ስንክሳር
7.32K subscribers
825 photos
4 videos
37 files
237 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ተደርጎ ስለሚወሰድ ልደት በ29 መከበሩን የሚቃወሙ አሉ ከላይ
እንደተገለጸውም በ29 ይገደፍ የሚሉትንም ጸጋና ቅባት ይሏቸው እንደነበረ፣ ነገር ግን
ከቅባትና ከጸጋ ጋር የሚያይዘው እንደሌለ መምህር አባ ምሕረቱ ገልጸዋል፡፡
ስናጠቃልለው ሁሉም የኔ ሐሳብ ብቻ ይደመጥ ከማለት ርቆ ምእመኑም ይህ ግልጽ የሆነ
ጉዳይ ስለሆነ ወደአንድነት እስኪመጣ ድረስ ጾሙ ከ44 መጉደል የለበትም ቅዱስ ሲኖዶሱ
ከሊቃውንት ጋር ሁኖ አንድ እልባት እስኪሰጠው ድረስ ጾሙ ከ44 ሊጎድል አይገባውም
በ15 ጀምረን በ29 ብንገድፍ ሁላችንም ደስ ይለን ነበር ነገር ግን የልደት በዓል
በአብዛኛው የኢትዮጵያ ክፍል በ4 ዓመት አንድ ጊዜ በዘመነ ዮሐንስ በ28 ስለሚከበር ያን
ጊዜም በዓል እያከበርን ጾም ስለሌለ መፈሰካችንም ስለማይቀር አባቶቻችን ወደአንድ
ሐሳብ መጥተው ውሳኔያቸውን እስክናውቅ ድረስ በ14 ብንጀምረው ጾሙ ይሞላልናል
የሚል እምነት አለኝ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ።
ንጉሥ ቴዎድሮስ ማን ነው?
መነሻው ከየት ነው?
ከቴዎድሮስ ዘመን የሚደርሱት ደጉን ዘመን የሚያዩት ሦስቱ ናቸው እነሱ እነማን ናቸው?
ቴዎድሮስ ከመምጣቱ በፊት አሕዛብ ከጸለይን ለሦስት ወር ይገዙናል ካልጸለይን ለሦስት
ዓመት ይገዙናል ይህ እንዴት ይሆናል?
በመከራው ዘመን የመከራው ትንቢት መፈጸምያ የመከራው ማብረጃ እነማን ናቸው?
ንጉሥ ቴዎድሮስ ከመምጣቱ በፊት አራቱ ታላላቅ መከራዎች ይመጣሉ እነሱ ምንድን
ናቸው?
ይህ ሁሉ ትንቢት ይፈጸማል ወይስ ያልፋል?
ንጉሥ ቴዎድሮስ መቼ ነው የሚመጣው?
በኢትዮጲያ አይደለም ጠማማ ትውልድ ጠማማ እንጨት አይኖርም
/ይህ ትንቢት የሚፈጸመው በዘመነ ቴዎድሮስ ነው/
በቀሲስ መምህር ሄኖክ ወልደ-ማርያም
ማሳሰቢያ ፦ ጽሑፉ ረጅም ቢሆንም የሀገራችን እና የቅድስት ቤተ ክርስትያናችን ብሎም
የእኛም መጻኢ ዕድል ነውና ታግሳችሁ አንብቡት፡፡
ሼር በማድረግ ስለ መከራው፣ስለ ትንሣኤው እና ስለ ታላቁ ስለ ንጉሥ ቴዎድሮስ ለወዳጆን
ያሰውቁ!
ተወዳጆች ሆይ ስለ ኢትዮጲያ ከጥንት ጀምሮ ከጅማሬዋ እስከ ፍጻሜዋ ትንቢት ተነግሯል፡፡
ከትንቢቶቹም የተፈጸሙና ያልተፈጸሙ ወደ ፊት የሚፈጸሙ አሉ፡፡ ግን አሁን ወደ ትንቢቱ
ፍጻሜ እየደረስን ስለሆነ ሊመጣ ስላለው እና እየመጣ ስላለው የቤተ ክርስትያናችን
መጻሕፍት እና አባቶች ምን ይላሉ የሚለውን እናያለን፡፡
አሁን ባለንበት ሁኔታ ሀገራችን ኢትዮጲያ መንታ መንገድ ላይ መሄድ አቅቷት ቆማለች፡፡
የሀገራችን የኢትዮጲያ የወደፊት መጻኢ እድልና ሕልውና የተንጠለጠለው በቅድስት ቤተ
ክርስያናችን ላይ ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ወደፊቱ የሀገራችን ሁናቴና ተስፋ ለማወቅ የግድ
በቅድስት ቤተ ክርስትያናች ውስጥ ያሉትን መጻሕፍትን ማወቅ እና መመርመር ብሎም
ማየት ያስፈልጋል፡፡
ወዳጆቼ እንደ ምታውቁት ‹‹ንጉሥ ቴዎድሮስ›› ስለሚባለው ደግ እና ጸሎተኛ ባሕታዊ
የወደፊት በኢትዮጲያ ትንሳኤ ውስጥ የተቀባ እና የኢትዮጲያ ትንሳኤ መሪ እና አብሳሪ
እንደሆነ ይታመናል፡፡ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሾጥ የሚያደርጋቸው እንደ ማበድ ያሉ ሰዎች
እየተነሱ ‹‹ቴዎድሮስ እኔ ነኝ›› እያሉ ሲወሸክቱ ሰምተናል አይተናል፡፡ እነዛ ሰዎች እንኳን
ታላቁን ንጉሥ ቴዎድሮስን ቀርቶ እራሳቸውንም በአግባቡ መሆነ ያቃታቸው ሰዎች ናቸው፡፡
ንጉሥ ቴዎድሮስ ማንነው?
ተወዳጆች ሆይ ስለ ታላቁ የወደፊት የሀገራችን ንጉሥ ‹ቴዎድሮስ› ማንነት በትንቢት
የምናገኘው በፍካሬ ኢየሱስ፣በድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል፣በገድለ ፊቅጦር ላይ ነው፡፡ በጀምስ
ብሩስ ተሰርቆ በብሪትሽ ሙዝየው ውስጥ የሚገኘው ታላቁ የትንቢት መጽሐፍ የሆነው
በፍካሬ ኢየሱስ ላይ ንጉስ ቴዎድሮስን ‹ቴ› በማለት የስሙን የመጀመርያ ፊደል በመጥቀስ
ስለ ቴዎድሮስ ይናገራል፡፡ ይህ ብቻ አይደለም ቴዎድሮስ የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ኃይልን
ተላብሶ ከመምጣቱ በፊት ስለሚፈጠሩት አስቸጋሪ ክስተቶች እና ምጦች ይተነብያል፡፡ ይህ
ታላቅ ንጉሥ ቴዎድሮስ ንግሥናው ከሀገራችን ከኢትዮጲያ ትንሣኤ ጋር የተያያዘ ነው፡፡
አባቶቻችንን የዚህን ንጉሥ መምጣትና የሀገራችንን የማይቀረውን የወደፊት ትንሣኤ ቅዱስ
የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በገለጠላቸው መጠን ለኛ ከትበውልናል፡፡ ለምሳሌ ስለ
ኢትዮጲያ ትንሣኤ ብቻ በፍካሬ ኢየሱስ፣በድርሳነ ዑራኤል፣በገድለ ፊቅጦር፣በገድለ አቡነ
ሲኖዳ፣በራዕየ ሳቤላ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በጻፉት በመጽሐፈ ምስጢር እና በትርጓሜ
ወንጌል ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ሁሉ የወደፊት የኢትዮጲያ የማይቀረው ትንሣኤ ከቴዎድሮስ ጋር
የተያያዘ ነው፡፡
በድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ላይ ስለ ቴዎድሮስ ከመላኩ ከቅዱስ ዑራኤል አፍ የሰማው ዲያቆኑ
ባሮክ ነው፡፡ ይህ ባሮክ የተባለ የተባረከ ዲያቆን በኢየሩሳሌም የጌታን መቃብር በመጠበቅ
የሚኖር ነበር፡፡ ባሮክ እንደ ነብዩ ኤርሚያስ ደቀ መዝሙር እንደ አቤሜሌክ የኢየሩሳሌምን
ጥፋት አታሳየኝ እያለ የሚጸልይ ደግ ሰው ነበር፡፡ እግዚአብሔርም የባሮክን ጸሎት ሰምቶ
የኢየሩሳሌምን ጥፋት እንዳያይ ለሰባ ዓመት እንቅልፍ ጣለበት፡፡ በዚህም ባሮክ ሥጋው
ሳይፈርስ ሳይበሰብስ በእግዚአብሔር መለኮታዊ ጥበብ ለሰባ ዘመን ተኝቶ ኖረ፡፡
ባሮክ ከእግዚአብሔር የተሰጠው ሰባ የእንቅልፍ ዘመን ካለፈ በኃላ በጎልጎታ ባለች
በጌታችን ስም በተሠራች ቤተ ክርስትያን ገብቶ እህል ሳይቀምስ ውኃ ሳይጠጣ ለአርባ
መዓልት እና ሌሊት ሱባኤ ገባ፡፡ ወዳጆቼ ከዚህ በኃላ ነው የቴዎድሮስ ነገር እና ምስጢር
