ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
59.3K subscribers
68 photos
70 videos
19 files
1.73K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ኢሥላም እና ሙሥሊም

ክፍል አንድ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

"ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ማለትም "ታዘዘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት ለአንዱ አምላክ በአምልኮ "መታዘዝ" "መገዛት" "እራስን መስጠት" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ለኢብራሂም "ታዘዝ" ሲለው እርሱም፦ "ታዘዝኩ" አለ፦
2፥131 ጌታው ለእርሱ "ታዘዝ" ባለው ጊዜ መረጠው፡፡ ለዓለማት ጌታ "ታዘዝኩ" አለ፡፡ إِذْ قَالَ لَهُۥ رَبُّهُۥٓ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ ٱلْعَٰلَمِينَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዝ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊም" أَسْلِمْ ሲሆን "ታዘዝኩ" ለሚለው ደግሞ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ነው፥ "አምላክ አንድ አምላክ ብቻ ነው" ብሎ ለአንድ አምላክ ብቻ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ "ታዘዙ"፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን "ኢሥላም" إِسْلَام በግንባር እና በጥሬ ትርጉም ለአንዱ አምላክ በአምልኮ "መታዘዝ" ማለት ነው፦
3፥20 ቢከራከሩህም፡- «ፊቴን ለአሏህ ሰጠው፥ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ሰጡ» በላቸው፡፡ فَإِنْ حَاجُّوكَ فَقُلْ أَسْلَمْتُ وَجْهِيَ لِلَّهِ وَمَنِ اتَّبَعَنِ

"ወጅህ" وَجْه የሚለው ቃል "ወጁሀ" وَجُهَ ማለት "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ" "ፊት" "ማንነት"Person" ማለት ነው፥ "አካል" የሚለው የግዕዝ ቃል "አካለ" ማለትም "ለየ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መለያ"Person" ማለት ነው። "Person" የሚለው የእንግሊዝኛው ቃል እራሱ "ፕሮሶፓን" πρόσωπον ከሚል የግሪክ ኮይኔ ቃል የመጣ ሲሆን "ፊት" ማለት ነው፥ ስለዚህ "ፊት" ሲባል "ማንነት" "መለያ" ማለት ከሆነ "ፊቴን ለአሏህ ሰጠው" ማለት "እራሴን ለአሏህ ሰጠው" "አካሌን ለአሏህ ሰጠሁ" ማለት ነው። "ሰጠው" ለሚለው የገባው ቃል ደግሞ "አሥለምቱ" أَسْلَمْتُ ነው፦
2፥112 አይደለም፤ እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአሏህ "የሰጠ" ሰው ለእርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳው አለው፡፡ بَلَىٰ مَنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَلَهُ أَجْرُهُ عِندَ رَبِّهِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የሰጠ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ሲሆን "ኢሥላም" إِسْلَام ለሚለው ቃል ሥርወ ቃል ነው፥ እራስን ለአንዱ አምላክ መስጠት የኢብራሂምንም መንገድ ነው፦
4፥125 እርሱ መልካም ሠሪ ኾኖ ፊቱን ለአሏህ "ከሰጠ" እና የኢብራሂምንም መንገድ ቀጥተኛ ሲኾን ከተከተለ ሰው ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ማን ነው? አላህም ኢብራሂምን ፍጹም ወዳጅ አድርጐ ያዘው፡፡ وَمَنْ أَحْسَنُ دِينًا مِّمَّنْ أَسْلَمَ وَجْهَهُ لِلَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ وَاتَّبَعَ مِلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۗ وَاتَّخَذَ اللَّهُ إِبْرَاهِيمَ خَلِيلًا

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ከሰጠ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው። "ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ፈረደ" "ደነገገ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ" "ሃይማኖት" ማለት ነው፥ "ሃይማኖት" የሚለው የግዕዝ ቃል "ሃይማነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሥርወ እምነት" "አንቀጸ እምነት" ማለት ነው። ከአንዱ አምላክ በግልጠተ መለኮት የሚመጣው መርሕ፣ ሥርወ እምነት፣ አንቀጸ እምነት በአምልኮ ለአንዱ አምላክ "መታዘዝ" ብቻ እና ብቻ" ነው፥ በአምልኮ ለአንዱ አምላክ ከመታዘዝ ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም። እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፦
3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ
3፥85 ከኢሥላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከእርሱ ተቀባይ የለውም፥ እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ
በባይብል አንድ ሃይማኖት እንዳለ እና ይህም ሃይማኖት ለቅዱሳን አንድ ጊዜ እንደተገለጠ ይናገራል፦
ኤፌሶን 4፥5 አንድ ጌታ "አንድ ሃይማኖት" አንዲት ጥምቀት።
ይሁዳ 1፥3 ለቅዱሳን "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት" እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።

ቅዱሳን የተባሉት ቅዱሳን ነቢያት እና ሐዋርያት ናቸው፥ የመጀመሪያው ነቢይ አዳም ነው፦
ኤፌሶን 3፥6 "ለቅዱሳን ሐዋርያት እና ለነቢያት" በመንፈስ አሁን እንደ ተገለጠ በሌሎቹ ትውልዶች ዘንድ ለሰው ልጆች አልታወቀም።
ቀሌምንጦስ 1፥40 በዚህ ጊዜ ንጉሥነትን እና ነቢይነትን ሠጠው በክብር መንበር ላይም አስቀመጠው።
ቀሌምንጦስ 1፥43 በዚህ ጊዜ መላእክት የእግዚአብሔር ቃል፦ "አዳም ሆይ! እነሆ ንጉሥ፣ ካህን እና "ነቢይ" መስፍን ለፍጥረት ሁሉ ገዢ ስላንተ በፈጠርሁት ሁሉ እንድትሆን አደረግሁ...ሲል ሰሙ።

ከ 451 እስከ 521 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረ ያዕቆብ ዘሥሩግ"Jacob of Serugh" በእንተ ወላዲተ አምላክ በሚል መጽሐፉ ላይ አዳም ነቢይ እንደነበረ ተናግሯል፦
"አዳም ድንግል ሔዋንን አስገኝቷል፥ "የሕይወት እናት" ብሎ ጠርቷታል። እርሱ ነቢይ ነበረ"።
On the Mother of God (Jacob of Serugh) Homily (I)1 Number 634

ከአዳም ጀምሮ በመገለጥ የተሰጠ አንድ ሃይማኖት አለ፥ ይህንን ሃይማኖት ባይብል በግልጽ ስለማያስቀምጥ አይሁዳውያን ከኪሳቸው "የሁዲ ሃይማኖት" ሲሉ ክርስቲያኖች ከኪሳቸው "የክርስትና ሃይማኖት" ይላሉ። ነገር ግን የሁዱ በይሁዳን ነገር የመጣ "አይሁድ" የሚል ዘር እንጂ ሃይማኖት አይደለም፥ "ክርስትና" የሚለውንም ቃል ኢየሱስ ሆነ ሐዋርያት የማያውቁት ሲሆን "ክርስትና" ብሎ ለመጀመርያ ጊዜ ያሰፈረው አግናጥዮስ ዘአንጾኪያው"Ignatius of Antioch" በ 110 ድኅረ ልደት ነው።
ስለ ኢሥላም ግን በግሥ መደብ ደረጃ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ ይገኛል፦
መዝሙር 56፥12 አምላክ ሆይ! እኔ የምስጋና ስእለት "የምሰጥህ" ከእኔ ዘንድ ነው። עָלַ֣י אֱלֹהִ֣ים נְדָרֶ֑יךָ אֲשַׁלֵּ֖ם תֹּודֹ֣ת לָֽךְ׃

"የምሰጥ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "አሻሌም" אֲשַׁלֵּ֖ם ሥርወ ቃሉ "ሸለም" שָׁלַם ሲሆን "ታዘዘ" "ተገዛ" የሚል ነው፥ በዐረቢኛ "ዩሥሊም" يُسْلِمْ ሲባል እራስን ለአሏህ መስጠት ነው፦
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አሏህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፡፡ የነገሩም ሁሉ ፍጻሜ ወደ አሏህ ነው፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ ۗ وَإِلَى اللَّهِ عَاقِبَةُ الْأُمُورِ

"የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ እንደሆነ ልብ አድርግ! አንድ ሰው "ከአንዱ አምላክ ከአሏህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም" ሲል ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ፥ "ስእለት" ማለት "ብፅዓት" "ስጦታ" ማለት ሲሆን ለአምላክ የሚሰጠው ትልቁ ስእለት ውስጥን መስጠት ነው፦
ሉቃስ 11፥40 እናንት ደንቆሮዎች የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።

"በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ" ሲል ለአምላክ ውስጥን መስጠት ኢሥላም ይባላል። አምላክ ያለውን ሁሉ ማድረግ እና መታዘዝ ኢሥላም ይባላል፦
ዘጸአት 24፥7 የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፦ “አምላክ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም" አሉ።

ለአንዱ አምላክ በአምልኮ መገዛት ኢሥላም ከሆነ በመለኮታዊ ቅሪት ውስጥ ከጥንት ጀምሮ ነፍስን ለአምላክ የማስገዛት እሳቤ አለ፦
መዝሙር 62፥1 ነፍሴ ለአምላክ የምትገዛ አይደለችምን?
መዝሙር 2፥11 ለአምላክ በፍርሃት ተገዙ! በረዓድም ደስ ይበላችሁ።
መዝሙር 100፥2 በደስታም ለአምላክ ተገዙ! በሐሤትም ወደ ፊቱ ግቡ።
ያዕቆብ 4፥7 እንግዲህ ለአምላክ ተገዙ! ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል።

ኢንሻ አሏህ ክፍል ሁለት ይቀጥላል........

