አላህ "ፍፁም ፍትሐዊ " አምላክ ነው!
በአቡ ሀይደር
በአላህ ሥም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
ክብርና ምሥጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን(አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
ከጌታ አላህ መለኮታዊ ባሕሪያት አንዱ ‹‹አል-ዐድል›› ነው፡፡ ትርጉሙም ፍፁም ፍትሐዊነት ማለት ነው፡፡ ጌታ አላህ ከሱ በላይ የኾነ የበላይ ተቆጣጣሪ ሳይኖርበት፣ ምንም የሚፈራውም ሆነ የሚጎድልበት ነገር ሳይኖር፡ ከፍጡራኑም ምንም የሚጠቀመው ነገር ሳይኖር፡ ለባሪያዎቹ ፍጹም ፍትሐዊ የኾነ አምላክ ነው፡፡ በደል የሚለው ቃል አላህ ዘንድ መገለጫ የለውም፡፡ መገለጫው እኛው ደካማ ባሮቹ ዘንድ ነው፡፡ በደል ማለት፡- አንድን ነገር ተገቢው ስፍራ ላይ አለማኖር ወይንም በሌላ ንብረት ያለ-ፈቃድ መጠቀም ማለት ነውና፡ የአላህን ህግ በመጣስ ወይንም የታዘዝነውን ግዳጅ ባለመፈጸም እራሳችንን ለቅጣት በመዳረግ ነፍሲያችንን እንበድላለን፡፡ እንዲሁም መሰሎቻችን የኾኑ ሰዎችን ሐቃቸውን ያለ-አግባብ በመውሰድ፣ እንሰሳትን ያለ አግባብ በማሰቃየት በደል እንፈጽማለን፡፡ የአላህ ቃልም ይህን በደለኛነታችንን እንዲህ ይገልጸዋል፡-
"እኛ አደራን በሰማያትና በምድር፣ በተራራዎችም ላይ አቀረብናት፡፡ መሸከሟንም እንቢ አሉ፡፡ ከእርሷም ፈሩ፡፡ ሰውም ተሸከማት፡፡ እርሱ በጣም በደለኛ ተሳሳች ነውና፡፡" (ሱረቱል አሕዛብ 33፡72)፡፡
ጌታ አላህ ግን በደልን በራሱ ላይ እርም አደርጎታል፡፡ ታላቁ ሐዲሥ አል-ቁድሲይ ላይ በሰፈረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡- አቢ ዘር (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- አላህ እንዲህ ይላል፡- ‹‹ባሮቼ ሆይ! እኔ በደልን በራሴ ላይ እርም አድርጌዋለሁ፡፡ በመሀከላችሁም እርም አድርጌዋለሁና አትበዳደሉ…›› (ሙስሊም የዘገበው)፡፡
በቁርኣን ላይ እራሱን እንደገለጸውም፡ እሱ ማለት በፍትሕ (በማስተካከል) የቆመ የዓለሙ አስተዳዳሪ ነው፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡- "አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው፡፡" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡18)፡፡
ቅዱስ ቁርኣን የአላህን ፍፁም ፍትሐዊነት፡ ባሮቹን ፈጽሞ የማይበድል አምላክ መሆኑን በብዙ መንገድ አስተምሮናል፡፡ ከነዚህም መካከል፡-
1ኛ. በቃላት በመናገር፡-
አላህ ቃሉ ታማኝ ነው፡፡ ንግግሩ ፍፁም እውነት ነው፡፡ እንደሱም ፍጹም እውነተኛ የለም!፡፡
"አላህ ከርሱ በስተቀር አምላክ የለም፤ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡87)፡፡
"እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሠሩ፣ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ እናገባዋቸዋለን፤ አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው። በንገገርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማን ነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡122)፡፡
"እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ #እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 6፡73)፡፡
ከዚህ እውነተኛ ማንነቱ በመነሳት፡ በቃሉ ውስጥ እሱ ባሮቹን ፍፁም የማይበድል፡ ለዓለማትም በደልን የሚሻ አምላክ አለመሆኑን እንዲህ ነግሮናል፡-
