የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.03K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ግብረ ሰዶማዊነት ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊና ለትውልድ እንቅፋት በመሆኑ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ሊያወግዙት እንደሚገባ #የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ቦርድ አሳወቀ ።

ሚያዚያ 9 ቀ 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሕይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ዋና ጽህፈት ቤት አዳራሽ በተካሄደው በ9ኛው የካውንስሉ ቦርድ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ የተቋሙ አጀንዳዎችና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል። የካውንስሉ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዚዳንት በሆኑት በዶ/ር ጣሰው ገብሬና በምክትል ፕሬዚዳንቱ በዶ/ር ቤተ መንግስቱ በተመራው በዚህ ስብሰባ፥ የካውንስሉ የእ.ኤ.አ 2023 የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስ ሪፖርት ቀርቦ የጸደቀ ሲሆን፥ እንዲሁም የ2024ን የስትራቴጂክ ዕቅድና በጀትን መርምሮ በመቀበል ጠቅላላ ጉባኤው እንዲያጸድቀው ለውሳኔ መምራቱ ታውቋል።

ከተለያዩ የካውንስሉ መስራች አባላት ከሆኑ ህብረቶችና ቤተ እምነቶች የተወጣጡ ተሳታፊዎች በተገኙበት በዚሁ መደበኛ ስብሰባ ከዚህ ቀደም የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በተመለከተ በአውሮፓ፥ በአፍሪካና በካሪቢያን ሀገራት መካከል የተደረገውን የሳሞዓ ስምምነት እንደሚቃወም ቦርዱ አበክሮ አስታውቋል። #ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/LxjvR-0KDAY
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
4👍1