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ኢሥላም እና ሙሥሊም

ክፍል ሁለት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ የተወደደ ሃይማኖት ኢሥላም ብቻ ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

"ኢሥላም" إِسْلَام ማዕዘናቱ ጦም፣ ሶላት፣ ዘካህ ወዘተ ናቸው፥ ለምሳሌ፦ ጦም ከነቢያችን"ﷺ" በነበሩት ነቢያት እና ሕዝቦቻቸው እንደተደገገ አሏህ ይናገራል። ወደ ነቢያት መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረደ፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ጦም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ
21፥73 በትእዛዛችንም ወደ በጎ ሥራ የሚመሩ መሪዎች አደረግናቸው፡፡ ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን፡፡ ለእኛ ተገዢዎችም ነበሩ፡፡ وَجَعَلْنَاهُمْ أَئِمَّةً يَهْدُونَ بِأَمْرِنَا وَأَوْحَيْنَا إِلَيْهِمْ فِعْلَ الْخَيْرَاتِ وَإِقَامَ الصَّلَاةِ وَإِيتَاءَ الزَّكَاةِ ۖ وَكَانُوا لَنَا عَابِدِينَ

"በትእዛዛችን" የሚለው ይሰመርበት! ይህም ትእዛዝ ኢሥላም ሲሆን በኢሥላም ማዕቀፍ ጦም፣ ሶላት፣ ዘካህ ወዘተ ከአሏህ የተወረደ ግልጠተ መለኮት ስለሆነ "ወደ እነርሱም መልካም ሥራዎችን መሥራትን፣ ሶላትንም መስገድን፣ ዘካንም መስጠትን አወረድን" ይለናል፥ ይህንን መመሪያ የተከተሉት ለአሏህ ተገዢዎችም ነበሩ። ከሰው ወገን ለመጀመርያ አሏህ ወሕይ ያወረደው ወደ አደም ነው፦
20፥115 ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን በእርግጥ አወረድን፡፡ وَلَقَدْ عَهِدْنَآ إِلَىٰٓ ءَادَمَ مِن قَبْلُ

"ከዚህ በፊት" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! "ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን ጊዜን ታሳቢ ያደረገ ነው፥ "ከዚህ በፊት" አሏህ በአደም ጊዜ "ታዛዦች" ብሎ ሰየመ፦
22፥78 "እርሱ "ከዚህ በፊት" "ሙሥሊሞች" ብሎ ሰይሟችኋል፡፡ هُوَ سَمَّاكُمُ الْمُسْلِمِينَ مِن قَبْلُ

"ከዚህ በፊት" ለሚለው የገባው ቃል "ሚን ቀብሉ” مِنْ قَبْلُ ሲሆን የአደምን ጊዜ ያስታውሰናል። "እርሱ" የተባለው "አሏህ" የሚለውን ስም ተክቶ የመጣ ተውላጠ ስም ነው፥ አሏህ ወደ አደምም ከዚህ በፊት ኪዳንን ሲያወርድ "ሙሥሊሞች" ብሎ የጠራን ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት አንዱን አምላክ በአምልኮ "ታዛዥ" ማለት ነው፦
29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፥ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን»። وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ሲሆን "ሙሥሊም" مُسْلِم ለሚለው ቃል ብዜት ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት እራሱ ለአሏህ በአምልኮ የሚታዘዙ ናቸው፦
3፥83 በሰማያት እና በምድር ያሉ በውድም በግድም ለእርሱ "የታዘዙ" ወደ እርሱም የሚመለሱ ሲኾኑ ከሓዲዎች ከአሏህ ሃይማኖት ሌላን ይፈልጋሉን? أَفَغَيْرَ دِينِ اللَّهِ يَبْغُونَ وَلَهُ أَسْلَمَ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ طَوْعًا وَكَرْهًا وَإِلَيْهِ يُرْجَعُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት ሆነ በምድር ላይ ያሉት ሰዎች በግዴታ አሏህ ላስቀመጠው የተፈጥሮ ሕግ የታዘዙ ሲሆኑ በውዴታ ደግሞ ለሸሪዓው ሕግ ይታዘዛሉ። "ከርህ" كَرْه ማለት "ግዳጅ" ማለት ሲሆን "ጦውዕ" طَوْع ማለት ደግሞ "ፈቃደኝነት" ማለት ነው፥ በሰማያት ያሉት መላእክት ሆነ በምድር ላይ ያሉት ሰዎች ለአሏህ በግዴታ መታዘዛቸው "አል ኢሥላም ከውኒይ" الإِسْلَام كَوْنِيّ ሲባል በውዴታ መታዘዛቸው "አል ኢሥላም ሸርዒይ" الإِسْلَام شَرْعِيّ ይባላል። "ሰው ሲወለድ ሙሥሊም ነው" የሚባለው አል ኢሥላም ከውኒይ ሲሆን አምላካችን አሏህ በሸሪዓህ "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲለን አል ኢሥላም ሸርዒይ ነው፦
5፥44 እነዚያ ትእዛዝን የተቀበሉት ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በርሷ ይፈርዳሉ፡፡ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا
እዚህ አንቀጽ ላይ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለሙ" أَسْلَمُوا ሲሆን "የታዘዙ" ማለት ነው። ኢብራሂም ወደ ጌታው በንጹሕ ልብ የመጣ ሰው ነው፦
37፥84 ወደ ጌታው "በ-ንጹሕ ልብ” በመጣ ጊዜ የኾነውን አስታውስ!፡፡ إِذْ جَاءَ رَبَّهُ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ
26፥89 ወደ አሏህ "በ-ንጹሕ ልብ" የመጣ ሰው ቢኾን እንጂ፡፡ إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ንጹሕ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ሠሊም" سَلِيم ነው፥ አንድ በኢሥላም ልቡን ሢያሠልም ልቡ ውስጥ "ሠላም" سَلَام ስላለ ልቡ ሠሊም ስትሆን እርሱ ደግሞ "ሣሊም" سَالِم‎ ይሆናል፦
ኢማም አሕመድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 17027
ዐምር ኢብኑ ዐባሣህ እንደተረከው፦ "አንድ ሰው የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" ሆይ! ኢሥላም ምንድን ነው? ብሎ ጠየቀ፥ እርሳቸውም"ﷺ"፦ "ልብህን ለአሏህ ዐዘ ወጀል ማሥለም ነው" አሉት"። عَنْ عَمْرِو بْنِ عَبَسَةَ قَالَ قَالَ رَجُلٌ يَا رَسُولَ اللَّهِ مَا الْإِسْلَامُ قَالَ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنْ يُسْلِمَ قَلْبُكَ لِلَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

አንድ ሰው ልቡን ለአሏህ ካሠለመ ጀነት ይገባል፥ ልቡን ለአሏህ ያሠለመ ሰው ከጀሀነም ይድናል፦
አል አደቡል ሙፍረድ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 260
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለው፥ እስካልሠለማችሁ ድረስ ጀነት አትገቡም"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ‏:‏ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لاَ تَدْخُلُوا الْجَنَّةَ حَتَّى تُسْلِمُوا
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 12, ሐዲስ 163
ዐምር ኢብኑ አል ዓስ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "የሠለመ ዳነ"። عَنْ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ قَدْ أَفْلَحَ مَنْ أَسْلَمَ ‏"‏ ‏.‏

"ሠሊመ" سَلِمَ ማለት "ታዘዘ" "ሰጠ" "ሰላም ሆነ" ሲሆን በዕብራይስጥ "ሸሊመ" שׁ־ל־ם ነው፥ በዕብራይስጥ "ሙሽሊም" משלם ማለት "ታዛዥ" "ሠላማዊ" "እራሱን የሰጠ" ማለት ነው፦
ኢዮብ 22፥21 አሁንም ከእርሱ ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም በጎነት ታገኛለህ። הַסְכֶּן־נָ֣א עִמֹּ֑ו וּשְׁלם בָּ֝הֶ֗ם תְּֽבֹואַתְךָ֥ טֹובָֽה׃

"ሰላምም ይኑርህ" የግሥ መደብ "ዩሻልም" וּשְׁלם ሲሆን ሥርወ ቃል "ሸለም" שָׁלַם ነው፥ ባይብል ሀብ"Bible Hub" ይህንን ቃል ሲያብራራ እንዲህ ይላል፦ "በዐረቢኛ "ሠሊም" سَلِمَ ሲሆን "ደህና መሆን" "አስተማማኝ" "ከጥፋት ነጻ" "የበላይ" "መስጠት" "መስጠት ወይም ራስን ማስረከብ በተለይ ለአምላክ" በሥማዊ ግሥ "ሙሥሊም" እና በግሥ መሠረት "ኢሥላም" በመደበኛ ለአምላክ መታዘዝ ነው"Arabic سَلِمَ be safe, secure, free from fault, make over, resign to, resign or submit oneself, especially to God, whence participle Muslim, and infinitive Islam properly submission to God."

