በሀዋሳ ቅድስ ገብርኤል ገዳም መራሔ ድኅነት ሰንበት ት/ቤት 51 ዓመት የምስረታ
በዓላችንን አብረን በክርስታናዊ አለባበስ ደምቀን በ21 እመብርሃንን በጉባኤ አዘክረን
ቅዳሜ በሰርክ ጉባኤ ታድመን እሁድ በ7 ሰዓት ከሰ/ት ቤት አዳራሽ መንፈሳዊውን ማዕድ
ተመግበን በmk በeotc በሰ/ት ትቤታችን ቀረፃ ክፍል ተቀርፀን ኑ በአንድነት በረከትን
አግንተን መስዋዕትነት ከፍለን እንበላ እንጠጣ ዘንድ ከመንፈሳዊው ማዐድ ርቀት
ያላደረሳችሁ በረከቱ ባላችሁበት ይድረሳችሁ

"አንተ በየዕለቱ ጠዋት ጠዋት ከእንቀልፍ ስትነቃ የምትጨነቀው ስለምንድር ነው፣ የምትጨነቀው ፊትህን መታጠብህ፣ ቁርስህን መብላትህ፣ ልብስህን መልበስህና ለመሄድ መዘጋጀትህ የቀን ተቀን ሕይወትህ ነውን ወይስ የመጀመሪያ ጉዳይህ ዕለቱን በጸሎት በንባብና በተመስጦ ከእግዚአብሔር ጋር መጀመር ነውን...እንደዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ላይ አንዳንዶች 'ለመጸለይ ጊዜ የለኝም' ይላሉ። እኔ ግን እውነተኛ ምክንያት ነው ብዬ አልቀበለውም። አንተ ግን ጸሎትህንና ተመስጦህን ካስቀደምክ ያ አጣሁት የምትለው ጊዜህን ታገኘዋለህ። ስለሆነም በሁሉም ነገር ላይ ለእግዚአብሔር ቅድሚያ ስጥ።
" (ከ'መንፈሳዊ ሰው' መጽሐፍ የተወሰደ ገጽ ፳፩)
" (ከ'መንፈሳዊ ሰው' መጽሐፍ የተወሰደ ገጽ ፳፩)
የእግዚአብሔር ቃል ስለሐሰተኞች ይናገራል
በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ከረከሱበት አንዱ ሐሰት ነው ሐሰትን የሚጽፉ እጅግ ሞልተዋል
ሐሰተኞች አሰፈሪና አሰጨናቂ ቅጣት ይደርስባቸዋል ፡፡ ሐሰት የእግዚአብሔርን ፍርድ
ያመጣል
ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 2ኛ
11-12 ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ
ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።
ሐሰተኛ የዲያብሎስ ልጅ ነው ነፍሰ ገዳይም ነው
የዮሐንስ ወንጌል 8
44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ።
እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም።
ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ሐሰተኞች
ከእግዚአብሔር መንግሥትና ከዘለአለም ሕይወት ርቀው ከባድ ፍርድ የሚፈረድባቸው
የሚከተሉት ናቸው፤ የዮሐንስ ራእይ 22
15 ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት
ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ። ስለዚህ የሰው ልጆች በሙሉ፤ ኋላ
እንዳታዝኑ የዘለአለም ጸጸት እንደያገኛችች ዛሬ አትዋሹ ሐሰት የሰይጣን ነው፡፡ የሐሰት
ትነታኔ እየፈጠራችሁ ሕዝብን የመታጫርሱ የእግዚአብሔር ፍርድ ይጠበቃችኋል፡፡
እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥር በቋንቋ በዘር እንዲከፋፈል አይደለም መከፋፈል የሰይጣን
ነው፡፡ የእግዚአብሔርን መንግሥትና የዘለአለምነን ሕይወት ማጣት እጅግ ከባድ ነው፡፡
የማያመልጡት ቅጣት አለ፡፡ማንም ሰው መሞቱ አይቀርም ለምን በቀሪው ዘመናችን
መልካም አንሰራበትም ፡፡

+++የአባ ጊዮርጊስና የአባ ሳሙኤል ክርክር+++
በአንድ ወቅት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመንገድ ላይ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባን ያገኟቸዋል።
ተያይዘውም አባ ሳሙኤል ወዳቀኑት ወደ ዋልድባ ገዳም ይሔዳሉ። በዋልድባ ገዳም
እንግዳ የሆኑት አባ ጊዮርጊስ በዋልድባ በቀን 7 ጊዜ ሲጸለይ ያዩና "እንዴት በቀን 7 ጊዜ
ብቻ ትጸልያላችሁ?" በሚል ከአባ ሳሙኤል ጋር ይከራከራሉ። ክርክራቸው ሐዋርያት በዓለም
ወንጌልን ለመስበክ ሊበተኑ ሲሉ እንደተከራከሩት ለበጎ ነበር። በመጨረሻም አባ ጊዮርጊስ
ከአባ ሳሙኤል በመለየት ወደ ሥፍራቸው በቁጭት ይሔዳሉ። በቅዱስ ቅንዐትም ቅዱስ
መንፈስ አነሳሥቷቸው "ለአምላክ በቀን ከ7 ጊዜ በላይ መጸለይ ይገባል" ለማለት ሰዓታትን
ደረሱ። ከዚህም በኋላ የአባ ሳሙኤል ገዳም ዋልድባም ሆነ ማንኛውም ቤተክርስቲያን
ድርሰቱን ተቀብሎ በቀን ለ22 ሰዓታት ማመስገን ሥርዐት ሆነ።
(ይህ በማኅበር የሚፈጸም ሲሆን ጊዜ ሳይገድባቸው ዕድሜ ልካቸውን በግል የሚያመሰግኑ
እንዳሉ ልብ ይሏል)
ታድያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት
ቤተ ክርስቲያንን እንደቸችቦ ሲያቃጥሉ ካህናትን ሲያርዱ ምዕመናን በግፍ ሲገደሉ እኛም
እንደሞቱት ሰማዕትነትን ለመቀበል እንዲያበቃን ሰቆቃው እንዲቆም አፅራረ ቤተ
ክርስቲያንን እንዲያስታግስልን ዛሬ በተጀመረችሁ ምህላ አንዳንድ ሰዎች ጥያቄ ያነሳሉ አየ
አለመታደል ብንችል ምናለ ሁሌም ምህላ ባደረስን በነበር፡፡ እስኪ የሸፈተውል ልቦናችን
ይመልስልን፡፡

!!!!!!!!ተዋህዶ!!!!!!!
(መነባነብ )
አሳምረሽ የቀመርሽው- ልኩን የይዞ ከቀመሩ
በአበባዮሽ ያጌጡበት- በውበቱ ሲዘምሩ
የጅረቶች መፍለልለቂያ- የሜዳዎች ውብ እይታ
ከህጻናት ብሩህ ተስፋ- ከሴቶችሽ ድንቅ እልልታ
ልትሰሚ ከቋመጥሺው- የልጅሽን ፍስሃ ተድላ
ሰማያዊ ቤት መጓዣ- ያድስ ዘመን ሠረገላ
አቁመሻል
አድርሰሻል፡፡
ግን እኮ እማ
ፊትሽ ወዝቶ ካየሁበት- ተጎሳቁሎ ይታየኛል
ሰንበር አለ በጀርባሽ ላይ- ጥዝጣዜሽ ይሰማኛል
የደስታ ምንጭ ብትሆኚም- ፊትሽ ጠቁሯል በሀዘኑ
ዘመን ቆጥረሽ ያደመቅሺው- የለችም ሊል ከዘመኑ
ሸማ ሠርተሸ ያለበስሽው- ሊያራቁትሽ ከመልበሻው
በጫንቃ ላይ ያዘልሽውም- ሊያስቀርሽ ከመድረሻው
ፍትፍት ሠርተሸ የመገብሽው- ያንችን ረሃብ በእድሜው ሊያይ
በጽድቅ ጥም አፍሽ ደርቆ- ሊያወራብሽ ያንችን ስቃይ
በከበበሽ በታጠርሽው- በዚህ አጀብ ስትተክዢ
ከዳር ቆሜ እንዳላይሽ- ካንቺው ልጓዝ እጄን ያዢ፡፡
እማ፡-
ተሠርታለች ስትባዪ- በመሠረት በዋጀሽ ደም
አይችሏትም ስትባዪ- በነዚያ ደጅ በገሃነም
ያልታመነ ቃል መስሎአቸው- ሰላቢ ቀን የሚውጥሽ
ድንገት ወድቀሽ ሊተርኩሽ- ቅቡል አጥቶ ሙዳይ ውስጥሽ
ስለ ማጥቆር ስለ ማክፋት- ስለ ማድከም ስለ ማድቀቅ
አፍ አውጥተው መዳብ ሲሉ- ያልታያቸውን የእጅሽን ወርቅ
ወይም ደግሞ፡-
ከይሁዳ እንዳደረ- እንደ ግብሩ ተጠናውቶት
መሸጥ ይሉት የህሊና አረም- ሲያስፈግገው በእናቱ ሞት
በዛሬው ቀን በዘመኔ- ለሚያይሽ ለእንደኔው ሰው
እስቲ አንዴ ማን እንደሆንሽ- አንጀት ካለው ይታወሰው!!!
ተዋህዶ ተዋህዶ - ተዋህዶ የብርሃን ደጅ
ነሽ እያለ የገለጠሸ- በውስጥና በውጭ አዋጅ
እንዳልፈራው ከለባቱን- የውሾች ጥርስ ያልበገረው
እንኳን ሆዱን መግዛት ቀርቶ- ነፍሱን መስጠት ያልቸገረው
በዚህ ዓይነት ልብ- (ውስጥ) የተተከልሽ ያባቶቼ አቢይ ጉዳይ
የሀፍረት ሳይሆን የኩራት ምንጭ- የዓለም መቅረዝ ትልቅ ሙዳይ
መሆንሽን ረስቼ ይሆን?
ቀራንዮ የቆመልሽ- ስላንቺ ፍቅር ነፍስ የሠጠ
እንዲያጫት ያልተገኘች- ካንቺ ውበት የበለጠ
መሠረትሽ የሱ ደም ነው- ሚመጥንሽ ክቡር ዋጋ
ቅድስናሽ የሐዋርያት- የአንበሶችን አፍ የዘጋ
የሞቱልሽ የተረዱሽ- የቀመሱሽ ያከበሩሽ
በጭንቅ ቀን የወለድሻቸው- ጣፍጠሻቸው የሚጠሩሽ
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ እማ ይበሉሽ!!!
በሆድ ህመም አልታመሙ- ባያገኙም አልተራቡ
ድሎት ሽተው አልተጓዙ- በዓለም ፍቅር አልወየቡ
ጥሪው ነበር አልታደሙም- ተጋበዘዋል ንቀው ተውት
ሴሰኝነት አልጣላቸው- አልቀጨጩም በእርኩስ ዝሙት
ኋላ አላዩም ሰዶም ጥለው- አልናፈቁም አልታያቸው
በአስኬማው ለዓለም ሞተው- አልቆጠሩም ዘር ግንዳቸው
ሥጋ ፈቃድ ሥጋ ድሎት- ሥጋ መሪ ሥጋ ጠሪ
የኔ ብለው አልደከሙ- ለዚህ ከንቱ ለዚህ ቀሪ
በየዱሩ በየዋሻው- ፍቅር ሽተው ሕይወት መርጠው
ክርስቶስን በሕይወታቸው- ሊያስተምሩ በእውነት ቆርጠው
ተሠደዱ ወደ ዋሻ - አልጋው ምቾት ወደ ሌለው
ተናቁለት ለወደዱት- ዓለም ገብቶት ግን አላየው፡፡
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ የድል ዓርማ
ከጸላኢው ታዳጊው ነሽ - ለባህታዊው የሌት ግርማ
እነኚህ ናቸው የተረዱሽ- የቀመሱሽ አንቺንማ!!
እኮ እማ፡-
ምን ይለኛል ያ ድካሙ? የአትናቴዎስ ያ አደራው
ሶስት ሺውን ያበቀለው- ያንድ ጵጥሮስ ያ አዝመራው
ምን ይበለኝ? ዲዮስቆሮስ- ላንቺ እውነት የደከመው
ያም ሰማእት ምን ይበለኝ? ላንቺ ደስታ የታመመው
ምን ይታየው ለባስልዮስ? ለአፈ ወርቁ ለዮሐንስ
ለመነኩሴው እንጦንዮስ- ለሰባኪው ጎርጎርዮስ
ድንግል ብሎ ያልጠገበው- ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
የጋስጫው ጊዮርጊስም- ተክለሃይማኖት ኢትዮጵያዊ
ምኔን ይዩ ልታያቸው? በስጋዬ ስጠጋብሽ
ልጄ ብለሽ ስትጠሪኝ- ቆሜ በሃሜት ለምሰድብሽ
እኮ እኔው ልጠራብሽ? ተገብቶኝ ልሰየመው?
