ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.85K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Gitem Sitem presents you the marvelous Migbar Siraj and his works along with other outstanding poets.
Poetry, Music, Campfire, Foods and Drinks and so much more.
Please RSVP by sending your full name to gitemsitem@gmail.com or @seifdman on telegram.

ግጥም ሲጥም ልዩ ባለቅኔ የሆነውን ምግባር ሲራጅን ከሌሎች እጹብ ገጣሚያን ጋር ይዛላችሁ መጥታለች!

ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የእሳት ዳር ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎች አሉን።

ዝግጅቱን ልዩ ጥሪ የተደረገላቸው እና ቀድመው ቦታ ያስያዙ ሰዎች ብቻ በአካል ይታደሙታል። (መግቢያ አናስከፍልም) ቦታ ለማስያዝ በኢሜይል ወደ gitemsitem@gmail.com ወይም በተሌግራም @seifdman ላይ ሙሉ ስማችሁን እና ስልካችሁን/ የቴሌግራም አድራሻችሁን ላኩልን።


https://goo.gl/maps/EiCpLt2RCoYHLXoK7

በገለጥነው የኛው ቀለም
ጥዑም ግጥም እናጣጥም

#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ

https://goo.gl/maps/EiCpLt2RCoYHLXoK7
ለአዳዲስ ከዋክብት ሰማይ ለመሆን ያወጣነውን ጥሪ ተከትሎ ካገኘናችው ምርጥ ገጣሚያን አንዷ - ሮዛ ሽታ (ግሩም ነን መቼም)ን ተዋወቁልን!

#ሮዛሽታ #ግሩምነንመቼም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
[♣️እብን ይወክላል ልብን?♣️]

የመውደድ ገላ መዓዛ
ከአሪቲ ዛላ መዝዛ
ሸተተኝ የማፍቀር ለዛ።
ከአልባጥሮስ፣ ከእጣን፤ ከርቤ
የሰማሁት፤ ተደልቄ እንደ ድቤ
ተሽቀንጥሬ እንደ ፈትል
መሬት ስሜ ልክ እንደትል
ፍቅር ተማገኝ መልኩ
ታየኝ የተዘነጋ ልኩ፡፡
♣️
ኮከብ ከመሬት ተለቅማ
ሰማይ እንደ ጉንጭ ተስማ
እንደ ቃላብ ለፍቅር ተሞ
ድምጽ አውጥቶ እንዳታሞ
'ገዳም ሳይቀረው ገሞ'።
♣️
ልቡን መውደድ አሸተው
ድካሙ ዓይኑን ሸተተው
[የጠጠሮች “ቋ..ቀጭ” ዜማ
በአፍንጫው ጠረን ጽፎ
የብሌኑን ሞራ ገፎ]
ሄደ፤ ሄደ በረረ
ሽታው ግን ዕጹብ ነበረ፡፡

ለ ምግባር ሲራጅ

#ቶማሰአድማሱ #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
ግጥም ሲጥም አዲስ ተሰጥዖ ፍለጋ ባደረገችው ቅኝት ካገኘቻቸው ምርጥ ገጣሚዎች አንዱ የሆነውን ቃለአብ አባይነህን ተዋወቁልንማ።

#ቃለአብአባይነህ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
ፍርፋሪ ታሪክ
- - - — - - -
"ከጅምሩ ማን ፍጠር አለህ እንዲህ ያለ ነገር? ይሄ ነው ፍርድህ? ዛሬስ አትወርድም፣ አትጽፍም ከግንባሩ ላይ ኃጢያቱን የሚያጽፍ ድፍን የቀዮ ጎረምሳ ተሰልፏል..."
"ተው አርዮስ! ተው! ከፈጣሪ አትጋፋ!...አዋቂ ነው...ተው"
"ድንቄም አዋቂ! ሲታወቅ እንዲህ ከሆነ እውቀት በአፍንጫዬ ይውጣ። አይገርምህም!"
"ለአንዲት ጋለሞታ ፈጣሪህን...ትክዳለህን!"