በመለኮታዊ ቅሪት እንዲህ ዓይነት ቃል እና አሳብ ከቀረ ነቢያቱ ከአምላክ በቀጥታ በመጣላቸው በሥርወ መሠረቱ ምን ሊኖር እንደሚችል መገመት አያዳግትም፥ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ግልጠተ መለኮት የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልእክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት የተላለፈበት ሰነድ በዚህ ዘመን የለም። ጌታዬ ሆይ! ሙሥሊም ሆኜ ውሰደኝ፥ በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ! ሙሥሊሞች ኾነን ውሰደን፦
12፥101 «ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ፡፡ ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፡፡ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፡፡ ሙሥሊም ሆኜ ውሰደኝ፡፡ በመልካሞቹም አስጠጋኝ» አለ፡፡ رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ ۚ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَنتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۖ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ
7፥126 «የጌታችንም ተአምራት በመጡልን ጊዜ ከማመናችን በቀር ከእኛ አትጠላም፡፡ ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ! ሙሥሊሞች ኾነን ውሰደን» وَمَا تَنقِمُ مِنَّا إِلَّا أَنْ آمَنَّا بِآيَاتِ رَبِّنَا لَمَّا جَاءَتْنَا ۚ رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَتَوَفَّنَا مُسْلِمِينَ

አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ሙሥሊም አርጎ ይውሰደን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በቅርብ ቀን ኢንሻ አሏህ!
ማንም ሚሽነሪ ተነስቶ "ኢየሱስ ያድናል" በማለት የኩፍር እና የሺርክ ጎጆ ሠርቶ አይፈለፍላትም።
ሸምሥ እና ቀመር

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 ሌሊት እና ቀንም ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ

"ሸምሥ" شَّمْس ማለት "ፀሐይ" ማለት ሲሆን "ሸምሥ" شَّمْس የሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በሡረቱል በቀራህ ምዕራፍ 2 ቁጥር 258 ላይ ነው፦
2፥258 ወደዚያ አሏህ ንግሥናን ስለሰጠው ኢብራሂምን በጌታው ነገር ወደ ተከራከረው ሰው አላየህምን? ኢብራሂም «ጌታዬ ያ ሕያው የሚያደርግ እና የሚያሞት ነው» ባለ ጊዜ «እኔ ሕያው አደርጋለሁ አሞታለሁም» አለ፡፡ ኢብራሂም፡- «አሏህ ፀሐይን ከምሥራቅ በኩል ያመጣል፥ አንተ ከምዕራብ በኩል አምጣት» አለው፡፡ ያም የካደው ሰው ዋለለ እና መልስ አጣ፥ አሏህም በዳዮች ሕዝቦችን አይመራም፡፡ أَلَمْ تَرَ إِلَى الَّذِي حَاجَّ إِبْرَاهِيمَ فِي رَبِّهِ أَنْ آتَاهُ اللَّهُ الْمُلْكَ إِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ رَبِّيَ الَّذِي يُحْيِي وَيُمِيتُ قَالَ أَنَا أُحْيِي وَأُمِيتُ ۖ قَالَ إِبْرَاهِيمُ فَإِنَّ اللَّهَ يَأْتِي بِالشَّمْسِ مِنَ الْمَشْرِقِ فَأْتِ بِهَا مِنَ الْمَغْرِبِ فَبُهِتَ الَّذِي كَفَرَ ۗ وَاللَّهُ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الظَّالِمِينَ

"ሸምሥ" شَّمْس የሚለው ቃል ለመጨረሻ ጊዜ የተጠቀሰው በሡረቱ አሽ ሸምሥ ምዕራፍ 91 ቁጥር 1 ላይ ነው፦
91፥1 በፀሐይና በብርሃኗ እምላለሁ፡፡ وَالشَّمْسِ وَضُحَاهَا

በሡረቱል በቀራህ ምዕራፍ 2 ቁጥር 258 ላይ እና በሡረቱ አሽ ሸምሥ ምዕራፍ 91 ቁጥር 1መካከል ያለው የአናቅጽ ብዛት 5778 ነው፥ የፀሓይ የሙቀት መጠን"Temperature" በኬልቪን"kelvin" ሲለካ 5778 k የገጽታ ምስል"Photosphere" ይሆናል።

"ቀመር" قَمَر ማለት "ጨረቃ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ በቁርኣን "ቀመር" قَمَر የሚለውን ቃል የተጠቀመው "27" ጊዜ ብቻ ነው፥ የጨረቃ ፈለክ ምድራችንን በ 384,408 km በሆነ ዑደት”Revolution” ለመዞር የሚወስድባት ጊዜ 27 ቀናት ነው።
"ሠናህ" سَنَة ማለት "ዓመት" ማለት ሲሆን "ሠናህ" سَنَة የሚለው ቃል በቁርኣን የተጠቀሰው "19" ጊዜ ብቻ ነው፥ ጨረቃ ፕላኔታችንን በምእራባዊ አቅጣጭ 360 ድግሪ ለመዞር 19 ዓመት ይፈጅባታል። ይህ የሆነበት ምክንያት የዓለማቱ ጌታ አሏህ ነገርን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ነው፦
72፥28 እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር እውቀቱ የከበበ እና "ነገሩን ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ" ሲሆን የጌታቸውን መልእክቶች ያደረሱ መሆናቸውን ያውቅ ዘንድ ጠባቂ ያደርጋል። لِّيَعْلَمَ أَن قَدْ أَبْلَغُوا رِسَالَاتِ رَبِّهِمْ وَأَحَاطَ بِمَا لَدَيْهِمْ وَأَحْصَىٰ كُلَّ شَيْءٍ عَدَدًا

ፀሐይ እና ጨረቃ የዓለማቱ ጌታ አሏህ ለመኖሩ ከምልክቶቹ ናቸው። ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፦
41፥37 ሌሊት እና ቀንም ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው። ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

አምላካችን አሏህ እነዚያ ቆመው እና ተቀምጠው፣ በጎኖቻቸው ተጋድመው እርሱ የሚያወሱ እና በበፈጠረው ፍጥረት አፈጣጠር የሚያስተነትኑ ከሆኑት ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሏህ ታማኝ ነው!

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥23 እርሱ አሏህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፣ ከጉድለት ሁሉ የጠራ፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኃያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አሏህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ

ከአሏህ በቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም። "አል መሊክ" الْمَلِك ማለት "ንጉሡ" ማለት ነው፣ አል ቁዱሥ" الْقُدُّوسُ ማለት "ቅዱሱ" "ከጉድለት ሁሉ የጠራ" ማለት ነው፣ "አሥ ሠላም" السَّلَام ማለት "የሰላም ባለቤት" ማለት ነው፣ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ማለት "ታማኝ" "ጸጥታን ሰጪው" ማለት ነው፣ "አል ሙሀይሚን" الْمُهَيْمِن ማለት "ጠባቂው" ማለት ነው፣ "አል ዐዚዝ" الْعَزِيز ማለት "አሸናፊው" ማለት ነው፣ "አል ጀባር" الْجَبَّار ማለት "ኃያሉ" ማለት ነው፣ "አል ሙተከቢር" الْمُتَكَبِّر ማለት "ታላቁ" "ኩሩው" ማለት ነው፦
59፥23 እርሱ አሏህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ፣ ንጉሡ፣ ከጉድለት ሁሉ የጠራ፣ የሰላም ባለቤቱ፣ ጸጥታን ሰጪው፣ ባሮቹን ጠባቂው፣ አሸናፊው፣ ኃያሉ፣ ኩሩው ነው፡፡ አሏህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጸጥታን ሰጪው" ለሚለው የገባው ቃል "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ሲሆን "ታማኝ"Faithful" ማለት ነው፥ አሏህ የተናገረው ነገር፣ የገባውን ኪዳን እና የሰጠውን ተስፋ በመፈጸም ታማኝ ነው። ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች፦ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ማለት "አማኝ" ማለት ነው፥ አሏህ አማኝ ነው" በማለት ለፍጡር የሚውለውን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
16፥97 ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ "አማኝ" ኾኖ በጎን የሠራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً

እዚህ አንቀጽ ላይ "አማኝ" ለሚለው የገባው ቃል "ሙእሚን" مُؤْمِن ሲሆን ለአሏህን ግን "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ማለት "ታማኝ" እንጂ "አማኝ" የሚለውን አያሲዝም። ለምሳሌ፦ አሏህ "ሸሂድ" شَهِيدٌ ነው፦
22፥17 አሏህ በነገሩ ሁሉ ላይ በእርግጥ ዐዋቂ ነውና፡፡ إِنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ዐዋቂ" ለሚለው የገባው ቃል "ሸሂድ" شَهِيدٌ ነው፥ አሏህ "ምስክር" ነው፦
6፥19 «በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነው?» በላቸው፡፡ ሌላ መልስ የለምና «አሏህ ነው፡፡ በእኔ እና በእናንተ መካከል "መስካሪ" ነው» በላቸው። قُلْ أَيُّ شَيْءٍ أَكْبَرُ شَهَادَةً ۖ قُلِ اللَّهُ ۖ شَهِيدٌ بَيْنِي وَبَيْنَكُمْ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ምስክር" ለሚለው የገባው ቃል "ሸሂድ" شَهِيدٌ ነው፥ "ሸሂድ" شَهِيدٌ ማለት "ሰማዕት" በሚል ይመጣል፦
4፥69 አሏህን እና መልእክተኛውን የሚታዘዝ ሰው እነዚያ ከእነዚያ አሏህ በእነርሱ ላይ ከለገሳቸው ከነቢያት፣ ከጻድቃን፣ ከሰማዕታት፣ ከመልካሞቹ ጋር ይኾናሉ፡፡ የእነዚያም ጓደኝነት አማረ፡፡ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَالرَّسُولَ فَأُولَـٰئِكَ مَعَ الَّذِينَ أَنْعَمَ اللَّهُ عَلَيْهِم مِّنَ النَّبِيِّينَ وَالصِّدِّيقِينَ وَالشُّهَدَاءِ وَالصَّالِحِينَ ۚ وَحَسُنَ أُولَـٰئِكَ رَفِيقًا