“ነኝ”ን ብዬ ልወክልሽ? ለዚህ አጠራር ልታደመው?
እዚያ ደጅሽ እጣን የለም- መቀደሻ ጧፍ አለቀ
ያም ካህንሽ ተቸገረ- ትጉህ ዲያቆን ተጨነቀ
ወር መድረሻው ስጋት ሆኖ- ሰው ናፈቀው ሰው አማረው
ብዙ ደጅሽ ደራሽ አጣ- ጣሪያው ዝሎ መፍረስ ቀረው
ምዕመንሽ ስጋት ገባው- የከበበው ጅብ ዘለለ
ማነቂያ ጥፍር አረዘመ- መጋጫ ጥርስ አበቀለ
እዚህ ደግሞ፡-
በንጹሑ መቅደስ ቆሜ- የርኩሰትን ውጥን ሳስብ
በተራራው ቦታ ሆኜ- ሲያናውጠኝ ሸለቆ ልብ
እንከን አልባ ስፍራ አድሬ- ጭቃ ውስጤን ሲያሻክረው
የሆድ ህመም የሆድ ናፍቆት- ቃሌን ለነውር ሲያሳድረው
በድንግሉ አደባባይ- የሕሊና ግልሙትና
ከብርሃን ዘር ቆጥሬ- ከጨለማም በዝምድና
አጣቅሼ እበላለሁ- ከሁለት ማዕድ ከሁለት ወጪት
ሲያጎርሱኝ አንዱን በቀን- ሳያጎርሱኝ አንዱን ሌሊት፡፡
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ አንቺ እናት
ላንቺ መኖር ሳልረዳ- እንኳ ቀርቶ ላንቺ መሞት
እንዴት ብዬ ልናገረው? በምን መኖር አለሁ ልበል?
መንጋው ገዶኝ አንዳች ልሰጥ- እንደ ሰጡኝ ሳልቀበል!!
በዘመን ወንዝ ለሚጠይቅ- ስንቱን ፍሬ ልናገረው?
ስለ ክሬ ልሙት ለሚል- ምን ይዤለት ልሻገረው?
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ ንጹህ ሀገር
ላቆሰልኩሽ ተሸክመሽ- ያረመምሽው እንድናገር
እባክሽን ይብቃ በይኝ- እኔ እንደሆን ልቤ ክፉ
ከግንባሬ የሚነበብ- የኃጢአቴ ቀለም- ጽሑፉ
አንቺው በዪኝ ተዋህዶ- ጨለማዬን አንቺው አብሪ
የዛለውን “እኔ”ን ንደሽ- የንስሃን “እኔ” ስሪ
ቁስል ሆኜ ላሳመምኩሽ- ፈውስ ሆነሺኝ ተናገሪ
አለስልሰሽ ድንጋይ ልቤን- የሚበቅል እህል ዝሪ
ከዚያም እኔም:-
እማ ልበል ስምሽን ልጥራ- ላላቆስልሽ እንደገና
ቅዱሳኑ ሁሉ እንዳሉሽ- እኔም ሆኜ በትህትና
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ የእውነት ፋና
በተመስጦ ላይለይሽ- ልቤ ጠዋት ሁሌ ማልዶ
ውብ ሃይማኖት ንጹህ ሙዳይ
ተዋህዶ
ተዋህዶ
ተዋህዶ፡፡
(መነባነብ )
አሳምረሽ የቀመርሽው- ልኩን የይዞ ከቀመሩ
በአበባዮሽ ያጌጡበት- በውበቱ ሲዘምሩ
የጅረቶች መፍለልለቂያ- የሜዳዎች ውብ እይታ
ከህጻናት ብሩህ ተስፋ- ከሴቶችሽ ድንቅ እልልታ
ልትሰሚ ከቋመጥሺው- የልጅሽን ፍስሃ ተድላ
ሰማያዊ ቤት መጓዣ- ያድስ ዘመን ሠረገላ
አቁመሻል
አድርሰሻል፡፡
ግን እኮ እማ
ፊትሽ ወዝቶ ካየሁበት- ተጎሳቁሎ ይታየኛል
ሰንበር አለ በጀርባሽ ላይ- ጥዝጣዜሽ ይሰማኛል
የደስታ ምንጭ ብትሆኚም- ፊትሽ ጠቁሯል በሀዘኑ
ዘመን ቆጥረሽ ያደመቅሺው- የለችም ሊል ከዘመኑ
ሸማ ሠርተሸ ያለበስሽው- ሊያራቁትሽ ከመልበሻው
በጫንቃ ላይ ያዘልሽውም- ሊያስቀርሽ ከመድረሻው
ፍትፍት ሠርተሸ የመገብሽው- ያንችን ረሃብ በእድሜው ሊያይ
በጽድቅ ጥም አፍሽ ደርቆ- ሊያወራብሽ ያንችን ስቃይ
በከበበሽ በታጠርሽው- በዚህ አጀብ ስትተክዢ
ከዳር ቆሜ እንዳላይሽ- ካንቺው ልጓዝ እጄን ያዢ፡፡
እማ፡-
ተሠርታለች ስትባዪ- በመሠረት በዋጀሽ ደም
አይችሏትም ስትባዪ- በነዚያ ደጅ በገሃነም
ያልታመነ ቃል መስሎአቸው- ሰላቢ ቀን የሚውጥሽ
ድንገት ወድቀሽ ሊተርኩሽ- ቅቡል አጥቶ ሙዳይ ውስጥሽ
ስለ ማጥቆር ስለ ማክፋት- ስለ ማድከም ስለ ማድቀቅ
አፍ አውጥተው መዳብ ሲሉ- ያልታያቸውን የእጅሽን ወርቅ
ወይም ደግሞ፡-
ከይሁዳ እንዳደረ- እንደ ግብሩ ተጠናውቶት
መሸጥ ይሉት የህሊና አረም- ሲያስፈግገው በእናቱ ሞት
በዛሬው ቀን በዘመኔ- ለሚያይሽ ለእንደኔው ሰው
እስቲ አንዴ ማን እንደሆንሽ- አንጀት ካለው ይታወሰው!!!
ተዋህዶ ተዋህዶ - ተዋህዶ የብርሃን ደጅ
ነሽ እያለ የገለጠሸ- በውስጥና በውጭ አዋጅ
እንዳልፈራው ከለባቱን- የውሾች ጥርስ ያልበገረው
እንኳን ሆዱን መግዛት ቀርቶ- ነፍሱን መስጠት ያልቸገረው
በዚህ ዓይነት ልብ- (ውስጥ) የተተከልሽ ያባቶቼ አቢይ ጉዳይ
የሀፍረት ሳይሆን የኩራት ምንጭ- የዓለም መቅረዝ ትልቅ ሙዳይ
መሆንሽን ረስቼ ይሆን?
ቀራንዮ የቆመልሽ- ስላንቺ ፍቅር ነፍስ የሠጠ
እንዲያጫት ያልተገኘች- ካንቺ ውበት የበለጠ
መሠረትሽ የሱ ደም ነው- ሚመጥንሽ ክቡር ዋጋ
ቅድስናሽ የሐዋርያት- የአንበሶችን አፍ የዘጋ
የሞቱልሽ የተረዱሽ- የቀመሱሽ ያከበሩሽ
በጭንቅ ቀን የወለድሻቸው- ጣፍጠሻቸው የሚጠሩሽ
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ እማ ይበሉሽ!!!
በሆድ ህመም አልታመሙ- ባያገኙም አልተራቡ
ድሎት ሽተው አልተጓዙ- በዓለም ፍቅር አልወየቡ
ጥሪው ነበር አልታደሙም- ተጋበዘዋል ንቀው ተውት
ሴሰኝነት አልጣላቸው- አልቀጨጩም በእርኩስ ዝሙት
ኋላ አላዩም ሰዶም ጥለው- አልናፈቁም አልታያቸው
በአስኬማው ለዓለም ሞተው- አልቆጠሩም ዘር ግንዳቸው
ሥጋ ፈቃድ ሥጋ ድሎት- ሥጋ መሪ ሥጋ ጠሪ
የኔ ብለው አልደከሙ- ለዚህ ከንቱ ለዚህ ቀሪ
በየዱሩ በየዋሻው- ፍቅር ሽተው ሕይወት መርጠው
ክርስቶስን በሕይወታቸው- ሊያስተምሩ በእውነት ቆርጠው
ተሠደዱ ወደ ዋሻ - አልጋው ምቾት ወደ ሌለው
ተናቁለት ለወደዱት- ዓለም ገብቶት ግን አላየው፡፡
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ የድል ዓርማ
ከጸላኢው ታዳጊው ነሽ - ለባህታዊው የሌት ግርማ
እነኚህ ናቸው የተረዱሽ- የቀመሱሽ አንቺንማ!!
እኮ እማ፡-
ምን ይለኛል ያ ድካሙ? የአትናቴዎስ ያ አደራው
ሶስት ሺውን ያበቀለው- ያንድ ጵጥሮስ ያ አዝመራው
ምን ይበለኝ? ዲዮስቆሮስ- ላንቺ እውነት የደከመው
ያም ሰማእት ምን ይበለኝ? ላንቺ ደስታ የታመመው
ምን ይታየው ለባስልዮስ? ለአፈ ወርቁ ለዮሐንስ
ለመነኩሴው እንጦንዮስ- ለሰባኪው ጎርጎርዮስ
ድንግል ብሎ ያልጠገበው- ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
የጋስጫው ጊዮርጊስም- ተክለሃይማኖት ኢትዮጵያዊ
ምኔን ይዩ ልታያቸው? በስጋዬ ስጠጋብሽ
ልጄ ብለሽ ስትጠሪኝ- ቆሜ በሃሜት ለምሰድብሽ
እኮ እኔው ልጠራብሽ? ተገብቶኝ ልሰየመው?
“ነኝ”ን ብዬ ልወክልሽ? ለዚህ አጠራር ልታደመው?
እዚያ ደጅሽ እጣን የለም- መቀደሻ ጧፍ አለቀ
ያም ካህንሽ ተቸገረ- ትጉህ ዲያቆን ተጨነቀ
ወር መድረሻው ስጋት ሆኖ- ሰው ናፈቀው ሰው አማረው
ብዙ ደጅሽ ደራሽ አጣ- ጣሪያው ዝሎ መፍረስ ቀረው
ምዕመንሽ ስጋት ገባው- የከበበው ጅብ ዘለለ
ማነቂያ ጥፍር አረዘመ- መጋጫ ጥርስ አበቀለ
እዚህ ደግሞ፡-
በንጹሑ መቅደስ ቆሜ- የርኩሰትን ውጥን ሳስብ
በተራራው ቦታ ሆኜ- ሲያናውጠኝ ሸለቆ ልብ
እንከን አልባ ስፍራ አድሬ- ጭቃ ውስጤን ሲያሻክረው
የሆድ ህመም የሆድ ናፍቆት- ቃሌን ለነውር ሲያሳድረው
በድንግሉ አደባባይ- የሕሊና ግልሙትና
ከብርሃን ዘር ቆጥሬ- ከጨለማም በዝምድና
አጣቅሼ እበላለሁ- ከሁለት ማዕድ ከሁለት ወጪት
ሲያጎርሱኝ አንዱን በቀን- ሳያጎርሱኝ አንዱን ሌሊት፡፡
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ አንቺ እናት
ላንቺ መኖር ሳልረዳ- እንኳ ቀርቶ ላንቺ መሞት
እንዴት ብዬ ልናገረው? በምን መኖር አለሁ ልበል?
መንጋው ገዶኝ አንዳች ልሰጥ- እንደ ሰጡኝ ሳልቀበል!!
በዘመን ወንዝ ለሚጠይቅ- ስንቱን ፍሬ ልናገረው?
ስለ ክሬ ልሙት ለሚል- ምን ይዤለት ልሻገረው?
