የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.05K photos
131 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#ይህንን_በማድረጋችን_ምንም_አንጎዳም_ምንም_አይጎድልብንም

ሰላም ቅዱሳን መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደሚናገረው "ባንዝል በጊዜው እናጭዳለን መልካምን ስራ ለመስራት አንታክት እንግዲያስ ግዚውን ካገኘን ደግሞ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሀይማኖት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ" ይላል።

የእግዚያብሄር ቃል የሚፈጸምበት ጊዜ እና ሁኔታ ይፈልጋል። አሁን ይሄ ቃል አካል የሚይዝበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። እግዚያብሄር አምላክ መጽናናት እና መበርታትን ለመካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን እንደዚሁም ደግሞ ልጆቻቸውን ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ቤተሰቦች ሁሉ እንዲሰጥ እንጸልያለን እንመኛለን።

መካነ ኢየሱስ ሴሚናሪ ለደረሰው የጎርፍ አደጋ ሁላችንም ቅዱሳን የሆንን ቤተሰቦች በአንድነት አብረናቸው ልንቆም መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደሚያዘው ልንተባበር ይገባል።

እኛ የወንጌል አማኞች በአንዱ የክርስቶስ እምነት ላይ የተመሰረትን በአንድነት ከሆንበት ከካውንስሉ ጀምሮ በህብረት አብረን ልንቆም ይገባናል።

እግዚያብሄር አምላክ ይሄንን መልካም እድል አምጥቶልናል። መልካም ስራችንን፤ መተባበራችንን፤ አንድነታችንንን እና እርስ በእርስ እንደ ወንድማማች የምንደጋገፍ እንደ አንድ ቤተሰብ የምንተያይበት ጊዜ መጥቷል።

በዚህ ሰዓት ከመካነ ኢየሱስ እና ሴሚናሪ አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው አካላት ጋር ልንቆም ይገባናል። የኛ ቤተክርስቲያን በዚህ ነገር ላይ ቀዳሚ ሆና ለመስራት የ100ሺህ ብር ድጋፍ ታደርጋለች።

እንዲሁም ደግሞ አዳማ (ናዝሬት) ላይ በተዘጋጀው ኮንፍራንስ ላይ ህዝቡን አስተባብረን የአንድ ቀን ገቢያችንን በመስጠት የምንችለውን እናደርጋለን። ይሄንን የምናደርገውን ልንነግራችሁ ሳይሆን የሁላችሁ ሃላፊነት እንደሆነ እና ከልባችሁ እንድትነሳሱ ስለምንፈልግ ነው።