የሚጀምረው፡፡ ነገረ ቴዎድሮስ በትንግርት ሳይሆን በሱባኤ በሆነ ጸሎት የመጣ መሆኑን ልብ
በሉ፡፡
ባሮክ ሰባ ዘመን ተኝቶ የመከራውን ዘመን ስላሳለፈ ነው እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም እስከ
ሀገራችን ኢትዮጲያ ያለው የወደፊት የመከራ እና የትንሣኤ ዘመን ትንቢት የነገረው፡፡ ቅዱስ
ዑራኤል ለባሮክ ስለ ወደፊቱ ሲነግረው ግድ ይፈጸም ስለነበር ‹‹የምነግርህን ልብ አድርገህ
ስማ›› እያለው የሚነሱትን ነገሥታት የስማቸውን የመጀመርያ ፊደል ለምልክት እየነገረው
ዘርዝሮ ገልጾለታል፡፡
ቅዱስ ዑራኤል ለዲያቆን ባሮክ ‹‹በመጨረሻውም የአረማውያን ዘመን በመሆኑ ፍቅር
በየጊዜው እየጎደለ ይመጣል፡፡ በዚያን ዘመን ስለ እግዚአብሔር ብሎ ሃይማኖትን
ማጠንከርና ደጋግ ሰዎች መውደድ እውነትና መልካም ሥራ መሥራት ፈጽሞ የለም፡፡
ከመነኮሳት ማህበር ሆነ ከካህናት ወገን ሁሉ ወንዶችም ሴቶችም በመልካም ሥራ
አይሄዱም፡፡ ጻድቃን ይመስላሉ በውስጣቸው ግን ተንኮለኞችና ሐሰተኞች ሴሰኞች
ናቸው››/ይህ ትንቢት በዘመናችን መፈጸሙን ልብ ይሏል?/ በማለት የጊዜውን ሁኔታ
ካስረዳው በኃላ ስለ መጪው ንጉሥ ቴዎድሮስ ‹‹አመድ ከዘነመ ከአራት ዓመት በኃላ
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት የሆነ በፊቅጦር በገድሉ መጽሐፍ እንደተነገረው
የስሙ ምልክት ‹ቴ› ተብሎ የተመለከተው ይነግሳል ብሎ አስረድቶታል፡፡ ግን በዘመኑ
የግብጻውያን ጳጳሳት እና የኢትዮጲያውያን ጳጳሳት በአባ ሲኖዳ ገዳም ስለ ሃይማኖት ታላቅ
ጉባኤ ያደርጋል፡፡ ይህም የሚሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢረ ሥጋዌ ላይ
ነው፡፡ በጉባኤውም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አካላዊ ቃል ከሥጋ ጋር አንድ ባሕርይ መሆኑን
በማስረዳት ይፈጽማሉ፡፡ ቅዱስ ዑራኤልም በዚህ አላበቃም ስለ ደጉ ዘመን በኢትዮጲያ
ውስጥ እና በዓለም ላይ ሁሉ ሰላም ደስታ ጥጋብና ፍጹም ተድላ እንደሚሆን ነግሮታል፡፡
ተወዳጆች ሆይ የጥቅምት ድረሳነ ዑራኤል ላይ ስላለው የኢትዮጲያ መጻኢ መከራ እና
ትንሳኤ በአጭሩ በዚህ መልኩ ካየን ዘንዳ ወደ ገድለ ቅዱስ ፊቅጦር ደግሞ ጉራ እንበል፡፡
ቅዱስ ፊቅጦር የአንጾኪያው መስፍን ርህራሄ የሌለው የህርማኖስ ልጅ ነው፡፡ እናቱም
ማርታ ትባላለች፡፡ ቅዱስ ፊቅጦር ገና በሕፃንነቱ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ የወርቅ
ልብስ አውርዶለት የለበሰ ወጣት ሰማዕት ነው፡፡ ቅዱስ ፊቅጦር እጅግ ብዙ መከራና ስቃይ
ተቀብሎ በጣኦት አምላኪው በአርያኖስ እጅ ሚያዝያ 27 ቀን ሰማዕት የሆነ ነው፡፡
ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕትነት ተቀብሎ ካረፈ በኃላ የከበረውን ሥጋውን እናቱ ማርታ ሃይማኖቱ
በጸና እና ቤተ ጣኦትን አጥፍቶ አብያተ ክርስትያንን ባነጸው፣አምልኮተ ጣኦትን አጥፍቶ
አምልኮተ እግዚአብሔርን ባስፋፋው ደጉ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነገሠበት ዘመን በልጇ
ስም በወርቅና በብር አስጊጣ በእስክንድርያ ቤተ ክርስትያን አሳነጸች፡፡ ከዚህ በኃላ ማርታ
ሌሊት ተኝታ ሳለች ሰማዕቱ ቅዱስ ፊቅጦር በራዕይ ተገልጾላት በግብጽ ላይ አሕዛብ
እንደሚነግሱባት እና እሷ በወርቅ እና በብር አስጊጣ ያሠራችው ቤተ ክርስትያን ለወርቁና
ለብሩ ብለው አሕዛብ እንደሚፈርሱት ነገራት፡፡ ማርታም በግብጽ ሀገ
ር አሕዛብ
እንደሚነግሡ ከልጅዋ ከቅዱስ ፊቅጦር በሰማች ጊዜ እጅጉን አዝና ‹‹እንደዚህ ከሆነማ
ቤተ ክርስትያን በመሥራት ለምን እደክማለሁ›› አለች የዚህን ጊዜ ነው ቅዱስ ፊቅጦር
እግዚአብሔር የገለጸለትን ስለ ኢትዮጲያዊው ደግ ንጉሥ ቴዎድሮስ ቅድስናውን ገልጾ
ስሙን ሸፈን አድርጎ የነገራት፡፡
ወዳጆቼ ቅዱስ ዑራኤል ለዲያቆኑ ለባሮክ እግዚአብሔር የገለጠለትን ሲነግረው የቅዱስ
ፊቅጦር ገድል ላይ ያለውንም ትንቢት አጣምሮ ነው የነገረው፡፡ ይህም የሆነው ባሮክ
ከመላኩ ከቅዱስ ዑራኤል አንደበት የሰማውን በገድለ ቅዱስ ፊቅጦር እንዲያመሳክረው
ነው፡፡ ለዚህም ነው መልአኩ ‹‹የኢየሱስ ክርስቶስ ሰማዕት የሆነ በፊቅጦር በገድሉ
መጽሐፍ እንደተነገረው የስሙ ምልክት ‹ቴ› ተብሎ የተመለከተው ይነግሳል›› ያለው፡፡
እዚህ ላይ ቅዱስ ዑራኤል የደጉን ንጉሥ ስም ‹ቴ› ብሎ ተናግሯል፡፡ ገድለ ፊቅጦር ግን
‹‹በኢትዮጲያ ሀገር ክርስቶስን የሚወድ ቅዱስ ሰው ይነግሣል›› አለ፡፡ ቅዱስ ዑራኤል
የንጉሡ የቴዎድሮስን የስሙን የመጀመርያ ፊደል ጠቆም አድርጎ ሲናገር ቅዱስ ፊቅጦር
ደግሞ የንጉሥን ቅድስና ገልጾ ‹‹ቅዱስ ሰው›› አለው፡፡
ይህንንም ቅዱስ ፊቅጦር ‹‹አሕዛብ መንግሥት ጥቂት ዘመናት ናቸው፡፡/ይህቺ ጥቂት
ዘመናት ትያዝልኝ ልብ ትባልልኝ/ ከጥቂት ዘመናት በኃላ እግዚአብሔር በኢትዮጲያ ሀገር
ክርስቶስን የሚወድ ቅዱስ ሰው ያነግሳል፡፡ አረማውያንም በእርሱ እጅ ይደመሰሳሉ፡፡ ከዚህ
በኃላ ወደ ግብጽ ሄዶ አሕዛቦችንና መንግሥታቸውን ሁሉ ያጠፋል›› ይላል፡፡ ከዚህ ሁለት
ነገር መረዳት እንችላለን፡፡ አንደኛው ‹‹የአሕዛብ ጥቂት ዘመን›› የተባለው ነው፡፡ ይህም
አሁን ያሉት እነ እከሌ የማንላቸው ግን በሂደት ላይ ያሉት የአሕዛብን መንግስት በሀገራችን
ላይ ለመመስረት መንገድ ላይ ናቸው፡፡ አንዱ ትንቢት ይህ ነው፡፡ ሁለተኛው ንጉሥ
ቴዎድሮስ ትንቢት ከኢትዮጲያ እስከ ግብጽ ነው፡፡ እኛንም ግብጾችንም ከአሕዛብ ቀንበር
በእግዚአብሔር ኃይል ነጻ ያወጣናል፡፡
ወዳጆቼ በደጉ ንጉሥ ዘመን የቁስጥንጥንያው ጳጳስና የእስክንድርያው ጳጳስ የእኔ ሃይማኖት
ይበልጣል ብለው በአባ ሲኖዳ ቤተ ክርስትያን ገብተው ሁለቱም በአንድ ታቦታ ላይ ቀድሰው
መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል በገሃድ ወርዶ የእስክንድርያው ጳጳስ በሰዋው ቅዱስ
ቁርባን ላይ መውረዱንና በዚህም የሮሙ ጳጳስ ሊዎንን ረግሞት የኑፋቄ እንክርዳድ
የተዘራበትንና የበቀለበትን መጽሐፎቻቸውን ጥለው የእኛንና የእስክንድርያን ሃይማኖት
ስለመምሰላቸው በሰፊው በገድለ ፊቅጦር፣በአቡነ ሲኖዳ ገድል ላይ ስለተጻፈ እሱን
አንብቡት፡፡
መነሻው ከየት ነው?
