ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
#ኦ ምዕራግ እምድር አስከ ሰማይ
ከምድር አስከ ሰማይ የምትደርሽ መሰላል አንቺ ነሽ፡፡ በዚህች መሰላል የላዩ ወደ ታች የታቹ ወደ ላይ ይወጣባታል እመቤታችንም የቃል ርደት የስጋ እርገት ምክንያት ሆናለችና፡፡ #አንድም ጌታ አረገ መባሉ በእስዋ ስጋ ነውና፡፡ ቅዱሳን አረጉ መባላቸውም ዐእስዋ ነውና፡፡ #አንድም ድንግል ሆይ ምራገ ፀሎት አንቺ ነሽ፡፡
#ወብኪ ታሐደሰ ቀዳሜ ኵሉ ፍጥረት፡፡
ከፍጥረት ሀሉ አስቀድሞ የነበረው አዳም የታሰብሽ አንቺ ነሽ፡፡ አዳም ምክረ ከይሲ ሰምቶ አምላክነትን ሽቶ ህጉን ተላልፎ ዕፀ በለስን ቀጥፎ እምነቱን አጉድሎ ፈጣሪውን በድሎ ብልሔት እርጅና አግኝቶት ነበርና አዳም የታደሰብሽ አንቺ ነሽ፡፡ #አንድም ድንግል ሆይ ፬ ባሕርያት የታደሱብሽ አነንቺ ነሽ፡፡ በሐጥያት ምክንያት ባህርያችን አድፎ ነበርና፡፡ #አንድም ከፍጥረት ሁሉ ቀድሞ የነበረ ቀውስጦስ የተባለ መልዕክት የታደሰብሽ አንቺ ነሽ፡፡ ይህስ እንዴት ነው ቢሉ ሕፃነ ገምዲ በድለው መልዕክት ቅሰፉ ተብለው ታዘው ሄዱ ለቀውስጦስ መልከ መልካም ብላቴና ደረሰው መልኩን አይቶ ቢራራለት ይሄንንስ የፈጠረው ይግደለው ብሎ ራርቶ ትቶታል ሌሎች ቀስፈው ሲወጢ እሱም ወጣለው ሲል ረድዔት ተነስቶት ወደ ትች ወደ ታች አለው ዲያቆኑ በቀትር ለተልዕኮ  ወደ ቤቴልሔም ሲመጣ አየው ሰማንያዊ ወይስ ምድራዊ ነክ ብሎ ቢጠይቀው  በግብሬ ምድራዊ ሆንኩ እንጂ ሰማያዊ ነበርኩ አባ ሳሙዔልን ንገርልኝ ከእመቤተ ዘንድ ያመልክትልኝ፡፡ አባ ሳሙዔልም ማህበረ ካህናቱን ሰብስቦ  ስዕለ ማርያምን አውጥቶ 400 እግዚኦታ 41 ኪራላይሶ አድርሰው ሲፈፅሙ እመቤታችን በቀኝ እጅክ ቀኝ ክንፋን በግራ እጅክ ግራ ክንፋን ይዘክ ተንስ በስሙ እግዚነ እየሱስ ክርስቶስ ወበስለታ ወላዲቱ ድንግል በለክ አስነሳው አለችው፡፡ የተባለውን ፈፅሞ አስነስቶታል፡፡
 #አንቲ ወእቱ ተስፋሁ ለአዳም አመ ይሰደድ እምገነት
...........................ይቀጥላል
                 ምንጭ ውዳሴ ማርያም እና ቅዳሴ           ማርያም ትርጓሜ
#ኦ ማርያም በእንተዝ ናፈቅረኪ ወናዓብየኪ: ቃለ አክብሮ ቃለ አህስሮ ቃለ አራህርሆ ይሆናል: ቃል አክብሮ ድንግል ምልእተ ውዳሴ ብሎ የሚያመጣው ነው: ቃለ አራህርሆ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ቃለ አህስሮ ሃናንያ አብዳን ሰብአ ገላትያ ነው:: በእንተዝ ያለፈውን አጠፈ እንደገና ብሎ መጽሃፍ ያለፈውንም የሚመጣውንም ማጠፍ
ልማድ ነውና የሚመጣውን አጠፈ እመቤታችን ሆይ እናከብርሻለን እናገንሻለን::
#ሐተታ:- እኛ እሷን የምናከብራት የምናገናት ሆነን አይደለም ክብርሽን ገናንነትሽን እንናገራለን ሲል ነው::