"ሹሀዳእ" شُّهَدَاء ማለት "ሰማዕታት" ማለት ሲሆን "ሸሂድ" شَهِيدٌ ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ "ሸሂድ" شَهِيدٌ ሲባል አሏህ "ዐዋቂ" "ምስክር" በሚል እንጂ "ሰማዕት" በሚል እንደማንረዳው ሁሉ በተመሳዳይ አሏህ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ሲባል አሏህ "ጸጥታን ሰጪው" "ታማኝ" በሚል እንጂ "አማኝ" በሚል አንረዳውም። ተጨማሪ ምሳሌ፦ አሏህ "አት ተዋብ" التَّوَّاب ነው፦
2፥160 እኔም "ጸጸትን በጣም ተቀባይ" አዛኙ ነኝ፡፡ وَأَنَا التَّوَّابُ الرَّحِيمُ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ጸጸትን በጣም ተቀባይ" ለሚለው የገባው ቃል "አት ተዋብ" التَّوَّاب ሲሆን "ይቅር ባይ" ማለት ነው። ነገር ግን "ተዋብ" تَّوَّاب የሚለው ቃል "በንስሓ ወደ አሏህ ተመላሽ" በሚል ቃል ይመጣል፦
2፥222 "አሏህ "ከኃጢአት ተመላሾችን" ይወዳል፥ ተጥራሪዎችንም ይወዳል" በላቸው፡፡  إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ التَّوَّابِينَ وَيُحِبُّ الْمُتَطَهِّرِينَ

"ተዋቢን" تَّوَّابِين ማለት "ከኃጢአት ተመላሾችን" ማለት ሲሆን "ተዋብ" تَّوَّاب ሚለው ብዙ ቁጥር ነው፥ አሏህ "ተዋብ" تَّوَّاب ሲባል አሏህ "ጸጸትን ተቀባይ" "ይቅር ባይ" በሚል እንጂ "በንስሓ ወደ አሏህ ተመላሽ" በሚል እንደማንረዳው ሁሉ በተመሳዳይ አሏህ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ሲባል አሏህ "ጸጥታን ሰጪው" "ታማኝ" በሚል እንጂ "አማኝ" በሚል አንረዳውም።

ዐረቢኛ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም እንደሌለው እሙን ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹ ምህዋር፣ የምዕራፉ አውታር፣ የመጽሐፉ ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው።
እሩቅ ሳንሄድ አምላክ በባይብል "ምስክር" ተብሎአል፦
ኤርምያስ 29፥22 እኔም አውቃለሁ "ምስክርም" ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
1ኛ ሳሙኤል 20፥23 አንተ እና እኔ ስለ ተነጋገርነው እነሆ እግዚአብሔር ለዘላለም በመካከላችን "ምስክር" ነው። καὶ τὸ ρῆμα ὃ ἐλαλήσαμεν ἐγὼ καὶ σύ, ἰδοὺ Κύριος μάρτυς ἀνὰ μέσον ἐμοῦ καὶ σοῦ ἕως αἰῶνος.

እዚህ ጥቅስ ላይ "ምስክር" ለሚለው በግሪክ ሰፕቱአጀንት የገባው ቃል "ማርትይስ" μάρτυς ነው፥ ነገር ግን "ማርትይስ" μάρτυς የሚለው ቃል "ሰማዕት" በሚል ይመጣል፦
የሐዋርያት ሥራ 22፥20 "የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር" አልሁ። καὶ ὅτε ἐξεχύννετο τὸ αἷμα Στεφάνου τοῦ μάρτυρός σου, καὶ αὐτὸς ἤμην ἐφεστὼς καὶ συνευδοκῶν καὶ φυλάσσων τὰ ἱμάτια τῶν ἀναιρούντων αὐτόν.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ሰማዕት" ለሚለው የገባው ቃል "ማርትይስ" μάρτυς ነው። እና ያህዌህ ሰማዕት ነውን? "አይ "ማርትይስ" μάρτυς ለያህዌህ "ምስክር" ማለት ነው፥ ለእስጢፋኖስ ደግሞ "ሰማዕት" ማለት ነው" ከተባለ እንግዲያውስ እኛም፦ "አል ሙእሚን" الْمُؤْمِن ለአሏህ "ታማኝ" ማለት ነው፥ ለሰው "ሙእሚን" مُؤْمِن ደግሞ "አማኝ" ማለት ነው" እንላለን። አምላክ ደግሞ "ታማኝ" ነው፦
ኤርሚያስ 42፥5 እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛ እና "ታማኝ" ምስክር ይሁን።

ስለዚህ "አሏህ አማኝ ነው፥ የሚያምነው ምንድን ነው" ብላችሁ ላፀፃችሁት አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of Equivocation" መልሱ ይህንን ይመሳል፥ "አንድ ቃልን ለሁለት የተለያዩ ነገሮችን የሚለውን"Two different things by the same word" አንድ ነገር አርጎ መውሰድ አሻሚ ሕፀፅ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ያልተወለደ አምላክ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ጥንት ላይ የነበሩ ነቢያት እንዲሁ ኢየሱስ እና ሐዋርያት አሓዳዊያን"Unitarian" የነበሩ ሲሆን ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱ የቤተክርስቲያን አበው ደግሞ በሂደት "አንድ አምላክ አብ ነው፥ ኢየሱስ ሁለተኛ አምላክ ሌላ አምላክ ነው" የሚል አቋም ያላቸው "ክልዔታውያን"Binitarian" ነበሩ። ከክልዔታውያን አበው መካከል ከ 100 እስከ 165 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ዮስጦስ ሰማዕቱ"Justin Martyr" ስለ አልተወለደው አምላክ "ብቸኛውን ያልተወለደ አምላክ"The only unbegotten God" በማለት እንዲህ ይለናል፦
"እኛም እንዲሁ ደግሞ በቃሉ ስላሳመንን ከእነርሱ(ከአጋንንት) ርቀን ቆመን "ብቸኛውን ያልተወለደ አምላክ" በልጁ እንከተላለን"።
The First Apology (St. Justin Martyr) Chapter 14

"ብቸኛውን ያልተወለደ አምላክ" የሚለው ይሰመርበት! ይህ አምላክ ብቻ የማይወለድ እና የማይሞት ነው፥ ምክንያቱም እርሱ አምላክ ነው። ነገር ግን ከእርሱ ወዲህ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩ እና የሚሞቱ ናቸው፦
"አምላክ ብቻ የማይወለድ እና የማይሞት ነው፥ ምክንያቱም እርሱ አምላክ ነው። ነገር ግን ከእርሱ ወዲህ ያሉት ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩ እና የሚሞቱ ናቸው"።
Dialogue with Trypho (Justin Martyr) Chapter 5

አስቂም አሰቃቂም የሚሆነው ይህ ያልተወለደ አምላክ "የሰማይ ነገርን ሁሉ ትቶ በትንሽ የምድር ክፍል ላይ ታየ" የማይባል መሆኑን መናገሩ ነው፦
"በጣም ትንሽ ዕውቀት ያለው ሰው ካልሆነ በቀር፦"የሁሉም ነገር ፈጣሪ እና አባት የሰማይ ነገርን ሁሉ ትቶ በትንሽ የምድር ክፍል ላይ ታየ" ብሎ ለማስረገጥ አይደፈርም"።
Dialogue with Trypho (Justin Martyr) Chapter 60

ከ 130 እስከ 202 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ኢራንዮስ ዘልዮን"Irenaeus of Lyon" ይህ አንድ አምላክ "ለተፈጠሩ ነገሮች ሁሉ አይገዛም" በማለት ተናግሯል፦
"አምላክ ለተፈጠሩ ነገሮች ሁሉ አይገዛም፥ ነገር ግን የተፈጠሩ ነገሮች ሁሉ ለአምላክ ይገዛሉ"።
Against Heresies (St. Irenaeus) Book V(5), Chapter 5 Number 2

ከ 169 እስከ 183 ድኅረ ልደት የአንጾኪያ ኤጲስ ቆጶስ የነበረው ቴዎፍሎስ ዘአንጾኪያ"Theophilus of Antioch" ደግሞ አንዱ አምላክ ጅማሮ የሌለው፣ ያልተወለደ፣ የማይለወጥ፣ የማይሞት እንደሆነ ነግሮናል፦
"እርሱ ጅማሮ አልባ ነው፥ ምክንያቱም ያልተወለደ ነው። እርሱ የማይለወጥ ነው፥ ምክንያቱም እርሷ የማይሞት ነው"።
To Autolycus (Theophilus of Antioch) Book I(1) Chapter 4