ተወዳጆች ሆይ ከላይ እንዳየነው የጥንቱ ፍካሬ ኢየሱስ ስለ መጪው ንጉሥ ቴዎድሮስ
አመጣጥ እና ቤተሰብ ይናገራል፡፡ ይህንን ለጊዘው እንለፈውና አሁን ባለበት ሁኔታ ንጉሥ
ቴዎድሮስ መነሻው በቅርባችን ባለው ኤረር በዓታ እንደሆነ አባቶቻችን ይናገራሉ፡፡
የሚመጣውም አዛውንት ሆኖ ነው፡፡ ሥጋው በጾም በጸሎት በገድል የደከመ መንፈሱ ግን
በእግዚአብሔር ጸጋ የበረታ ሆኖ ነው፡፡ የሚመራን በእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ እና ጸጋ
ነው፡፡ የሚገዛንም በእግዚአብሔር ሰማያዊ ሕግ ነው፡፡ ኢትዮጲያንም ለአርባ ዓመታት
ይመራታል፡፡ ጊዜው ደርሶ፣የደፈረው ጠርቶ እስኪመጣ በዚሁ በኤረር በዓታ በጾም፣በጸሎት
ተወስኖ እንዳለ ነው አባቶቻችን የሚያስረዱን፡፡
ከቴዎድሮስ ዘመን የሚደርሱት ደጉን ዘመን የሚያዩት ሦስቱ ናቸው እነሱ እነማን ናቸው?
ስለ ቴዎድሮስ የተጻፉት መጻሕፍትና አባቶቻችን እንደሚሉት ከደጉ ዘመን ከንጉሥ ቴዎድሮስ
የሚደርሱት ሦስት ናቸው፡፡ አንደኛው በዓለም ሆነው ቢያንስ በቀን አንዴና ሁለቴ ስመ
እግዚአብሔርን የሚጠሩና የሚጸልዩ ናቸው፡፡ እነዚህም በንስሐ ተወስነው የበረቱትም
በቅዱስ ቁርባን ታትመው ከሆነ ከደጉ ዘመን ይደርሳሉ ደጉንም ንጉሥ ያያሉ፡፡ ሁለተኛው
በደዌ፣በአጋንንት እና በተለያየ ነገር ተይዘው ዘመናቸውን በመከራ በገዳማት በአድራት
የሚገፉ ናቸው፡፡ ሦስተኛ እውነተኛ የእግዚአብሔር ፍቅር አገብሯቸው ቃለ እግዚአብሔርን
ለመማር የሚንከራተቱ ተማሪዎች ናቸው ይላሉ፡፡
ቴዎድሮስ ከመምጣቱ በፊት አሕዛብ ከጸለይን ለሦስት ወር ይገዙናል ካልጸለይን ለሦስት
ዓመት ይገዙናል ይህ እንዴት ይሆናል?
ተወዳጆች ሆይ ከላይ እንዳየነው በገድለ ቅዱስ ፊቅጦር ላይ ‹‹የአሕዛብ ጥቂት ዘመን››
ያለው ነው፡፡ ይህም የሚሆነው አሁን ባለው የፖለቲካ ምህዳር እንደ ግብጽ የሃይማኖት
ፓርቲን በማቋቋም ስም ነው አሕዛብ ወደ መንበሩ የሚመጡት፡፡ የፖለቲካ ፓርቲን
በሃይማኖት ከባ በመሸፈን በመምጣት ወንበሩ ላይ በመውጣት ሊገዙን ብሎም
ሊያስጨንቁን ይችላሉ፡፡ እንዲሁም አሕዛብ ሰው ወደ መሪነቱ በመምጣት በመሪነት ስምና
ሽፋን የአሕዛብን ሃይማኖት በማስፋፋት ይገዙናል፡፡ ግን ይህ ከበረታን በጸሎት የሚያልፍ
ነው፡፡ በርትተን ካልጸለይን ግን የትንቢቱ ሰለባ በመሆን ወደ እግዚአብሔር አልጮህ ብለን
ወደ አሕዛብ እንጮኻለን፡፡
አገዛዛቸውም እንደ ሴት ልጅ ምጥ ነው፡፡ የሴት ልጅ ምጥ እሷም ባልዋም ቤተሰቦችዋም
ከአሁን አሁን ወለደች ወይስ ሞተች ብለው እንደሚጨነቁ ሁሉ እነሱ ወደ መንበሩ ከመጡ
የሃይማኖት እና የአምልኮት ነጻነት በማጣት ከዛሬ ነገ ፈጁን ገደሉን በማለት በስጋት
ስለምንኖር ነው ጭንቀታችን መከራችን በሴት ልጅ ምጥ የተመሰለው፡፡ ትንቢቱም
‹‹የኢትዮጲያ ሕዝብ ከጸለየ የመከራውን ዘመን ሦስት ወር አደርግለታለሁ ካልጸለየ ግን
ሦስት ዓመት ይሆናል›› የሚል ነው፡፡ ስለዚህ ትንቢት ስለ ተነገረለት የአሕዛብ መንግስት
እና አገዛዝ እድሜውን ማሳጠርም ማስረዘምም ብሎም ማሳለፍ የምንችለው እኛው ነን፡፡
በመከራው ዘመን የመከራው ትንቢት መፈጸምያ የመከራው ማብረጃ እነማን ናቸው?
ወዳጆቼ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደሚነግረን በሁለቱ የመከራ ዘመናት የመከራው እሳት
ያቃጠላቸው መከራው ይመጣል እየተባለ እየተነገራቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው በኃጢአት
በመርከስ የኖሩት ናቸው፡፡ ለዚህም እንደ ምሳሌ ብናይ በኖኀ ዘመን ለንስሐ የተሰጣቸውን
አድሜ እና እድል ሳይጠቀሙት የቀሩት ከወጣት እስከ አዛውንት ያሉት በሙሉ በጥፋታቸው
የጥፋት ውኃ አንፍሮ ገሏቸዋል፡፡ እነሱ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር አልመለስም በማለታቸው
የእነሱ ዕዳ ለሕፃናትም ተርፎ እነሱም አልቀዋል፡፡ እንዲሁም በሎጥ ዘመንም ዘማውያን
ግብረ ሰዶማውያን በእሳት ተቃጥለው አልቀዋል፡፡ ይህ የሚያሳየን ኃጢአት ሠርቶ ኃጢአቱን
ትቶ በንስሐ ሳይዘጋጅ የሚኖር የመከራው ማብረጃ እና የትንቢቱ ሰለባ ይሆናል፡፡
በተለይ ወጣቱ ከቤቱ እንደ ወጣ መቅረቱ አይቀርም ይላሉ፡፡ እራሳቸውን በንስሐ
ያላዘጋጁ፣ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት ያልተወዳጁ የመከራው ማዕበል ያሰጥማቸዋል፡፡
በዝሙት የሚደሰቱ በአጠቃላይ በኃጢአት ፈጣሪን የሚያሳዝኑ የሚነደው እሳት ይበላቸዋል
ከደጉ ዘመንም ሳይደርሱ ሞት ይቀድማቸዋል፡፡ ወዳጆቼ ጊዜው ደርሶ ሞት ቀድሞን በሥጋ
ከደጉ ዘመን ሳንደረስ፣በነፍስ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ መንግስት ሳንወርስ እንዳንቀር
ንስሐ እንግባ ወደ ፈጣሪም እንመለስ፡፡
ንጉሥ ቴዎድሮስ ከመምጣቱ በፊት አራቱ ታላላቅ መከራዎች ይመጣሉ እነሱ ምንድን
ናቸው?