እስመ ወልድኪ ለነ መብልዓ ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ ህይወት ዘበአማን:: እውነተኛውን ምግብ እውነተኛውን መጠጥ አስገኝተሽልናልና ስላስገኘሽልን::
#ሐተታ:- ዘበአማን አለ ከመስዋዕተ ኦሪት ሲለይ ያ ስጋዊ ይህ መንፈሳዊ ያ አፍአዊ ይህ ውሳጣዊ ያ ምድራዊ ይህ ሰማያዊ ነውና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ጥዋት በልቶ ለማታ ማታ በልቶ ለጠዋት ያሻል ይህ ግን በሚገባ ከተቀበሉት በሃጥያት ካላሳደፉት
ህማሙን ሞቱን ለማዘከር ነው እንጂአንድ ግዜ ከተቀበሉት በሌላ ግዜ አያሻምና:: አንድም የዚህ አለም ምግብ ሃሰር ይሆንል ይለወጥል በሱ ግን ይህ ሁሉ የለበትምና አንድም የዚህ አለም ምግብ ሞትን ያስከትላል ይህ ግን የዘላለም ህይወት ይሆናል አንድም ከማናዊት
እመቤታችን ስለተገኘ መብልአ ጽድቅ ዘበአማን ውስቴ ህይወት ዘበአማን አለ::
#ይካ ንፍቅ ጸሎተ ቡራኬ
#ይ ዲ ንፍቅ መሐረሙ እግዚኦ
#ይ ካ ለዑልኒ፡፡ ቄሱ ያነሳቸውን፡፡
ወለኲሎሙ፡፡ ያላነሳቸውን አንድም ከእሱ ጋር ያሉ ልእካኑ በቅድስት አሉትን አንድም በቅድስት ያሉትን በዝንቦ ያሉትን አንድም በቆመ ብእሲ ያሉትን በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን ያሉትን አንድም በዐጸደ ቤተ ክርስቲያን ያሉትን በብህንሳ ያሉትን፡፡ እንድም እጣን ያረገላቸውን መስዋእት
የተሰዋላቸውን፡፡ ወለኲሙ፡፡ ይህ ሁሉ ያልተደረገላቸውን፡፡ #ኦ መስተምህርት አስተምህሪ ኀበ ወልድኪ፡፡ ቸሪቱ አማላጅቱ ሆይ ከልጅሽ ዘንድ አማልን ይበል ከመ ያዕርፍ ነፍሰ ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳተ ዋዌ የቀረው ነው የጳጳሳት የሊቃነ ጳጳሳት የኤጲስ ቆጶሳትን ነፍስ ዕረፍተ ነፈሰን ሰጥቶ ያሳርፈ ዘንድ፡፡
#ቀሳውስት ወዲያቆናት፡፡
ዋዌ የቀረው ነው የቀሳውስትን የዲያቆናትን ነፍስ ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ ቀሳውስተ ወዲያቆናተ ይላል ቀሳውስት ዲያቆናተን ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡
#እለ ያረትዑ ፍኖተ ቃል ዘበአማትን፡፡
ዕውነተኛ ሕገ ወንጌልን የሚያስተምሩ አንድም ፍኖተ ግስ ነው የረትዑ ካልሁ ብሎ አንዲህ አለ እንጂ ወንጌልን የሚያስተም አንድም ፍኖተ ወንጌል፡፡ ቀቃል አካላዊ ቃል ነው፡፡ አካላዊ ቃል ያስተመረው ወንጌልን የሚያስተምሩ፡፡ ነገሥተ ነገሥታቱን፡፡ ወመኳንንት፡፡ ቀኛዝማች ግራዝማቹን፡፡ ወመሳፍንተ፡፡ ደጃዝማቹን፡፡
#ወእለ በሥልጣናት፡፡ ተወራጅ ነገሥታት፡፡ እንደ ሸዋ መርድ አዝማች እንደ ጎጃም ጣፌ ላምነት፡፡
አንድም ወመሳፍንተ፡፡ ተወራጅ ነገሥታት፡፡
ወእለ በሥልጣናት፡፡ ሥሉጣነ ነገር እንደ ጥቁር ከብቴ እንደ ቆብ አሰጥል ኃይሉ ያሉ ናቸው፡፡
ወራኩተ፡፡ ወራዙተን የነዚህ ተወራጅ ናቸው፡፡