ከ 313 እስከ 386 ድኅረ ልደት ይኖር የነበረው ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም"Cyril of Jerusalem" አንድ አምላክ የሚለው የክርስቶስን አባት ሲሆን ስለ አልተወለደው አንዱ አምላክ፦ "አምላክ አንድ፣ ብቻውን ያልተወለደ፥ መጀመሪያ፣ ለውጥ፣ ወይም ልዩነት የሌለው ነው" ይለናል፦
፨ "አንድ አምላክ አለ፥ እርሱም የክርስቶስ አባት ነው"።
Catechetical Lectures (Cyril of Jerusalem) Lecture 4 Number 16
፨ "በመጀመሪያ ስለ አምላክ ያለው ትምህርት በነፍስህ ውስጥ እንደ መሠረት ይኑር! አምላክ አንድ፣ ብቻውን ያልተወለደ፥ መጀመሪያ፣ ለውጥ፣ ወይም ልዩነት የሌለው ነው"።
Catechetical Lectures (Cyril of Jerusalem) Lecture 4 Number 4

እንደ ክልዔታውያን እምነት አንዱ አምላክ ያልተወለደ አብ ሲሆን ኢየሱስ ግን "ሁለተኛ አምላክ" "ሌላ አምላክ" ነው፦
፨ "ቢሆንም እኛ "ሁለተኛ አምላክ" ብለን ልንጠራው እንችላለን፥ "ሁለተኛ አምላክ" በሚለው ቃል ስንጠራው ሌሎችን በጎነቶችን የማካተት ችሎታ ካለው በጎነት በቀር ምንም ማለት እንዳልሆነ ይወቁ።
Origen Against(Contra) Celsum, Book 5 chapter 39
፨ "መጻሕፍትን ስለ ተረዳችሁ ላሳምናችሁ እሞክራለሁ፥ እኔ ከምለው ነገር አለ እና አለ ከተባለው፣ ለሁሉን ነገር ፈጣሪ የሚገዛ "ሌላ አምላክ" እና ጌታ አለ። እርሱም መልአክም ተብሎም ተጠርቷል"።
Justin Martyr, Dialogue with Trypho, chapter 56
በዚህ ዳራ በ325 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት የተጠራው የኒቂያ ጉባኤ የማታ ማታ ኢየሱስን "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ብሎታል፥ "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ማለት "ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" ማለት ነው። "አምላክ አምላክን አህሎ እና መስሎ፣ ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ፣ ከአካል አካል ወስዶ ተወለደ" በማለት "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዮስ" Ο Θεός ο γιος ብለውታል፥ "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዮስ" Ο Θεός ο γιος ማለት "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" ማለት ነው።

"ሞኖጌኔስ" μονογενὴς የሚለው ቃል "ሞኖስ" μόνος እና "ጌኑስ" γένος ከሚል ሁለት ቃላት ውቅር ነው፥ "ሞኖስ" μόνος ማለት "ብቸኛ" ማለት ሲሆን "ጌኑስ" γένος ማለት ደግሞ "የተወለደ" ማለት ነው። ኮዴክስ አሌክሳንድሪነስ ኢየሱስን "ሞኖጌኔስ ሁዮስ" μονογενὴς υἱός ይለዋል፦
ዮሐንስ 1፥18 መቼም ቢሆን አምላክን ያየው አንድ ስንኳ የለም፥ በአባቱ እቅፍ ያለ ብቸኛ የተወለደ "ልጅ" ተረከው። Θεὸν οὐδεὶς ἑώρακεν πώποτε· μονογενὴς υἱός ὁ ὢν εἰς τὸν κόλπον τοῦ Πατρὸς, ἐκεῖνος ἐξηγήσατο.

"ሁዮስ" υἱός ማለት "ልጅ" ማለት ሲሆን "ሞኖ ጌኔስ ሁዮስ" μονογενὴς υἱός ማለት "ብቸኛ የተወለደ ልጅ"the only begotten son" ማለት ነው። ኮዴክስ ቫቲካነስን ደግሞ ኢየሱስን "ሞኖጌኔስ ቴዎስ" μονογενὴς υἱός ይለዋል፦
ዮሐንስ 1፥18 መቼም ቢሆን አምላክን ያየው አንድ ስንኳ የለም፥ በአባቱ እቅፍ ያለ ብቸኛ የተወለደ "አምላክ" ተረከው። Θεὸν οὐδεὶς ἑώρακεν πώποτε· μονογενὴς Θεὸς ὁ ὢν εἰς τὸν κόλπον τοῦ Πατρὸς, ἐκεῖνος ἐξηγήσατο.

"ቴዎስ" Θεὸς ማለት "አምላክ" ማለት ሲሆን "ሞኖ ጌኔስ ቴዎስ" μονογενὴς Θεὸς ማለት "ብቸኛ የተወለደ አምላክ"the only begotten God" ማለት ነው። "አንዱ አምላክ ሌላ እና ሁለተኛ አምላክ ወለደ" ማለትስ ጤነኛ ትምህርት ነውን? አምላክ አምላክን ከወለደ ያልተወለደ አምላክ እና የተወለደ አምላክ ካለ ስንት አምላክ አለ? በእርግጥ የእነርሱ እምነት "ያልተወለደ እግዚአብሔር" እና "የተወለደ እግዚአብሔር" የሚል ነው፦
ሃይማኖተ አበው ምዕራፍ 25 ቁጥር 2
"ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን፤ "ያልተወለደ እግዚአብሔር" አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው፥ "የተወለደ እግዚአብሔር" ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው።

በ381 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቀዳማይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የተጠራው የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ የማታ ማታ መንፈስ ቅዱስን "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ብሎታል፥ "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለት "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" ማለት ነው። እንደ ሥላሴአውያን አስተምህሮት መንፈስ ቅዱስ የሚባለው አምላክ ያልወለደ እና ያልተወለደ ነው፥ ይህ አምላክ በባሕርይ ግብሩ አይወልድም አይወለድም።
እኛ ሙሥሊሞች፦ "አሏህ አልወለደም፤ አልተወለደምም" ስንል እርር እና ምርር ብለው የሚያጨረጭራቸው እና የሚያንተከትካቸው በክርስትና ያልወለደ እና ያልተወለደ አምላክ መኖሩን ሲያውቁ ምን ይውጣቸው ይሆን? በእርግጥም እውነተኛው አምላክ አሏህ አልወለደም፤ አልተወለደምም፦
112፥3 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ያልተወለደ አምላክ አብ፣ የተወለደ አምላክ ኢየሱስ፣ ያልወለደ እና ያልተወለደ አምላክ መንፈስ ቅዱስ ከሚል እሹሩሩ እና እሽኮለሌ ውዝግብ ወጥታችሁ አንዱን እና እውነተኛውን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። የኢየሱስ አምላክ አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ

ዳዕወቱል አንቢያ ኢሥላማዊ ድርጅት ሚድያ እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በተለያዩ ፕላትፎርሞች ላይ አስተማሪ ዳዕዋዎችን እያሰራጨ የሚገኝ መሆኑ ይታወቃል፥ ➤ ዩቲዩብ :- https://www.youtube.com/@daio_YT07
➤ ፌስቡክ :-  https://www.facebook.com/daioFB07
➤ ቲክቶክ :- https://www.tiktok.com/@daio07
➤ ኢንስታግራም :- https://www.instagram.com/daio_in07
➤ ቴሌግራም :- https://tttttt.me/daio_TG07

ታድያ ሚድያዎችን ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆኑ የፎሎው ቻሌንጅ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል። በዚህ መርሐ ግብር 7 መቶ ሺህ ፎሎው በቲክ ቶክ ላይ ካገኘ ለወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ሥር ከቤት ለሚባረሩ ሠለምቴዎች 1 ሚልዮን ብር ለመስጠት ቃል ገብቷል። ይህንን ቅዱስ አሳብ ተከትሎ ቻሌንጁን ለማስጀመር ነገ ሐምሌ 23/2017 ከምሽቱ 03:00 ሰዓት ላይ በቲክቶክ ፕላትፎርም #ኡሥታዝ_ወሒድ ቤት የላይቭ ፕሮግራም ስለያዝን እርሶም ከወዳጆ ጋር እንድትገኙ በአክብሮት ተጠርተዋል። ሰዓቱ ሲደርስ ይህን የኡሥታዝ ወሒድ የቲክ ቶክ አካውንት ያስፈንጥሩ፦ https://www.tiktok.com/@wahidislamicapologist?_t=ZN-8yRUiX9fxbC&_r=1
የአብ ስም ኢየሱስ?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥45 መላእክት፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ ያበሥርሻል» ያሉትን አስታውስ!። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

መርየም በጌታዋ ቃላት አምናለች፥ የጌታዋ ቃላት "ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" የሚል ነው፦
66፥12 በጌታዋ ቃላት እና በመጻሕፍቱ አረጋገጠች፥ ከታዛዦቹም ነበረች፡፡ وَصَدَّقَتْ بِكَلِمَاتِ رَبِّهَا وَكُتُبِهِ وَكَانَتْ مِنَ الْقَانِتِينَ
3፥45 መላእክት፡- «መርየም ሆይ! አሏህ ከእርሱ በኾነው ቃል "ስሙ አል መሢሕ ዒሣ፣ የመርየም ልጅ፣ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ፣ ከባለሟሎችም በኾነ ልጅ" ያበሥርሻል» ያሉትን አስታውስ!። إِذْ قَالَتِ الْمَلَائِكَةُ يَا مَرْيَمُ إِنَّ اللَّهَ يُبَشِّرُكِ بِكَلِمَةٍ مِّنْهُ اسْمُهُ الْمَسِيحُ عِيسَى ابْنُ مَرْيَمَ وَجِيهًا فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ وَمِنَ الْمُقَرَّبِينَ

