ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ነጥብ ሶስት
“የምድር ንጣፍ”
ምድር ልክ እንደ ሰጎን እንቁላል ቅርፅ እንዳላት ካየን ዘንዳ አሁን ደግሞ የምድርን ንጣፍ ከእንቁላል ጋር የሚያመሳስላትን ነገር እናያለን፤ የምድር መዋቅር ልክ እንደ እንቁላል ሶስት ክፍል አለው፤ እርሱም፦
1ኛ. የላይኛው ቅርፊት “ክረስት”crust” ይባላል፣በአብዛኛው ከተለያዩ የቋጥኝ አይነቶች የተገነባ ሲሆን ህይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ የሚኖሩት በዚህኛው የመሬት ክፍል ላይ ነው፤ ይህ ክፍል ውፍረቱ በውቅያኖሶች ስር ያለው ውፍረት 5000 ሜትር እስከ 10000 ሜትር ሲሆን በአህጉሮች ላይ ደግሞ 30 ኪሎ ሜትር እስከ 50 ኪሎ ሜትር ነው፤ ይህም በእንቁላል የላይኛው ቅርፊት ጋር ይመሳሰላል።

2ኛ. የመካከለኛው ፈሳሽ ክፍል “ማንትል”mantle” ይባላል፤ ፈሳሽ የሆነ “ቅልጥ አለት”Magma” በከፍተኛ የሙቀት መጠን የቀለጠ አለት ነው፤ ይህም በእንቁላል የመካከለኛው ነጭ ፈሳሽ ጋር ይመሳሰላል።

3ኛ. የውስጠኛው አስኳል ክፍል “ኮር”core” ይባላል፤ይህ ክፍል እጅግ በጣም ሞቃት ሲሆን የፀሐይን የውጨኛ ክፍል መጠነ ሙቀት ይኖርዋል፤ ይህ ክፍል መጠኑ አነስተኛ ሲሆን በራዲየስ እስከ 1220 ኪሎ ሜትር ነው፤ በእንቁላል የውስጠኛው አስኳል ጋር ይመሳሰላል።

ይህንን ግንዛቤ ይዘን ለሰዎች መኖሪያ የሆነው የላይኛው የምድር ቅርፊት አላህ ለእኛ ዝግር አድርጎ ፈጥሯል፤ መዘርጋት ከእኛ እይታ አንጻር ነው፤ ለዛ ነው ብዙ አናቅፅ ላይ አላህ “ለኩም” لَكُم “ለእናንተ” የሚለው ሁለተኛ መደብ ተውላጠ ስም የሚጠቀመው፦
2፥22 እርሱ ያ *ለእናንተ* لَكُمُ ምድርን ምንጣፍ ሰማይንም ጣራ ያደረገ ነው፤
20፥53 እርሱ ያ ምድርን *ለእናንተ* لَكُمُ ምንጣፍ ያደረገላችሁ፣
43፥10 እርሱ ያ ምድርን *ለእናንተ* لَكُمُ ምንጣፍ ያደረገላችሁ፣
71፥19 አላህም ምድርን *ለእናንተ* لَكُمُ ምንጣፍ አደረጋት።

አላህም ምድርን ለእኛ ምንጣፍ ያደረገበት ምክንያት “ከእርሷ ሰፋፊዎችን መንገዶች ትገቡ ዘንድ” ነው ይለናል፤ መኪና ስንነዳ መንገዶች ሁሉ ለእኛ ዝርግ ናቸው፦
71፡19-20 አላህም ምድርን *ለእናንተ* لَكُمُ ምንጣፍ አደረጋት፤ ከእርሷ ሰፋፊዎችን “”መንገዶች ትገቡ ዘንድ””፡፡
43፥10 እርሱ ያ ምድርን *ለእናንተ* لَكُمُ ምንጣፍ ያደረገላችሁ፣በእርሷም ውስጥ ትመሩ ዘንድ “”ለእናንተ መንገዶችን”” ያደረገላችሁ ነው።

በእርግጥ አላህ የፈጠረውን ምድር ታምር ነው፤ለሚያስተነትኑ አዋቂዎች ታምር አለበት፤ ወደፊት ይህንን ታምር ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ ብሎ ቃል በገባልን ኪዳን በዘመናችን አሳይቶናል ፦
30:22 ሰማያትንና “ምድርንም” መፍጠሩ፥ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት “ከአስደናቂ “ታምራቶቹ” آيَاتِهِ ነው፤ በእዚህ ውስጥ ለአዋቂዎች “ታምራቶች” لَآيَاتٍ አሉበት።
27:93 ምስጋና ለአላህ ነው፤ #ታምራቶቹን ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ በላቸው።

ከወንድም ወሒድ ዑመር
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሰላሙ አለይኩም

ወሰላሙ አለይኩም ።
ሥነ-ፅንስ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

መግቢያ
ሥነ-ፅንስ ጥናት ኢምብሪዮሎጂይ”Embryology” ሲባል “ኢምብሮ” ἔμβρυον “ያልተወለደ” እና “ሎጂአ” λογία, “ጥናት” ከሚል ሁለት የግሪክ ቃል የተዋቀረ ነው፤ ይህንን ፅንስ እናቱ ማህፀን ውስጥ በሚፈልገው መልኩ የሚቀርፀው አንዱ አምላክ አላህ ነው፦
3:6 እርሱ ያ “በማሕፀኖች” ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ “የሚቀርጻችሁ” ነዉ፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤

ይህ ፅንስ ማህፀን ውስጥ እንዴት እንደሚፈጠር ሙሉ እውቀት ያለው የዓለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፦
31:34 አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ “በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል”፤
53:32 ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ “ማሕፀኖች” ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ እርሱ በእናንተ ሁኔታ “አዋቂ” ነው።
13:8 አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፤ “ማሕፀኖችም የሚያጐድሉትን የሚጨምሩትንም፥ ያውቃል”፤ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው።

በማሕፀኖችም ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቀ አምላክ የሥነ-ፅንስ እውቀት ወደፊት እንደሚያሳየና እንደሚያሳውቀን ለማመልከት፦ “በራሶቻችሁ ውስጥ ያሉትም ታምራት ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ” በማለት ቃል ገብቷል፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥ እና #በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?
27:93 ምስጋና ለአላህ ነው፤ #ታምራቶቹን #ወደፊት #ያሳያችኋል#ታውቁታላችሁ በላቸው።

አላህ ይህንን እውቀት በራሳችን አካላት ከማሳየቱ በፊት በቁርአን አንድ ሽል በማህፀን ውስጥ እንዴት የተለያየ ደረጃዎችን”stages” እንደሚያሳልፍ በተከበረ ቃሉ ይነግረናል፦
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” النُّطْفَةَ አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” عَلَقَةً አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም “ቁራጭ ሥጋ” مُضْغَةً አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጯንም ሥጋ “አጥንቶች” عِظَامًا አድርገን ፈጠርን፤ አጥንቶቹንም ሥጋን لَحْمًا አለበስናቸው፤ ከዚያም “ሌላ ፍጥረትን” خَلْقًا آخَرَ አድርገን “አስገኘነው” أَنْشَأْنَاهُ፤ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