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ ንጹህ ሀገር
ላቆሰልኩሽ ተሸክመሽ- ያረመምሽው እንድናገር
እባክሽን ይብቃ በይኝ- እኔ እንደሆን ልቤ ክፉ
ከግንባሬ የሚነበብ- የኃጢአቴ ቀለም- ጽሑፉ
አንቺው በዪኝ ተዋህዶ- ጨለማዬን አንቺው አብሪ
የዛለውን “እኔ”ን ንደሽ- የንስሃን “እኔ” ስሪ
ቁስል ሆኜ ላሳመምኩሽ- ፈውስ ሆነሺኝ ተናገሪ
አለስልሰሽ ድንጋይ ልቤን- የሚበቅል እህል ዝሪ
ከዚያም እኔም:-
እማ ልበል ስምሽን ልጥራ- ላላቆስልሽ እንደገና
ቅዱሳኑ ሁሉ እንዳሉሽ- እኔም ሆኜ በትህትና
ተዋህዶ ተዋህዶ- ተዋህዶ የእውነት ፋና
በተመስጦ ላይለይሽ- ልቤ ጠዋት ሁሌ ማልዶ
ውብ ሃይማኖት ንጹህ ሙዳይ
ተዋህዶ
ተዋህዶ
ተዋህዶ፡፡
ባልንጀራህን አትቀየመው ።
ወኢትትቀየም ቢጸከ ⇨ ባልንጀራህን አትቀየም ⇨ be not angry with thy
neighbour" [ሢራ. ፳፰፥፯]
. እመቤታችን ያለ ምንም ነውር ፣ ሰይጣን ግን ያለ ምንም ክብር ሆነው ይኖራሉ።
. ቅዱሳን በሚደነቅ ንጽሕና እኛም በታላቅ ስንፍና የምንመላለስ ነን።
ነገር ግን ከበጎዎች ጥቂት ድክመት ከደካሞች ጥቂት በጎነት አይታጣም ።
ለዚህ ነው መጽሐፋችን ⇨ ፍጡር ከሆነ ከ #እመቤታችን በቀር ጥቂት ጽነት የሌለበት
የለም! ከነጭ ላም ከጉያዋ ከብሻሻዋ (ከብሽሽቷ) ቢፈልጉ ጥቂት ጥቁር እንዳይጠፋ፤
⇨ ፍጡርም ሆኖ ከ #ዲያብሎስ በቀር ጥቂት ቸርነት የሌለው የለምና! ከጥቁር ላም
ከጉያዋ ከብሻሻዋ ቢፈልጉ ጥቂት ነጭ እንዳይጠፋ፤
⇝ የኃጥኡ ምግባር ለጻድቁ ክብር ያበዛለታል የጻድቁም ክፋት በኃጥኡ ፍዳ የመጣበታልና
፦
እንደነ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት
እንደነ #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ያለ ቢሆንሳ ቢሉ ዝክራቸውን ለዘከረ ስማቸውን
ለጠራ ክብር ሲያሰጡ ይኖራሉ ይላል ፍትሕ መንፈሳዊ።(ፍትሐ ነገሥት ምዕ ፲ ቁ ፫፻፶፭
ትርጓሜ)
✧ መቼም #እኔ_ደካማ_ነኝ ! በሀገራችን እና በቤተክርስቲያናችን ላይ በዘመናችን
የመጣው ይኼ ፈተና በእኔ ምክንያት
① ነፍሴን በማጉደሌ፣ ② አምላኬን በመበደሌ እና ③ ባልንጀራዬን በማቃለሌ መሆኑን
አምናለሁ!
☞ለነፍሴ ድርሻዬን ለመወጣት እጥራለሁ!
☞ እግዚአብሔር ይቅር እንዲለኝ ለምኑልኝ (ክፍለ ሥላሴ) መቼም እርሱ እግዚአብሔር
ይቀየም ዘንድ እንደሰው አይደለምና በምሕረቱ እታመናለሁ ( ኢኮነ ከመ ዕጓለ መሕያው
ዘይትቄየም ዮዲ.፰ ፥፲፮)
☞ እናንተን ባልንጀሮቼን አልሜ ሰው ለመጉዳት አልያም ተሳስቼ ለመርዳት በጻፍኩት፣
በተናገርኩት ባደረኩትም ይቅር በሉኝ ከዚህ አልፎም ከእኔ በሚጠበቀውም መጠን
ድርሻዬን ሳልወጣ ሳልጽፍ፣ ሳልናገር እና ሳላደርግ በቀረሁትም ጭምር በእጅጉ ይቅርታ!
ሐሳቤን የበለጠ ያጠነክራል ብዬ ይኽን ከቅዱስ መጽሐፍ [የጠቢቡ ሢራክን ቃልና የሊቁን
የሕማማት ሰላምታ ክፍል] ለትምህርትና ለተማጽኖ አስቀምጬ ለ"ጥቂት" ጊዜ ልሰናበት።
“ አንተ ሰው ሆነህ እንዳንተ ያለውን ሰው ሳትቀየም እግዚአብሔርን እንዴት ይቅር
በለኝ ትለዋለህ? እንዳንተ ያለ ሰው ይቅር ሳትል ኃጢዓትህን ያስተሰርይልህ ዘንድ
እንግዲህ እንዴት ትለምነዋለህ ኃጢዓትህን አስበህ ጠብን ተዋት ሞትን አስበው
መቃብርንም አስበው ትእዛዙንም ጠብቅ፤ ሕጉን አስበህ ባልንጀራህን አትቀየም" ሢራ ፳፰፥
፪–፯
በከመ ልማድኪ በሊ ኀበ ወልድኪ ከሃሊ
.ኦ ርኅሩኅ ኢተበቃሊ
.ያጠፍኦኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፦ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ።
እንደዚህ በዪ እንደልማድሽ
. ሁሉን ወደሚችለው ልጅሽ
. የምትራራ ነህና የማትበቀል
. የእጅህን ድንቅ ሥራ ጠብቅ ፣ የቀደመውን ያንተን አምሳል
ሠዓሊ ሥዕሉን እንደምን ያጠፋል?!
‘እናታችን ድንግል’ ቂም ይዞ ከማይበቀለው ጽድቀ አሚንን ፣ ርትዓተ ልቡናን
ከሚያድለው ልጅሽ ይቅርታውን ይልክልን ዘንድ ለምኚልን!

እንኳን ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ
መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
✤፨✤ አቡነ መብዓ ጽዮን
አቡነ መብዓ ጽዮን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል (ጥቅምት
27 ቀን) ጋር አብረው የሚታሰቡ ታላቅ የተጋድሎ አባት ናቸው፡፡ የጻድቁ አቡነ መብዓ ጽዮን
መታሰቢያቸው ከመድኃኔዓለም በዓል ጋር ስለሆነ በዚህ ጽሁፍ ሥር ታሪካቸውን ይዘን
ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ!
አቡነ መብዓ ጽዮን የተገኙት እግዚአብሔርን እያስደሰቱ ያለነቀፋ ከሚኖሩ ቅዱሳን ነው፡፡
በክህነታቱ፣ በየዋህነቱ ከሰዎች የተስማማው አባታቸው ሀብተጽዮን፣ በደግነቷና በቸርነቷ
የምትታወቀው እናታቸው ጽዮንትኩና በሕግ በንፅህና በጋብቻ ተወስነው ሲኖሩ የተባረከ ልጅ
ይሰጣቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይለምኑ ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ክርስቶስም
መብዓ ጽዮን የተባለ ደግ ልጅ ሰጣቸው፡፡
መብዓ ጽዮን ከልጅነቱ ጀምሮ ማስተዋል እና የእግዚአብሔር ፍቅር ያደረበት ሰው እንደነበር
ገድሉ ይናገራል፡፡ ይኸውም በአንዲት ቀን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብሎ
ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ይሄድ የነበረ ሰው እግሩን እንቅፋት ተመቶ ደሙ ከመሬት ሲፈስስ
በአየ ጊዜ እውቀት በልጅነቱ የሞላ መብዓ ጽዮን የደማው ጣቱ እስኪደርቅ ድረስ ጠባው፡፡
በመሬት የፈሰሰ ደሙን ከአፈሩ ጋር በላ፡፡ ይህ ሥራው ከልጅነቱ የመስቀሉ ፍቅር በልቡ
የቸነከረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
#ያገባ ሰው ሚስቱን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል፡፡ ያላገባ ግን እግዚአብሔርን ደስ
የሚያሰኘውን ሥራ ያስባል$ የሚለው የመጽሀፍ ቃል ያፀናው ወጣቱ መብዓ ጽዮን
ከቤተሰቡ የመጣለትን የጋብቻ ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ ኃጢአትን ከመጨመር ውጭ ምን
እጠቀማለሁ እያለ የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቃት፡፡ በዚህም ቤተሰቦቹ ተውት፣ እርሱም
ራሱን ይበልጥ ለእግዚአብሔር አስገዛ፡፡
የምንኩስና እና ተጋድሎ ሕይወቱ
የምንኩስ እና የተጋድሎ ሕይወት የጣመ የላመ የሌለበት ፍፁም ራስን ለእግዚአብሔር
ማሳለፍ ነው፡፡ ይህንን የማይወድ ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ፍፁም ፈተናን ያበዛል፡፡
ቅድሳንም በረድኤተ እግዚአብሔር እና በተጋድሏቸው ያልፉታል፡፡ ሠይጣንን ድል
ይነሡታል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮንም የምንኩስና ቀንበር ከተሸከመ ጊዜ ጀምሮ ከፈረስ፣
ከበቅሎ፣ ከአልጋ፣ ከምንጣፍ ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ መኖሩን ገድሉ ይነግረናል፡፡
ለዚህም ተጋድሎ ሕይወቱ ያግዘው እና ይረዳው ዘንድ ክህነትን አባ ገብርኤል ከተባለ ጳጳስ
ተቀብሏል፡፡ ቄስም ሆኖ የመድኃኔዓለምን ሥጋው እና ደሙን እያቀበለ ብዙ ዘመን ኖሯል፡፡
የምንኩስና ሕይወቱና ትጋቱም ታላቅ አባት እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ትልቅ ድንጋይ በደረቱ ተሸክሞ ከምድር ከአመድ በተቀመጠም ጊዜ በራሱ ተሸክሞ፣
በሚሰግድም ጊዜ በጀርባው አዝሎ ስለ ክርስቶስ መከራ ያስባል፡፡ ራሱን ይበድላል፣
ስጋውን ያደክማል፡፡ ይኸውም ያለሰንበት እና ያለበዓላት በቀር በዚህ ተጋድሎ የምንኩስና
ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከዛም ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ከአቡነ ተክለሃይማኖት መቃብር
በረከትን እንደተቀበለ ገድለ መብዓ ጽዮን ይነግረናል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን ራሱን
ለእግዚአብሔር በሰጠ ቁጥር መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋወደሙ እየተገለፀ፤
እመቤታችንም እየታየች ትመክረው ታስተምረው ነበር፡፡
ቅዱሳንን ማክበር በዓላቸውን መዘከር እንዲገባ ከምንማርባቸው ታሪኮች አንድ የአቡነ
መብዓ ጽዮን ታሪክ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን እና የእናቱን የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል
አብዝቶ ያከብር ነበር፡፡ በዚህም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከቅድሳን ጋር
መጥቶ ባርኮታል፡፡ የመለኮት ምሥጢርም ሥርዓትም በአካባቢው ላሉ ሠዎችም
ተሠጥቷቸዋል፡፡ መናፍቃን በዓል ማክበር አይገባም ቢሉ የበዓል ማክበር ውጤቱ እዚህ
ድረስ መሆኑን እናያለን፡፡
በፀሎቱም #ኦ እግዚኦ አንተ ትብለኒ ሰአል ኩሎ ዘፈቀድከ ወአነ እሁበከ፣ ጌታ ሆይ አንተ
የወደድከውን ሁሉ ለምን እኔ እሠጥሃለሁ አልከኝ፡፡ አሁንም የለመንኩን ግለጽልኝ$ በማለት
የቀራንዮን መስቀል መከራውን ያሳየው ዘንድ ሁልጊዜ ይለምን ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ
መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን የሆኑ እጆቹን በመስቀሉ እንዲዘረጋ፣ እግሮቹም
እንዲቸነከሩ፣ የሾህ አክሊልም በራሱ ተሸክሞ የጥቅምት 27 ቀን ታየው፡፡ ለሙሴ
ሊታያቸው እንዳልቻለ አባ መብዓ ጽዮን ከመሬት ወደቀ፡፡ እንደ ሞተም ሆነ፡፡ ማንም
የመስቀሉን መከራ ሕማሙን ማየት እንደማይችል ነገረው፣ በቸርነቱም አነሳው፡፡ የሞቱ
ገናንነት የሚያስፈራ እና የሚያስደነግጥ መሆኑን አሳውቀው፡፡ መከራው ታላቅ በሰው
አእምሮ አይታሰብምና ነው፡፡
ኃጢአትን ያልሠራ ሐሰትም በአፉ ያልተገኘበት ስለሠው ኃጢአት ስለሞተው
ስለመድኃኔዓለም ክርስቶስ የሞቱ መታሰቢያ በምትሆን በዕለተዓርብ ታላቅ ተጋድሎን
በማድረጉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለት በዓል በሚታሰብበት
በ27 በመድኃኔዓለም ዕለት የአቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያ ተደረገ፡፡ ይኸውም ጥቅምት
27 ነው፡፡

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