ቴዎድሮስ ከመምጣቱ በፊት ሊመጣ ያለው ግድ የሆነው መከራ አሉ፡፡ እነሱም
ሞት፣ረሃብ፣በሽታ፣ጦርነት ናቸው፡፡
ሞት ፦ ሞት የተባለው በተለይ የወጣቶች ሞት ይበዛል፡፡ ደማቸውም በከንቱ ይፈሳል፡፡
ከሞት እና በግፍ ከሚፈው የወጣቶች ደም የተነሳ አስከሬን እስኪረገጥ ደም እንቦጭ
እስኪል ነው፡፡ ንስሐ ያልገቡት በጸሎት ወደ ፈጣሪ ያልተመለሱት ለ
ሞት ሲሳይ ይሆናሉ፡፡
ቀባሪው ግራ ይጋባል ማንን ቀብሬ ማንን ልተው ይላል፡፡ አንዱ የአንዱን ለቅሶ አይደርስም
የሚያላቅሰውም አያገኝም፡፡ ለቀስተኛውም ለቅሶ ማዳረስ ያቅተዋል፡፡
ረሃብ ፦ በድርሳነ ዑራኤል ላይ ‹‹አመድ ከሰማይ ይዘንባል›› የተባለው ከሰማይ የተዘዘ ክፉ
ረሃብ እና መከራ ናቸው፡፡ ረሃቡ በሀገራችን ታሪክ ታይቶ እና ተሰምቶ የማይታወቅ ነው፡፡
እስራኤላውያን በረሃም ዘመናቸው የአህያ ጭንቅላት ገዝተው በልው ነበር፡፡ እግዚአብሔር
ሲቆጣ የናቅኸውን በጭራሽ ያላሰብከውናን ልታስበው የማትችለውን ለረሃብህ
ሊያደርግብህ ይችላል፡፡ እኛም እስራኤል ዘነፍስ ነንና ካልጸለይን እየነሱን የጥንት ጽዋ
መጠጣታችን አይቀርም፡፡
አንዳንድ ሞኞች ረሃቡ ክፉ ነውና የማይነቅዝ እህል ገዝታችሁ አስቀምጡ ለረሃቡ ዘመን
ይሆናችኃል እየተባሉ እህል እየገዙ የሚያስቀምጡ አሉ፡፡ ምን አለ እህል ከሚገዙ ልብ
ቢገዙ፡፡ ወዳጄ አንተ ገንዘብ ስላለህ በገንዘብህ የማይነቅዝ እህል ገዝተህ ጎተራህን ትሞላ
ይሆናል፡፡ ግን ምንም የሌለው ድኃ የረሃቡ ዘመን አንተን ነው የሚበላህ፡፡ ደግሞስ እንደ
ሽኮኮ ቤትህን ዘግተህ እየበላህ የረሃቡን ዘመን የምታልፍ ይመስልሃል? በፍጹም፡፡ የረሃቡ
ዘመን የሚያልፈው የማይነቅዝ እህል በማስቀመጥ ሳይሆን ተባብሮ በመጸለይ ነው፡፡
ደግሞም አትርሳ ጌታ አምላከ ነደያን ነው የተባለው፡፡ የነደያን አምላክ ድሆችን አይተውም፡፡
እህል ብታከማችም ያከማቸኸውን የሚያስበላህ ዘመን ይመስልሃል? ያለ ጸሎት
ያከማቸኸው እህል የድሆች ቀለብ ሊሆን ይችላል፡፡ በር ዘግተን የምንበላበት የረሃብ ዘመን
ከሆነማ ቤትህ የድሆች የጨረባ ተስካር ይሆናል፡፡ በዛን ዘመን የሚያስበላን ሲኖር ነው
እየበላን ዘመኑን የምንገፋው የምናልፈው፡፡ በቤታችሁ እህል ከምታከማቹ የጽድቅ ሥራ
አከማቹ እሱ ነው በክፉ ዘመን ማለፊያ ቀለብ የሚሆናችሁ፡፡ በኃጢአት ስንጨማለቅ
ከርመን እህል አከማችተን የመከራውን ዘመን ልናልፍ? አሄሄ ….
በሽታ ፦ በሽታ የተባለው ተላላፊና ወረርሽኝን ጨምሮ ነው፡፡ ረሃቡን ባስቀመጥነው እህል
እናልፋለን ብለን በሥጋ ብንጠበብ ከገዳይ በሽታ እና ከወረርሽን ላናመልጥ እንችላለን፡፡
ለዚህም ነው ጊዜው የሚያልፈው እህል በማከማች ሳይሆን በጸሎት ነው የምለው፡፡
ወረርሽን ሰውን እንደ ቅጠል ያረግፋል ብዙዎችንም ይገድላል ግን በጸሎት ያልፋል፡፡
ካልጸለይን በረሃብ ብቻ ሳይሆን በበሽታም እንወረራለን፡፡
ጦርነት ፦ ጦርነት የተባለው ሁለት ነው፡፡ አንደኛው ከውጭ በሚመጣ በወራሬ ኃይል ሲሆን
ሁለተኛው ከውስጥ ነው፡፡ ወራረው ሃይማኖችን ተገን አድርጎ የሚመጣ ነው፡፡ የውስጡ
ሃይማኖትንና ብሔርን ተገን ያደረገ ነው፡፡ በዚህም ከፍተኛ የእርስ በእርስ ጦርነት ሊነሳና
ብዙዎች ሊያልቁ እና ሊዋደቁ ይችላሉ፡፡ ይህም የሚያልፈው በጸሎት ነው፡፡ የሃይማኖቱንና
የብሔሩን የጦርነት ዋዜማ በየቦታው እያየን ነውና መጸለዩ ስለሚያሳልፈው እንጸልይ፡፡
ይህ ሁሉ ትንቢት ይፈጸማል ወይስ ያልፋል?
ተወዳጆች ሆይ ትንቢት በባሕርይው ይፈጸማል ይልፋል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተነገሩት
ትንቢቶች የተፈጸሙ አሉ፡፡ ወደ ፊት የሚፈጸሙም አሉ፡፡ የሚያልፉም አሉ፡፡ ከላይ ያየናቸው
ትንቢቶች ይፈጸማሉ ወይስ ያልፋሉ ለሚለው እድሉ ያለው በእኛ እጅ ነው፡፡ እኛ ከጸለይን
ጌታችን የሚመጣውንና ሊመጣ ያለውን ትንቢት ያሳልፋል፡፡ ግን ይህ የሚሆነው በብርቱ
ጸሎት እና ምህላ ነው፡፡ ለምሳሌ የነነዌን ትንቢት ብንመለከት ያቺ ከተማ ከነ ሕዝቦችዋ
እንደ ትንቢትዋ ቢሆን አትተርፍም ነበር፡፡ ግን እግዚአብሔር የነነዌን ሕብዝ ጸሎት እና ብረቱ
ጩኸት ሰምቶ ከተማዋም ሕዝቡም ከተነገረለት ትንቢት ተርፏል፡፡
እግዚአብሔር በዳዊት ላይ በተቆጣ ጊዜ መልአኩን ልኮ ኢየሩሳሌምን እንዲያጠፋት አዞ
ነበር፡፡ ግን እግዚአብሔር የዳዊትን ጸሎት እና ጩኸት በማየት በመጸጸት ኢየሩሳሌምንና
ሕዝቧን ሊያጠፋ የላከውን መልአክ መልሶ ‹‹በቃህ አሁን እጅህን መልስ›› አለው፡፡ /1ኛ
ዜና 21÷15/ ዛሬም እንደ ዳዊት ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ከጮኽን እግዚአብሔር
ተጸጽቶ ‹በቃችሁ›› ይለናል፡፡ ስለዚህ ትንቢቱ እንዲፈጸም እና እንዲያልፍ የምናገደርገው
እኛው ነን፡፡ እንዲሁም ንጉሥ ሕዝቅያስን እግዚአብሔር ‹‹ትሞታለህ እንጂ በሕይወት
አትኖርምና ቤትህን አስተካክል›› ብሎ በነብዩ ኢሳያስ አንደበት ቢነግረውም የሕዝቅያስን
ጸጸት ለቅሶ እና ጸሎት የተመለከተው እግዚአብሔር በሞት ከተቆረጠ ቀኑ ላይ አሥራ
አምስት ዓመት ጨምሮለታል፡፡ /ት.ኢሳ 38÷1/
እኛም ከዚህ ሁሉ ሊመጣ ካለው ትንቢት ከጸለይህ እግዚአብሔር ሞታችንን ወደ ሕይወት
ይቀይረዋል፣በሞት በተቆረጠው እድሜያችን ላይ ሌላ እድሜ ይሰጠናል፡፡ ለዚህም ነው
ትንቢት በጸሎት ያልፋል ያልኳችሁ፡፡
ንጉሥ ቴዎድሮስ መቼ ነው የሚመጣው?