#ወደናግለ፡፡ ደናግለ ሥጋ ደናግለ ነፍስን፡፡ ወመነኮሳተ፡፡ መነኮሳትን ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡
#ሐተታ፡፡ መነኮሳት ደናግልም ወራዙትም ካላቸው የገባሉ፡፡ በድንግልና የሚመነኩሱ አግብተውም ነረው ኋላ የሚመነኩሱ አሉና ባዕለ ወነዳየ፡፡ ባለጸጋውን ደኋውን፡፡ ዐቢየ ወንዑሰ፡፡ ታላቁን ታናሹን፡፡ ሐተታ፡፡ የማዕርግ የዕድሜ ነው፡፡ ዕቤተ፡፡
ጎመን ዘሪ ቤ ሠሪ ባል ልጅ የሌት ባለቴቲቱን፡፡ ወዕጓለ ማውታ፡፡ አባት እናት የሚቱበት ድኋውን፡፡ ግዩረ፡፡ ካጣዖት ፊልሶ የመጣውን፡፡ አንድም በድ መትቶበት አንበጣ በልቶበት የሰደውን አንድም የምግባር ቁርጭኝ፡፡
#ወምሰኪነ፡፡ የለት ራት የጣት ቀለበት የሌለውን ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡ አንድም የነዚህን ነፍስ ዕረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ፡፡
#ወኲሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን እለ አዕረፋ እማኅበረ ቤተ ክርስቲያን መቅድመ፡፡
ውሎ ውሎ ከቤት ኑሮ ኑሮ ከመሬት እንዲሉ ከክርስቲያን አንድነት አስቀድሞ የሚቱት የክርስቲያን ወገን የሚሆኑ እነዚህን፡፡ አንድም የእንዚህን ነፍስ እረፍተ ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ አማልጅን፡፡ አንድም ከክርስቲያን አንድነት ተለይትው የሞቱ የእነዚህ ነፍስ እረፍት ነፍስ ሰጥቶ ያሳርፍ ዘንድ ሀተታ፡- ፡፡ ወቅመ ዓለም ሰው እንደ መከር ነው፡፡ መከር እኩሉ ሲዘረዝር እኩሉ ይታጨዳል ሰው እኩሉ ሲወለድ እኩሉ ይሞታል እና፡፡
09 ወፈድፋደሰ በእንተ እለኖሙ ውስተ ዛንቲ መካን፡፡ ይልቁንም በብህንሳ ያረፉትን አስቀድመሽ፡፡ እንቲ ዘበእንቲ አሆሙ አስተበቁኢ ጽፋቀ፡፡
አብዝተሽ መላልሰሽ አማለጂ ወጽፋቅ በዋዔ ቤታ እንዲል ጽሁቀ ይላል ተግተሸ አማለጂን ከመ ያዕርፍ ነፍሶሙ ንሁየ፡፡ ነፍሳቸውን ፈጽሞ ያሳርፍ ዘንድ፡፡ አንድም በጎ እረፍትን ያሳርፍ ዘንድ ተደሞ ታህየ ምንዱባን አንዲል፡፡ #ሀተታ፡- አስቀድሞ ላለበት ሀገር መጸለይ ይገባል አስራት በኩራቱን ይቀበላልና፡፡ ህሱ ሰላማ ለእግዚአብሔር እግዚኦ ተሳሀል በይበይከ ላእለ ዛቲ ሀገረ አርመኒያ እንዳለ ጎርጎርዮስ፡፡ የእክንድሪያው ሊቀ ጳጳስ ለሀገሩ ሳይጸልይ ለሌላው እንዳይፀልይ፡፡
#በህበ ኩሉ ዘተሰምዬ መካነ ሰማእት መዋእያን፡፡ በብህንሳ ያሉትን ባማልድ በሌላው አገር ያሉትን ማማለድ እንደምን ይሆንልኛል ትዪኝ እንደሆነ አላውያን ነገስታት አላውያን መኳንንት፡፡ ፍትሰታት አኩያት አጣውእን ድል የነሱ የሰማእታት ስማቸው በተጸራበት ቤተ ክርስቲያንና በታነጸበት ታቦታቸው በተቀረበት ስእታለቸው በታለበት በዚህ ሁሉ፡፡ #ወመካነ ጻድቃን ብሩካን:: ይቀጥላል.......