"ጋለሞታ? ጋለሞታ አልህ?...የት አየህ ስትዘሙት?...የት?...አዘሟች ከሌለ ዘማዊት ትፈጠር ይመስል።እንደወይራ፣እንደቀጋ አትበቅል ዘማዊት..."
"ይወራል።...ድፍን መቂ እሱኑ ነው የሚያወራው"
"እና አመንህ አንተ?"
"ምን አማራጭ ይኖራል? ሰው ተኩኖ።...ሁሉ አምኗል እኔ ማነኝና ሰው ያመነውን አላምን የምለው?"
"አልገባኝም?"
"አይገባህም። አንተ ብቻ ከሰው፣ ከቀየው ተነጥለህ፣ ለዘማዊት ሴት ጥብቅና የሚያስቆምህ ነገር። ብቻህን ከአድባር ትጋጫለህ?...ሴት ጠፋ? ከሸርሙጣ?"
"ዝም በል አንተ!!...ምፅዋ ሸርሙጣ አይደለችም።"
"ነች!"
"አይደለችም! ምፅዋ ሸ...ር...ሙ...ጣ... አይደለችም!! ትሰማኛለህ...አንተ ካላባለግኃት አንዲት ምስኪን ሯጭ ከመሬት ተነስታ ሸርሙጣ አትሆንም።"
"ትጠረጥረኛለህ?"
"አላምንህም"
"አህመድንስ ትጠረጥራለህ? ከእርሳቸው አፍ ነው ቀድሜ የሰማሁት።"
"እሳቸው ቅዱስ ገብርኤል ናቸው? የማልጠረጥራቸው?"
"እና እርሳቸውንም ጠርጥረህ?"
"እንክት! ምፅዋዬ እኮ ናት!"
"በል ወግድልኝ ልሂድበት መንገዴን! እውነትም አሪዎስ!...ያሳደጉህ የእናትህ ጡት ሳይሆን ስምህ እንደሆነ ገና ዛሬ ገባኝ!"
"የምን መንገድ?...የሰው መንገድ አበላሽቶ ...ወዴት?"
"የማን መንገድ ተበላሸ? አንተ ኩሩሩ ወግድልኝ!"
"የምፅዋ። የምስኪኗ...በወሬ ገፍታችሁ የጣላችኋት።...ህልሟ መንገዷ አልነበረም? እ!"
"የምን ህልም አላት ደግሞ ሸርሙጣ? ምን ትሰራበታለች ቢኖራትስ?"
"አንተም አለህ አይደል፤ አይደል እሷ? ሯጭ ነበረች ታውቃለህ።... አቦ ሸማኔ የሚያሳድድ ፍጥነት ነበራት።...የጥንቸል ሳንባ ምታስተፋ ነበረች ይህን አንተም ታውቃለህ....ምን ያረጋል!"
"ጋለሞቶች።"
"አልገለሞተችም።....አንተ ውሻ እንዳልዘነጥልህ በዚህ ከዘራ!"
"ኧረ በህግ...በህግ አምላክ!...ምን ታረግበት ነው እሱ...ኧረ ኡ!...ኡ!...ኧረ በህግ!..."
"ልጄን!...አይኔን!...በማህፀኗ...እንደያዘች...አስኮበለላችኋት...ምፅዋዬን አሸሻችኋት"
"ተው አሪዎስ!...ተው አንተ ከሐዲ!...ባለውለታህን?"
"የት ብዬ ልፈልጋት እሺ አሁን?...ንገረኝ!...እ!..."
"እንካ ቅመስ ይችን ለምፅዋዬ!!...እ!...ይህችን ደግሞ በማህፀኗ ይዛ ለተሰደደችው ልጄ...እንካ!!"
"ኡ!...ኡ!...ኡ!...ኧረ የሰው ያለህ!!!"
"የት ብዬ ነው የምፈልጋት አሁን?...እ!...ምፅዋዬ...የበኩር ልጄን እናት?"