ተወዳጆች ሆይ ብዙዎችን የሚያጓጓ ይሄ ጥያቄ ነው፡፡ አንዳንዶች የሚመጣበትን ዓመተ
ምህረት ጠቅሰው እርግጠና ሆነው ይጽፋሉ ይናገራሉ፡፡ ግን የንጉሥ ቴዎድሮስን መምጣት
የምናስተዝመው፣የምናዘገረው የምናቀርበውም እኛው ነን፡፡ ዓመተ ምህረቱ ይህ ነው
ባይባልም ቅርብ መሆኑ ግን እርግጠኛ ነው፡፡ ምክንያቱም ከመምጣቱ በፊት የሚመጡት
መከራዎች፣መሻገሪያ ድልድዮች እየታዩ ስለሆነ በተስፋ መጠበቁ ያዋጣል፡፡
እግዚአብሔር ሰውን እያማከረ አይሠራም የሚሠረውን ሥራ ለቅዱሳን ወዳጆቹ ይነግራል፣
የሚመጣውን ይገልጻል፡፡ አንዳንዶች ከእግዚአብሔር ጋር ሲመካከሩ የከረሙ ይመስል
ዓመተ ምህረቱ ይህ ነው እያሉ እርግጠኛ ይሆናሉ፡፡ ግን ቴዎድሮስ ከመምጣቱ በፊት
የሚመጡ ብዙ ነገሮች መኖራቸው እሙን ነው፡፡ ስለዚህ መምጫውን እግዚአብሔር ነው
የሚያውቀው ከእኛ የሚጠበቀው ይህንን የመከራ ዘመን አሳልፈኸን ከደጉ ንጉሥ እና
ከኢትዮጲያ የትንሣኤ ዘመን አድርሰኝ ማለት ነው፡፡ ግን ሩቅ እንዳልሆነ ቅርብ እንደሆነ
እወቁ፡፡
በኢትዮጲያ አይደለም ጠማማ ትውልድ ጠማማ እንጨት አይኖርም
/ይህ ትንቢት የሚፈጸመው በዘመነ ቴዎድሮስ ነው/
የትንሣኤው ዘመን በረከት እና ቡራኬ
ተወዳጆች ሆይ እድሜ ቢሰጠን ከደጉ ዘመን ከቴዎድሮ ቢያደርሰን ዘመኑ ‹‹አይደለም
ጠማማ ትውልድ ጠማማ እንጨት አይኖርም›› የተባለለት ነው፡፡ ይህ የንጉሡን ደግነት
የሚያሳይ ነው፡፡ ይህም የትንሣኤው የብሥራት ቃል ነው፡፡ በዘመኑ የእህል በረከት
ይትረፈረፋል፣ በጥቂት እህል በረከት ሰው ሁሉ ይኖራል፡፡ የጤና በረከት አለው ታማሚ
ይጠፋል፡፡ መተት ይሻራል ጠንቋን አስጠንቋይ ይበናል፡፡ መታች እና አስመታች አብረው
ይጠፋሉ፡፡ የእድሜ በረከት አለው ሁሉም ዘለግ ያለ ዘመን ይኖራል፡፡ ከሀገራችን የወጡት
ሁሉ ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ፡፡ ኢትዮጲያም ልዕለ ሀያል ሀገር ትሆናለች፡፡ የዓለም ዓይን
ሁሉ ወደ እሷ ይሆናሉ፡፡ መሬትዋን ለመርገጥ የውጭ ሀገር ዜጎች ይጎርፋሉ፡፡ ፍቅር እንደ
ሸማ ይነጠፋል፣ሰው ከሰው ጋር በአንድነት በመግባባት ይኖራል፡፡
ሃይማኖት ይስፋፋል፣እምነት በሰው ልብ ሰርጾ ይጠነክራል፡፡ ‹‹ኢትዮጲያ እጆችዋን ወደ
እግዚአብሔር ትዘረጋለች›› የሚለው የዳዊት ትንቢት በግልጽ የሚፈጸመው ያኔ ነው፡፡ /መዝ
68÷31/ በዘመኑም ‹‹ፀሐይ›› የተባለው ጳጳስ ይነሳል፡፡ እሱም በጸሎቱ ኦርቶዶክስን
ይመራል በቡራኬውም በረከትን ለሰዎች ይሰጣል፡፡ ንጉሡ እና ጳጳሱ ኢትዮጲያንና ኤርትራን
አንድ ያደርጓቸዋል፡፡ በአንድነትም እንኖራለን፡፡ ጥላቻ ዘረኝነት ይጠፋል፡፡
ረሃብ፣በሽታ፣ጦርነት እስከ መኖሩም ይረሳል፡፡ ብቻ ከደጉ ዘመንና ንጉሥ የደረሰ ብዙ ያያል፡፡
ለዚህም ነው አባቶቻችን ስትጸልዩ ‹‹ከደጉ ዘመንና ከደጉ ንጉሥ አድርሰን በ
ሉ›› የሚሉን፡፡
የአባቶቻችን አምላክ ከደጉ ዘመን ያድርሰን!
#ባሌን_እጠብቃለሁ

አንድ ሰው ሌላ አገር ሄዶ ገንዘብ ለማግኘትና ለመነገድ ያስባል። ሚስቱን ማማከር ስለነበረበት ከእርሷ ጋር በጠረጴዛ ዙርያ ተቀመጡ።
"ሚስቴ ሆይ አንድ ሐሳብ ላማክርሽ ወደድኩ። ሌላ አገር ሄጄ ወጥቼ ወርጄ ትርፍንም አግኝቼ ይዤ ለመመለስ አስቤያለሁ።" ብሎ ሐሳቡን አቀረበላት። ከተወሰነ ውይይት በኋላም
"አሁን የሚያስፈልግሽ ሁሉ እተውልሻለሁ፤ ስንት ዓመት እንደምቆይ ስለማላውቅ አብዝቼ እሰጥሻለሁ።" አላት ። በመንፈስ የበረታ አልነበረምና እያመነታ እንዲህ ሲል ሃሳቡን ቀጠለ "አንድ በጣም ሊያስቸግርሽ የሚችል ነገር ቢኖር የሥጋዊ ፍላጎት ሐሳብና ፈተና ነው። እሱንም ላንቺ ትቼዋለሁ ። በራስሽ ጥበብና ዘዴ ተወጪው አላት ። "
በዚህ ተስማምተው እንባ ተራጭተው ተሰነባበቱ።

#ባል_ሳይመለስ_ብዙ_ዘመናት_አለፉ ። ሚስት ወደፊት የሚሆነው አይታወቅም ብላ ትንሽ ገቢ የሚያስገኝላት ቀለል ያለ ሥራ መስራት ጀመረች ። ጊዜ እየገፋ ሲሄድ የሥጋ ነገር ስራው መስራት ጀመረ ። ብዙ ጊዜ ብትታገስም እያዳከማት መጣ ። እንዲህ ዓይነት ፈተና እንዴት እንደምታሸንፍ ምክር ስላልተሰጣት፣ በዚያ ላይም ሐሳቡ ለእርስዋ ብቻ መተዉ እንደ ሙሉ ነፃነት ቆጥራው አእምሮዋ እየተዳከመ፣ እየተሸነፈች መጣች ።
ታድያ የምትሰራበት ቦታ ውስጥ አንድ ሰው ዓይኗ ውስጥ ገባ ። እሱ ባለበት ሁሉ ትሄዳለች። እሱ ባለበት ኅብረት
ውስጥ ትገኛለች፤ ባጠቃላይ እሱ በሚገኝበት ቦታ የምታደርጋቸው ትዕይንቶች ሁሉ እሱን ወደ ወጥመዷ ለማስገባት ያተኮሩ ነበሩ ።
እሱ ባያስበውም። አንድ ቀን መንገድ ላይ ጠብቃ "አንድ የማዋይህ ነገር ስላለኝ አንድ ቦታ ለብቻችን ተገናኝተን ብናወራ ምን ይመስልሃል? " አለችው።
እሱም እውንታውን ገልፆላት በቀጠሮ ተለያዩ።

በተባለው ቀን፣ ቦታና ሰዓት ተገናኙ።
ከትንሽ ጨዋታ በኋላ ወደ ዋናው ቁምነገር እንግባ ተባብለው እሷ ጀመረች። ታሪኳ ሁሉ ነግራው ስሜቷን ይረዳላትና የፈለገችውን ይፈጽምላት እንደሆነ ጠየቀችው።
ትንሽ እንደማሰብ ብሎ "ችግር የለውም ግን
" አለና አንድ ታሪክ ያጫውታት ጀመር።
"የግቢ (የ university) ተማሪ እያለሁ ከአቅሜ በላይ፣ ልቋቋመው የማልችል ችግር ደርሶብኝ ነበር። ይህ ችግር ሊፈታው የሚችል እግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ተረድቼ እንባዬን ወደ እግዚአብሔር አፈሰስኩ። በጸሎቴ ውስጥም 'እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ ከእኔ ከኃጢአተኛው ልጅህ የምትወጣውን ይህች ጸሎት ሰምተህ ችግሬን ብታስወግድልኝ፣ ከዚህ ግቢ ተመርቄ ስወጣ አንድ ዓመት ሙሉ ምሳዬን አንድ ዳቦና አንድ ብርጭቆ ውሃ እራቴንም እንዲሁ እያደረግሁ የቻልኩትን እየጸለይኩና እየሰገድኩ አሳልፈዋለሁ።'
ስል ስዕለት ገባሁ። አሁን የቀረኝ 60 ቀን ነው። ምናልባት ፈቃደኛ ከሆንሽ 30 ውን ቀን እኔ 30 ውን አንቺ ተከፋፍለን ቶሎ ብንጨርሰውና ከዛ በኋላ ብንወስን ምን ይመስልሻል?"