መርየም ከአሏህ በኾነው ቃላት ከተበሠረችበት ቃላት አንዱ ልጇ ስሙ "አል መሢሕ ዒሣ" መባሉ ነው፥ "ዒሣ" عِيسَى የሚለው ስም የልጇ የተጸውዖ ስሙ"Proper Name" ሲሆን "አል መሢሕ" الْمَسِيح ደግሞ የማዕረግ ስሙ"Generic Name" ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ "ያህሹዋ" יְהוֹשֻׁעַ የሚለው ስም የፍጡር ስም እንደሆነ ከዚህ ቀደም በአንድ መጣጥፍ አስቀምጫለው፥ መጣጥፉን ይመልከቱ፦ https://tttttt.me/Wahidcom/4033
ይህ ሆኖ ሳለ ከ 160 እስከ 240 ድኅረት ልደት ይኖር የነበረው ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ"Tertullian of Carthage" ኢየሱስ የአብ ስም እንደሆነ ተናግሯል፦
"የእግዚአብሔር አብ ስም ለማንም አልተገለጠም፥ በዚህ ጉዳይ ላይ የጠየቀው ሙሴ እንኳ ሌላ ስም ሰምቶ ነበር ዘጸአት 3፥13-6። ለእኛም በልጁ ተገለጠልን፥ አሁን ልጁ(ኢየሱስ) የአብ አዲስ ስም ነውና። እርሱ "በአባቴ ስም መጥቻለው" ዮሐንስ 5፥43 ብሎአልና፥ እንደገና "አባት ሆይ! ስምህን አክብረው" ብሎአልና። እንደገናም በግልጽ "ለሰጠከኝ ስምህን ገለጥሁላቸው" ዮሐንስ 17፥6 ብሎአል፥ ስለዚህም ስም የተቀደሰ እንዲሆን እንጸልያለን"።
On Prayer (Tertullian) Chapter 3

ጠርጡሊያኖስ "በእንተ ጸሎት"On Prayer" በሚል መድብሉ "በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ ስምህ ይቀደስ" ማቴዎስ 6፥9 በሚል ማብራሪያ በሰማይ የሚኖረው አብ የሚቀደሰው ስም "ኢየሱስ" የሚለው ስም እንደሆነ አብራርቷል፥ አሳቡን ስንረዳው ብሉይ ኪዳን ላይ ለሙሴ የተገለጠው ስም "ያህዌህ" አሮጌ የአብ ስም ሲሆን "ኢየሱስ" ደግሞ በአዲስ ኪዳን የተገለጠለ የአብ አዲስ ስም ነው። ጠርጡሊያኖስ በሚኖርበት በሦስተኛ ክፍለ ዘመን በ 215 ድኅረ ልደት ገደማ ሰባልስዮስ ዘሊብያ"Sabellius of Libya" እራሱ "ኢየሱስ የአብ ስም ነው" የሚል አቋም ነበረው፥ የእርሱ አንጃ እና ጎጥ ሰባልዮሳውያን"Sabellians" ይባላሉ።
ኢየሱስ "አባት ሆይ! ስምህን አክብረው" ብሎ በጸለየው መሠረት ከሆነ አብ ያከበረው ስም "ኢየሱስ" የሚለውን ስም ነው፥ የሲና ጥራዝ"Codex Sinaiticus" በሚባለው እደ ክታብ"Manuscript" ላይ "ስምህን" የሚል ተቀምጧል፦
ዮሐንስ 12፥28 አባት ሆይ! "ስምህን" አክብረው። ስለዚህም፦ “አከበርሁት ደግሞም አከብረዋለሁ” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። Πάτερ, δόξασόν σου τὸ ὄνομα. ἦλθεν οὖν φωνὴ ἐκ τοῦ οὐρανοῦ Καὶ ἐδόξασα καὶ πάλιν δοξάσω.

እዚህ የሲና ጥራዝ በሆነው እደ ክታብ ላይ "ሱ ቶ ኦኖማ" σου τὸ ὄνομα ማለት "ስምህን" ማለት ነው፥ ይህ ጥቅስ እልም ያለ ሰባልዮሳዊነት"Sabellianism" ነው። ቅሉ ግን የቫቲካን ጥራዝ"Codex Vaticanus" በሚባለው እደ ክታብ ላይ "ስሜን" የሚል ተቀምጧል፦
ዮሐንስ 12፥28 አባት ሆይ! "ስሜን" አክብረው። ስለዚህም፦ “አከበርሁት ደግሞም አከብረዋለሁ” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። Πάτερ, δόξασόν μου τὸ ὄνομα. ἦλθεν οὖν φωνὴ ἐκ τοῦ οὐρανοῦ Καὶ ἐδόξασα καὶ πάλιν δοξάσω.

እዚህ የቫቲካን ጥራዝ በሆነው እደ ክታብ ላይ "ሙ ቶ ኦኖማ" μου τὸ ὄνομα ማለት "ስሜን" ማለት ነው፥ "አባት ሆይ" እያለ የሚጸልየው ወልድ እስከሆነ ድረስ በሁለተኛ መደብ "ስምህ" ከሆነ የአብን ስም ሲያመለክት በመጀመርያ መደብ "ስሜን" ከሆነ የወልድን ስም ያመለክታል። የከበረው "ኢየሱስ" የሚለው ስም ስለሆነ "ስሜን" የሚለው ሥነ መለኮታዊ ውስብስብ"Theological Jargon" የለውም፥ ይህ እራሱን የቻለ ግጭትም ነው። ጥቅሉ ግን የእንግሊዝ ጥራዝ"Codex Angelicus" በሚባለው እደ ክታብ ላይ "ልጅህን" የሚል ተቀምጧል፦
ዮሐንስ 12፥28 አባት ሆይ! "ልጅህን" አክብረው። ስለዚህም፦ “አከበርሁት ደግሞም አከብረዋለሁ” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ። Πάτερ, δόξασόν σου τὸ Υἱόν. ἦλθεν οὖν φωνὴ ἐκ τοῦ οὐρανοῦ Καὶ ἐδόξασα καὶ πάλιν δοξάσω.

እዚህ የእንግሊዝ ጥራዝ በሆነው እደ ክታብ ላይ "ሱ ቶ ሁዮን" σου τὸ Υἱόν ማለት "ልጅህን" ማለት ነው፥ ኢየሱስ በትክክል ያለው የትኛውን ነው? "ስምህን" "ስሜን" "ልጅህን"? ይህንን መመዘኛ ሥረ መሠረታዊ የእጅ ጽሑፍ"Orginal Autography" ስለሌለ ለክርስትናው የቤት ሥራ ነው። "ልጅህን አክብረው" የሚለውን እንደ አማራጭ ብንይዝ እንኳን "ልጅህን አክብረው" የሚለው ድምዳሜ ላይ ያደርሳል፦
ዮሐንስ 17፥1 ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፦ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ "ልጅህን አክብረው"። Ταῦτα ἐλάλησεν Ἰησοῦς, καὶ ἐπάρας τοὺς ὀφθαλμοὺς αὐτοῦ εἰς τὸν οὐρανὸν εἶπεν Πάτερ, ἐλήλυθεν ἡ ὥρα· δόξασόν σου τὸν Υἱόν, ἵνα ὁ Υἱὸς δοξάσῃ σέ,

"ልጅህን አክብረው" የሚለው ይሰመርበት! ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዓይኖቹን አንሥቶ ለሚጸልየው ጸሎት የሰማዩ አምላክ “አከበርሁት ደግሞም አከብረዋለሁ” የሚል ድምፅ ከሰማይ አሰምቷል። በእርግጥ የአብርሃም፣ የይስሐቅ እና የያዕቆብ አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ ባሪያውን ኢየሱስን አከበረው፦
የሐዋርያት ሥራ 3፥13 የአብርሃም፣ የይስሐቅ እና የያዕቆብ አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቈርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን "ባሪያውን" ኢየሱስን አከበረው። ὁ Θεὸς Ἀβραὰμ καὶ Ἰσαὰκ καὶ Ἰακώβ, ὁ Θεὸς τῶν πατέρων ἡμῶν, ἐδόξασεν τὸν Παῖδα αὐτοῦ Ἰησοῦν, ὃν ὑμεῖς μὲν παρεδώκατε καὶ ἠρνήσασθε κατὰ πρόσωπον Πειλάτου, κρίναντος ἐκείνου ἀπολύειν·

"ፓይዳ" Παῖδα "ፓይዶስ" παιδὸς" "ፓይስ" παῖς ማለት "ባሪያ" ማለት ሲሆን ኢሳይያስ 42፥1 የብሉይ ኪዳን ግሪክ ሰፕቱጀንት ላይ ማቴዎስ 12፥18 የአዲስ ኪዳን ግሪክ ኮይኔ ላይ "ባሪያ" ለሚለው የገባው ቃል ተመሳሳይ ነው፥ "NIV" "NLT" "ESV" "NKJV" "NASB" የሚባሉ የተለያዩ የእንግሊዝኛ ዕትሞች"Versions" ሳያቅማሙ "ባሪያውን"his servant" ብለው አስቀምጠውታል። የኢየሱስ አምላክ የፍጡርን ስም ማክበሩ ብርቁ አይደለም፥ እሩቅ ሳንሄድ የአብርሃምን ስም አክብሮታል፦
ዘፍጥረት 12፥2 ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ "ስምህንም አከብረዋለሁ"፤ ለበረከትም ሁን።