ኅዳር 3-አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኮሳቱ ‹‹ገዳሙን በአህያ አታስረግጥ›› ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ ያደረጉት አቡነ ፍሬ ካህን ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ እነ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን አስተምረው ያመነኮሱትና ውኃ ይቀዳላቸው የነበረውን አህያቸውን አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ አንበሳውን 7 ዓመት ለገዳማቸው ውኃ ያስቀዱት የደብረ በንኮሉ ታላቁ አባት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ የተሰወረበት ዕለት ነው፡፡
+ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መና ሲመግባቸውና የጌታችንንም ቅዱስ ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው የነበሩት ሰማዕቱ አቡነ ዓምደ ሚካኤል ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ አባ አትናቴዎስና እኅቱ ቅድስት ኢራኢ በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
+ ከቆሮንቶስ አገር የተገኙት ቅዱስ አባ ኪርያቆስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አባ አትናቴዎስና እኅቱ ቅድስት ኢራኢ፡- እነዚህንም ቅዱሳን ከሃዲው ንጉሥ መክሲምያኖስ ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃያቸው፡፡ ንጉሡም ቅዱሳኑ ጌታችንን በማመን እስከመጨረሻው መጽናታቸውን ባየ ብዙ መከራ አደረሰባቸው፡፡ በመጨረሻም ማሠቃየት በሰለቸው ጊዜ ራቁታቸውን ከጉድጓድ ውስጥ በመጨመር በላያቸው ላይ የጉድጓዱን አፍ ዘግቶ ደፈነው፡፡ አባ አትናቴዎስና እኅቱ ቅድስት ኢራኢም በዚያው የሰማዕትነታቸው ፈጻሜ ሆኖ የክብር አክሊልን ተቀዳጁ፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አቡነ ዓምደ ሚካኤል፡- ትውልዳቸው ወሎ ቦረና ነው፡፡ ወላጆቻቸው ገላውዲዮስና ኤልሳቤጥ ሁለቱም በሃይማኖትና በዓለም ገንዘብ የበለጸጉ ናቸው፡፡ ይህንንም ጻድቅ ልጃቸውን የአርባዕቱ እንስሳ በዓል ዕለት ወለዱትና ስሙን ዓምደ ሚካኤል ብለው ጠሩት፡፡ ለዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ ለዐፄ በእደ ማርያምና ለዐፄ እስክንድር የሠራዊት አለቃ የነበረ ጻድቅ ነው፡፡ በአንድ ዓመቱ ወላጆቹ ወደ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ይዘውት እንደሄዱ ከወላጆቹ ተለይቶ ጠፍቶ ሳይገኝ ቀረ፡፡ መልአክም ከቤተ መቅደስ አግብቶ እየመገበው 3 ቀን አቆይቶታል፡፡ በ3ኛው ቀን ቄሱ ሊያጥን ሲገባ በከርሰ ሐመሩ ውስጥ ሕፃኑን አገኘውና ወስዶ ለወላጆቹ ሰጣቸው፡፡
ባደገም ጊዜ በመመጽወትና አብያተ ክርስቲያናትን በማደስ የሚተጋ ሆነ፡፡ ለድኆችም በቅንነት በመፍረድ በታላቅ ተጋድሎ የሚኖር ሆነ፡፡ ለነገሥታም ገዥ ከሆነ በኋላ በጸሎቱና በበረከቱ በሀገራችን ላይ ሁሉ ሰላም ሆነ፡፡ ጠላቶችም ሁሉ ለነገሥታቱ ተገዝተው ይገብሩ ነበር፡፡ በበጎ ምግባሩ የቀኑ ዐመፀኞችም በክፋ ተነሡበት፡፡ ጻድቁ በመንፈስ አድጎ መንኩሶ በታላቅ ተጋድሎ ሲኖር ነገር ሠሪዎች በሐሰት ወንጅለው ከሰሱት፡፡ ንጉሡም እጅግ ስለሚወደው የራራለት ቢሆንም በነገራቸው ባስጨነቁት ጊዜ ወደ ሩቅ አገር አስሮ አጋዘው፡፡ አባታችንም በግፍ ታስረው ሳሉ በእስር ቤቱ ውስጥ ብርሃን ወረደላቸው፣ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ሰማያዊ መና እያመጣ ይመግባቸው ነበር፡፡ የጌታችንንም ሥና ደም በሰንበት እያመጣለቸው ያቆርባቸው ነበር፡፡ ነገረ ሠሪዎቹ ይገድሏቸው ዘንድ ንጉሡን ለመኑት፡፡ በዓመፃቸውም ብዛት ወደ ፍርድ ሸንጎ አምጥተው ገደሏቸው፡፡
አንድ ጻድቅ መነኩሴ የቅዱስ ዓምደ ሚካኤልን ሥጋ ሦስት ቅዱሳን መላእክት ሲያጥኑ አገኛቸውና ያየውን ለሕዝቡ ተናገረ፡፡ በሌላም ጊዜ የብርሃን ፋና ከሰማይ ሲወርድላቸው ብዙ ቀን የተመለከቱ ብዙ ቅዱሳን ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡ ንጉሡም ይህንን ሁሉ ሲሰማ በአሳቾቹ ልበ ደንዳናነትና ክፋት እጅግ ተጸጽቶ በሞት ቀጣቸው፡፡ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤልንም በአባቶች መቃብር በክብር አስቀበራቸው፡፡ ስማቸውንም በበጎ እንጂ በክፋ ማንም እንዳያነሳቸው በአዋጅ አስነገረ፡፡ መታሰቢያም አቆመላቸው፡፡
ከዚህም በኋላ ዐፄ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ የአባቱን የበእደ ማርያምን ቃል ኪዳን ሰምቶ ዐፅማቸውን አፍልሶ ወደ አትሮንስ ማርያም ወሰደውና በቅዱሳን ነገሥታት መቃብር በክብር አኖረው፡፡ ሊቀ ብርሃናት መርቆሬዎስ አረጋም ጻድቁ ሲያርፉ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የተቀበሩ ቢሆንም ከብዙ ዘመን በኋላ ዐፅማቸውን አፍልሰው በተድባበ ማርያም እንደቀበሯቸው ጽፈዋል፡፡
የአቡነ ዓምደ ሚካኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አባ ኪርያቆስ፡- ወላጆቹ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ የሆኑት አባ ጴጥሮስ አናጉስጢነት ሹሙት፡፡ (አናጉስጢስ ማለት መጽሐፍን ለሕዝቡ እንዲያነቡ የሚሰጥ የቤተ ክርስቲያን ማዕረግ ነው፡፡) አባ ኪርያቆስ ቅዱሳት መጻሕፍትን ዘወርት የሚመረምር ሆነ፡፡ ትርጓሜያቸውንና ምሥጢራቸውንም በመመርመር የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ሕግ አጸና፡፡ በትምህርቱና በዕውቀቱም ከሁሉም ይልቅ ከፍ ከፍ አለ፡፡ ዕድሜውም 18 ዓመት በሆነው ጊዜ ሚስት ያጩለት ዘንድ ወላጆቹ ግድ አሉት ነገር ግን አባ ኪርያቆስ ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ይልቁንም ከገዳማት ወደ አንዱ ይሄድ ዘንድ እንዲያሰናብቱት ወላጆቹን ለመናቸው፡፡ ወደ ኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ አባ ቄርሎስ ዘንድ በመሄድ መመንኮስ እንደሚፈልግ ነገራቸው፡፡ እርሳቸውም በአባ ኪርያቆስ አማካኝነት የብዙዎች ነፍሳት ብሩሃን እንደሚሆኑ ትንቢት ተናገሩለትና የመነኮሳት አባት ወደሚሆን ወደ ክቡር አባ ሮማኖስ ላኩት፡፡ አባ ሮማኖስም በደስታ ተቀብለው አመነኮሱትና የሰይጣንን የማሰናከያ መንገዶች ሁሉ ዘርዝረው አስተማሩት፡፡ አባ ኪርያቆስም በጸም በጸሎት በስግደት ተወስኖ እየተጋደለ በገዳሙ አባቶችን እያገለገለ ተቀመጠ፡፡ ከብዙ ተጋድሎውም በኋላ እግዚአብሔር የመፈወስን ሀብት ሰጠውና ብዙ ድውያንን የሚፈውሳቸው ሆነ፡፡ የትሩፋቱና የቅድስናው ዜና በሁሉም ቦታ በተሰማ፡፡
ከዚህም በኋላ ኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ አባ ቄርሎስ የክብር ባለቤት የሆነ መንፈስ ቅዱስን መቅዶንዮስ ስላቀለለ አባ ቄርሎስ 150 እጅግ የከበሩና ቅዱሳን የሆኑ ሊቃውንት ኤጲስቆጶሳትን አንድነት ወደሚሰበስብበት ወደ ቁስጥንጥንያ በሚሄድ ጊዜ ይህን አባ ኪርያቆስን አስከትሎት ሄደ፡፡ እነርሱም በላያቸው ባደረ መንፈስ ቅዱስ ስም ተከራክረው ከሃዲ መቅዶንዮስን ረቱት፣ አስተምረው መክረው ዘክረው የማይመለስ ሆኖ ቢያገኙት አውግዘው ረግመው ለዩት፡፡ አባ ኪርያቆስም እግዚአብሔርን ሲያገለግል ኖሮ በመልካም ሽምግልና ሆኖ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ከዕረፍቱም በኋላ ከሥጋው ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ቅዱስ ሥጋው በኢየሩሳሌም ካሉ ገዳማት በአንደኛው በክብር ይኖራል እርሱም በሕይወት ያለ ይመስላል እንጂ የሞተ አይመስልም፡፡ እስከዛሬ ድረስ ሥጋው አልተለወጠም ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄዱ ሁሉ ያዩታል፡፡ የሚያዩትም ሁሉ በቅርብ ቀን ያረፈ ይመስላቸዋል ነገር ግን አባ ኪርያቆስ ያረፈው ለደጋጎቹ ነገሥታት ለአኖሬዎስና ለአርቃዴዎስ አባታቸው በሆነ በታላቁ ንጉሥ በቴዎዶስዮስ ዘመን ነው፡፡ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + +
አቡነ መድኃኒነ እግዚእ፡- ከደጋግ ክርስቲያኖች ከቀሲስ ሰንበት ተስፋነ እና ከኅሪተ ማርያም በ1180 ዓ.ም በሥዕለት የተወለዱት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እጅግ አስደናቂ ገድልና ትሩፋት ያላቸው ጻድቅ ቢሆኑም ብዙው ሕዝበ ክርስቲያን እንደሚገባቸው መጠን ያላወቃቸው ታላቅ አባት ናቸው፡፡ መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጩን አባቶች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚወስዱት የደብረ በንኮሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ እስቲ ቀጥሎ ስማቸውን የጠቀስኳቸውን እነዚህን ቅዱሳ

ን አባቶች ታሪካቸውንና የጽድቅ ሕይወታቸውን አስታውሱት፡- እነርሱም አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘቆየፃ፣ አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ፣ አቡነ ታዴዎስ ዘባልታርዋ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤ እና አቡነ ዮሐንስ ዘጉራንቄ እነዚህን የመላእክትን ሕይወት በምድር የኖሩ ታላላቅ የሀገራችንን ቅዱሳን አስተምረውና አመንኩሰው ለጽድቅ ያበቋቸው አባት አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡
አቡነ መድኃኒነ እግዚእ እነዚህን ሰባቱን ቅዱሳን በአንድ ጊዜ ሲያመነኩሷቸው በዚያው ቅጽበት መንፈስ ቅዱስ ወርዶ ገዳሙን ደብረ በንኮልን በብርሃን አጥለቅልቆት ታይቷል፡፡ ከሰማይም የምስክርነት ድምፅ ተሰምቷል፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ላይ የመነኮሱት እነዚህ ሰባቱ ቅዱሳን ‹‹ሰባቱ ከዋክብት›› እየተባሉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህም ሰባቱ ከዋክብት የጣናን ባሕር በእግራቸው ጠቅጥቀው ተሻግረው ብዙዎቹን ደሴቱ ላይ ያሉ አስደናቂ የጣና ገዳማትን የመሠረቱት ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ትልቅ ጠፍጣፋ ድንጋይን እንደጀልባ ተጠቅመው በእርሱ ላይ ሆነው ወደ ደሴት የገቡ አሉ፡፡ በእግራቸውም እየረገጡ ባሕሩን የተሻገሩ አሉ፡፡ በሌላም ቦታ በየብስ የተሰማሩትም ቢሆኑ መጻሕፍቶቻቸውን በአንበሳ ጭነው የተጓዙ አሉ፡፡
