#በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የደራይታ #አዲስ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ በጊዶሌ ከተማ በድምቀት ተመረቀ።
የትርጉም ሥራው ከ1996-2012 ዓ.ም በድምሩ 16 ዓመታት የወሰደው የደራይታ አዲስ ኪዳን የህትመት ሥራው ተጠናቆ በጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተመርቋል።
የደራሼ ማህበረሰብ ወንጌልን ካገኘ 75 ዓመታት ቢቆጠሩም መጽሐፍ ቅዱስን በአፍ መፍቻ ቋንቋው አላገኘም ነበር። የደራይታ አዲስ ኪዳን ተመርቆ ለምዕመናን መድረሱ አማኞች ያለ ምንም ችግር በልብ ቋንቋቸው የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ እና መስማት እንዲችሉ ያስችላል።
የትጉሙም ሂደቱ ብዙ አመታትን ከመፍጀቱ ባሻገር በቡዙ ፈተናዎች ውስጥ ማለፉን እና ለዚህ ውጤት በመድረሱ እግዚአብሔርን እንደሚያመሰግኑ የደራይታ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ቡድን መሪ ቄስ ሐታኖ ሐይቶሳ ገልፀዋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩም የቤተ ክርስቲያኒቱ የሚስዮን እና ቲኦሎጂ ዳይሬክተር ቄስ ዶ/ር ለሊሳ ዳንኤል፣ የደቡብ ምዕራብ ሲኖዶስ ፕሬዚደንት እና ማኔጅመንት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱ የትርጉም አገልግሎት ብሄራዊና የክልል ማስተባበሪያ ቢሮ ባለሙያዎች፣ በፕሮጀክቱ በአጋርነት ሲሰሩ የነበሩ ተቋማት፣ የዞኑ የመግሥት ቢሮ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
መረጃዉን ከኢትዮዽያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ላይ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

👍5🙏5❤2🔥2