የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.69K subscribers
9.51K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
በዓለም አቀፍ የሚሽን ጉባኤ ላይ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በፕሬዚደንቷ መወከሏን አስታወቀች።

የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ጨመሮ የተለያዩ አለም አቀፍ አብያተክርስቲያናት በመስራች አባልነት በሚመሩት አለም አቀፍ የሚሽን ጉባኤ (International Mission Association/#IMA) አዘጋጅነት በማዕከላዊ አሜሪካ ሁንዱራስ ዋና ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ስብሰባ ላይ የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን በፕሬዚዳንቷ ተወክላለች።


በያዝነው ሳምንት በጀመረውና ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የተወጣጡ የቤተክርስቲያን መሪዎች በወንጌል አገልግሎት ዙሪያ እየመከሩ በሚገኙበት ስብሰባ ላይ የታደሙት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበ በጉባኤው የቤተክርስቲያኒቱን የወንጌል እንቅስቃሴ ልምድ ከማካፈል በተጨማሪ በሌሎች አለማት ያለውን የወንጌል ተልዕኮ አካሄድ ከስብሰባው ተሳታፊዎች ጋር የሚለዋወጡ ይሆናል።


ይህ ጉባኤ ለቤተክርስቲያኒቱ ልምድ ከመለዋወጥ ባሻገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሚኖራት የወንጌል ተጽዕኖ አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሎ ይታስባል።
መረጃውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ የማህበራዊ ሚድያ ገጽ ላይ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
5👍3
በናይጄሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ በተፈጸመ ጥቃት አማክኝነት 5 ክርስቲያኖች መገደላቸው ተገለጸ።

በሚሊየን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች የሚገኙባት ናይጂሪያ የክርስቲያኖች ግድያ የተመለደ እየሆነባት መጥቷል። አርብ ቀን በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ላይ በነበሩ አማኞች ላይ በደረሰ ጥቃት አማካኝነት 5 ክርስቲያኖች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን 3 ሰዎች ደግሞ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በሰሜን ምስራቃዊዋ የናይጄሪያ ግዛት ካዱና ወደ 110 የሚጠጉ ክርስቲያኖች ታግተዋል።


በካጁር አውራጃ ቪክቶር ዊኒንግ ኦል የተሰኘች ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ላይ በፉላኒ ታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት አማካኝነት ነው በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና በጸሎት ላይ የነበሩ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት የተፈጸመው።በካጁሪ አውራጃ በተፈጸመ ጥቃት ምክንያት ከታገቱት ሰዎች መካከል የማህበረሰብ መሪዎች የሚገኙበት ሲሆን እገታው የሚደረገውም ብዙ የወንጌል አማኞች በሚገኙባቸው መንደሮች ላይ ነው።

በናይጄሪያ እና በሳሄል ቀጠና በሚሊይን የሚቆጠሩ እና የእስልምና እምነት የሚከተሉ ፉላኒዎች የሚገኙ ሲሆን አብዛዎቹ ፉላኒዎች ጽንፈኛ አቋምን የሚያራምዱ አይደሉም፡ ሆኖም እንዳንድ የፉላኒ ጎሳዎች ጽንፈኛ የሆነ ሐይማኖተኝነትን የሚያራምዱ መሆናቸውን ዓለም አቀፍ የክርስቲያኖች መብት ተሟጋቾች ይጠቅሳሉ።


በናይጄሪያ የሚገኙ ክርስቲያን መሪዎች በሀገሪቱ ማዕከላዊ ክፍል ላይ ክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ጥቃት የክርስቲያኖችን መሬትን መንጠቅን ያለመ ነው በማለት ይሞግታሉ፤ ለዚህም እንደ ምክንያት ሚነሳው የፉላኒ ታጣቂዎች የያዙት ቦታ በበረሀማነት አማካኝነት ለከብቶቻቸው የማይመች እየሆነ መምጣቱ ነው።
በዚህ እና ተያያዥ ምክንያቶችም በዓለማችን ላይ በዓመት ክርስቲያን በመሆናቸው ምክንያት ከሚገደሉ ሰዎች 69 በመቶ የሚሆኑት ሕይወታቸው የሚያልፈው በናይጄሪያ ነው።