©ምግባር ሲራጅ
ዘንባባ
ከገፅ 132 - 134

#ዘንባባ #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
በተለያዩ የግጥም መድረኮች ላይ ተወዳጅ ስራዎቹን የሚያቀርበው ኤሊያስ ሽታሁን የራሱን መጽሐፍ ለአንባቢያን ሊያደርስ በተቃረበበት ጊዜ በጥዑም ግጥም ዝግጅታችን ላይ የምግበር ሲራጅን ግሩም ግጥሞች በሱ አቀራረብ ሊጋብዛችሁ ተዘጋጅቷል።

#ኤልያስሽታሁን #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
Meet one of the poets we've spotted following our call to artists. This emerging poet is ready to share her perspectives and express her self through poetry.

#AdomiaFekede #gitemsitem #poeticsaturdays #migbarsiraj
#አዶሚያፈቀደ #ግጥምሲጥም #ግጣምዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
መልክዐ ሮዝ

ቅዠቴ..
ቀድሞ
ከማይታረም ግዜ መሀል
ራሳችንን ልናስበልጥ
በየጫካው ስንኮበልል
መመለሻው እንዳይጠፋን
ከየሳሩ ከየዛፉ
ጠረንሽን እየቀባን
አልፈን መጣን::
ጉዱ (ተዐምራቱ)
እጣኔዋ
እጣኒቱ::
ካለፍንበት ስመላለስ
ከዚህ ቀደም ከኔ ቀድመሽ
ያለፍሽበት እየቀባሽ
ከዛፍ ከሳሮቹ
ከሀረግ ከእሾሆቹ
ከመሀከላቸው አንድም አልሸበተ
<ፎስት> እንደቀመሳት
ጠበል ጠዲቅ ሁሉ
ወጣት ነው ዘላለም አንቺን ያሸተተ::

©ምግባር ሲራጅ

#ዘንባባ #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
ተዋወቁልንማ፣ ይህን ጥዑም ግጥም ሰናኝ! ቴዲ ካሳ በግሩም ግጥሞቹ ቆይታችንን ሊያጥም ተዘጋጅቷል።

#ቴዎድሮስካሳ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ምግባርሲራጅ #ጥዑምግጥም
Gitem Sitem presents you the marvelous Migbar Siraj and his works along with other outstanding poets.
Poetry, Music, Campfire, Foods and Drinks and so much more.

ግጥም ሲጥም የዘንባባ መጽሐፍ ደራሲ ምግባር ሲራጅን ከሌሎች እጹብ ገጣሚያን ጋር ይዛላችሁ መጥታለች!