ብሎ ሐሳቡን በጥያቄ አጠቃለለ።
'እንዴት ዓይነት ችግር ቢገጥመው ነው?' ብላ እያሰበች ነበርና አሳዘናት። ነገር ግን ባቀረበላት ሐሳብ ደግሞ ደስ አላት ።
የተባለችው በትክክል ከፈፀመች እሺ የማለቱ ዕድል በጣም ሰፊ ነውና።

በተባለችው መሰረት በአንድ ዳቦና በአንድ ብርጭቆ ውሃ ተጋድሎዋን ቀጠለች።
29 ኛው ቀን ሲትደርስ ሌላ ጭንቀት ውስጥ ገባች። ነገሮች ሁሉ ተቀያይረዋል። ድሮ የነበራት ስሜት አሁን የለም።
የሥጋ ነገር መድኃኒቱ ገብቷታል ። ያስጨነቃትም ይህ ነበር።
ሐሳቧ እንዴት ትቀይር?! እራሷ ጀምራ እራሷ እምቢታዋን እንዴት ትግለፅ? -- ጨነቃት።
በ 30 ኛው ቀን በቀጠሯቸው መሰረት ተገናኙ። ሌላ አማራጭ አልነበራትምና እንደምንም ብላ የሆነውን ሁሉ
ከነገረችው በኋላ "-- #ባሌን_እጠብቃለሁ " ስትል ሥጋ ሲያስቸግር በእንዲህ ዓይነት ተጋድሎ በትዳሯ መጽናት እንደምትፈልግ ነገረችው። መልሱ እንዴት ሊሰቀጥጥ እንደሚችል ቢገባትም ተራራን የሚያክል የስድብ ናዳ ብወርድባትም ለመቀበል ተዘጋጅታለች። እሱም በምስጋና ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አንጋጠጠ። በፈገታም ያላት ሁሉ እውነት እንዳልነበረ ነገራት። ለካ እሱስ የፆምን ኃይል ሊያሳያት፣ ሊያስረዳትና በተግባርም ሊያስተምራት ፈልጎ እንጂ እሱም ሐሳቡን ፈልጎት አልነበረም።
"ጾም ትፌውስ ቁስለ ነፍስ፣ ወታጸምም ኩሎ ፍትወታተ ዘሥጋ፣ ወትምሄሮሙ ለወራዙት ፅሞና ፦ ጾም የነፍስን ቁስል ትፈውሳለች፣ የስጋ ፍትወታትም ሁሉ ጸጥ ታደርጋቸዋለች፣ ለወጣቶችም ጽሞናን፣ ትዕግስትን፣ ጸጥታን ታስተምራቸዋለች"

#ወዳጆቼ ከዚ ፅሑፍ ከሥጋዊ ባልና ሚስት ባሻገር ሰፊ ምስጢር እንደምትረዱ ተስፋ አደርጋለሁ ። ምክንያቱ ሚስት ሴት ብቻ አደለችምና ። ምን ለማለት ፈልጎ ነው ? ከሴት ውጪ ሚስት አለችን ?? ! ብላችሁ በአግራሞት ልትጠይቁ ይሆናል ። እኔ ግን አዎ ከሴት ውጪ ማግባት ያለብን ማፍቀር ያለብን ብዙ ሚስቶች አሉ ብዬ እመልሳለሁ ። ለምሳሌ ንፅህና ፣ ጾም ጸሎት ፣ ምጽዋት... ሚስት መሆን ይችላሉ ። እነሱን አግብተን በቅድስናና በንፅህና በመኖር ሰማያዊው ሰርግ ቤት መንግስተ ሰማያት ማግኘት ይቻላል ። ቅዱሳን አባቶቻችን ይህንን በተግባር አሳይተውናልና ።
#ዛሬ_አንድ_በጣም_የገረመኝ_ነገር_አንድ_ወዳጄ " ሁሉም ነገር ( ሙዝቃ ፣ መጠጥ ፣ ጭፈራ ወዘተ ) ማቆም እችላለሁ ። አንድ የከበደኝ ነገር ግን ማመንዘርን እንዴት ላቁም?" ብሎ ጠየቀኝ ። ጥያቄው ለመለወጥ ካለው ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ በመሆኑ በጣም ደስ ብሎኛል ። እና የጠየከኝ ወዳጄ እድሁም ውድ ይህንን ፅሑፍ የተመለከታችሁ ሁሉ ቢከብድም መልሱ ከላይ ያነበባችሁት ታሪክ ነው የሚሆነው ። እና የፍትወት መድኃኒቱ ጾም ጸሎት ነውና ሁላችንም በጾሙ ልንበረታ ያስፈልጋል ።
ጾሙ የፍቅር የደስታ እንድሁም የቁስለ ሥጋ የቁስለ የፍስ መፈወሻ የጽድቅ መውረሻ እንድንሆንልን የአምላካችን ፈቃድ ይሁንልን ።

" ባሌን እጠብቃለሁ !"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
✥ ብስራተ ገብርኤል ለማርያም ድንግል
✥በዚህ ዕለት በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ብስራተ ገብርኤል ይባላል፤ ይህም ቅዱስ ገብርኤል ለእመቤታችን ጌታን እንደምትወልድ ብስራቱን የነገረበት ቀን ነው፤ እንዴት ብስራቱንማ የነገራት መጋቢት 29 ቀን ካሉ ትክክል ነው፤ ብስራቱን የነገራት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሁድ ከቀኑ ሦስት ሰዓት ላይ ነው፡ ታዲያ ዛሬ ለምን እናከብረዋለን ካሉ ምክንያቱ እንዲህ ነው፤ ምንግዜም ወርሃ መጋቢት ታላቁ ዓቢይ ጾም የሚውልበት ወር ነው በዚህ በዓቢይ ጾም ደግሞ ሐዘን፤ ለቅሶ፤ ጾም፤ ጸሎት እንጂ ደስታ፤ ፌሽታ እልልታ፤ ጭብጨባ የለም።

✥ ፍጹም የሐዘን ወራት ነው ታቦት አውጥቶ በዓል ማክበርም ስህተት ነው ፍትሃ ነገስት አንድምታ አንቀጽ 15 ተመልከት ፤ ታዲያ ቅዱሳን አባቶቻችን እንደዚህ ዓይነት ስርዓት ሰሩ የመጋቢት 27 ስቅለቱን ጥቅምት 27 ቀን እንዲሁም የመጋቢት 5 አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍት ቀን ወደ ጥቅምት 5 ቀን ዞሮ እንዲከበር አደረጉ፡፡ የመጋቢት 29 ብስራቱን ደግሞ ታህሳስ 22 ቀን ዞሮ እንዲከበር ያደረገው ታላቁ አባት የጥልጥልያ ኤጲስ ቆጶስ ደቅስዮስ ይባላል በእመቤታች ፍቅር ልቡ የነደደ ታላቅ ጻድቅ ነው የእመቤታችንን ታአምራቷን የሚናገር መጽሐፍ የሰበሰበ አባት ነው፡፡