"ስምህንም አከብረዋለሁ" የሚለው ይሰመርበት! ፈጣሪ የአብርሃምን ስም ማክበሩ "አብርሃም" የሚለው ስም የአብ አሊያም የአምላክ ስም እንዳማያደርገው ሁሉ ፈጣሪ የኢየሱስን ስም ማክበሩ "ኢየሱስ" የሚለው ስም የአብ አሊያም የአምላክ ስም አያደርገውም። ስለዚህ "ኢየሱስ" የሚለው ስም የአብ አሊያም የአምላክ ስም በፍጹም አይደለም። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 19ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadology"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ጀሙቲ፦ http://tttttt.me/Mydearprophet
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://tttttt.me/arhmanu
አኅት ዘሃራ፦ https://tttttt.me/Zhara_mustefa
እኅት ሐዊ https://tttttt.me/hawin922
እኅት ቢብት https://tttttt.me/Hewuli2

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
ዝምድና

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

47፥22 ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን እና ዝምድናዎቻችሁን መቁረጥን ከጀላችሁን? فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِن تَوَلَّيْتُمْ أَن تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ

ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ ተመሳሳይ ቃል ቢኖር እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም እንደሌለው እሙን ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው። ለምሳሌ፦ "ረሒም" رَّحِيم ማለት "አዛኝ" ማለት ነው፦
9፥128 ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ እምነት ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን ላይ ርኅሩኅ "አዛኝ" የኾነ መልእክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡ لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِّنْ أَنفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُم بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَّحِيمٌ

"በምእምናን ላይ ርኅሩኅ "ዝምድና" የኾነ መልእክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ" ወይም "በምእምናን ላይ ርኅሩኅ "ማኅፀን" የኾነ መልእክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ" ትርጉም ይሰጣልን? "ረሒም" رَّحِم ማለት "ማኅፀን" ማለት ነው፥ የረሒም ብዙ ቁጥር "አርሓም" أَرْحَام ሲሆን "ማኅፀኖች" ማለት ነው፦
3፥6 እርሱ ያ "በማኅፀኖች" ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው፡፡ هُوَ الَّذِي يُصَوِّرُكُمْ فِي الْأَرْحَامِ كَيْفَ يَشَاءُ

"እርሱ ያ "በአዛኞች" ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው" ወይም "እርሱ ያ "በዝምድናዎች" ውስጥ እንደሚሻ አድርጎ የሚቀርጻችሁ ነው" ትርጉም ይሰጣልን? "ረሒም" رَّحِم ማለት "ዝምድና" ማለት ነው፥ የረሒም ብዙ ቁጥር "አርሓም" أَرْحَام ሲሆን "ዝምድናዎች" ማለት ነው፦
47፥22 ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን እና ዝምድናዎቻችሁን መቁረጥን ከጀላችሁን? فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِن تَوَلَّيْتُمْ أَن تُفْسِدُوا فِي الْأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 78, ሐዲስ 18
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ፍጥረትን ሲፈጥርና ፍጥረቱን ፈጥሮ በጨረሰ ጊዜ፦ "ዝምድና፦ "ይህ ቦታ እኔ ከቆራጮች በአንተ እጠበቃለው" አለች፥ አሏህም፦ "አዎ! ከአንቺ ጋር የቀጠለን እንድቀጥል የቆረጠን እንድቆርጥ አትፈልጊምን? አለ። እርሷም፦ "እፈልጋለው! ጌታ ሆይ! አለች፥ አሏህም፦ "ይህ ላንቺ ይሁን" አለ"። የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ"፦ "ከፈቀዳችሁ፦ 47፥22 "ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?" የሚለውን አንቀጽ አንብቡ!" አሉ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ إِنَّ اللَّهَ خَلَقَ الْخَلْقَ حَتَّى إِذَا فَرَغَ مِنْ خَلْقِهِ، قَالَتِ الرَّحِمُ هَذَا مَقَامُ الْعَائِذِ بِكَ مِنَ الْقَطِيعَةِ‏.‏ قَالَ نَعَمْ أَمَا تَرْضَيْنَ أَنْ أَصِلَ مَنْ وَصَلَكِ‏.‏ وَأَقْطَعَ مَنْ قَطَعَكِ‏.‏ قَالَتْ بَلَى يَا رَبِّ‏.‏ قَالَ فَهْوَ لَكِ ‏"‌‏.‏ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ فَاقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ ‏{‏فَهَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ تَوَلَّيْتُمْ أَنْ تُفْسِدُوا فِي الأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ‏}‌‏"‌‏.‏

"አንድ ቃልን ለብዙ የተለያዩ ነገሮችን የሚውለውን"Many different things by the same Word" አንድ ነገር አርጎ መውሰድ "አሻሚ ሕፀፅ"Fallacy of Equivocation" ነው፥ እዚህ ሐዲስ ማብቂያ ላይ ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ" "ረሒም" رَّحِم የተባለችው ዝምድና እንደሆነች ለማመልከት የቁርኣኑን አንቀጽ ጠቅሰዋል። ቁርኣን እና ሐዲስ ላይ መቁረጥ እና መቀጠል ከዝምድና ጋር የተያያዘ ነው፦
4፥1 ያንንም በእርሱ የምትጠያየቁበትን አሏህን እና "ዝምድናዎችንም" ከመቁረጥ ተጠንቀቁ"፡፡ አሏህ በእናንተ ላይ ተጠባባቂ ነውና፡፡ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 65, ሐዲስ 451
አቢ ሁራይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ፍጥረትን ሲፈጥርና ፍጥረቱን ፈጥሮ በጨረሰ ጊዜ ዝምድና ተነስታ የአዛኙን አሏህ ልብስ ያዘች፥ አሏህም ለእርሷ፦ "ምንድን ነው? አላት። እርሷም፦ "ከነዚያ ዝምድናን ከሚቆርጡ ሰዎች በአንተ እጠበቃለሁ" አለች፥ አሏህም፦ "አዎ! ከአንቺ ጋር የቀጠለን እንድቀጥል የቆረጠን እንድቆርጥ አትፈልጊምን? አለ። እርሷም፦ "እፈልጋለው! ጌታ ሆይ! አለች፥ አሏህም፦ "ይህ ላንቺ ይሁን" አለ"። አቢ ሁራይራህ፦ "ከፈቀዳችሁ፦ 47፥22 "ብትሽሾሙም በምድር ላይ ማበላሸትን ዝምድናችሁንም መቁረጥን ከጀላችሁን?" የሚለውን አንቀጽ አንብቡ!" አለ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏"‏ خَلَقَ اللَّهُ الْخَلْقَ، فَلَمَّا فَرَغَ مِنْهُ قَامَتِ الرَّحِمُ فَأَخَذَتْ بِحَقْوِ الرَّحْمَنِ فَقَالَ لَهَا مَهْ‏.‏ قَالَتْ هَذَا مَقَامُ الْعَائِذِ بِكَ مِنَ الْقَطِيعَةِ‏.‏ قَالَ أَلاَ تَرْضَيْنَ أَنْ أَصِلَ مَنْ وَصَلَكِ وَأَقْطَعَ مَنْ قَطَعَكِ‏.‏ قَالَتْ بَلَى يَا رَبِّ‏.‏ قَالَ فَذَاكِ لَكِ ‏"‌‏.‏ قَالَ أَبُو هُرَيْرَةَ اقْرَءُوا إِنْ شِئْتُمْ ‏{‏فهَلْ عَسَيْتُمْ إِنْ تَوَلَّيْتُمْ أَنْ تُفْسِدُوا فِي الأَرْضِ وَتُقَطِّعُوا أَرْحَامَكُمْ‏}‏
ዝምድና ጠባይ እንጂ እራሷን የቻለች ማንነት ስላልሆነች ከአሏህ ጋር ያደረገችውን ንግግር "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ነው፥ "ኢስጢላሕ" اِصْطِلَاح ማለት "ፈሊጣዊ አገላለጽ"Idiomatic Expression" ነው። ለምሳሌ፦ በባይብል እራሳቸውን የቻሉ ማንነት ሳይኖራቸው የተናገሩ ቀላይ እና ባሕር ናቸው፦
ኢዮብ 28፥14 "ቀላይ፦ "በእኔ ውስጥ የለችም" ይላል፤ ባሕርም፦ "በእኔ ዘንድ የለችም" ይላል"። תְּהֹ֣ום אָ֭מַר לֹ֣א בִי־הִ֑יא וְיָ֥ם אָ֝מַ֗ר אֵ֣ין עִמָּדִֽי׃

ቀላይ እና ባሕር እራሳቸው የቻሉ ማንነት ሳይኖራቸው መናገራቸው ፈሊጣዊ አገላለጽ እንደሆነ ሁሉ የዝምድናን መናገር በዚህ መልክ እና ልክ መረዳት ይቻላል።
የዝምንድና መናገር ፍካሬአዊ እንደሆነ ሁሉ ዝምንድና መነሳቷ እና መያዟ ፍካሬአዊ ነው፥ መቼም "የአሏህ ልብስ" ሲባል ከጨርቅ የተሸመነ፣ የተደወረ፣ የተሰፋ ልብስ ማለት እንዳልሆነ ቅቡል ነው። የአዛኙን አሏህ ልብስ ደግሞ ግርማዊነት እንደሆነ እራሱ አቢ ሁራይራህ በተረከው ሠነድ ተቀምጧል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 71
አቢ ሁራይራህ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "አሏህ ዐዘ ወጀል፦ "ታላቅነት ካባዬ ነው፥ ግርማዊነት ልብሴ ነው" አለ"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، - قَالَ هَنَّادٌ - قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ قَالَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ الْكِبْرِيَاءُ رِدَائِي وَالْعَظَمَةُ إِزَارِي