ስነ-ግጥም፣ ሙዚቃ፣ የእሳት ዳር ጨዋታዎች፣ ምግብና መጠጥ እንዲሁም ሌሎች መዝናኛዎች አሉን።

https://tttttt.me/seifetemam

በገለጥነው የኛው ቀለም
ጥዑም ግጥም እናጣጥም

#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
አለ? ምልክት?
ላለመኖር ማስረገጫ
መኖርን በአንጻር ማስጌጫ?
ይገኛል ትርጉም?
ነፋስ ከሚወዘውዘው
ዐይኔ ከሚያየው ጀርባ
የለም እያልኩሽ ስላለው?
በማለም ሽንቁር ሾልኬ
ግልገል ሞቴን ተመርኩዤ
ከሐሳብ ቁልል መሐል
አለመኖርን መዝዤ
ስመላለስበት ባነጋ
(ሳውቅ)
ማመኔን ሳይደገፍ
መካድ ብቻውን እንዳይረጋ..
ጎሕ ቀደደ
እውኔ ብርሃን ሲያርፍበት
ሕልሜ ጥላ አረቀቀ
የካድሁትን ሆኜ ተነሳሁ
ያመንሁት ከእጄ ወደቀ
(እንዲህ እናምናለን
ስለማሰብ ሐሳብ ሆነን
ስለመፍጠር ተፈጥረን
ሕልሞቻችን እንዲያልሙ
መገፋት ደግፏቸው
ተቃርኖዎች እንደቆሙ...
እንዲህ እናምናለን
ስናምን እንክዳለን..
በማየት በማወቅ ብርታት ስልሽ
ከዚህ መለስ ህይወት የለም
የቱ ህይወት? ከየት ወዲያ?
ብለሽ ብትጠይቂ
መጥራት ህይወት አልፈጠረም?
በተቃርኖ እርቅ ጠራን
እንዲህ ክደን ማመን ዘራን!)
ግልገል ሞቴን ተንተርሼ
ነፍስ ስለመዝራት አስባለሁ
(ነጋ! ነቃሁ ብዬሽ ነበረ?)
ይሄን እየነገርኩሽ መምሸቱን ረስቻለሁ
(ስለማወቅ ስንታመም
መርሳት ደስታ አልሆነም?)
(ቃል ብርሃን ሆኖ ሕዋው ልብ ላይ ፈስሶኣል። እታች፥ ምድር እንደሕያው ዐይኖቼን በብልጭታው ተክዬ
እንዲህ ነን አይደለ?
ወደ'የሉም' ስንጠራ
ሰማይ ዜማ ልንሰራ
ግጥም ሆነን ልናበራ?
ባይ'ረዱን
የማይታይ ይቅር
የምንታይን ካዱን)
ጎሕ ቀደደ ዳግመኛ
በሄድሁበት ዞሬ መጣሁ
መኖሬ ላይ ሕይወት አጣሁ
አየሽ?
መንገድ መድረስን ሲረታው?
(ሕልሜና ዕውኔ መሐል የነበረች ስስ መጋረጃ ተገፈፈች። ነፋሱ የገፋት ቅጠል ተንሳፋ ፊቴ ላይ አረፈች... ሕይወት መገለጥ ሆነ!
ምን ነበረ የለም ያልኩሽ...?
እንዲህ እናምናለን
በማመን እንክዳለን!
በማየት በማወቅ ብርታት ስልሽ
ከዚህ መለስ ህይወት የለም
የቱ ህይወት? ከየት ወዲያ?
ብለሽ ብትጠይቂ
መጥራት ህይወት አልፈጠረም?
በተቃርኖ እርቅ ጠራን
እንዲህ ክደን ነፍስ ዘራን!)
በጀርባዬ ተንበልብዬ
ዐይኖቼን ሕዋው ልብ ላይ ተክዬ
እንደሌለሁ
እንደሌለሽ ይሄንን እውነት ስረሳ
(ብልጭ ያልነው እኛ አይደለን?)
ግጥሞች ሆነን ስንነሳ?
(እንረሳለን
እንጂ..
ካየነው ጀርባ አለን!)

ለ Migbar Siraj

#ማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል #ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
እንግዲህ በየወሩ የዘመናችንን የግጥም ጀግኖች እንዲህ አንዳቸውን ከፊት እያዘመትን ስራዎቻቸው የሚገባቸውን ቦታ እንዲያገኙ እንጮሃለን!


የመጀመሪያው የግጥም ሲጥም ዝግጅት 'ራስ' ይህ ድንቅ ገጣሚ ነው!

ምግባር ሲራጅን እስካሁን ለማታውቁ ጥሩ አጋጣሚ መጥቶላችኋል።



#ምግባርሲራጅ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ጥዑምግጥም
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ጥዑም ግጥም ቅመሱማ!

ዮሐንስ ላቀው በግጥም ሲጥም ዝግጅት ላይ

#ዮሐንስ_ላቀው #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #ምግባርሲራጅ
እንሆ የህዳር ወር የግጥም መጽሔ

በቀጣይ መጽሔታችን አሁንም የእናንተኑ ስራ እንጠብቃለን።

shorturl.at/duyO9 ገብታችሁ እዩልን፣ አውርዳችሁም የራሳችሁ ልታደርጉት ትችላላችሁ - ለሌሎችም አጋሩልን። አይታችሁ ስታበቁ አስተያየት አቀብሉን።

ግጥማቸውንና ምስሎቻቸውን እያቀበሉ ወሩን ላደመቁልን ሁሉ ምስጋና ይድረስ!!!
#ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ #የግጥምመጽሔት #ጥዑምግጥም #ምግባርሲራጅ
#gietmsitem #poeticsaturdays #artinaddis #poetrybooklet

Cover Photo Credit: Hermela