ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሥነ-ፅንስ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

መግቢያ
ሥነ-ፅንስ ጥናት ኢምብሪዮሎጂይ”Embryology” ሲባል “ኢምብሮ” ἔμβρυον “ያልተወለደ” እና “ሎጂአ” λογία, “ጥናት” ከሚል ሁለት የግሪክ ቃል የተዋቀረ ነው፤ ይህንን ፅንስ እናቱ ማህፀን ውስጥ በሚፈልገው መልኩ የሚቀርፀው አንዱ አምላክ አላህ ነው፦
3:6 እርሱ ያ “በማሕፀኖች” ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ “የሚቀርጻችሁ” ነዉ፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤

ይህ ፅንስ ማህፀን ውስጥ እንዴት እንደሚፈጠር ሙሉ እውቀት ያለው የዓለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፦
31:34 አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ “በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል”፤
53:32 ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ “ማሕፀኖች” ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ እርሱ በእናንተ ሁኔታ “አዋቂ” ነው።
13:8 አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፤ “ማሕፀኖችም የሚያጐድሉትን የሚጨምሩትንም፥ ያውቃል”፤ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው።

በማሕፀኖችም ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቀ አምላክ የሥነ-ፅንስ እውቀት ወደፊት እንደሚያሳየና እንደሚያሳውቀን ለማመልከት፦ “በራሶቻችሁ ውስጥ ያሉትም ታምራት ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ” በማለት ቃል ገብቷል፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥ እና #በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?
27:93 ምስጋና ለአላህ ነው፤ #ታምራቶቹን #ወደፊት #ያሳያችኋል#ታውቁታላችሁ በላቸው።

አላህ ይህንን እውቀት በራሳችን አካላት ከማሳየቱ በፊት በቁርአን አንድ ሽል በማህፀን ውስጥ እንዴት የተለያየ ደረጃዎችን”stages” እንደሚያሳልፍ በተከበረ ቃሉ ይነግረናል፦
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” النُّطْفَةَ አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” عَلَقَةً አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም “ቁራጭ ሥጋ” مُضْغَةً አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጯንም ሥጋ “አጥንቶች” عِظَامًا አድርገን ፈጠርን፤ አጥንቶቹንም ሥጋን لَحْمًا አለበስናቸው፤ ከዚያም “ሌላ ፍጥረትን” خَلْقًا آخَرَ አድርገን “አስገኘነው” أَنْشَأْنَاهُ፤ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡
ሥነ-ፅንስ

ክፍል ሁለት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

“ደረጃ ሁለት”
“ዐለቃ”
“ዐለቃ” عَلَقَة አንስታይ ሲሆን “ዐለቅ” عَلَق ደግሞ ተባእታይ ነው፤ ትርጉሙም “አልቅት”leech” ወይም “የረጋ ደም”blood-clot” ማለት ነው፤ ይህን የፅንስ ሁለተኛው ደረጃ ከሚታይ አልቅት ከሚባል የባህር ትል”insect” እና ከረጋ ደም ጋር ስለሚመሳሰል ነው፤ ወደዚህ ሂደት ለመምጣት በህዋሳት ውህደት ወቅት “ክሮሞሶም”Chromosomes” ከአንዱ ለጋሽ ወላጅ ወደሌላው ለጋሽ ወላጅ ይተላለፋል፤ እያንዳንዱ ተሣታፊ ህዋስ የለጋሾችን ግማሽ ክሮሞሶም ይይዛል፤ የአባት ክሮሞሶም ግማሽ 23% የእናት ክሮሞሶም 23% ተገናኛተው 46% ይዋሃዳሉ ማለት ነው፤ ተወራሽ የዘር ምልክቶች በምፃረ-ቃል “ዲ-ኤን-ኤ”(DNA) ወይም በዝርዝር “ዲኦክሲሪቦ ኒውክሊክ አሲድ”(deoxyribonucleic acid) በመባል በሚታወቀው በክሮሞሶሞች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ-ነገር ውስጥ ሰፍረው ይገኛሉ። ክሮሞሶሞች “በጥንድ” ሆነው በሚገኙበት ጊዜ “ዳይፕሎይድ”(diploid) ይባላሉ፤ ክሮሞሶሞች በነጠላ ግዜ “ሃፕሎይድ”(haploid) ይባላሉ፤ በዚህ ሂደት አንድ ሴል የነበረው የወንድ የዘር ህዋስ ከሴት የእንቁላል ህዋስ ጋር ከተዋሐደ በኃላ 2, 4, 8, 16, 32, 64 እያለ በቲሪልየን ብዜት በ 21 ቀን የረጋ ደም”blood-clot” የሚለው ደረጃ ይጀምራል፤ ይህንን ደረጃ አምላካችን አላህ እንዲህ ይለናል፦
22:5 እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ፤ እኛም ከአፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም “ከረጋ ደም” عَلَقَةٍ ፣ ከዚያም ከቁራጭ፣ ስጋ ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች ችሎታችንን ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤
40:67 እርሱ ያ ከአፈር፣ ከዚያም ከፍትወት ጠብታ፣ ከዚያም “ከረጋ ደም” عَلَقَةٍ፣ የፈጠራችሁ ነው።
96:1-2 አንብብ በዚያ ሁሉን በፈጠረው ጌታህ ስም፤ ሰውን “ከረጋ ደም” عَلَقٍ በፈጠረው ጌታህ ስም።