በደብረ ሊባኖሱ ሐዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ ብርሃኗ በሆኑት በአቡነ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከመነኮሱ በኋላ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በተራቸው ያስተማሯቸውና ያመነኮሷቸው መነኮሳት ቁጥራቸው በውል አይታወቅም፡፡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትም ለአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ‹‹ስፍር ቁጥር የሌላቸው ከዋክብት ቅዱሳንን›› በመንፈስ ቅዱስ እንደሚወልዱ ትንቢት ተናግረውላቸው ነበር፡፡ የተንቤኑን አቡነ ዐቢየ እግዚእን፣ የዞዝ አምባውን አቡነ አብሳዲን ጨምሮ አባታችን መድኃኒነ እግዚእ ብርሃን ሆነው በጣም ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን›› ይባላሉ፡፡
የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ልጆች ዛሬ ግሸን ላይ በክብር ተቀምጦ ሀገራችንን ከመዓት እየጠበቀ ያለውን የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ያመጡትም እነርሱ ናቸው፡፡ ዐፄ ዳዊት በዘመናቸው ረኃብ ስለነተሳ የደብረ ቢዘኑን አቡነ ፊሊጶስን ከገዳማቸው አስጠርተው ‹‹ምን ባደርግ ይሻለኛል?›› ብለው አማከሯቸው፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ‹‹የጌታችንን መስቀል ያስመጡ›› ብለው መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው ዓሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን መርጠው ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ በጽድቅ ሥራቸውና ተአምራትን በማድረግ በወቅቱ ታዋቂ የነበሩትና ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዐሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡
የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ተአምራታቸው እጅግ ብዙ ነው፡፡ አራዊት ሁሉ እንደሰው ያገለግሏቸው የነበር፡፡ ውኃ የሚያመላልስላቸውንና የሚያገለግላቸውን አህያ አንበሳ ቢበላባቸው በአህያው ምትክ አንበሳውን ድፍን 7 ዓመት ለገዳማቸው ውኃ አስቀድተውታል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡- ለአባታችን ውኃ የሚያመላልስላቸውና የሚያገለግላቸው አንድ አህያ ነበራቸው፡፡ ውኃው የሚገኘው እርሳቸው ካሉበት በጣም እርቆ በእግር የ3 ሰዓት መንገድ ከተሄደ በኋላ ነው፡፡ ነገር ግን አህያቸው እንደ ሰው እየተላላካቸው ይቀዳላቸው ነበር፡፡ አንድ ግን ከመንገድ አንበሳ አግኝቶት ግማሽ አካሉን በልቶት ሄደ፡፡ አባታችንም የአህያቸውን ተረፈ በድን አግኝተው በማዘን ‹‹ውኃ የሚያመላልስልኝ ረዳቴ ይህ አህያ ብቻ ነበር፣ አሁንም አህያዬን የበላህ አውሬ እንድታነጋግረኝ እፈልጋለሁ›› ቢሉ በአንበሳ ተበልቶ የሞተው የአህያው ግማሽ አካል አፍ አውጥቶ አንድ አንበሳ እንደበላው ነገራቸው፡፡ አቡነ መድኃኒነ እግዚእም በዚህ እጅግ ደስ ተሰኝተው ፈጣሪያቸውን ካመሰገኑ በኋላ አህያቸውን የበላውን አንበሳ ከጫካው ውስጥ ጮኸው ጠሩት፡፡ አንበሳውም ከሌሎቹ አንበሳ ተለይቶ ወደ እርሳቸው በመምጣት እግራቸው ሥር ወድቆ ሰገደ፡፡ አባታችንም ‹‹አህያዬን የበላኸው አንተ ነህን?›› ብለው ሲጠይቁት አንበሳውም በሰው አንደበት ‹‹አዎ እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ፈጣሪያቸውን በድጋሚ ካመሰገኑ በኋላ አንበሳውን ‹‹በል ና ተከተለኝ በአህያዬ ምትክ ታገለግለኛለህ›› አሉት፡፡ አንበሳውም ተከትሏቸው ወደ በዓታቸው በመግባት ለ7 ዓመታት እንደ አህያቸው ውኃ እየቀዳ አገልግሏቸዋል፡፡ የአንበሳው ቆዳ ዛሬም በገዳማቸው ደብረ በንኮል በክብር ተቀምጠቷል፡፡
አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባንም አመንኩሰው መርቀው ሲሸኟቸው እንዲያገለግሏቸው አንበሶችን ከጫካ ጠርተው ያዘዙላቸው አባታቸው አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ናቸው፡፡ የዋልድባው አቡነ ሳሙኤል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ከመነኮሱ በኋላ በደብረ በንኮል 12 ዓመት አባታችንን ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ እሳት እስከማያቃጥላቸው ድረስ ከብቃት ደረጃ ላይ ሲደርሱ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ መርቀው በማሰናበት በዓት እንዲያጸኑ ሲያደርጓቸው አቡነ ሳሙኤል በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ጣና ደሴት ገብተው ሱባኤ ያዙ፡፡ በዚያም ሳሉ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ማረፋቸውን በመንፈስ ዐውቀው ሲያለቅሱ ጌታችን የአቡነ መድኃኒነ እግዚእን ነፍስ በእቅፉ አድርጎ ወደ ገነት ሲያሳርጋት አሳያቸው፡፡ ወዲያውም ጌታችን በብርሃን ሰረገላ አድርጎ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባን ደብረ በንኮል አድርሷቸዋል፡፡ በዚያም እስከ 40ኛው ቀን ከቆዩ በኋላ በዚሁ ዕለት ሲቀድሱ ክንድ ከስንዝር ከመሬት ከፍ ብለው ቅዱሳን ሐዋርያት እየተራዱዋቸው ከቀደሱ በኋላ ወደነበሩበት መልሷቸዋል፡፡ የጻዲቁ የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ቀን 1360 ዓ.ም ሲሆን ጠቅላላ ዕድሙያቸውም 180 ዓመት ነው፡፡
ዐፄ ፋሲል ጻድቁ የተከሏቸውን የጥድ ዛፎች በሙሉ ተቆርጠው የአክሱም ቤ/ክ እንዲሠራበት አዋጅ አወጁና መልእክተኞች መጥተው ዛፎቹን ሲቆርጡ መነኮሳቱ ግን ‹‹ጻድቁ አባታችን የተከሏቸው የጥድ ዛፎች መቆረጥ የለባቸውም›› ብለው ቢከራከሩም ሰሚ አላገኙም፡፡ መነኮሳቱም ወደ እግዚአብሔር ቢያመለክቱ ጩኸታቸው ተሰምቶላቸው ወዲያው እየተቆረጡ ያሉት የጥድ ዛፎች በሙሉ በተአምራት ወደ ወይራ ዛፍነት ተለወጡ፡፡ የወይራ ዛፎቹም ለዐፀድ እንጂ ለሕንፃ የማይመቹ ጎባጣ ሆኑ፡፡ የዚህም ምልክቱ ዛሬም ድረስ አለ፡፡ ግንዱ ጥድ ዛፉ ግን ወይራ የሆነ ትልቅ ዛፍ ‹‹ወይራ ዘገብረ ተአምር›› በሚባል ቦታ አሁንም ድረስ ቆሞ ይታያል፡፡
ጻድቁ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ በ1312 ዓ.ም የመሠረቱት ገዳማቸው ደብረ በንኮል ከአክሱም በእግር ሦስት ሰዓት ያስኬዳል፡፡ ይኸውም በንግሥተ ሳባ ቤተ መንግሥት አድርጎ የቀዳማዊ ሚኒሊክን መቃነ መቃብር አልፎ በመሄድ ነው፡፡ ወይም በመኪና ለመጓዝ አክሱም ጉበዱራን አቋርጦ ውቅሮ ማራይ ከተማን አልፎ በስተ ሰሜን አቅጣጫ 10 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ በስተ ምዕራብ የአቡነ አላኒቆስ ዘማይበራዝዮን ገዳም፣ በስተ ምሥራቅ የአቡነ ሰላማን ገዳም እየተለመከቱ እንደተጓዙ ጥቅጥቅ ባለ ደን የተሸፈነውን ደብረ በንኮልን ያገኙታል፡፡ ኅዳር 20 ጻድቁ ስለሚነግሱ ገዳሙም ለአክሱም ቅርብ ስለሆነ ይህ ለአክሱም ጽዮን ተጓዦች ተጨማሪ ትልቅ በረከት ነው፡፡
ደብረ በንኮል ማለት ‹‹ሙራደ ቃል›› ማለት ነው፡፡ ትርጉሙም የምሥጢር መውረጃ ማለት ነው፡፡ በቦታው ላይ ሱባኤ

ለያዘ ሰው እንደ ቅዱስ ያሬድና እንደ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ምሥጢር እንደሚገለጥለት የሚጠቁም ነው፡፡ በ14ኛው መ/ክ/ዘ የነበሩት ደጋግ መነኮሳት ሕይወታቸውን በሙሉ በምንኩስና፣ በጸሎትና በታላቅ ተጋድሎ መኖር ሲፈልጉ ከደብረ ዳሞ፣ ከሐይቅ እስጢፋኖስ፣ ከደብረ ሊባኖስና ከሌሎቹም የሀገራችን ክፍሎች እየተነሡ ወደ ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ነበር የሚሄዱት፡፡
የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ቃልኪዳን፡- ጻድቁ ባርከው ያፈለቁት ጸበላቸው ላበደ ሰው መድኃኒት ነው፡፡ ከመቃብራቸው ላይ የሚነሣውን አፈር ጻድቁ ባርከው ባፈለቁት ጸበላቸው ታሽቶ በእጃቸው መስቀል ተባርኮና ታሽቶ የሚዘጋቸውን የአቡነ መድኃኒነ እግዚእን እምነታቸውን በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው ንብረቱን ሌባ ቀማኛ ዘራፊ አይሰርቀውም፤ የመኪና አደጋ አይደርስበትም፤ ጥይት አይመታውም፡፡ ‹‹በእምነት ሆኖ የያዘን ሰው›› መባሉን ልብ ይሏል፡፡ ይኸውም ለጻድቁ የተሰጣቸው ታላቅ ቃልኪዳን ነው፡፡
የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አቡነ ፍሬ ካህን፡- ጻድቁን በመጀመሪያ ከጎጃም ተነሥተው በታዘዘ መልአክ መሪነት ትግራይ ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ሄደው መንነው መነኮሱ፡፡ ጻድቁ ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው ሲሆኑ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ይታወቃሉ፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን ወንጌልን ሲሰብኩ ሙታንን እያስነሡ በሲኦል ውስጥ ስላለው መከራና ሥቃይ እንዲመሰክሩ ያደርጓቸው ነበር፡፡ ጻድቁ ሐይዳ ገዳም ታቦት ተቀርጾላቸው ገድል የተጻፈላቸው ቢሆንም ሙሉ ገድላቸው ታትሞ ለምእመኑ አልተዳረሰም፡፡ አቡነ ቶማስ ካረፉ በኋላ አቡነ ፍሬ ካህን ገዳማቸውን ተረክበው በጽድቅ መንገድ መነኮሳቱን አስተዳድረዋል፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኮሳቱ ‹‹ገዳሙን በአህያ አታስረግጥ›› ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ አድርገዋቸዋል፡፡
አባታችን ሽሬ ደብረ ሐይዳ አቡነ ፍሬ ካህን የተባለ ትልቅ ገዳም አላቸው፡፡ ገዳሙ ከአቡነ ቶማስ ዘሐይዳ ገዳም ጋር አንድ ነው፡፡ ወደዚህ ገዳም ውስጥ ሥጋና ቅቤ ተበልቶም ሆነ ተይዞ መውጣት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ አልታየሁም ተብሎ በድብቅ ሥጋ ተይዞ ቢገባ ሥጋው ይተላል፡፡ ሥጋና ቅቤ የበላ ሰውም ዕለቱን በድፍረት ወደ ገዳሙ ቢገባ ሆዱ በኃይል ይነፋል በዚህም ይታወቅበታል፡፡ ከብቶችም ቢሆኑ ወደ ገዳሙ አይወጡም፣ ማንም ሳይመልሳቸው ራሳቸው ይመለሳሉ፡፡ የአቡነ ፍሬ ካህን ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ነው፡፡
