የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.28K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በአሜሪካን ኮሎራዶ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የዉይይት እና የአንድነት ጊዜ አካሄደ።

ሚያዚያ 25 ቀን 2017ዓ/ም በተካሄደዉ የዉይይት መድረክ በኮሎራዶ የሚገኙ የካዉንስሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አመራሮች የቤተክርስቲያን መሪዎች እና ልዩ ልዩ የሚንስትሪ አገልጋዮች በዉይይት መድረኩ ተሳትፈዋል።

በኮሎራዶ የካዉንስሉ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ጌታቸው ታደሰ በእለቱ የእንኳን ደህና መጣቹ መልዕክት በማስተላለፍ የእግዚአብሔርን ቃል አካፍለዉ የካውንስሉ አመሰራረት እና ጠቃሚነቱን በመግለፅ አብራርተዋል።

የቅርንጫፍ ፅ/ቤቱን በዋና ፀሃፊነት እያገለገሉ የሚገኙት ዶ/ር አድያምሰገድ ወልደማርያም የካዉንስሉ አጠቃላይ እንቅስቃሴ ፥ ዓላማ ፥ ራዕይ እንዲሁም ቀጣይ ተግባራቶችን ለአባላቱ  በዘርዝር አቅርብዋል። ካዉንስሉ በአሜሪካ እና በአለም አቀፍ ሊሰሩ የታሰቡ ስራዎችን በማብራራት በኮሎራዶ ከሚገኙ አብያተክርስቲያናት እና ህብረት ጋር አሁንም ለመስራት ዝግጁ እንደ ሆኑ አስረድተዋል። በዚህም ከካውንስሉ ጋር በመተባበር አብረን ታላቁን ተልዕኮ በፍቅር እና በአንድነት እናገልግል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

መጋቢ ያሬድ ፀጋዬ ምክትል ዋና ፀሐፊ ሲሆኑ የካውንስሉ የትኩረት መስክ ፣ ሚዲያ ፣ የአባለት መብትና ግዴታ ዙሪያ በተመለከተ ማብራሪያ ሰተዋል።

በመጨረሻም ከአባል ቤተ እምነቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ሰፊ ማብራሪያ ተሰቶባቸዉ ስብሰባዉ ተጠናቋል።

#ሪፖርተር_ብንያም_ሱፋ

#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!
👍71