ከፍትወት ህዋስ ወደ የረጋ ደም የሚሄድበት ሂደት እና ደረጃ ለማመልከት “ሱምመ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ይጠቀማል፤ ከዚህ ከተቀላቀለው የፍትወት ህዋስ ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን ይመጣል፦
75፥36-39 ሰው ስድ ሆኖ መትተውን ይጠረጥራልን? የሚፈስስ ከሆነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን? “ከዚያም” ثُمَّ “የረጋ ደም” عَلَقَةً ሆነ፤ ሰው አድርጎ ፈጠረውም፤ አስተካከለውም። “ከእርሱም” ሁለት ዓይነቶችን “ወንድና ሴትን” አደረገ።

“የዘረ-መል ጥናት”(Genetic) እንደሚያስተነትነው የተባእት ክሮሞሶም ‘XY’ ሲሆን የእንስት ክሮሞሶም ደግሞ ‘XX’ ነው፤ ከወንድ ‘Y” መጥቶ ከሴት ‘X’ ከመጣ ሽሉ የአባቱን ፆታ በመያዝ ወንድ ይሆናል፤ ከወንድ ‘X” መጥቶ ከሴት ‘X’ ከመጣ ሽሉ የእናቱን ፆታ በመያዝ ሴት ይሆናል፤ ልብ አድርግ የወንድ ክሮሞሶም ‘XY’ ሲሆን የሴት ክሮሞሶም ደግሞ ‘XX’ መሆኑ ማለቴ ነው፤ የዘረ-መል ጥናት ይህንን ከማወቁ በፊት አላህ ለመልእክተኛው ይህንን የሩቅ ነገር ሚስጥር አሳውቋል፦
ኢማም ቡሃሪ መጽሐፍ 60 , ቁጥር 4 :
وَأَمَّا الشَّبَهُ فِي الْوَلَدِ فَإِنَّ الرَّجُلَ إِذَا غَشِيَ الْمَرْأَةَ فَسَبَقَهَا مَاؤُهُ كَانَ الشَّبَهُ لَهُ، وَإِذَا سَبَقَ مَاؤُهَا كَانَ الشَّبَهُ لَهَا ‏”‌‏.‏
የአላህ መልክተኛ አሉ፦ የልጆች ከወላጆቻቸው መመሳሰል እንዲህ ነው፤ ተባእት ከሚስቱ ጋር ተራክቦ ሲያደርግ የእርሱ ከተለቀቀ ህፃኑ እርሱን ይመስላል፤ የእንስት ከተለቀቀ ደግሞ ህፃኗ እርሷን ትመስላለች።

