ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
'እኔ ማን ነኝ?' የሚለውን ጥያቄ ለራሳችሁ ጠይቁና በአንድ ቃል ወይም ሐረግ ብቻ መልሱን አቀብሉን። በአዲሱ አደባባይ በኢንተርኔት አማካኝነት በሚካሄደው የዚህ አመት የ ጥበብ በአደባባይ ኦንላይን ፌስቲቫል ላይ መልሳችሁን ግጥማችን ውስጥ ተካትቶ ታገኙታላችሁ።

መልሳችሁን ከስር ባለው
Show Comments በሚለው ቁልፍ በጽሁፍ አድርሱን ወይም እራሳችሁን በቪድዮ በመቅረጽ መልሱን ብቻ በመናገር #ግጥምሲጥም ብላችሁ በማንኛውም የማህበራዊ ሚድያ በኩል አጋሩን።

ማን ነሽ? - ማን ነህ? - ማን ናችሁ?

በአንድ ቃል ወይም ሐረግ ብቻ በመመለስ ቃልና ሃሳብ አቀብሉን - አብረን ግጥም እንጻፍ። ምናልባትም ብዙ ሰው በማሳተፍ ቀዳሚው የሚሆን ግጥም አብረን እንፈጥር ይሆናል።

ተመስገኑልን!

#ግጥምሲጥም #ጥበብበአደባባይ #ስነ_ግጥም #ሙዚቃ #gitemsitem #tibebbeadebabay #poetry #music #Yisaacandfriends #digitalartfestival #artinaddis #tba

http://tibebbeadebabay.org/
የፀባዖት ጣሪያ
(ከ ሰይፈ ተማም)

ከደሜ ደም ተጣብቆ
የልቤን ልብ አርቆ
ከ ́እኔ ́ በላይ ዘልቆ
በመምጠቅ ህዋ ላይ
ከዛ በላይ
መጥቆ
ሲፍለቀለቅ
ሲንዠቀዠቅ
ሲያብረቀርቅ
ሲርቅ
ሲመጥቅ
... ሲደባለቅ
አዩትና ይህን ልዩ
አዩትና ́ከኔ ́በላይ
ካለው በላይ ከበላዩ
አዩትና በእንቅልፍልብ
አዩትና ባሳብ ክልብ
አዩትና . . .
(አይ ሰው ሞኙ
ስም ወዳጁ ርዕስ ቀኙ)
. . .
ከደሜ አንጓ ተፈልቅቆ
ከ ́እኔ ́ በላይ ካጥናፍ ዘልቆ
በመምጠቅ ህዋ ላይ
ከዛ በላይ መጥቆ

ዘመን አልባ
ቅጽበት አልባ
የማይነጋ የማይጠባ
የማይተጋ የማይገባ
የማይለማ የማይሰባ
የጸጋ ለምድ የክብር ካባ
የንቁ አጸድ የፍቅር አምባ
መሻትን የማይሻ
ምሉዕ የሁሉ ድርሻ
ሰቶም እማይጎድል
ነዶም እማይከስል . . .

ያዩትን ብቻ ́'ሚያዩ
ከትውስታ ሳይለዩ
አዩትና ይሄን ልዩ
አዩትና ካ ́ለምጋራ የዘገዩ
አይተው መስሏቸው ያዩ
ጻፍልን አሉኝ ስሙን
ጻፍልን አሉ ማሰሪያ
ጻፍልን አሉ ማጠሪያ
ጻፍልን አሉ መጠሪያ
ስም ያለው ይመስል
የፀባዖት ጣሪያ

#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ስነ_ግጥም
በድጋሚ የቀረበ
Forwarded from ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem (S e i f e - T e m a m)