በደቡባዊ ናይጄሪያም ለክርስቲያኖች አስጊ የሆኑ ጽንፈኛ ቡድኖች ብቅ ማለት መጀመራቸውን ተከትሎ በሰሜናዊ ናይጂሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች እያስተናገዱ ያሉት ጥቃት በደቡብ ናይጄርያ ላሉትም ስጋትን መጫሩ አልቀርም።
መረጃውን ከክርስቲያን ቱዴይ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
2
የአውሮፓ ሕብረት ፓርላማ በሶሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች አስፈላጊው የሆነ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ጥሪውን አቀረበ።

የአውሮፓ ሕብረት በሶሪያ የሚገኙ ክርስቲያኖች እና ሌሎች አናሳ የማህበረሰብ ክፍሎች የበለጠ ጥበቃ እንዲደረግላቸው አስቸኳይ ጥሪ አቅርቧል።

የቀረበው ጥሪም በማር ኤሊያስ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የደረሰው የአጥፍቶ ማጥፋት የሽብር ጥቃት ያወገዘ ነበር። በማር ኤሊያስ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የሽብር ጥቃት አማካኝነት 25 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል።

ግኝቱ ከአልቃይዳ የሆነው ኤችቲኤስ ሳሪያን በመምራት ላይ የሚገኝ ሲሆን ምንም እንኳን መገኛው አልቃይዳ ቢሆንም በሳሪያ ውስጥ የሀያማኖት እኩልነትን እንደሚያከበር ሲናገር ቆይቷል።


በአውሮፓ ህብረት የቀረበው ጥሪም የሶሪያ መንግስት የማር ኤሊያስ ቤተ ክርስቲያን እንደገና መገንባቱን እንዲያረጋግጥ የሚጠይቅ ነው።
መረጃውን ከክርስቲያን ቱዴይ አገኝነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፡ አማኑኤል ዴቢሶ
👍2
በሱዳን ቤተ ክርስቲያኖች ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት አማካኝነት 5 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።


በባለፈው ወር በሶስት ቤተ ክርስቲያኖች ላይ በደረሰ የአየር ጥቃት አማካኝነት የ5 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ብዙዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን በያዝነው ሳምንት ይፋ አድርጓል።

የክርስቲያን ሶሊዳሪቱ ወርልድ ዋይድ ፕሬዚደንት የሆኑት መርቪን ቶማስ በቤተ ክርስቲያናቱ ላይ የደረሰው ጥቃት በህንጻዎች ላይ ብቻ የደረሰ ጥቃት ሳይሆን በእምነት ነጻነት ላይ የተደረገ ግፍ ነው።” በማለት ገልጸውታል። “በኤል ፋሸር 3 ቤተ ክርስቲያናት ላይ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን… የአርኤስኤፍ አላማ የቤተ ክርስቲያኖችን ህንጻ እንደ ወታደራዊ ጣቢያ መጠቀም እና አረባውያን ያልሆኑ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ማድረስ ነው።” ሲሉም አክለዋል።


የሰሜዊ ዳርፉር ዋና ከተማ የሆነችው ኤል ፋሸር በሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ የሆነ ውጊያ ሲካሄድባት የቆየች ቦታ ነች። እናም በከተማው የሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት በታሪክ ውስጥ እንደ ማምልኪያ ቦታ ብቻ ሳይሆን በጦርነት እና ግጭት ጊዜም እንደ መጠለያነት በማገልግላቸው ይታወቃሉ።


ይህም አገልግሎታቸው ነው በቤተ ክርስቲያናቱ ላይ የደረሰውን ጥቃት የበለጠ አስከፊ የሚያደርገው።


መረጃውን ከፐርስኪውሽን ዶት ኦርግ አገኘነው።

ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ አማኑኤል ዴቢሶ
7😢6🙏5