ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ከገነት በተሰደደ ጊዜ #የአዳም ተስፋ አንቺ ነሽ፡፡ በግፍ የተገደለ #የአቤል የውሃቱ አንቺ
ነሽ፡፡ #የሴት ቸርነት አንቺ ነሽ፡፡ #የሄኖክ ሥራዎቹ ከክፉ ጥፋት የዳነባት #የኖህ መርከብ
#የሴም ቡራኬው ዕድል ፈንታውም አንቺ ነሽ፡፡
# የአብርሃም እንግድነት #የይስሃቅ መዓዛ #የያዕቆብም መሰላል አንቺ ነሽ፡፡
#ዮሴፍንም የምታረጋጊው አንቺ ነሽ፡፡
#የሙሴ ጽላት #ጳጦስ የተባለች የሲና ዕፅ በካህን #አሮን ልብስ የነበረች ጸናጽል
ዳግመኛም የበቀለች እና ያበበች ያፈራችም በትር አንቺ ነሽ፡፡ #የኢያሱ የምስክሩ ሐወልት
#የጌድዮን ፀምር #የሳሙኤል የሽቱ ሙዳይ እና የዘይት ቀንድ አንቺ
ነሽ፡፡ የተመካባት #የዕሴይ ሥር #የአሚናዳብ ሠረገላ #የዳዊት መሰንቆ #የሰሎሞንም
አክሊል አንቺ ነሽ፡፡ የታጠረች ተክል የተዘጋች የውሃ ምንጭ አንቺ ነሽ፡፡ #የኤልያስ የወርቅ
መሶብ #የኤልሳዕ ጋን አንቺ ነሽ፡፡ #ኢሳይያስ ፅንስን ከድንግልና ጋር የተናገረልሽ #ዳንኤልም ያለሩካቤ መውለድን የተናገረልሽ አንቺ ነሽ፡፡ #ፋራን የምትባል #የዕንባቆም
ተራራ የተዘጋች #የሕዝቅኤል ምስራቅ የቤቴ-ልሔም ሕግ መውጫ #ኤፍራታ የምትባል
ምድር አንቺ ነሽ፡፡ #የሲሎንዲስ ዕፀ ሕይወት #የናሆምንም ቁስል የምታድን #የዘካርያስ
ደስታው #የሚልክያስ ንፅሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ፡፡
#ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ቸር አምላካችንና
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ከሰማያዊ
ክብሩ ወደ ምድር ወርዶ: በማሕጸነ #ማርያም_እግዝእት
በኪነ ጥበቡ ተጸንሶ: በኅቱም ድንግልና ተወልዶ: በፈቃዱ
መከራ መስቀልን ተቀብሎ:
ከግራ ቁመት:
ከገሃነመ እሳት:
ከሰይጣን ባርነት:
ከኃጢአት ቁራኝነትም አድኖናል::
እምእቶነ እሳት ዘይነድድ አንገፈነ እንዳለ
ሊቁ::
ምንም መስቀል በብሉይ የወንጀለኞች መቅጫ ሆኖ
ቢቆይም እግዚአብሔር ለዓለም መዳኛነት የመረጠው
ነውና ሕብረ ትንቢቶች ሲነገሩለት: በብዙ ሕብረ
አምሳልም ሲመሰል ኑሯል:: ከተፈጥሯችን ጀምሮ ዓለም
ራሷ አርአያ #ትዕምርተ_መስቀል ናት::
እግዚአብሔር ለቃየን እንዳይገድሉት ከሰጠው ምልክት
(ዘፍ. 4:15) ጀምሮ
#ይስሐቅ ሊሰዋ የተሸከመው እንጨት (ዘፍ. 22:6):
#ቅዱስ_ያዕቆብ ያያት የወርቅ መሰላል (ዘፍ. 28:12):
ያዕቆብ የዮሴፍን ልጆች የባረከበት መንገድ (ዘፍ.
48:14):
ባሕረ ኤርትራን የከፈለችው #የሙሴ_በትር (ዘጸ.
14:15):
# የናሱ_ዕባብ የተሰቀለበት እንጨት (ዘኁ. 21:8)
ጨምሮ በርካታ ምሳሌዎች ለቅዱስ መስቀሉ
መኖራቸውን መተርጉማን ተናግረዋል::
# ቅዱስ_ዳዊትን የመሰሉ ነቢያት ደግሞ "ለሚፈሩሕ
ከቀስት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሰጠሃቸው" እያሉ
መስቀሉን ከርቀት ተመልክተዋል:: (መዝ. 59:4)
በሐዲስ ኪዳን ግን ምሳሌው ገሃድ ሆኖ: ጌታ በዕፀ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ሥጋውን ቆረሰበት: ደሙን
አፈሰሰበት: ዓለምንም አዳነበት::
ስለዚህም "#መስቀል_ብርሃን_ለኩሉ_ዓለም :
#መሠረተ_ቤተ_ክርስቲያን " ተብሎ የሚመሰገን ሆኗል::
#ቅዱስ_ያሬድ ሊቁ አክሎ "መስቀል መልዕልተ ኩሉ
ነገር: ያድኅነነ እምጸር" ብሎ ጠላትን ማሳፈሪያ መሆኑን
ይነግረናል:: #ብርሃነ_ዓለም #ቅዱስ_ዻውሎስም ስለ
መስቀሉ አምልቶ አጉልቶ አስተምሯል:: መመኪያችን
ነውና:: (1ቆሮ. 1:18, ገላ. 6:14)
አንዳንዶቹ እኛን 'የተሰቀለውን ትታቹሃል' ይሉናል::
የተሰቀለውማ የጌቶች ጌታ: የነገሥታት ንጉሥ:
የአማልክት አምላክ: ሁሉ በእጁ የተያዘ:
#ኢየሱስ_ክርስቶስ ነውና ከኦርቶዶክስ በላይ የሚያመልክ
በወዴት አለና::
ነገር ግን መስቀሉን ንቆ የተሰቀለውን ማክበር
አይቻልምና እኛ ለመስቀሉ የጸጋ ስግደትን እንሰግዳለን:
እናመሰግነዋለን: እናከብረዋለን: ቤዛ: ጽንዕ: መድኃኒት:
ኃይል እያልንም እንጠራዋለን:: አባቶቻችን በመስቀሉ
ምርኩዝነት ማዕበለ ኃጢአትን: ባሕረ እሳትን
ተሻግረዋል::
በመስቀሉ ቢመኩ አጋንንትን ድል ነስተዋል:: ጠላትንም
አሳፍረዋል:: እኛም በመስቀሉ አምነን ከብረን: ገነን
እንኖራለን:: ተጠቅመንበታልና ከራሳችን ሕይወት በላይ
ምስክርን አንፈልግም::