ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"
58.4K subscribers
68 photos
69 videos
19 files
1.72K links
ዳዒ ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!
Download Telegram
ሥነ-ፅንስ

ክፍል አንድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

31:34 አላህ የሰዓቲቱ እውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ #በማሕፀኖችም #ውስጥ #ያለን #ሁሉ #ያውቃል

መግቢያ
ሥነ-ፅንስ ጥናት ኢምብሪዮሎጂይ”Embryology” ሲባል “ኢምብሮ” ἔμβρυον “ያልተወለደ” እና “ሎጂአ” λογία, “ጥናት” ከሚል ሁለት የግሪክ ቃል የተዋቀረ ነው፤ ይህንን ፅንስ እናቱ ማህፀን ውስጥ በሚፈልገው መልኩ የሚቀርፀው አንዱ አምላክ አላህ ነው፦
3:6 እርሱ ያ “በማሕፀኖች” ዉሰጥ እንደሚሻ አድርጎ “የሚቀርጻችሁ” ነዉ፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፤

ይህ ፅንስ ማህፀን ውስጥ እንዴት እንደሚፈጠር ሙሉ እውቀት ያለው የዓለማቱ ጌታ አላህ ብቻ ነው፦
31:34 አላህ የሰዓቲቱ ዕውቀት እርሱ ዘንድ ብቻ ነው፤ ዝናምንም ያወርዳል፤ “በማሕፀኖችም ውስጥ ያለን ሁሉ ያውቃል”፤
53:32 ከምድር በፈጠራችሁ ጊዜ እናንተም በእናቶቻችሁ “ማሕፀኖች” ውስጥ ሽሎች በሆናችሁ ጊዜ እርሱ በእናንተ ሁኔታ “አዋቂ” ነው።
13:8 አላህ ሴት ሁሉ የምታረግዘውን ያውቃል፤ “ማሕፀኖችም የሚያጐድሉትን የሚጨምሩትንም፥ ያውቃል”፤ ነገሩም ሁሉ እርሱ ዘንድ በልክ የተወሰነ ነው።

በማሕፀኖችም ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያውቀ አምላክ የሥነ-ፅንስ እውቀት ወደፊት እንደሚያሳየና እንደሚያሳውቀን ለማመልከት፦ “በራሶቻችሁ ውስጥ ያሉትም ታምራት ወደፊት ያሳያችኋል፤ ታውቁታላችሁ” በማለት ቃል ገብቷል፦
41፥53 እርሱም ቁርአን እውነት መሆኑ ለነርሱ እስከሚገለጽላቸው ድረስ፣ በአጽናፎቹ ውስጥ እና #በራሶቻቸውም ውስጥ ያሉትን #ታምራቶቻችንን በእርግጥ #እናሳያቸዋለን፤ ጌታህም እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ መሆኑ አይበቃቸውምን?
27:93 ምስጋና ለአላህ ነው፤ #ታምራቶቹን #ወደፊት #ያሳያችኋል#ታውቁታላችሁ በላቸው።

አላህ ይህንን እውቀት በራሳችን አካላት ከማሳየቱ በፊት በቁርአን አንድ ሽል በማህፀን ውስጥ እንዴት የተለያየ ደረጃዎችን”stages” እንደሚያሳልፍ በተከበረ ቃሉ ይነግረናል፦
23:12 በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው፤ ከዚያም በተጠበቀ መርጊያ ውስጥ “የፍትወት ጠብታ” النُّطْفَةَ አደረግነው፤ ከዚያም ጠብታዋን “የረጋ ደም” عَلَقَةً አድርገን ፈጠርን፤ የረጋውንም ደም “ቁራጭ ሥጋ” مُضْغَةً አድርገን ፈጠርን፤ ቁራጯንም ሥጋ “አጥንቶች” عِظَامًا አድርገን ፈጠርን፤ አጥንቶቹንም ሥጋን لَحْمًا አለበስናቸው፤ ከዚያም “ሌላ ፍጥረትን” خَلْقًا آخَرَ አድርገን “አስገኘነው” أَنْشَأْنَاهُ፤ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