እውነት ነው፤ አላህም ከወንድ ክሮሞሶም ‘XY’ ወንድን እና ከሴት ክሮሞሶም ‘XX’ ደግሞ ሴትን በምድር ላይ ፈጥሮ የበተነ ነው፤ ይህም የሁለቱ አስተዋእፆ የአባት ክሮሞሶም ግማሽ 23% የእናት ክሮሞሶም 23% ተገናኛተው 46% ሲሆኑ ነው፦
4:1 እላንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ(ከአዳም) የፈጠራችሁን፣ ከእርስዋም መቀናጆዋን(ሔዋንን) የፈጠረውን፣ #ከእነርሱም ብዙ “ወንዶችን” እና “ሴቶችን” የበተነውን፣ ጌታችሁን ፍሩ።
49፥13 እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ “ከወንድ እና ከሴት ፈጠርናችሁ”፡፡ ኢንሻላህ ይቀጥላል…..

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም
ሥነ-ፅንስ

ክፍል ሶስት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

ደረጃ ሶስት
“ሙድጋ”
“ሙድጋ” مُضْغَة ማለት “ቁራጭ ስጋ”embryonic lump” ወይም “የታኘከ ስጋ”chewed gum” ማለት ሲሆን ልክ ጥርስ እንዳረፈበት ስጋ የሚመስልበት የፅንስ ደረጃ ነው፤ ይህን ደረጃ ለማመልከት “ሱምሙ” ثُمَّ “ከዚያም” የሚል መስተፃምር ከመጠቀም ይልቅ “ፈ” فَ “ም” የሚል ቅፅበታዊ መስተፃምር ይጠቀማል፤ ምክንያቱም 21-24 ቀናት የረጋ ደም ጊዜ ሲሆን 24ኛ ቀን ላይ በቅፅፈት የታኘከ ስጋ ቅርፅ ይጀምራል፤ በዚህ ጊዜ “”ፍጥረትዋ ሙሉ ካልሆነች”” ጅማት፣ አንጀት፣ ስስ ጡንቻ፣ ስስ የደም ስር ወዘተ ስለሚፈጠሩ ነው፦
22:5 እላንተ ሰዎች ሆይ! ከመቀስቀስ፣ በመጠራጠር ዉስጥ እንደ ሆናችሁ አፈጣጠራችሁን ተመልከቱ፤ እኛም ከአፈር ፈጠርናችሁ ከዚያም ከፍቶት ጠብታ፣ ከዚያም ከረጋ ደም፣ ከዚያም ከቁራጭ ስጋ مُضْغَةٍ “”ፍጥረትዋ ሙሉ ከኾነችና ሙሉ ካልሆነች”” ችሎታችንን ለእናንተ ልንገልጽላችሁ ፈጠርናችሁ፤
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውን”ም” ደም “ቁራጭ ሥጋ” مُضْغَةً አድርገን ፈጠርን፤

“ፍጥረትዋ ሙሉ የሆነች” ቁራጭ ሥጋ በአምተኛው ደረጃ ላይ ይመጣል፤ ይህንን ለማመልከት “ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል” ይላል፦
39:6 በእናቶቻችሁ ማህፀኖች ውስጥ፣ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ፣ “ከመፍጠር በኋላ ሙሉ መፍጠርን ይፈጥራችኋል”፤

ሶስት ጨለማ የተባሉት፦ ሆድ፣ ማህፀንና የእንግዴ ልጅ ናቸው።

ደረጃ አራት
“ዐዝም”
“ዐዝም” عَظْم በነጠላ ሲሆን “ዒዛም” عِظَام ደግሞ በብዜት ነው፤ ትርጉሙም “አፅም”skeleton” ወይም “አጥንት”bone” ማለት ነው፤ ከ 24-35 ቀናት የቁራጭ ስጋ ሂደት ሲሆን ከመቅፅበት 35ኛው ቀን የደም ዝውርውር፣ የነርቭ ሥርዓት፣ አፅም ወዘተ የሚፈጠርበት ሂደት ነው፤ ይህን አጭር ጊዜ ለማመልከት “ፈ” فَ “ም” የሚል ቅፅበታዊ መስተፃምር ይጠቀማል፦
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም “ቁራጭ ሥጋ” አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጯን”ም” ሥጋ “አጥንቶች” عِظَامًا አድርገን ፈጠርን፤