የአቡነ ፍሬ ካህን ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ነዓኵቶ ለአብ፡- ከላስታ (ከዛጉዌ) ነገሥታት መካከል ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ገብረ ማርያም፣ ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነአኵቶለአብ እነዚህ አራቱ ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ 14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅድስና አገልግለው አልፈዋል፡፡ በንግሥናቸው አገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሎአቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው፡፡ ከእነርሱም ውስጥ ሞትን ሳያይ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ የተሰወረ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ በባሕር ላይ ቤተ መቅደሱን ያነጸ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር ራሱ ጌታችን በቃሉ ያስረዳው አለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በክህነቱ ሲቀድስ 40 ዓመት ሙሉ ቅዱስ ቁርባኑን መላእክት ከሰማይ እያመጡለት የነበረ አለ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ ነው፡፡
የእነዚህ ቅዱሳን ነገሥታቱን የዘር ሐረጋቸው ከሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ ‹‹የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት›› ወይም ‹‹የላስታ መንግሥት›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከዛጉዌ ነገሥታት ውስጥ የመጀመሪያው ንጉሥ መራ ተክለሃይማኖት የዐፄ ድልነአድን ልጅ መሶበወርቅን አግብቶ አራት ልጆችን ወልዷል፡፡ ሦስቱ ወንዶች ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ይባላሉ፡፡ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ቅዱስ ገብረማርያምንና ቅዱስ ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ መስቀልም ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማያስገባውን ገዳም መሠረቱትን የዘመቄቱን ታላቁን አባት አቡነ አሮንን ወለደ፡፡ ቅዱስ ገብረማርያም ደግሞ ቅዱስ ነዓኵለአብን ወለደ፡፡ ይኸውም ቅዱስ ነዓኵ ለአብ በዛሬዋ ዕለት ሞትን ሳያይ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ የተሰወረ ነው፡፡
‹‹ነዓኵቶ ለአብ›› ማለት የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚብሔር አብን እናመስግነው›› ማለት ነው፡፡ የቅዱስ ላሊበላ የወንድም ልጅ ሲሆን ከ11ዱ የዛጉዌ ነገሥታት ውስጥ 10ኛው ነው፡፡ አባቱ ቅዱስ ገብረ ማርያም ሥልጣኑን ለወንድሙ ለቅዱስ ላሊበላ ትቶ በመመንኮስ በበዓት ተወስኖ በጾም በጸሎት ሲጋደል ጌታ ተገልጾለት ‹‹ክብሩ እንደ መላእክት የሆነ ልጅ ትወልዳለህና ወደቤትህ ተመለስ›› ብሎ አዘዘው፡፡ ንጉሡ ገብረማርያምም ‹‹40 ዓመት ስነግሥ ያልወለድኩትን አሁን ዓለም በቃኝ ስል ትወልዳለህ የተባልኩት ልጅ ምን ዓይነት ልጅ ይሆን!›› እያለ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ሚስቱን መርኬዛንም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ካበሰራት በኋላ ነአኵቶለአብ ጌታ በተወለደበት ዕለት ታኅሳስ 29 ቀን ተወለደ፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ቀደም ብሎ የተወለደው እንዲሁ በጌታ የልደት ቀን ታኅሳስ 29 ቀን 1101 ዓ.ም ነው፡፡
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነአኵቶ ለአብ እንደሚወለድ ቀድሞ ለንጉሥ ላሊበላ ነግሮት ነበርና እንደነገረውም እርሱ ሲወለድ ‹‹ያ የነገርኩህ ሕፃን ተወልዷልና ወስደህ በሃይማኖት አንጸህ አሳድገው›› ብሎታል፡፡ ቅዱስ ላሊበላም ሃይማኖቱን ጠንቅቆ እያስተማረ በእንክብካቤ አሳደገው፡፡ ግብፅ ሄዶ ከአቡነ ቄርሎስ ዲቁናን ተቀበለ፡፡ በኋላም ቅስናን ተቀበለ፡፡ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሶቹን ሠርቶ ከጨረሰ በኋላ በሕይወት ሳለ መንግሥቱን ስላወረሰው ከላሊበላ በኋላ ነግሦ ኢትዮጵያን ለ40 ዓመት (ከ1197 ዓ.ም-1237 ዓ.ም) ድረስ መርቷል፡፡ ዕድሜው ሲደርስ መልአኩ ሚስት እንዲያጭለት ለቅዱስ ላሊበላ ነግሮት ሲያጭለት እግዚአብሔርን በድንግልና ማገልገል ይፈልግ ነበርና በዚህም እጅግ ሲያዝን እመቤታችን ተገልጻለት ጋብቻው ከእግዚአብሔር መሆኑን ነግራ አጽናንታዋለች፡፡ ‹‹የጌታህ ፈቃድ ነውና አትዘን ይልቁንም አግባ፣ ክብርህም ከደናግላን አያንስም›› ብላ ስለነገረችው ሚስት ቢያገባም ልክ እንደ ቅዱስ ዲሜጥሮስና ልዕልተወይን ንጽሕናቸውንና ድንግልናቸውን ለመጠበቅ በመማከር በግብር ሳይተዋወቁ ለ25 ዓመታት በድንግልና ሆነው በትዳር ኖረዋል፡፡ እህት ወንድሞች ሆይ እስቲ ልብ በሉ! በሕግ ካገባት ሚስቱ ጋር ለዚያውም በእመቤታችን ትእዛዝ አግብቶ ሳለ በግብር ሳያውቃት አብሮ ከድንግል ሴት ጋር በትዳር 25 ዓመት መኖር ይህ እንዴት ያለ ቅድስና ነው በእውነት!!!
ከዚህ በኋላ መልአክ መጥቶ ‹‹በንጽሕና የተጋባችሁት ልትወልዱ ነው እንጂ ዝም ብላችሁ ልትኖሩ አይደለም›› ብሏቸው አንድ ቀን ብቻ በግብር ተዋወቁና እጅግ የሚያምርና የሚያሳሳ ልጅ ወለዱ፡፡

ልጁም እጅግ የሚያምርና የሚያሳሳ ቢሆንም ንጉሡ ቅዱስ ነአኵቶለአብ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ የወደፊቱን ያውቅ ነበርና ሱባኤ ገብቶ ‹‹በእኔ እግር ተተክቶ ሲነግሥ ፍርድ አጣሞ አንተንም ሰውንም ከሚበድል ይህን ልጄን ቅሰፍልኝና ሄሮድስ ካስፈጃቸው ሕፃናት ጋር ደምርልኝ›› በማለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ እንደጸሎቱም ጌታችን የካቲት 16 ቀን ልጁን በሰላም አሳርፎለት ሄሮድስ ካስፈጃቸው ሕፃናት ጋር ደምሮለታል፡፡ በዚህም ጊዜ መኳንንቶቹ፣ መሳፍንቶቹና ሕዝቡ ሁሉ ለልቅሶ ቢመጡ እርሱ ግን በቤተ መንግስቱ በልቅሶ ፈንታ ታላቅ የደስታ ድግስ አድርጎ ስለጠበቃቸው ‹‹የንጉሡ ልጅ ሞተ የተባለው ውሸት ነው›› ብለዋል፡፡
ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ክህነትን ከንግሥና ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አስተባብረው ይዘው ኢትዮጵያን ከመሩ ከአራቱ የዛጉዌ ነገሥታት አንዱ ሲሆን በነገሠበት 40 ዓመት ሙሉ ዓርብ ዓርብ ቀን የክርስቶስን ሕማም እያሰበ በዕንቁና በወርቅ በተሽቆጠቆጠው ዘውዱ ፈንታ የእሾህ አክሊልን ደፍቶና በአምስቱ ቅንዋተ መስቀሎች ምሳሌ አምስት ጦር ዙሪያውን ተክሎ እያለቀሰ ይጸልይና ይሰግድ ነበር፡፡ በዙፋኑም ላይ ለፍርድ በተቀመጠ ጊዜ ከንግሥና ልብሱ ውስጥ በስውር ማቅ ለብሶና ሰውነቱን በሰንሰለት አስሮ ከላይ ግን በክብር ልብሱ ተሸፍኖና በወርቅ ወንበር ተቀምጦ ይፈርድ ነበር፡፡ ፍርድ ሲሰጥም ሁሉንም ነገር በመንፈስ ቅዱስ እያውቅ ነበር፡፡ ምስክሮችን አይሻም ይልቁንም ሰዎቹ ገና ሳይመጡ ሌሊት በምን ወንጀል ተካሰው እንደሚመጡ በመንፈስ ይገለጽለት ነበር፡፡ ወደ እርሱም በመጡ ጊዜ እነርሱ ጉያቸውን ከመናገራቸው በፊት እርሱ አቀድሞ አስማምቶ በጽድቅ ፈርዶላቸው ወደየመጡበት ይመልሳቸዋል፡፡ ሰዎቹም ‹‹…ይህስ በእውነት የመንፈስ ቅዱስ ፍርድ እንጂ የሰው ፍርድ አይደለም›› እያሉና እያደነቁ ይመለሳሉ፡፡
ጻዲቁ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ በዘመኑ ግብፆች ‹‹ግብር አንሰጥም›› ብለው ስላመፁበት የዓባይን ወንዞች በጸሎቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዲፈስ ስላደረገባቸው ግብፆች ከበፊቱ ጨምረው ግብራቸውን አምጥተው ሰጥተውት ግዝቱን አንስቶላቸዋል፡፡
ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ መላ ዘመኑን ሁሉ የክርስቶስን መከራ እያሰበ ያለቅስ ስለነበር የመድኃኔዓለምን መራራ ሐሞት መጠጣት እያሰበ ሁልጊዜ ዓርብ ዓርብም ኮሶ ይጠጣ ነበር፡፡ በመጨረሻም ውለታን የማይረሳ አምላክ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ተገልጦለት እንዲህ አለው፡- ‹‹ወዳጄ ነአኵቶ ለአብ ሆይ! እኔ ለዓለም ደሜን ያፈሰስኩት አንድ ቀን ነው፤ አንተ ግን 40 ዓመት ሙሉ ስለ እኔ ብለህ ደምህንንና እንባህን ስታፈስ ኖርክ፣ ይበቃሃል አሁን ወደ እኔ ልወስድህ ነው›› አለው፡፡ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብም ጌታችንን ‹‹ጌታዬ ሆይ! እዚህ ቦታ እኔን ብለው የሚመጡ ወገኖቼን ማርልኝ›› አለው፡፡ ጌታችንም ‹‹እውነት እልሃለው ከተፀነስክበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለውን ገድልህን እያነበበ ዝክርህን የዘከረውን፣ በዓልህን ያከበረውን፣ ለቤተ ክርስቲያንህ መባ ያገባውን ሁሉ ኃጢአቱ ቢበዛም ‹ቅዱስ ነአኵቶ ለአብ አማልደኝ› ያለውን ኃጢያቱ ምን ቢበዛ እምርልሃለው፤ ዳግመኛም እልሃለው 40 ዓመት ሙሉ እንባህን ያፈሰስክባት ይህች ምድር እስከ ዕለተ ምጽአት እያነባች ትኖራለች፣ ይኸውም የእኔን መከራ እያሰብክ ከዐይንህ ዕንባ ሳይቋርጥ እንዳለቀስክልኝ ሁሉ ከቤተ መቅደስህ በእንባ መልክ የሚንጠባጠብ ጠበል ይፍለቅልህ፣ ይህም የዕንባህ ምሳሌ ነው፤ ከዚህ ለሚጠጡ ለሚጠመቁ ድኅነት ይሁናቸው›› የሚል የምሕረት ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ጌታችን ይህን አስገራሚ ቃልኪዳን ከሰጠው በኋላ ቅዱስ ነአኵቶ ለአብን በሞት ፈንታ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ ኅዳር 3 ቀን ሰውሮታል፡፡ በቃልኪዳኑም መሠረት ብዙ ፈውስን የሚሰጠው ጠበሉ ዛሬም ድረስ ልክ እንደሰው ዕንባ ቤተ መቅደሱ ካለበት ዋሻ ላይ እየተንጠባጠበ ወደ ታች ይወርዳል፣ ምንም እንኳን ከዋሻው በላይ ያለው መሬት ሜዳ ቢሆንም ቃልኪዳኑ ነውና የጠበሉ መጠን ክረምት ከበጋ አይጨምርም አይቀንስም፡፡ ይልቁንም በሰው ዕንባ መጠን ጠብ ጠብ እያለ በመውረድ ከእርሱ ለሚጠመቁት ፈውስን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የቅዱስ ነአኵቶ ለአብ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!