"ዐዘማህ" عَظَمَة "ግርማዊነት" "ሞገስ" "ልዕልና" "ገናናነት" ማለት ነው፥ ካባ እና ልብስ በፍካሬአዊ እንጂ በእማሬያዊ የሚወሰድ እንዳልሆነ ይህ ሐዲስ ቁልጭ እና ፍንትው አርጎ ያሳያል። ያህዌህ እኮ ልብስ አለው፦
ኢሳይያስ 6፥1 ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት አዶናይን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ "የልብሱ" ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር። בִּשְׁנַת־מֹות֙ הַמֶּ֣לֶךְ עֻזִּיָּ֔הוּ וָאֶרְאֶ֧ה אֶת־אֲדֹנָ֛י יֹשֵׁ֥ב עַל־כִּסֵּ֖א רָ֣ם וְנִשָּׂ֑א וְשׁוּלָ֖יו מְלֵאִ֥ים אֶת־הַהֵיכָֽל׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ልብስ" ለሚለው የገባው ቃል "ሹል" שׁוּל ሲሆን "ቀሚስ" ማለት ነው፦
ዘጸአት 28፥34 የወርቅ ሻኵራ ሮማንም፥ ሌላም የወርቅ ሻኵራ ሮማንም በ"ቀሚሱ" ዘርፍ ዙሪያውን ይሆናሉ። פַּעֲמֹ֤ן זָהָב֙ וְרִמֹּ֔ון פַּֽעֲמֹ֥ן זָהָ֖ב וְרִמֹּ֑ון עַל־שׁוּלֵ֥י הַמְּעִ֖יל סָבִֽיב׃

እዚህ አንቀጽ ላይ "ቀሚስ" ለሚለው የገባው ቃል "ሹል" שׁוּל ነው፥ እና ያህዌህ ቃል በቃል ቀሚስ ይለብሳልን? ወይስ "ቀሚስ" ማለት "ክብር" "ኃይል" "ግርማ" ማለት ነው? እንደተግባባን ተስፋ አደርጋለው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
ዘፈን

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአሏህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት "አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ"፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ

"ዐዝፍ" عَزْف የሚለው ቃል "ዐዘፈ" عَزَفَ ማለትም "ሞዘቀ" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "ሙዚቃ" ማለት ነው፥ ሙዚቃ ሐራም መሆኑን በጥልቅ ያብራራው ከነቢያችን"ﷺ" ተወዳጅ ሶሓቢይ መካከል ኢብኑ መሥዑድ"ረ.ዐ." ነው። ከቀደምት ሠለፎች አንዱ እርሱ ቁርኣንን የተረዳበት መንገድ መረዳት የጤናማ ሥነ አፈታት ጥናት ነው፥ እርሱ ይህንን የቁርኣን አንቀጽ ይዞ ስለ ዘፈን እንዲህ ይላል፦
31፥6 ከሰዎችም ያለ ዕውቀት ሆኖ ከአሏህ መንገድ ሊያሳስትና ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት "አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ"፡፡ እነዚያ ለእነርሱ አዋራጅ ቅጣት አላቸው፡፡ وَمِنَ النَّاسِ مَن يَشْتَرِي لَهْوَ الْحَدِيثِ لِيُضِلَّ عَن سَبِيلِ اللَّهِ بِغَيْرِ عِلْمٍ وَيَتَّخِذَهَا هُزُوًا ۚ أُولَـٰئِكَ لَهُمْ عَذَابٌ مُّهِينٌ
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 31፥6
"ኢብኑ መሥዑድ እንደተናገረው፦ "ከሰዎችም ከአላህ መንገድ ሊያሳስት ማላገጫ አድርጎ ሊይዛት አታላይ ወሬን የሚገዛ አለ" የሚለው ወሏሂ እርሱ "ዘፈን" ነው"። كما قال ابن مسعود في قوله تعالى : ( ومن الناس من يشتري لهو الحديث ) قال : هو - والله - الغناء .

"ለህወል ሐዲስ" لَهْوَ الْحَدِيث ማለትም "አታላይ ወሬ" ማለት ሲሆን "ጊናእ" غِنَاء ነው፥ "ጊናእ" غِنَاء የሚለው ቃል "ገና" غَنَّى‎ ማለትም "ዘፈነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ዘፈን" ማለት ነው። አምላካችን አሏህ ኢብሊሥ የሚከተሉትን በድምጹ እንደሚያታልላቸው ተናግሯል፥ ይህም ድምጹ መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣ እና ስላቅ ነው፦
17፥64 ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል፡፡ وَاسْتَفْزِزْ مَنِ اسْتَطَعْتَ مِنْهُم بِصَوْتِكَ
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 17፥64
"ከእነርሱ የቻልከውንም ሰው በድምጽህ አታል" የተባለው እርሱ ዘፈን ነው፥ ሙጃሒድም አለ፦ "ድምጽ የተባለው መደበሪያ፣ ዘፈን፣ ላግጣና ስላቅ ነው"። واستفزز من استطعت منهم بصوتك قيل هو الغناء قال مجاهد باللهو والغناء أي استخفهم بذلك

እዚህ ተፍሢር ላይ "ዘፈን" ለሚለው የገባው ቃል "አል ጊናእ" الغِنَاء እንደሆነ ልብ አድርግ! "ሐላል" حَلَال ማለት "የተፈቀደ" ማለት ሲሆን “ሐራም” حَرَام ማለት "የተከለከለ" ማለት ነው፥ ዝሙት እና አስካሪ መጠጥ ሐራም እንደሆነ ሁሉ ሙዚቃም ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ ጋር ተያይዞ ክልክል መሆኑ በነቢያችን"ﷺ" ሐዲስ ተነግሯል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 74, ሐዲስ 16
አቡ ዐሚር ወይም አቡ ማሊኩል አሽዐሪይ እንደተረከው፦ "ወሏሂ አልዋሸውም! ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቷል፦ "ከኡመቴ ውስጥ ጥቂት ሰዎች ለራሳቸው ዝሙትን፣ ሐር ልብስን፣ አስካሪ መጠጥን እና ሙዚቃን ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ። قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو عَامِرٍ ـ أَوْ أَبُو مَالِكٍ ـ الأَشْعَرِيُّ وَاللَّهِ مَا كَذَبَنِي سَمِعَ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ "‏ لَيَكُونَنَّ مِنْ أُمَّتِي أَقْوَامٌ يَسْتَحِلُّونَ الْحِرَ وَالْحَرِيرَ وَالْخَمْرَ وَالْمَعَازِفَ

"ሙዚቃን ሐላል የሚያደርጉ ይሆናሉ" ማለት ሙዚቃ ሐራም ነው ማለት ነው። ዛሬ ላይ የጽዮናውያን አጀንዳ የተሰጣቸው ሰዎች ሙዚቃ፣ ዝሙት፣ ኸምር ሐላል እያረጉ ነው፥ "ሙዚቃ መልእክቱ እንጂ በጎ ነገር ከተላለፈበት ሐላል ነው" "ኒካሕ ማለት ሁለት ጥንዶች በተራክቦ መስማማት እንጂ ምስክር እና ወሊይ አያስፈልግም" "ድራግ የሆኑት ሻይ፣ ቡና እና ለስላሳ ለሰውነት እንደሚያስፈልግ ሁሉ ዝቅተኛ የአልኮል መጠን ያላቸውን አማሩላ፣ ሳንቡካ፣ ሚሎ ወዘተ ያስፈልጋል" የሚሉ ፈሣድን የሚያስፋፉ ብቅ እያሉ ያሉበት ሁኔታ የትንቢቱ ፍጻሜ ነው። የሚድያ ሰዎች ጥቅማቸው እንዳይጠርርባቸው አወዛጋቢ አጀንዳን በማንሳት የሚታወቁ ሲሆኑ እነዚህ ሙፍሠዲዎች በማቅረብ ያስተዋውቃሉ፥ ሙሥሊም ሆኖ ይህንን መድረክ የሚያዘጋጅ ሰው በፈሣዱ የሚጠሙትን ሰዎች የሚያገኛቸው ቅጣት ከእነርሱ ላይ ሳይቀነስ ሳይጨመር ይቀጣል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 210
አነሥ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው፤ የአሏህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ “ማንም ጠሪ ሰዎችን ወደ ጥመት የሚጣራ የተከተሉት ሰዎች የሚሸከሙትን ኃጢአት ከእነርሱ ላይ ሳይጓደል ይሸከማል"። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ أَيُّمَا دَاعٍ دَعَا إِلَى ضَلاَلَةٍ فَاتُّبِعَ فَإِنَّ لَهُ مِثْلَ أَوْزَارِ مَنِ اتَّبَعَهُ وَلاَ يَنْقُصُ مِنْ أَوْزَارِهِمْ شَيْئًا

አምላካችን አሏህ ከሙፍሢዶች ፈሣድ ይጠብቀን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://tttttt.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም