِمْ رَبُّكَ سَوْطَ عَذَابٍ * إِنَّ رَبَّكَ لَبِالْمِرْصَادِ " سورة الفجر 14-6
"ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታዉቅምን? በኢረም፣ በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፤በዚያች ብጤዋ በአገሮች ዉስጥ ያልተፈጠረ በሆነችዉ፤በሰሙድም፣ በእነዚያ በሸለቆዉ ቋጥኝን የቆረጡ በሆኑት።፤በፈርዖንም ባለ ችካሎች በሆነዉ፣በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፣ በዕርሷም ዉስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሠራ አታዉቅምን?) በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸዉ። ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነዉና።" (ሱረቱል ፈጅር 6-14)፡፡
ለ. አመጣጡ፡-
"አል-ቀሓር" የሚለው መለኮታዊ ስም በቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ስድስት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ በጣም የሚገርመው በስድስቱም ስፍራዎች ላይ ከአንድነቱ ጋር ነው ተያይዞ የመጣው፡፡ ይህ የሚያመላክተው በትክክልም እሱ "አል-ቀሓር" መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም፡- አንድን ነገር ብቻውን የተወጣ አካል ነው "አል-ቀሓር" (አሸናፊ) የሚባለው፡-
" يَا صَاحِبَيِ السِّجْنِ أَأَرْبَابٌ مُتَفَرِّقُونَ خَيْرٌ أَمِ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ " سورة يوسف 39
"የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን ወይንስ አሸናፊው አንዱ አላህ?" (ሱረቱ ዩሱፍ 39)፡፡
" قُلْ مَنْ رَبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ قُلْ أَفَاتَّخَذْتُمْ مِنْ دُونِهِ أَوْلِيَاءَ لَا يَمْلِكُونَ لِأَنْفُسِهِمْ نَفْعًا وَلَا ضَرًّا قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الْأَعْمَى وَالْبَصِيرُ أَمْ هَلْ تَسْتَوِي الظُّلُمَاتُ وَالنُّورُ أَمْ جَعَلُوا لِلَّهِ شُرَكَاءَ خَلَقُوا كَخَلْقِهِ فَتَشَابَهَ الْخَلْقُ عَلَيْهِمْ قُلِ اللَّهُ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ " سورة الرعد 16
"የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው? በላቸው፤ አላህ ነው በል፤ ለነፍሶቻቸው ጥቅምንም ጉዳትንም የማይችሉን ረዳቶች ከርሱ ሌላ ያዛችሁን? በላቸው፤ ዕውርና የሚያይ ይተካከላሉን? ወይስ ጨለማዎችና ብርሃን ይተካከላሉን? ወይስ ለአላህ እንደርሱ አፈጣጠር የፈጠሩን ተጋሪዎች አደረጉለትና ፍጥረቱ በነሱ ላይ ተመሳሰለባቸውን? በል፤ አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፤ እርሱም አንዱ አሸናፊው ነው በል።" (ሱረቱ-ረዕድ 16)፡፡
" يَوْمَ تُبَدَّلُ الْأَرْضُ غَيْرَ الْأَرْضِ وَالسَّمَاوَاتُ وَبَرَزُوا لِلَّهِ الْوَاحِدِ الْقَهَّارِ " سورة إبراهيم 48
"ምድር በሌላ ምድር የምትለወጥበትን ሰማያትም (እንደዚሁ) አንድ አሸናፊ ለሆነው አላህም (ፍጡራን ሁሉ) የሚገለጹበትን ቀን (አስታውሱ)።" (ኢብራሂም 48)፡፡
" قُلْ إِنَّمَا أَنَا مُنْذِرٌ وَمَا مِنْ إِلَهٍ إِلَّا اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ " سورة ص 65