#አሳዛኝ_ዜና_
#ሰለ_ቅድስት_ቤተከርስቲያን_ጸልዮ
ኅዳር 3 /2012 ዓ.ም. በምሥራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት የሚገኙ 2ት አብያተክርስቲያናትና በተለያዩ ቦታዎች (በተለይም በቀርሳና ወተር) በሚገኙ ምዕመናን ላይ ከፍተኛ ጥቃት መድረሱን የምስራቅ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ገልጿል፡፡ የተቃጠሉት አብየተ ክርስቲያናትም፤#ዋቅጅራ_መድኀኔ_ዓለም_#ጥንታዊና_ታሪካዊቷ_ገንዲድ_ቅድስት_ማርያም_ቤተ_ክርስቲያን_ ሲሆኑ የጥፋት ኀይሎች አደጋውን ወደ ቊልቢ ቅዱስ ገብርኤል ለመውሰድም ስለሚሠሩ ሁላችንም፤ በተለይም በቊልቢ አቅራቢያ የምንገኝ
#ክትትል_ወደ_ቊልቢ_ ልናደርግ #እና_ቤተከርስቲያንናችንን_ልንጠብቅ_ይገባል፡፡

የጾመ ነቢያት መግቢያና መውጫ
ከአራት ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ዮሐንስ ጾመ ነቢያት መጀመሪያውና መጨረሻው ላይ ብዙ
ውዝግብ ይነሣል በዚህም ምክንያት በተለይ ሕዝቡ በየጊዜው ግራ ሲጋባ ይታያል
በእርግጥ ሁሉም ሰው ጥያቄ የሚያነሣው መግቢያው ላይ እንጅ መጨረሻው (ፋሲካው)
ላይ አይደለም ፋሲካው ላይ ጥያቄ የማያነሣውም በ28 መፈስክን ስለለመደ ነው
ለመሆኑ እንዲህ ዓይነት ልዩነት የመጣው ከመቼ ጀምሮ ነው ጾሙስ መግባት ያለበት መቼ
ነው
ጾሙ ስንት ቀን ነው የሚጾመው የሚለውንና ከዚሁ ጋር ተያይዘው የሚነሡ መከራከሪያ
ነጥቦችን
ሁሉንም በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን
በመጀመሪያ ታኅሣሥ 28 ልደትን ማክበር የተጀመረ ከመቼ ወዲህ ነው የሚለውን እንይ
የጾመ ነቢያት መጨረሻ ላይ ክርክር የሚነሣው ከመቼ ጀምሮ ነው የሚለውን መሪጌታ ልሳነ
ወርቅ ገ/ ጊዮርጊስ ጥንታዊ ሥርዓተ ማኅሌት ዘአቡነ ያሬድ በሚለው መጽሐፋቸው በገጽ
187፣188 189 ላይ የከተቡትን እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ
የበዓለ ልደት አከባበር መፋለስ
ንዑስ ክፍል 1
የበዓለ ልደት አከባበር ስለተፋለሰበት ዘመን
ከ871 ዓመተ ምሕረት ጀምሮ የኢትዮጵያ ንጉሥ ውድም አስፈሬ የግብፅ ንጉሥ መቅትር
ነበሩ መቅትር በነገሠ በ18 ዘመነ መንግሥቱ በ889 ዓመተ ምሕረት አባ ቆዝሞስ የተባለ
ብፁዕ መነኰስ በመንበረ ማርቆስ ላይ ሊቀ ጳጳሳት ተሾመ ርእሱም የተማረውንና ደግ
የሆነውን አባ ጴጥሮስን ጵጵስና ሹሞ ወደኢትዮጵያ ላከው ከጥቂት ዘመን በኋላ
የኢትዮጵያው ንጉሥ ውድም አስፈሬ 30 ዓመት እንደነገሠ ድንገት በጠና ታመመ በዚህ
ጊዜ አባ ጴጥሮስን አስጠርቶ ወደቤተ መንግሥቱ አስመጥቶ አርማሕ ሰገድና ድግናዠን
የተባሉ ሁለቱ ልጆቹን በፊቱ አቅርቦ አክሊለ መንግሥቱን አንስቶ ለጳጳሱ አባ ጴጥሮስ ሰጥቶ
እነሆ እኔ በአካለ ነፍስ ወደጌታየ ኢየሱስ ክርስቶስ መሔዴ ነውና ከሁለቱ ልጆቼ
ለመንግሥት የሚበቃውን አንተ ራስህ መርጠህ አውቀህ የተሻለውን ከኔ በኋላ አንግሠህ
አክሊለ መንግሥቴን አቀዳጅተህ በዙፋኔ አስቀምጥልኝ አለው ከዚህ በኋላ ወዲያው
በ901 ዓመተ ምሕረት አረፈ ያን ጊዜ ጳጳሱ አባ ጴጥሮስና መኳንንቱ፣ የሠራዊቱ አለቆች፣
የቤተ መንግሥቱ ታላላቆች አማካሮች ሊቃውንት ተሰብስበው ተማክረው ከታላቁ ታናሹ
ለመንግሥትነት እጅግ የተገባ ነው ተባብለው ታናሹ አርማሕ ሰገድን አንግሠው በአባቱ
ዙፋን አስቀመጡት ከዚያ በኋላ አባቱ ንጉሥ ውድም አስፈሬን በአባቶቹ ነገሥታተ አክሱም
መቃብር አክሱም ላይ ቀበሩት
ልጁ አርማህ ሰገድም 5 ዓመት እንደነገሠ በርሱ ዘመን ሰይጣን ያደረባቸው አባ ሚናስና
አባ ፊቅጦር (እንድራዎስ)የሚባሉ ሁለት ሐሳውያን መነኰሳት ከሦርያ ተነሥተው ከሀገር
ወደሀገር ሲዞሩ ከአባ እንጦንስ ደብር (ገዳም)ገብተው ጥቂት ቀን እንደተቀመጡ የክሕደት
ትምህርት ስላመጡና ሁከት ስላስነሡ የደብሩ መነኰሳት አባ ሚናስንና አባ ፊቅጦርን
በክሕደታቸውና በክፋታቸው ከደብራቸው አስወጥተው አባረሯቸው
እነዚያ ሁለቱ ሐሰተኞች መነኰሳትም ርእስ በርሳቸው ተማክረው አባ ጴጥሮስ የተባለው
ሰው እኛ ሳንሾመውና ሳንልከው ጳጳስ ነኝ ብሎ ወደእናንተ (ወደኢትዮጵያ) መምጣቱን
ስለሰማን እነሆ እኛ ከእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ቆዝሞስ ጵጵስና ተሹመን መጥተናል
ርእሱ አባ ጴጥሮስ የሐሰት ጳጳስ ነው እውነተኛ ሹመን የላክነው ጳጳስ ግን በዚህ ደብዳቤ
የተጻፈ አባ ሚናስ ነው ሁለተኛም ታላቁን ትቶ ታናሹን ያነገሠው ሐሰተኛው አባ ጴጥሮስ ነው
ብለው የሐሰት ደብዳቤ ጽፈው ወደኢትዮጵያ መጥተው አክሱም ደረሱ ደብዳቤውን
ሰውረው ከደገኛውና እውነተኛ ኦርቶዶክሳዊ ጳጳስ አባ ጴጥሮስ ዘንድ ገብተው ለነገር
ምክንያት ፈልገው ጉቦ ወርቅ እንዲሰጣቸው ጠየቁት ርእሱም ጉቦ መስጠት ክልክል ነው
አልሰጥም አላቸው ያሰቡትን ነገር ለማቀጣጠል ተመቻቸውና ከእርሱ ወጥተው የጻፉትን
የሐሰት ደብዳቤ ላልነገሠው ለድግናይዠን ሰጡት
እርሱም ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ እውነት መስሎት በዓመፅ ተነሣሥቶ ብዙ አሽከሮች
ሰብስቦ ደብዳቤውን ዳግመኛ ከፊታቸው አንብቦ እንደፈጸመ ጦሩን አዘጋጅቶ ገስግሶ ሒዶ
በነገሠው ወንድሙ ላይ አዳጋ ጥሎ ይዞ አሠረው
አባ ጴጥሮስንም አሥሮ ወደሩቅ (ቦታ) ሀገር አባረረው ወዲያውም ታናሽ ወንድሙ ንጉሥ
አርማሕ ሰገድን ገድሎ በጉልበቱ ነገሠ በዚያ ጊዜ ሐሰተኛው ኣባ ሚናስን ጵጵስና ሹሞ
በአክሱም መንበረ ጵጵስና በአባ ጴጥሮስ መንበር አስቀመጠው ሐሰተኛው ፊቅጦርንም
የርሱ ምክትል አደርገው
ከዚህ በኋላ አባ ሚናስ ጳጉሜን 6 ሲሆን በዘመነ ዮሐንስ በዓለ ልደተ ክርስቶስን ታኅሣሥ
28 ቀን አክብሩ እርሱም ሰው ሁኖ ሲወለድ ከአብ በክብር አንሷል ብሎ ክሕደቱን
ለኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ባስተላለፈ ጊዜ በካህናቱና በምእመናኑ መካከል
የማያውቁት ሁከት ተፈጠረ
በዚህ የተነሣ በ318ቱ ሊቃውንተ ኒቅያ አምሳል 318 የኢትዮጵያ ሊቃውንት ተመርጠው
አክሱም ተሰበሰቡ ንጉሡ ባለበት ከሐሰተኛው አባ ሚናስ ጋር ክርክር ገጥመው፡-
1ኛ ወልድ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል መሆኑን፣ አነ ወአብ አሐዱ ንሕነ ወአሐዱ
ህላዌነ ያለውንና በሥላሴነታቸው አንድ ባሕርይ አንድ መለኮት አንድ ሥልጣን አንድ
መንግሥት አንድ አምላክ አንድ እግዚአብሔር ሁነው መኖራቸው አለ አሐዱ እሙንቱ
ሠለስቲሆሙ ያለውን፣ እንደዚሁ በለበሰው ሥጋ መሢህ ክርስቶስ መባሉንና ወኵሎ ኵነኔሁ
አወፈዮ አብ ለወልዱ ያለውን ይህን የመሰለውን ሁሉ ከቅዱሳት መጻሕፍት ጠቅሰው፤
2ኛ በዓለ ልደቱ ምንጊዜም በተወለደበት በታኅሣሥ 29 ቀን እየተከበረ እንዲኖር ሐዋርያት
በዲዲስቅልያ መጽሐፋቸው አንቀጽ 29 ወግበሩ በዓለ ልደት አመ ዕስራ ወሐሙሱ ለታሥእ
ወርኅ ዘዕብራውያን ዘውእቱ አመ እስራ ወተስኡ ለራብዕ ወርኅ ዘግብፃውያን ብለው
ወስነው ለመላው ክርስቲያን ማስተላለፋቸውን፣
3ኛ 6ኛ ጳጉሜን የሚባለው በዘመነ ዮሐንስ ጀምሮ እስከ ዘመነ ሉቃስ መጨረሻ ከየዓመቱ
ከ365 ቀን 15 ኬክሮስ (3 3 ሰዓት)ትርፍ የተገኘው ሲደመር 12 ሰዓት መሆኑንና ይኸውም
1 ቀን ሁኖ 6ኛ ጳጉሜን መባሉን ወደዘመነ ዮሐንስ አለመሸጋገሩን በሐሳበ አዝማን ገልጸው፣
4ኛ 318ቱ ሊቃውንተ ኒቅያ ይህን ሁሉ ሥርዓት ጠንቅቀው በፍትሐ ነገሥት ፍትሕ
መንፈሳዊ በአንቀጽ 19 ጽፈው ለሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ማስተላለፋቸውን ጠቅሰው፣ ዋና
ማስረጃውንም አቅርበው አባ ሚናስን ረትተው አሳፍረው መልሰውታል
ይሁን እንጅ አባ ሚናስ ቢረታም ለክፋት የማይታክት ነውና በጽሙና ከንጉሥ ድግናዠን
ዘንድ ሾልኮ ገብቶ ንጉሥ ሆይ እሊህ የተሰበሰቡት 318 የኢትዮጵያ ሊቃውንት በሞት
ካልተቀጡ የኢትዮጵያ ካህናትና ሕዝብ ሲታወኩ ይኖራሉ ወልድም ቅብዕ ነው፡፡ ጳጉሜን 6
ሲሆንም በዘመነ ዮሐንስ በዓለ ልደት ታኅሣሥ 28 ቀን ይከበር አይሉም ሲል አምርሮ
ነገረው ንጉሡም ስላልተማረና ስላልነቃበት ነገሩን ተቀብሎ የተሰበሰቡትን 315 ሊቃውንተ
ኢትዮጵያ አክሱም ላይ በሰይፍ አስፈጃቸው 3ቱ ሊቃውንት ግን የአክሱም ባላባት ስለሆኑ
ብናስገድላቸው የዓለም መንግሥታት መጥተው ይወጉናል ስለዚህ ከአክሱም አስወጥተን
ምድረ ተንቤን እናባርራቸው ተባብለው ወደተንቤን አሳደዷቸው (ወሰደድዎሙ ምድረ
ተንቤን እንዲል ክብረ ነገሥት ዘአክሱም)
