ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ድንግል ማርያም አምላክ ልጇን አዝላ ስደት ወጥታ
ምድረ ግብፅ ትደርሳለች:: በወቅቱ ከደረሱባት ችግሮች
አንዱ ደግሞ ረሃብና ጽሙ ነበር:: እንኩዋን ለስደተኛ በቤቱ
ላለም ረሃብና ጥም እንዴት እንደሚከብድ የደረሰበት
ያውቀዋል::
ታዲያ አንድ ቀን የበርሃው ፀሐይ አቃጥሏቸው ባረፉበት
ድንግል እመቤታችን ውሃ ልመና ወጣች:: ብዙ ለመነች :
ግን ጥርኝ እንኩዋ የሚሠጣት አጥታ በሐዘን ተመለሰች::
ስትመለስ ግን ይባስ ብሎ የልጇን ጫማ ሽፍቶች
ወስደውት ደረሰች::
ያን ጊዜ ልጇን ታቅፋ "ውሃ ሳላገኝልሕ : ጫማሕንም
አሰረቅኩብህ" ብላ ምርር ብላ አልቅሳለች::
ይሕንን የተመለከተ ልጇ የቆመችበትን መሬት ቢባርከው
ሕይወትነት ያለው ማይ (ጸበል) ፈለቀ:: # ጌታችን :
#እመቤታችን : #ዮሴፍና_ሰሎሜ ከውሃው ጠጥተጠዋል::
ሲሔዱ ግን ለእንግዶች ጣፋጭ (መድኃኒት) :
ለአካባቢው ሰዎች ግን መራራ ሁኗል::
ከመቶዎች ዓመታት በሁዋላም ጌታ ጸበል ያፈለቀበት :
ድንግል እመቤታችን የቆመችበት ቦታ ላይ በእመ ብርሃን
ስም #ቤተ_ክርስቲያን ታንጿል:: ቅዳሴ ቤቱም ተከብሯል::
ጸበሉም ሲባርክና ሲፈውስ ይኖራል::
እንኩዋን ለቅድስት #እናታችን_ማርያም_መግደላ
ዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ❖
#ቅድስት_ማርያም_መግደላዊት
ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ
"መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት
(ወንጌላውያን) ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ:-
በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ
ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች
በአንዱ (በመግደሎን) ተወልዳ ያደገች ናትና::
ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና
ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም 7
አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር::
በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና
ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች::
በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት
የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም (ይቀበላል): አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም
ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት
አልዘገየችም::
ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር
አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ
ሆነች:: ጌታም ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ
መርጦ ተከታዩ አደረጋት::
ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች::
እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ
ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው::
ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች::
ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ
#መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ
ነበረች:: (ዮሐ. 19:25) ቅዱሳኑ #ዮሴፍና #ኒቆዲሞስ ጌታን
ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች::
እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም
ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር
አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን
አልፈራችም:: ጌታችንም #ከእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት
ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ
አደላት::
በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም 2 መላእክትን
( #ሚካኤልና_ገብርኤልን ) ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ
የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም"
አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት::
ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ
መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት::
"ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን
ለደጋጉ #ሐዋርያት ሰበከችላቸው::
#ቅድስት_ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ
ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን : #ትምሕርተ_ኅቡዓትን
ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ: በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ
ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ #ቤተ_ክርስቲያን ውስጥም ልዩ
አገልግሎት ነበራት::
ቅዱሱ #እስጢፋኖስ 8 ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን
ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን
ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ #መንፈስ_ቅዱስ
የሚባርከውን #አጋፔ (የፍቅር ማዕድ) የምታዘጋጀው እርሷ
ነበረች::
እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ
በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል::
እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ #ቅዱስ_መልአክ ወርዶ
ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ
ይመግባቸው ነበር::
እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም
የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን
#ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች::
ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና
ግርፋትን ታግሳለች::
በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን
መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን
ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ (ከአንዳንዶቹ
በቀር) ያከብሯታል::