“ይህች በአንተ ላይ በእውነት የምናነባት ስትሆን የአላህ ታምራት ናት አላህም ለአለማት በደልን የሚሻ አይደለም፡፡” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡108)፡፡
“አላህ የብናኝን ክብደት ያህል አይበድልም መልካም ሥራ ብትሆንም ይደራርባታል ከርሱም ዘንድ ታላቅን ምንዳ ይሰጣል፡፡” (ሱረቱ-ኒሳእ 4፡40)፡፡
“አላህ ሰዎችን ምንም አይበድልም ግን ሰዎች ነፍሶቻቸውን ይበድላሉ፡፡” (ሱረቱ ዩኑስ 10፡44)፡፡
ለ. ሰዎችን ከአቅማቸው በላይ ባለማስገደድ፡-
አላህ ሰውን የፈጠረው ለአምልኮ ነው (አዝ-ዛሪያት 51፡56) አምልኮ ደግሞ የሚረጋገጠው በልብ በማመን ብቻ ሳይሆን በአንደበት በመመሥከር እና በተግባርም ሥራ ላይ በማዋል ነው፡፡ ስለዚህም ለአላህ እንድንሰግድ፣ እንድንፆም፣ ዘካን ለተቸገር እንድንሰጥ እንታዘዛለን፡፤ ኾኖም ሃይማኖታዊ ትእዛዛት በጠቅላላ የተደነገጉት በአቅማችን ልክ ነው፡፡ ከአቅም በላይ ኾኖ እንድንፈጽመው የታዘዝነው ነገር የለም!፡፡ ይልቁኑ በህመም ወይም በእርጅና ወይንም በሆነ ሰበብ የታዘዝነውን ነገር መፈፀም ያቃተን ጊዜ ግዳጅነቱ ቢነሳልን እንጂ፡፡ ይህም የአላህን ፍፁም ፍትሐዊነት ያሳያል፡፡ የአላህ ቃል እንዲህ ይላል፡-
“አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም ለርስዋ የሰራችው አላት በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኃጢአት) አለበት…፡፡” (ሱረቱል በቀራህ 2፡286)፡፡
“የየቲምንም ገንዘብ ብርታቱን (አካለ መጠን) እስኪደርስ ድረስ በዚያች እርሷ መልካም በሆነች ሁኔታ እንጂ አትቅረቡ ስፍርንና ሚዛንንም በትክክል ሙሉ ነፍስን ችሎታዋን እንጂ አናስገድድም…” (ሱረቱል አንዓም 6፡152)፡፡
“የችሎት ባለቤት ከችሎታው ይቀልብ በርሱም ላይ ሲሳይ የተጠበበበት ሰው አላህ ነፍስን የሰጣትን እንጂ አያስገድድም አላህ ከችግር በኋላ ምቾትን በእርግጥ ያደርጋል” (ሱረቱ ጦላቅ 65፡7)፡፡
በነዚህ አናቅጽ መሠረት፡ አላህ ሰዎችን እንዲተገብሩትና እንዲርቁት ያዘዛቸውን ነገር ሁሉ የመፈፀም ሂደቱን በአቅማቸው ልክ ነው ያደረገው፡፡ ከአቅም በላይ የሆነ ነገር በሚመጣ ሰዓት ግዴታ የሆነ ነገርም እንደሚነሳላቸው ክልክል የሆኑ ነገሮችም እንደሚፈቀድላቸው ራሱ ገልፆታል፡፡ ከእያንዳንዱ አንድ ወይም ሁለት ምሣሌዎችን እንውሰድ፡-
ግዳጅ ከሆኑት፡- ሶላት መስገድ በማንኛውም ሙስሊም ላይ ሃይማኖታዊ ግዳጅ ነው፡፡ ከሶላት ማእዘናቶች (አርካን) ውስጥ ደግሞ አንዱ ቆሞ መስገድ ነው፡፡ ታዲያ በእርጅና ወይም በህመም ምክንያት ቆሞ መስገድ የማይችል ሰው፡ ቁጭ ብሎ፡ እሱንም ካልቻለ በጐኑ ተጋድሞ በአይኑ እያመላከተ መስገድ ይችላል፡፡
"በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡ ታዛዦች ኾናችሁም ለአላህ ቁሙ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡238)፡፡
ዒምራን ኢብኑ ሑሰይን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡- "የኪንታሮት በሽታ ነበረብኝ፡፡ ስለ ሶላቴ መልክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ጠየቅኋቸው፡፡ እሳቸውም፡- ‹‹ቆመህ ስገድ፣ ካልቻልክ ተቀምጠህ፣ (እሱንም) ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ (ስገድ)›› አሉኝ" (ቡኻሪይ)፡፡
እንዲሁም ሌላኛው ሃይማኖታዊ ግዳጅ ፆም ነው፡፡ ይህ የረመዳን ወር ሲገባ በእርግዝናም ሆነ ጡት በማጥባት አልያም ስኳርና በመሳሰሉ በሽታዎች ወሩን በፆም መካፈል ካልቻሉ እንዲበሉና በሌላ ጊዜ የበሉበትን ቀን ቆጥረው እንዲክሱ ታዘዋል፡፡ ምንኛ ገር የሆነ ዲን ነው!