ከቀድሞ ጀምሮ መግቢያው 15 ፋሲካው 29 ሁኖ የቆየ ቢሆንም ከ29 ወደ28 የወረደበት
ምክንያት ይህ ነው
ስለጾሙ መግቢያና መውጫው የሚነሡ ሐሳቦችና መልሶቻቸው
1. በአሥራአምስት ገብቶ በ28 መገደፍ አለበት የሚለው አንዱ ነው በዘመነ ዮሐንስ በ15
ተጀምሮ በ28 ይገደፍ ለሚሉት ከላይ ያየነው መልስ በቂ ይመስለኛል ሐሳቡ ሲነሣም

የሚያቀርቡት መልስ ሲኖዶሱ ስለወሰነ የሲኖዶሱን ቃል አክብረን መቀበል አለብን በማለት
ነው ከዚህ የተለየ መጽሐፋዊ ማስረጃ ሲያቀርቡም አይደመጡም እሱንም እንመለስበታለን
2. በአሥራ አምስት ተጀምሮ በ29 መፈጸም አለበት የሚለው ነው ይህ ከሐዋርያት ጀምሮ
ሲያያዝ የመጣ ስለሆነ መልስም ስላለው ምንም ተቃውሞ የለውም እንዲያውም አንድ
ታላቅ የቤተ ክርስቲያን አባት በ15 ተጀምሮ በ29 መገደፍ እንዳለበት የጻፉትን
እንደሚከተለው ላካፍላችሁ፡፡
በዘመነ ዮሐንስ ልደትን በ29 የሚያከብር መናፍቅ ነው እያልን እኛ ያለዕውቀት አጥፍተን
በ28 ቀን ስናከብር እንኖር ነበር በሚበላበት ስንጾም በሚጾምበት ስንበላ ብንገኝ ሕግ
አፍራሾች እንባላለን ይላልና አቡሻኽር፡፡
አሁን ግን መጻሕፍትን ሁሉ ብንመለከት የአክብሮተ በዓልና የጾም ሥርዓት ብቻ ነው እንጅ
የጸጋን የቅባትን ሃይማኖት የሚነካ ምስጢር ምንም የለበትም ስለዚህ ልደት በታኅሣሥ 29
ቀን መሆኑ ዘለዓለም አይናወጥም ጾሙም 44 ነው ከ44 አይወጣም አይወርድም
በመጀሪያ ሐዋርያት በሲኖዶስ አዘዘነ ሲኖዶስ ዘጸሐፈ ቀሌምንጦስ ካለው ላይ ትዕዛት 8
ወይግበሩ በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ በዕለተ ተወልደ በበዓመት አመ እስራ ወተሥኡ
ለታኅሣሥ እስመ ውእቱ ርእሰ በዓላት የጌታችን የልደቱን በዓል በተወለደበት ዕለት
በታኅሣሥ 29 ቀን ያክብሩ ብለዋል
2ኛ ሐዋርያት በዲዲስቅልያ በ29 አንቀጽ ሠለስቱ ምዕትም በፍትሐ ነገሥት በ19 አንቀጽ
አኀውየ ተዐቀቡ በዕለተ በዓላት ዘውእቱ በዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወግበሩ አመ ዕስራ
ወሐሙሱ ለታስእ ወርህ ዘዕብራውያን ዘውእቱ አመ እስራ ወተስኡ ለራብእ ወርኅ
ዘግብጻውያን ብለዋል የግብጻውያንና የኢትዮጵያ ዘመን መለወጫ መስከረም ነውና
ከመስከረም ጀምሮ ቆጥሮ በታኅሣሥ 29 ልደቱን አክብሩ አለ
28ንስ ፍትሐ ነገሥት በአንቀጽ 15 ድራረ ልደት የልደት ዋዜማ አድርጎ እስከ ሠርክ ጹሙ
አለ እስከ ሠርክ ጹሙ ያለውን ፋሲካ ማድረግ ዓመጽ ድፍረት ነው
3ኛ የአባታችን የወንጌላዊ ማርቆስ ገድል፣
4ኛ ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ
5ኛ ሐዊ ልደትን በ29 አክብሩ አሉ እንጅ በ28 አክብሩ አላሉም
6ኛ አቡሻኽር ጌታ ከተወለደበት ቀን ጀምሮ እስኪሰቀል ድረስ ዘመነ ዮሐንስ 8 ጊዜ ዋለ
በዚህ ሁሉ እመቤታችን በ29 በ29 ቀን ቤተ ልሔም እየወጣች ልደትን ታከብር ነበር ብሏል
ሐዋርያትም በ29 ቀን ያከብሩ ነበርና ልደትን በየዓመቱ በ29 ቀን አክብሩ ብለዋል
ስድስተኛይቱ ጳጉሜን ከአራቱ ወንጌላውያን የተረፈው 6፣6 ሰዓት ተሰብስቦ (የሌሊቱን
ጨምሮ ነው) 24 ሰዓት ይሆናልና በዘመነ ዮሐንስ አንድ ዕለት ሆነ እንጅ ከዮሐንስ ብቻ
የተገኘ አይደለም
ከግራኝ በፊት በደገኛይቱ ዘመን የተጻፈ ስንክሳር በ29 ቀን አክብሩ ይላል እንጅ በ28
አይልም ይኸውም ሊታወቅ ጎንደር የደብረ ብርሃን ሥላሴ ስንክሳር፣ ጋይንት አንሰታ ቆላ
ከአንድ ቦታ ያለ ስንክሳር እስቴ የመሐልጌ ጊዮርጊስና የመሐልጌ ጽዮን ስንክሳር በ29 ቀን
አክብሩ ይላል እንጅ በ28 አይልም እኛ ግን ከግራኝ ወዲህ የተጻፈውን ስንክሳር እያየን
ስናጠፋ ኑረናል
ቅዱስ ያሬድም ተርታ በዓሉን ሁሉ ለእመ ኮነ እያለ ሲጽፍ ትልቁን የጌታን በዓለ ልደት ለእመ
ኮነት ጳጉሜን ስድስተ አመ እስራ ወሰሙኑ ሳይል ዮም ፍሥሓ ኮነ ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ
ዓለም ብሎ በ29 ቀን አምልቶ አጉልቶ ተናገረ
ደቅስዮስም በመቅድመ ተአምር አመ እስራ ወሰሙኑ ጌና ወአመ እስራ ወተስኡ በዘወለደቶ
ለመድኃኒነ አለ በ28 ጌና ነው በ29 እመቤታችን ጌታን የወለደችበት ነው፡፡ ጌና ማለት በዓለ
እግዝእት ማለት ነው ወበጽሐ ዕለተ ወሊዶታ የምትወልድበት ቀን ደረሰ ስለሚል ጌና ተብሎ
በዓሉ ቢከበርም መጾሙ አይቀርም (ጌና ማለት ጌታን ለመውለድ የወጣችበት፣
የእመቤታችን ጌታን የመውለዷ በዓል የሚከበርበት ማለት ነው)
ጳጉሜን ሰድስት ስትሆንስ ልደት ወደ28 የሚወርድ ከሆነ ግዝረትም ጥምቀትም የግንቦት
ልደታም እነዚህን የመሰሉ በዓላት ሁሉ ወደዋዜማቸው በወረዱ ነበር ስለዚህ ጾሙ 44 ነው
መጀመሪያው በኅዳር 15 መጨረሻው በታኅሣሥ 29 ነው 40 የነቢያት ሦስቱ የአብርሃም
ሦርያዊ፣ የአርድእተ ፊልጶስ አንዱ ጋድ ነው በማለት በጽሑፍ እንዲህ አስፍረውታል
መምህር አባ ዘገየ /ገብረ መድኅን/
ስለዚህ በ4ቱም ዘመን በ15 ተጀምሮ በ29 ቢፈሰክ ሁሉም የሚስማማበት የመጽሐፍ
ማስረጃ ያለው ነው ማለት ነው፡፡
3. በ14 ተጀምሮ በ28 የሚለው ሐሳብ የመጣው ጾሙን 44 ለመሙላት ነው ከ10ኛው
መቶ ክፍለ ዘመን ወዲህ አብዛኛው ሰው ልደትን ከአራት ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ዮሐንስ
በሃያ ስምንት መግደፍ ስለለመደ ያን ልማድ አባቶቻችን በአንድ ላይ ተገናኝተው
ባለመወሰናቸው ማስቀረት አልተቻለም
ስለዚህ ጉዳይ ውይይት ሲጀመር የብዙ ሊቃውንት አቋም በአሥራ አምስት ተጀምሮ በሃያ
ዘጠኝ ይፈጸማል የሚል ሲሆን ከላይ በጠቀስኩት በሃያ ስምንት ይፈጸማል በሚል ጣልቃ
ገብ ሐሳብ ጾሙን ማስፈጸም አልተቻለም እንዲህ በመሆኑ የጾሙ መጉደል የቆጫቸው
አባቶች በሃያ ስምንት የምንፈስክ ከሆነ ጾሙ ከሚሻር ቀኑ ቢቀየር ችግር አያመጣም፤
በአሥራ አራት እንጀምረው በማለት በአሥራ አራት እንዲጀመር ያደርጋሉ፡፡
እውነት ነው የቀኑ መቀየር ችግር አያመጣም ከዐቢይ ጾም ጀምሮ ጥንታቸውን ለቀው
በድሜጥሮስ ኢየአርግና ኢይወርድ በየዓመቱ የምንጾማቸው አጽዋማት አሉ ስለዚህ ችግር
እየሆነ ያለው የቀኑ መቀየር አይደለም የጾሙ መጉደል እንጅ ዓርብና ረቡዕም ልደትና
ጥምቀት ከዋለባቸው በዋዜማቸው ለውጥ ተደርጎላቸው እንጾማቸዋለን ረቡዕን ቀኑን
ቀይረን ማግሰኞ ዓርብን ሐሙስ በመጾማችን የቀኑ መቀየር ጾማቸውን አላስቀረባቸውም
ስለዚህ በ15 ጀምረን በ28 በመፈጸም ጾሙን ከምንሽረው በ14 ጀምረን በ28 ቢፈጸም
አንድ ስምምነት ላይ እስኪደረስ ድረስ ጾሙን ከማጉደል እንድናለን በ14ጀምረን በ28ም
ብንፈጽም፣ በ15 ጀምረን በ29 ብንፈጽምም ሁለቱም አንድ ናቸው ልዩነት የላቸውም
የሁለቱም ዓላማ ጾሙን ከ44 ላለማጉደል ነውና፡፡
የቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ
ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳለፈው ውሳኔ በ15 ተጀምሮ በ28 ይፈጸማል የሚል ነው የቅዱስ
ሲኖዶስን ውሳኔ ሁሉም ያከብራል ነገር ግን ይህ ውሳኔ ሁሉንም ያካተተ መሆን ነበረበት
የሚሉ ሰዎችም አሉ ምክንያቱም የልደት በዓል በድምቀት የሚከበርበት ላልይበላ ቤዛ ኵሉ
የሚባለው በ29 እንጅ በ28 አይደለም ሲኖዶሱ ከወሰነ በኋላም ከሲኖዶሱ አባላት
ውስጥም ሲየጠቁ በ15 እንደሚጀመርና በ29 እንደሚፈጸም የሚናገሩ ብፁዓን ሊቃነ
ጳጳሳት አሉ ከሊቃውንትም አብዛኛዎቹ የሚቀበሉት ይህንን ነው እነዚህ አባቶችም ጾሙን
የሚፈቱት በ15 ጀምረው በ29 ነው በዚህም ምክንያት አንደኛው ክፍል በ15 ተጀምሮ በ28
ይፈጸም ሲል 2ኛው ክፍል በ15 ተጀምሮ በ29 ይፈጸም ሲል 3ኛው ክፍል ጾሙን 44
ለማድረግ በ14 ተጀምሮ በ28 ይፈጸም ሲል በመካከል እየተጎዱ ያሉት ምእመናን ናቸውና
ቢታሰብበት ጥሩ ነው የሚመለከተውም አካል እነዚህ ልዩነቶች መኖራቸውን እያወቀ የኔን
ብቻ ተቀበሉ በማለት ወደመካፋፈል ከሚወስደን ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሊቃውንት አበው
ሰብስቦ አንድ መፍትሔ ቢሰጥ መልካም ነበር፡፡
4. ከ44ቱ አንዱ ገሀድ የሚጾመው ልደት ዓርብና ረቡዕ ሲውል ብቻ ነው የሚሉ ናቸው
ለነዚህም ፍትሐ ነገሥቱ አንቀጽ 15 ላይ እንዳይረሳ በየዓመቱ ይጾማል ብሎ መልስ
ሰጥቶበታል በሦስቱ ወንጌላውያን ዘመንም እየጾምነው ነው 28ኛው ቀን ጋድ ነውና፡፡
5. በአንዳንድ አካባቢዎች ልደትን በ28 ማክበር የኦርቶዶክስ ተዋሕዷዊነት፣ በ29 ማክበር
የጸጋና የቅባት መገለጫ