#ዜና_እረፍት
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን በዋና ጸሐፊነት የመሩት #ቄስ_ዓለሙ_ሼጣ ወደ ሚወዱትና ወዳገለገሉት አምላካቸው ተሰበሰቡ።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ የቲዮሎጂና ሚሽን መምሪያ ዳሬክተር እንዲሁም የቤተክርስቲያኒቱ የደቡብ ሲኖዶስ ፕሬዝዳንት በመሆን ያገለገሉት እንዲሁም የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረትን ከ1999 ዓ.ም እስከ ኅዳር 2008 ዓ.ም ለ9 አመታት በታማኝነትና በጥበብ በመምራት በብዙዎች ዘንድ ከበሬታን ያገኙት ቄስ አለሙ ሼጣ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የእግዚአብሔር ቃል በ1ኛ ተሰሎንቄ 4:14፤ "ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና" እንደሚል በጌታ ቀን እንደምናገኛቸው ተስፋ አለን::
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በወንድማችን እልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ፣ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸውና ለመላው ወንጌላውያን አማኞች መጽናናትን ይመኛል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://youtu.be/JH8xh0nRv8I
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

❤4👍3