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ የተቆጠሩን ቀኖች (ጹሙ)፡፡ ከእናንተም ውሰጥ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮች

ሐ. የምንወስደው ትምሕርት፡-
1. አላህ መኖሩ የተረጋገጠ መሆኑ፡- የፈጣሪ አምላካችን አላህ መኖር ምናባዊ ሳይሆን ፍጹም የተረጋገጠ እውነት ነው፡፡ የሱ መኖር scientifical truth ወይም Historical truth ሳይሆን Universal truth (ተፈጥሮአዊ እውነታ) ነው፡፡ የአላህን መኖር ለማረጋገጥ የከርሰ ምድር ጥናት ወይም የጠፈር ምርምር ወይም የታሪክ ማረጋገጫ አያስፈልግም፡፡ ማንም ሰው በተፈጥሮው ያለ-ምንም ሃይማኖታዊ ተጽእኖ አምኖ የሚቀበለውና የሚያድግበት እውነት ነው፡፡ ስለሆነም ጌታ አላህ "አል-ሐቅ" ተብሎ ይጠራል፡-
"يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِنْ كُنْتُمْ فِي رَيْبٍ مِنَ الْبَعْثِ فَإِنَّا خَلَقْنَاكُمْ مِنْ تُرَابٍ ثُمَّ مِنْ نُطْفَةٍ ثُمَّ مِنْ عَلَقَةٍ ثُمَّ مِنْ مُضْغَةٍ مُخَلَّقَةٍ وَغَيْرِ مُخَلَّقَةٍ لِنُبَيِّنَ لَكُمْ وَنُقِرُّ فِي الْأَرْحَامِ مَا نَشَاءُ إِلَى أَجَلٍ مُسَمًّى ثُمَّ نُخْرِجُكُمْ طِفْلًا ثُمَّ لِتَبْلُغُوا أَشُدَّكُمْ وَمِنْكُمْ مَنْ يُتَوَفَّى وَمِنْكُمْ مَنْ يُرَدُّ إِلَى أَرْذَلِ الْعُمُرِ لِكَيْلَا يَعْلَمَ مِنْ بَعْدِ عِلْمٍ شَيْئًا وَتَرَى الْأَرْضَ هَامِدَةً فَإِذَا أَنْزَلْنَا عَلَيْهَا الْمَاءَ اهْتَزَّتْ وَرَبَتْ وَأَنْبَتَتْ مِنْ كُلِّ زَوْجٍ بَهِيجٍ * ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّهُ يُحْيِ الْمَوْتَى وَأَنَّهُ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ " سورة الحج 6-5
"እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ (አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ)፤ እኛም ከዐፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ፣ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች (ችሎታችንን) ለናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤ የምንሻውንም፣ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ፣ በማህጸን ዉስጥ እናረጋዋለን ከዚያም ሕጻን ሆናችሁ እናወጣችኋለን። ከዚያም ሙሉ ጥንካሬያችሁን ትደርሱ ዘንድ፣ (እናሳድጋችኋለን)፤ ከናንተም የሚሞት ሰው አለ፤ ከናንተም ከዕውቀት በኋላ፣ ምንንም እንዳያውቅ ወደ ወራዳ ዕድሜ የሚመለስ ሰው አልለ፤ ምድርንም ደረቅ ሆና ታያታለህ፤ በስዋም ላይ ውሃን ባወረድን ጊዜ፣ ትላወሳለች፤ ትነፋለችም፤ ውበት ካለው ቦታ ሁሉ ታበቅላለችም። ይህ፣ አላህ እርሱ #መኖሩ-የተረጋገጠ፤ እርሱም ሙታንን ሕያው የሚያደርግ፤ እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 5-6)፡፡
"ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ هُوَ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة الحج 62
"ይህ አላህ እርሱ #እውነት በመሆኑ ከርሱም ሌላ የሚገዙት ነገር እርሱ ፍጹም ውሽት በመሆኑ አላህም እርሱ የሁሉ በላይ ታላቅ በመሆኑ ነው።" (ሱረቱል ሐጅ 62)፡፡
"يَوْمَئِذٍ يُوَفِّيهِمُ اللَّهُ دِينَهُمُ الْحَقَّ وَيَعْلَمُونَ أَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ الْمُبِينُ " سورة النور 25
