የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ይህንን_በማድረጋችን_ምንም_አንጎዳም_ምንም_አይጎድልብንም

ሰላም ቅዱሳን መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚናገረው "ባንዝል በጊዜው እናጭዳለን መልካምን ስራ ለመስራት አንታክት እንግዲያስ ግዚውን ካገኘን ደግሞ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሀይማኖት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ" ይላል።

የእግዚያብሄር ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ እና ሁኔታ ይፈልጋል። አሁን ይሄ ቃል አካል የሚይዝበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። እግዚያብሄር አምላክ መጽናናት እና መበርታትን ለመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እንደዚሁም ደግሞ ልጆቻቸውን ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ሁሉ እንዲሰጥ እንጸልያለን እንመኛለን።

መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ ለደረሰው የጎርፍ አደጋ ሁላችንም ቅዱሳን የሆንን ቤተሰቦች በአንድነት አብረናቸው ልንቆም መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደሚያዘው ልንተባበር ይገባል።

እኛ የወንጌል አማኞች በአንዱ የክርስቶስ እምነት ላይ የተመሰረትን በአንድነት ከሆንበት ከካውንስሉ ጀምሮ በህብረት አብረን ልንቆም ይገባናል።

እግዚያብሄር አምላክ ይሄንን መልካም እድል አምጥቶልናል። መልካም ስራችንን፤ መተባበራችንን፤ አንድነታችንንን እና እርስ በእርስ እንደ ወንድማማች የምንደጋገፍ እንደ አንድ ቤተሰብ የምንተያይበት ጊዜ መጥቷል።

በዚህ ሰዓት ከመካነ ኢየሱስ እና ሴሚናሪ አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው አካላት ጋር ልንቆም ይገባናል። የኛ ቤተክርስቲያን በዚህ ነገር ላይ ቀዳሚ ሆና ለመስራት የ100ሺህ ብር ድጋፍ ታደርጋለች።

እንዲሁም ደግሞ አዳማ (ናዝሬት) ላይ በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ ህዝቡን አስተባብረን የአንድ ቀን ገቢያችንን በመስጠት የምንችለውን እናደርጋለን። ይሄንን የምናደርገውን ልንነግራችሁ ሳይሆን የሁላችሁ ሃላፊነት እንደሆነ እና ከልባችሁ እንድትነሳሱ ስለምንፈልግ ነው።
#በአዲስ #አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስተባባሪነት #በኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ #ተዋህዶ #ቤተክርስቲያን #አዲስ አበባ ሃገረ ስብከት እና ጠቅላይ ቤተክህነት የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄደ።
ማክሰኞ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም “ትብብርና አብሮነትን ማጎልበት ለዘላቂ #ሰላም" በሚል #መሪ #ቃል በተካሄደው ጉብኝት #እና ምክክር ላይ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባላት አባቶች የተሳተፉበት ሲሆን በኢ/ኦ/ተዋሕዶ ቤ/ክ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የጉባኤው ቦርድ ሰብሳቢ ብጹዕ አቡነ ሄኖክ እና የሀገረ ስብከቱ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች መሪዎችን ተቀብለው አስተናግደዋል። በዚሁ የጉብኝት መርሐ ግብር ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል የዓለም አቀፍ ግኑኝነት ዳይሬክተር እና የአ/አ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አባል የሆኑት መጋቢ አሸብር ከተማ ተገኝተዋል።
ብጹዕነታቸው የቦርድ አባላቱን በጽ/ቤታቸው በተቀበሉበት ወቅት ወደ ታሪካዊው ሀገረ ስብከት እንኳን በሰላም መጣችሁ በማለት ሀገረ ስብከቱ ከምስረታው #ጀምሮ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ አገልግሎትን እየሰራ ይገኛል ያሉ ሲሆን #ይህ ጉብኝት አብሮነታችንን የሚያጠናክር በመሆኑ ሊቀጥል ይገባል በማለት እንግዶች በመምጣታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ #ዋና ጸሐፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው በሃይማኖቶች መካካል መቀራረብ፣ መተዋወቅ፣ መማማር እና መደጋገፍ አብሮነትን ይበልጥ የሚያጎለብት ሁነኛ መሳሪያ ነው። ያሉ ሲሆን ጉባኤው #ይህንን ጉብኝት ያዘጋጀው በሃይማኖቶች መካካል የሚኖረው መከባበር፣ ትብብር እና አብሮነትን ማጠናከር ለሃገራችንም ሆነ ለከተማችን ዘላቂ ሰላምና ልማት ያለው ፋይዳ #ትልቅ በመሆኑ ነው ብለዋል።
በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት የሊቀ ጳጳሱ ልዩ ጸሐፊ ሊቀ ሕሩያን #ዮሐንስ ቀኖ የሃገረ ስብከቱ መዋቅር ፤ #ከዚህ ቀደም የሰራቸውን ስራዎችን እና ሚሰራቸው ስራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።
በሃይማኖቶች መካካል የሚኖረው ትብብር እና አብሮነትን ማጠናከር አላማ ያደረገው የጉብኝት መረሃ ግብር መሰረት በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ የሚገኘውን ቤተመጽሐፍት ወመዘክር እንዲጎበኙ ተደርጓል።
የጉባኤያችን የቦርድ አመራር የሆኑ መሪዎች በጉብኝቱ እና ቤተክርስቲያኒቱ በመንፈሳዊ እና ማህበራዊ አገልግሎት ላይ እየሰራች ያለችውን ስራዎች በመመልከታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በሃይማኖት ተቋማት መከካል የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴቶቻቻንን ማጠናከር በመሆኑ በተቋማችን #ስራ አመራር ቦርድ ውሳኔ መሰረት ይህንን የአብሮነትና የወንድማማችነት እሴት ይበልጥ ለማጎልበት እንዲረዳ የአባል #ቤተ እምነቶቹ ጉብኝት የመጀመሪያ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በአዲስ አበባ #ከተማ #እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት የሚከወን ይሆናል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -https://youtu.be/eIQ2PeyOHN0
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!