"«እኔ አስፈራሪ ብቻ ነኝ፡፡ ኀያል አንድ ከኾነው አላህ በቀር ምንም አምላክ የለም» በላቸው፡፡" (ሷድ 65)፡፡
" لَوْ أَرَادَ اللَّهُ أَنْ يَتَّخِذَ وَلَدًا لَاصْطَفَى مِمَّا يَخْلُقُ مَا يَشَاءُ سُبْحَانَهُ هُوَ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ " سورة الزمر 4
"አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ፣ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፤ ጥራት ተገባው እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው።" (ዙመር 4)፡፡
"يَوْمَ هُمْ بَارِزُونَ لَا يَخْفَى عَلَى اللَّهِ مِنْهُمْ شَيْءٌ لِمَنِ الْمُلْكُ الْيَوْمَ لِلَّهِ الْوَاحِدِ الْقَهَّارِ " سورة غافر 16
"እነርሱ ከመቃብር (በሚወጡበት) ቀን፣ በአላህ ላይ ከነሱ ምንም ነገር አይደበቅም፤ ንግሥናው ዛሬ ለማን ነው? (ይባላል)፤ ለአሸናፊው ለአንዱ አላህ ብቻ ነው (ይባላል)።" (ሱረቱ ጋፊር 16)፡፡
"አል-ቃሒር" የሚለው መለኮታዊ ስም ደግሞ ሁለት ጊዜ ተጠቅሷል፡፡ -
" وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ " سورة الأنعام 18
"እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን አሸናፊ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 18)፡፡
" وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً حَتَّى إِذَا جَاءَ أَحَدَكُمُ الْمَوْتُ تَوَفَّتْهُ رُسُلُنَا وَهُمْ لَا يُفَرِّطُونَ " سورة الأنعام 61
"እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸነፊ ነው፡፡ በናንተም ላይ ጠባቂዎችን (መላእክት) ይልካል፡፡ አንዳችሁንም ሞት በመጣበት ጊዜ (የሞት) መልእክተኞቻችን እነርሱ (ትእዛዛትን) የማያጓድሉ ሲኾኑ ይገድሉታል፡፡" (ሱረቱል አንዓም 61)፡፡
ሐ. የምንወስደው ትምህርት፡-
1. ፍጹም አሸናፊነትና የበላይነት የአምላካችን የአላህ ብቻ በመሆኑ፡ በዚህ ደካማነታችን ትእቢት ተሰምቶን ከኛ በታች ናቸው የምንላቸውን ሰዎች በመጨቆንና በማመናጨቅ ኃይልን መጠቀም እንደሌለብን ነው፡፡ ኃይል ሁሉ የአላህ ነውና፡-
" فَأَمَّا الْيَتِيمَ فَلَا تَقْهَرْ * وَأَمَّا السَّائِلَ فَلَا تَنْهَرْ * وَأَمَّا بِنِعْمَةِ رَبِّكَ فَحَدِّثْ " سورة الضحى 11-9
"የቲምንማ አትጨቁን። ለማኝንም አትገላምጥ። በጌታህም ጸጋ አውራ፤ (ግለጻት)።" (ሱረቱ-ዱሓ 9-11)፡፡
Click and Like ➤➤ https://www.facebook.com/Ustaz.Abuhyder
Join us➤ t.me/abuhyder
18-20 "አል-ገፍፋር"፣"አል-ገፉር"፣"አል-ጋፊር"
በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2) ፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ሀ. ትርጉም፡-
"አል-ገፉር" የሚለው መለኮታዊ ስም ትርጉም፡- በጣም መሐሪ ማለት ነው፡፡ "አል-ገፍፋር" ደግሞ ፡- ትርጉሙ ተመሳሳይ ሆኖ ነገር ግን እጅግ በጣም መሐሪ የሚለውን የsuperlative degree form የሚገልጽ ነው፡፡ "አል-ጋፊር" የሚለውም ትርጉሙ ከመጀመሪያው አይለይም፡፡ ጌታችን አላህ ለባሪያዎቹ እጅግ በጣም ርኅሩህ፡ በጣም አዛኝ በመሆኑ፡ በኃጢአት ጊዜም መሐሪያቸው እሱ ብቻ ነው፡፡ ይህ መሐሪነቱ ነው አማኞችን በልባቸው ተስፋን በመሙላት፡ እሱን ለሚያስደስተው መልካም ስራ እንዲሽቀዳደሙ፡ ከሚጠላው መጥፎ ነገር እንዲርቁ የሚያደርጋቸው፡፡ አማኝ የአላህ ባሪያዎች ሁሌም መልካም ተግባርን ጌታችን ይደስትበታል ብለው ሲሰሩ ሁለት ነገርን ከፊት-ለፊታቸው አድርገው ነው፡-