"በዚያ ቀን አላህ እውነተኛ ዋጋቸውን ይመላላቸዋል አላህም እርሱ #መኖሩ-የተረጋገጠ (ሁሉን ነገር) ገላጭ መሆኑን ያውቃሉ።" (ሱረቱ-ኑር 25)፡፡
"ذَلِكَ بِأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْحَقُّ وَأَنَّ مَا يَدْعُونَ مِنْ دُونِهِ الْبَاطِلُ وَأَنَّ اللَّهَ هُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة لقمان 30
"ይህ፣ አላህ እርሱ #እውነት፣ ከርሱም ሌላ የሚገዙት (ጣዖት)ውሸት በመሆኑና አላህም እርሱ የበላይ ታላቅ በመኾኑ ነው።" (ሱረቱ ሉቅማን 30)፡፡
2. ንግግሩ እውነት መሆኑን፡- እውነተኛው አምላክ አላህ የሚናገረውም እውነትን ብቻ ነው፡፡ ውሸት እሱ ዘንድ በፍጹም የለም አይታሰብምም፡፡ በንግግርም ከርሱ የበለጠ እውነተኛ የለም፡-
"اللَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ لَيَجْمَعَنَّكُمْ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ لَا رَيْبَ فِيهِ وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ حَدِيثًا " سورة النساء 87
"አላህ ከርሱ በስተቀር አምላክ የለም፤ ወደ ትንሣኤ ቀን በርሱ ጥርጥር የሌለበት ሲሆን፣ በእርግጥ ይሰበስባችኋል። በንግግርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 87)፡፡
"وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ سَنُدْخِلُهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا وَعْدَ اللَّهِ حَقًّا وَمَنْ أَصْدَقُ مِنَ اللَّهِ قِيلًا " سورة النساء 122
"እነዚያም ያመኑና በጎ ስራዎችን የሠሩ፣ በስራቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ዘላለም በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲሆኑ እናገባዋቸዋለን፤ አላህ እውነተኛን ተስፋ ሰጣቸው። በንገገርም ከአላህ ይበልጥ #እውነተኛ ማን ነው?" (ሱረቱ-ኒሳእ 122)፡፡
"وَهُوَ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ بِالْحَقِّ وَيَوْمَ يَقُولُ كُنْ فَيَكُونُ قَوْلُهُ الْحَقُّ وَلَهُ الْمُلْكُ يَوْمَ يُنْفَخُ فِي الصُّورِ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ وَهُوَ الْحَكِيمُ الْخَبِيرُ " سورة الأنعام 73
"እርሱም ያ ሰማያትንና ምድርን በእውነት የፈጠረ ነው፡፡ «ኹን» የሚልበትንና ወዲያውም የሚኾንበትን ቀን (አስታውስ)፡፡ ቃሉ #እውነት ነው፡፡ በቀንዱም በሚነፋ ቀን ንግሥናው የርሱ ብቻ ነው፡፡ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም ጥበበኛው ውስጥ ዐዋቂው ነው፡፡" (ሱረቱል አንዓም 73)፡፡
"وَلَا تَنْفَعُ الشَّفَاعَةُ عِنْدَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ حَتَّى إِذَا فُزِّعَ عَنْ قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ قَالُوا الْحَقَّ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ " سورة سبأ 23
"ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ፣ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፤ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጠም ጊዜ (ተማላጆቹ) ጌታችሁ ምን አለ? ይላሉ፤ (አማላጆቹ) #እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው ይላሉ።" (ሱረቱ ሰበእ 23)፡፡