✥የጌታን ልደት ከመከበሩ አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ብስራቱ መከበር አለበት ብሎ ስርዓት ሰራ አገሬውንም ሰብስቦ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ እመቤታችን ተገለጸችለት ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ እንዳከበርከኝ እኔም አከብርሃለው አለችው ሰማያዊ ልብስና ሰማያዊ ወንበር ሰጠችው ይህችን ልብስ ካንተ ሌላ ማንም አይለብሳትም ይህችንም ወንበር ካንተ ሌላ ማንም አይቀመጥባትም አለችው፡ የዚህ ታላቅ አባት እረፍቱ ታህሳስ 22 በዛሬዋ ቀን ነው፡ ከእርሱ በኃላ ሌላ ኤጲስ ቆጶስ ተሾመ ልብሱን እለብሳለው በወንበሩም እቀመጣለው አለ ተው ይቅርብህ እመቤታችን እንዲህ ብላ ተናግራለች ይሉታል እርሱም ሰው እኔም ሰው እርሱም ኤጲስ ቆጶስ እኔም ኤጲስ ቆጶስ ብሎ በትዕቢት ልብሱን ለበሰው በወንበሩም ተቀመጠ ክፉኛ አወዳደቅ ወደቀ ሞተም ይህን ያዩ እመቤታችንን በጣም ፈሯት ይላል ተአምረ ማርያምን ተመልከት፡፡ ደቅስዮስ ሰርቶልን ያለፈውን ስርዓት ቤተክርስቲያን ተቀብላ ይኸው ዛሬም ድረስ ታከብረዋለች በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ታቦተ ህጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል፡፡ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን ።
ዜና ዕረፍት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት እና የጅቡቲ አብያተ ክርስቲያናት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ዐረፉ፡፡ ትላንት ማምሻውን በመንበረ ፓትርያሪኩ በሚገኘው መኖሪያቸው ያረፉት ብፁዕነታቸው፣ ከልብ ሕመም ጋራ በተያያዘ በሀገር ውስጥ እና በአሜሪካ የሕክምና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይቷል፡፡

ከሳምንት በፊት በአሜሪካ በነበሩበት ወቅት የልብ ቀዶ ሕክምና እንዲደረግላቸው ቢጠየቁም፣ "አልፈልግም፤ አገሬ ገብቼ ልሙት፤" ብለው እንደተመለሱ ታውቋል፡፡የቀብራቸው ሥነ ሥርዐት ነገ ዓርብ፣ ታኅሣሥ 24 ቀን 2012ዓ.ም. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚከናወን ተጠቁሟል፡፡

(ሐራ ዘተዋሕዶ )
ከሰባሰገል መካከል ኢትዮጵያውያን ነገስታት የመጀመሪያውን ድርሻ ይይዛሉ ።
የነገስታቱ ስም ማን ማን ይባላል?
ማንቱሱናል በደዲያስፍ መልሂቁ ይባላሉ ።
ለግብር የተነሱት ነገስታት 12ናቸው ለመገበር የበቁት እና የታደሉት ደግሞ 3ናቸው ።ለመገበር ከበቁት ከ 3ቱ ነገስታት መካከል አንዱ ኢትዮጵያዊው ንጉስ ባዚን አንዱ ነው ።(ትርጓሜ ዳዊት መዝሙር 71 ላይ የሳባው ንጉስ ብሎ ንጉስ ባዚንን ይገልጸዋል የምስራቅን የነገስታት ግን የተርሴስ ወይም የደሴቶች ነገስታት ብሎ ይጠቅሳቸዋል ።
አነሳሳቸው እንዴት ነበር?
የምስራቅ ነገስታት ሲነሱ በኮከብ እየተመሩ ነው።
የሳባ ነገስታት የተነሱት ደግሞ ትንቢቱ መድረሱን አውቀው ተገንዝበው ነው ።
አወጣጣቸውስ እንዴት ነበር?
የምስራቅ ነገስታት ሲነሱ ዥራድሽት እሚባል ጠቢብ ፈላስፋ  ድንግል በሰሌዳ ኮከብ ተቀርጻ ተስላ ህጻን ታቅፍ ቢያይ ይህስ ደግ ነገር ነው ሳይደረግ አይቀርም ብሎ በብርት ቀርፆ አስቀመጠው ።ለነሱም ሲነግራቸው ያ ኮከብ ሲዎጣ እንድትገብሩለት ብሏቸው ነው የወጡት ።
ኢትዮጵያዊው ባዚን ሲነሳ ደግሞ ትንቢቱ መድረሱን አውቆ ይገባዋል ብሎ ነው የተነሳው በዚህም ሃይማኖት ከክርስቶስ ልደት በፊት በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በኩል መሰበኩን ማዎቅ መረዳት እንችላለን ።
ከምስራቅ ነገስታት እና ከንጉስ ባዚን  በመጻፍ ቅዱስ ማን ይሁን ምሳሌ የተቀመጠለት ንጉስ?
መልሱ ንጉስ ባዚን ነው እሱ ነው ምሳሌ የተቀመጠለት ንጉስ የምስራቅ ነገስታት ግን ምሳሌ አልተቀመጠላቸውም ።ምን ያክል የከበረች ሀገር እንዳለችን እናስተውል ምሳሌው እንደሚከተለዉ ነው ።
ንግስተ ሳባ ሰለሞንን እጅ ልትነሳ ሄዳለች ሰለሞን የክርስቶስ ምሳሌ ነው ንግስተሳባ ደግሞ የሰባሰገል ምሳሌ ናት ።የወሰደችለት አመሃ ሰባሰገል የወሰዱለትን ወርቅ እጣን ከርቤ ምሳሌ ነው ።ሰባሰገል እና ነጉስ ባዚን የተገናኙት ኢየሩሳሌም በር ላይ ሲሆን አላማቸው አንድ መሆኑን አውቀው ተረድቸው ሊገብሩለት ገብተዋል ።2ቱ ከሩቅ ምስራቅ የመጡት ነገስታት ወርቅ እጣን ገብረውለታል ።ኢትዮጵያዊው ንጉስ ባዚን ግን ከርቤን ገብሮለታል ይህም ንግስተ ሳባ ለሰለሞን ከገበረችለት አንዱ የሽቱ አይነት ከርቤ ነው አለቃ አያሌው ስለ ኢትዮጵያው ንጉስ ሲናገሩ ትንቢትም ምሳሌም አለን በዚህ እኛ ከ አለም ህዝብ የታደልን ነን ።ከዛም ወስደው ገበሩለት ህጻኑን በእናቱ እቅፍ አገኙት የአምላክን እናት ለማየት ታደሉ ፈጣሪያቸውን በእናቱ እቅፍ ሆኖ አዩት ምንኛ ይሁን ደስታቸው የበረሃውን ጉዞ የረሱበት ያ መልክ ምን ያክል ያንጸባርቅ ይሁን ምን ያህል የህይዎት ውሃ ሙላት ሆነላቸው ለአዲስ ኪዳን መምጣት አብሳሪ የሆነውን ገጽ ለማየት የመጀመሪያዎቹ በመሆን ሰባሰገል ታደሉ ።ከልደቱ ረዴት በረከት ያድለን ድህነትን ያገኘንበት የመጀመሪያው ብስራት ነውና ለድነታችን የትውስታ ምክኛት ሆኖን ንሰሃ ገብተን በቤቱ ለመኖር ያብቃን ።መልካም ገና
አዘጋጅ ዲ.ን ኃይለሚካኤል ሮቤ
የገና ዛፍ እና የገና አባት ትውፊቱና ትርጉሙ ምንድነው?