እንኩዋን ለእመቤታችን
#ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል
በሰላም አደረሳችሁ
ቁጽረታ ( #ጽንሰታ ) ለማርያም
ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ
መድኃኒት_የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን
ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ
የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት
በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ
ናትና እንዲህ ይላሉ::
"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ
እማሕጸን ቅዱስ::"
" #ድንግል_ሆይ ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው:
የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ
ነው::" ( መጽሐፈ_ሰዓታት , ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)
ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ
የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል::
የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ከነገደ #ይሁዳ የሚወለድ #ቅዱስ_ኢያቄም የሚባል ደግ
ሰው ከነገደ #ሌዊ ( #አሮን ) የተወለደች #ሐና የምትባል ደግ
ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ
ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል
ይናቁ ነበር::
ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ
#እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና
ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ
አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት #የአብርሃምና_ሣራን
አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን
አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር
ሲጫወቱ የተመለከተች #ቅድስት_ሐና ፈጽማ አለቀሰች::
"እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ
የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ
ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::
ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ
ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን
2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- #ነጭ_ርግብ ሰማያትን
ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ
አየ::እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ
ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም
ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ
እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ
እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::
በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7)
#መልአከ_ብሥራት_ቅዱስ_ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ
እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ
የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው::
እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::
እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው
#እመ_ብርሃን ተጸነሰች::
" #ኦ_ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ
¤ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ
አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: ( #ቅዳሴ_ማርያም )
እንኳን ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ
መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
✤፨✤ አቡነ መብዓ ጽዮን
አቡነ መብዓ ጽዮን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል (ጥቅምት
27 ቀን) ጋር አብረው የሚታሰቡ ታላቅ የተጋድሎ አባት ናቸው፡፡ የጻድቁ አቡነ መብዓ ጽዮን
መታሰቢያቸው ከመድኃኔዓለም በዓል ጋር ስለሆነ በዚህ ጽሁፍ ሥር ታሪካቸውን ይዘን
ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ!
አቡነ መብዓ ጽዮን የተገኙት እግዚአብሔርን እያስደሰቱ ያለነቀፋ ከሚኖሩ ቅዱሳን ነው፡፡
በክህነታቱ፣ በየዋህነቱ ከሰዎች የተስማማው አባታቸው ሀብተጽዮን፣ በደግነቷና በቸርነቷ
የምትታወቀው እናታቸው ጽዮንትኩና በሕግ በንፅህና በጋብቻ ተወስነው ሲኖሩ የተባረከ ልጅ
ይሰጣቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይለምኑ ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ክርስቶስም
መብዓ ጽዮን የተባለ ደግ ልጅ ሰጣቸው፡፡
መብዓ ጽዮን ከልጅነቱ ጀምሮ ማስተዋል እና የእግዚአብሔር ፍቅር ያደረበት ሰው እንደነበር
ገድሉ ይናገራል፡፡ ይኸውም በአንዲት ቀን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብሎ
ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ይሄድ የነበረ ሰው እግሩን እንቅፋት ተመቶ ደሙ ከመሬት ሲፈስስ
በአየ ጊዜ እውቀት በልጅነቱ የሞላ መብዓ ጽዮን የደማው ጣቱ እስኪደርቅ ድረስ ጠባው፡፡
በመሬት የፈሰሰ ደሙን ከአፈሩ ጋር በላ፡፡ ይህ ሥራው ከልጅነቱ የመስቀሉ ፍቅር በልቡ
የቸነከረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
#ያገባ ሰው ሚስቱን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል፡፡ ያላገባ ግን እግዚአብሔርን ደስ
የሚያሰኘውን ሥራ ያስባል$ የሚለው የመጽሀፍ ቃል ያፀናው ወጣቱ መብዓ ጽዮን
ከቤተሰቡ የመጣለትን የጋብቻ ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ ኃጢአትን ከመጨመር ውጭ ምን
እጠቀማለሁ እያለ የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቃት፡፡ በዚህም ቤተሰቦቹ ተውት፣ እርሱም
ራሱን ይበልጥ ለእግዚአብሔር አስገዛ፡፡
የምንኩስና እና ተጋድሎ ሕይወቱ
የምንኩስ እና የተጋድሎ ሕይወት የጣመ የላመ የሌለበት ፍፁም ራስን ለእግዚአብሔር
ማሳለፍ ነው፡፡ ይህንን የማይወድ ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ፍፁም ፈተናን ያበዛል፡፡
ቅድሳንም በረድኤተ እግዚአብሔር እና በተጋድሏቸው ያልፉታል፡፡ ሠይጣንን ድል
ይነሡታል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮንም የምንኩስና ቀንበር ከተሸከመ ጊዜ ጀምሮ ከፈረስ፣
ከበቅሎ፣ ከአልጋ፣ ከምንጣፍ ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ መኖሩን ገድሉ ይነግረናል፡፡
ለዚህም ተጋድሎ ሕይወቱ ያግዘው እና ይረዳው ዘንድ ክህነትን አባ ገብርኤል ከተባለ ጳጳስ
ተቀብሏል፡፡ ቄስም ሆኖ የመድኃኔዓለምን ሥጋው እና ደሙን እያቀበለ ብዙ ዘመን ኖሯል፡፡
የምንኩስና ሕይወቱና ትጋቱም ታላቅ አባት እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ትልቅ ድንጋይ በደረቱ ተሸክሞ ከምድር ከአመድ በተቀመጠም ጊዜ በራሱ ተሸክሞ፣
በሚሰግድም ጊዜ በጀርባው አዝሎ ስለ ክርስቶስ መከራ ያስባል፡፡ ራሱን ይበድላል፣
ስጋውን ያደክማል፡፡ ይኸውም ያለሰንበት እና ያለበዓላት በቀር በዚህ ተጋድሎ የምንኩስና
ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከዛም ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ከአቡነ ተክለሃይማኖት መቃብር
በረከትን እንደተቀበለ ገድለ መብዓ ጽዮን ይነግረናል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን ራሱን
ለእግዚአብሔር በሰጠ ቁጥር መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋወደሙ እየተገለፀ፤
እመቤታችንም እየታየች ትመክረው ታስተምረው ነበር፡፡
ቅዱሳንን ማክበር በዓላቸውን መዘከር እንዲገባ ከምንማርባቸው ታሪኮች አንድ የአቡነ
መብዓ ጽዮን ታሪክ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን እና የእናቱን የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል
አብዝቶ ያከብር ነበር፡፡ በዚህም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከቅድሳን ጋር
መጥቶ ባርኮታል፡፡ የመለኮት ምሥጢርም ሥርዓትም በአካባቢው ላሉ ሠዎችም
ተሠጥቷቸዋል፡፡ መናፍቃን በዓል ማክበር አይገባም ቢሉ የበዓል ማክበር ውጤቱ እዚህ
ድረስ መሆኑን እናያለን፡፡
በፀሎቱም #ኦ እግዚኦ አንተ ትብለኒ ሰአል ኩሎ ዘፈቀድከ ወአነ እሁበከ፣ ጌታ ሆይ አንተ
የወደድከውን ሁሉ ለምን እኔ እሠጥሃለሁ አልከኝ፡፡ አሁንም የለመንኩን ግለጽልኝ$ በማለት
የቀራንዮን መስቀል መከራውን ያሳየው ዘንድ ሁልጊዜ ይለምን ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ
መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን የሆኑ እጆቹን በመስቀሉ እንዲዘረጋ፣ እግሮቹም
እንዲቸነከሩ፣ የሾህ አክሊልም በራሱ ተሸክሞ የጥቅምት 27 ቀን ታየው፡፡ ለሙሴ
ሊታያቸው እንዳልቻለ አባ መብዓ ጽዮን ከመሬት ወደቀ፡፡ እንደ ሞተም ሆነ፡፡ ማንም
የመስቀሉን መከራ ሕማሙን ማየት እንደማይችል ነገረው፣ በቸርነቱም አነሳው፡፡ የሞቱ
ገናንነት የሚያስፈራ እና የሚያስደነግጥ መሆኑን አሳውቀው፡፡ መከራው ታላቅ በሰው
አእምሮ አይታሰብምና ነው፡፡
ኃጢአትን ያልሠራ ሐሰትም በአፉ ያልተገኘበት ስለሠው ኃጢአት ስለሞተው
ስለመድኃኔዓለም ክርስቶስ የሞቱ መታሰቢያ በምትሆን በዕለተዓርብ ታላቅ ተጋድሎን
በማድረጉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለት በዓል በሚታሰብበት
በ27 በመድኃኔዓለም ዕለት የአቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያ ተደረገ፡፡ ይኸውም ጥቅምት
27 ነው፡፡