ታሪክ   የገና ዛፍን ያመጡት ሉተራውያን ናቸው ።1980ዓ/ም ገደማ እ.ኤ.አ የገና ዛፍን የሂዎት ዛፍ ምሳሌም አድርገው ይቆጥሩት ነበር ።ከዛም በግልጽ ዖሪት ዘፍጥረትን ምሳሌ አድርጎ jon poll the 2nd የተባለ ካቶሊካዊ ያስተምር ነበር Christmas tree የመጣውም የተስፍፍውም ከርሱ ትምህርት በዋላ ነው ።ይህም ሰው ይህንን ትምህርቱን እያስፍፍ ከ ምስራቅ አሜሪካ ወደጀርመን ገብቷል ።ነጮቹ ገና በደረሰ ቁጥር ከፍተኛ ወጪንም ያወጡበታል ።የክርስቶስን ልደት አስበው ይሁን ከሆነስ በየትኛው ትውፊት ተመርተው ነው የገና ዛፍን በመስራት ልደቱን እሚያከብሩለት? የኔ ምልከታ ዛፍን ትቆርጣላቹ ምስልንም ትሰራላቹ ያ ሁሉ ግን አይጠቅምም እሚለውን እየፈፀምን ያለን ይመስለኛል ሰባሰገል ወርቅ እጣን ከርቤን አመጡለት እንጂ የገና ዛፍን ሰሩለት አይለንም።ሳናውቀው በእጃዙር ባእድ አምልኮ ውስጥ ገብተናል ምክኛቱም የዚ ዛፍ መነሻ የሆኑትን ሀገራት ስናይ የአምላክን ልደት ከማሰብ ይልቅ የንግድ በአል አድርገውታል ገሚሶቹ ከፍተኛ ወጪን ሲያወጡበት ገሚሶቹ ደግሞ ያገኙበታል ንግድ ተኮር ብቻ ሆኗል በዓሉ።አሁን ባለንበት ወቅት Merry Christmass መባባሉ እንኳን ቀርቷል በውጪው አለም ያላቹ ማረጋገጫ ልትሆኑኝ ትችላላቹ happy holidays ነው ሚባባሉት ስለዚህ የጌታን ልደት እንዲያስታውሰን ነው ዛፍን እምንሰራው ይህ ከሆነ አላማችን ቤተክርስቲያናችን ቀድማ ስርዓቷን ገንብታለች ለምሳሌ ሃምሌ ታህሳስ 19 እምናከብረው በዓል መላኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሰረበት ነው ታህሳስ 22 ጽንሰት ነው እንደተጨማሪ ታህሳስ 29 የቅዱስ ላሊበላም ልደቱ ነው ታዲህ ይህ ሁሉ ማስታዎሻ ተቀምጦልን ተጨማሪ ለምን አስፈለገን ።
Santa Chloe's በነሱ ትውፊት የገና አባት ይባላል ታሪኩንም ስናይ ህፃናትን ለማስደሰት ነው የመጣው ይባላል ምክኛቱም ስጦታ ይዞላቸው ስለሚመጣ ።መልካምነቱም ምኑም አይመለከተንም እኛ የገና አባትነቱ ታውቆ ገናን ምናከብረው በክርስቶስ ልደት ነው የገና አባት መሆን ያለበት ክርስቶስ ነው ከጌታ ልደት ይልቅ ስለ ሳንታክሎውስ እሚዎራው ልቆብኛል አከባበራቸውም ትውፊታቸውም ከሃይማኖት ያዎጣል አከባበራቸው ።ማዎቅ ያለብን ትልቁ ነገር የኛ ያልሆነ ነገር የኛ አይደለም እኛንም ምናመልከውንም አይገልፀውም ።ለምናደርገው ነገሮች በሙሉ ምክኛት ቢኖረን መልካም ይመስለኛል ።ሁሉም የኛ አይደሉም እኛን አይመስሉንም ።
ሰላም ለከ #ዮሐንስ : ዘረፈቀ ውስተ ኅጽኑ #ለኢየሱስ

~በጌታ ደረት ላይ ለተጠጋህ::
~እሳቱ ላላቃጠለህ::
~መለኮት ለሳመህ::
~ድንግል ላቀፈችህ::
<ላንተ (ለዮሐንስ) ሰላምታ ይገባሃል!!>>

ከብዙ ጸጋህ . . . ለእኛ ለባሮችህ ጌታንና ድንግል እናቱን መውደድን እንድትሰጠን እንማጸንሃለን !!
አሜን!

@senkesar
ገሃድና ሰንበት ተገናኙ
ገሃድ ጾም የማይሻር የድነት ጾም ነው። ገሃድ ምትክ ወይም መታየት መገለጥ ማለት ነው።
የተሻረችው ሰንበትም የትንሣኤ ዋዜማ ብቸኛዋ ቀዳም ስዑር ናት። የዘንድሮው የጥምቀት
ዋዜማ ሁለት የማይሻሩ ጉዳዮች ማለትም ገሃድና ሰንበትን አገናኝታ ትውላለች። አባቶቻችን
ሁለቱንም ማክበር የምንችልበት ሥርዐት ነው የሠሩልን። ስለሆነም ገሃዱም አለ፤ እሑድም
የጾም ምግቦችን እየተመገብን ዕለቱን እናከብራለን ማለት ነው። አንዳንድ አላዋቂዎች
እንደሚሉት "ቅዳሜ አይጾምም እሑድ ግን ይጾማል" የሚል ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የለም።
ስለሆነም ገሃድም እሑድ ሰንበትም በዚሁ ዕለት ተቻችለው ይከበራሉ ማለትም በዚህች
እሑድ ዕለት ገሃድም አለ፤ ሰንበትም አለ ማለት ነው። ገሃድ የሚውለውም በዋዜማ ዕለት
ብቻ ነው። ስለዚህ የዘንድሮ የጥምቀት ገሃድ እሑድ እንጂ ቅዳሜ አይደለም። እሑድ ጧት
ቅዳሴ ይቀደሳል፤ ቆራቢዎች ጧት ይቆርባሉ፤ ጸበል ይታደላል፤ ይጠጣል፤ በውጭም ጸዲቀ
መበለት (የሰንበት ቂጣ) ይታደላል፤ አስቀዳሾች ይመገባሉ። ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን በዕለቱ
ሥጋና ወተት መሰል መብልና መጠጦች ሙሉ ቀን የተከለከሉ ናቸው ማለት ነው።የገሃድ ጾም የሚጾመው በጥምቀት ዋዜማ ብቻ ነው። አንዳንድ ሰዎች ግን ባለማወቅ
የልደትን ዋዜማም “ገሃድ” ብለው ይጾማሉ። ነገር ግን የልደት (ገና) ዋዜማ መጀመሪያውኑ
በጾመ ነቢያት ውስጥ ያለ በመሆኑ ድርብ ጾም የለምና ለብቻው አይጾምም። በተለምዶ ግን
ጾመ ነቢያትን ሳይጾሙ ቆይተው ዋዜማዋን ብቻ የሚጾሙ አሉ። ጾመ ገሃድ ግን የጥምቀት
ዋዜማ ብቻ መሆኑን መረዳት ይገባናል። ጥምቀት ረቡዕና ዐርብ በሚውሉበት ጊዜ
ቀድመው ያሉት ማክሰኞና ሐሙስ የፍስክ ቀንነታቸው ወደ ጾምነት ተለውጦ ይጾማሉ። በነሱ
ለውጥ ጥምቀት የሚውልባቸው የጾም ቀናት (ረቡዕና ዐርብ) የፍስክ ቀን ሆነው
ይከበራሉና።
ገሃድ የረቡዕና ዐርብ ለውጥ ነው ብለናል። ነገር ግን ጥምቀት በሌላም ቀን ቢውል
የጥምቀት ዋዜማ ይጾማል። በዓለ ጥምቀት እሑድ ቢውል ቅዳሜ ጥሉላት አይበላም።
ጥምቀት ሰኞ ቢውል እሑድ ጥሉላት አይበላም። እንደሌሎች የአጽማዋት ቀናት እህልና
ውሃ ግን አይጾሙም። አንዳንድ ሰዎች ግን ጥምቀት ሰኞ ሲውል ከቅዳሜና እሑድ
አዋጥተው በመጾም ቅዳሜና እሑድ ጥሉላት አይበላባቸውም ይላሉ። ነገር ግን “ገሃድ”
አንድ ስለሆነ (ስንክሳር ጥር 10 “ሰላም ለዕለት ዋሕድ ዘስሙ ገሃድ” እንዲል) ጥምቀት
ሰኞ ሲውል ቅዳሜን መጾም አጉል የገባ ልማድ ነው።
ምንጭ፦ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ታላቁ ያዘጋጁት “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ
ክርስቲያን ታሪክ” መጽሐፍ፤ ገጽ 130።