በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የተመራ ልዑክ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር መምከር ጀመረ ።
በኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተመራ የልዑካን ቡድን ወደ ትግራይ ክልል መቐለ አምርቶ፤ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ጋር መወያየት ጀምሯል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሁለት ሳምንት በፊት በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት፤ "በክልሉ ግጭት የሚጀመር ከሆነ ከዚህ በፊት ከምናውቀውም በላይ የከፋ በመሆኑ አስቀድሞ ማስቆም ያስፈልጋል" ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፤ “የሁሉም እምነት አባቶች በፍጥነት ትግራይ ወደ ግጭት፣ ወደ ጦርነት እንዳይገባ ሥራችሁን አሁን ጀምሩ፣ ከተጀመረ ወዲያ ብትናገሩ ዋጋ የለውም" ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ስለሆነም የኃይማኖት አባቶች፣ ምሁራን፣ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎችና ሌሎችም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ትግራይ ክልል ወደ ግጭት እንዳይገባ በፍጥነት ሥራ እንዲጀምሩ ጠይቀው ነበር፡፡
ይህንንም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ተከትሎ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከትግራይ ክልል ከተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች ተወካዮች ጋር በጋር በመሆን፤ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጋር መምከር መጀመራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፡፡
በጉባኤውም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚዳንትና ዶ/ር ጣሰው ገብሬ እና የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሀፊ ቄስ ደረጄ ጀንበሩ ተሳትፈዋል፡፡
ለኢቫንጀሊካል ቲቪ ፤ ቤተልሔም ደረጄ

❤1
ኢንተርናሽናል ባይብል ቲኦሎጂ ኮሌጅ በድግሪ መርሃ ግብር ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመረቀ ።
ሐምሌ 6 /2017 ዓ.ም ኢንተርናሽናል ባይብል ቲዮሎጂ ኮሌጅ በዲግሪ መርሃ ግብር ያሰተማራቸውን 15 ተማሪዎችን በህያው ድምጽ ቤ/ክ የ 14ኛ ዙር የምረቃ ሥነ-ሥርአት አካሄዷል ።
መርሃ ግብሩን የቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢ የሆኑት መጋቢ አሊ ከማል ፀሎት በማድረግ ያስጀመሩ ሲሆን ቃለ እግዚአብሔርንም በቤተ ክርስቲያኒቱ መጋቢ በኩል ዘመኑ አጭር ነው በሚል ርዕስ ያካፈሉ ሲሆን የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘማሪያን በአምልኮ አገልግለዋል ።
የምረቃት ስነ-ስርዓቱም የኮሌጁ ዲን በሆኑት በወንድም ገነት ቲርካሶ የተጀመረ ሲሆን ለጉባኤው እና ለተመራቂዎች የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አስተላልፈው የኮሌጁን ሪፖርት አቅርበዋል ። በንግግራቸውም ላይ ኢንተርናሽናል ባይብል ቲኦሎጂ ኮሌጅ በ2005 ዓ.ም በወንጌላዊ ተረፈ ጫኪሶ ባለራዕይነት እንደተጀመረ ያነሱ ሲሆን እስካሁን ድረስ በተለያዩ ከተሞች ቅርጫፎችን ከፍቶ በርካታ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ይገኛል ብለዋል ።
በምረቃ ሥነ -ሥራዓቱ ላይ የተማሪዎች ተወካይ የሆኑት ወንድም ጥበቡ ተሾመ ለዚህም ያበቃን ለክብሩም ያበቃን እግዚአብሔር ይመስገን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል እንዲሁም ኮሌጁንና ቤተ ክርስቲያኒቱን አመስግነዋል።
በመቀጠልም ለተመራቂ ተማሪዎች ሰርተፊኬት የመስጠት ሥነ-ሥርዓት የተደረገ ሲሆን ከፍተኛ ውጤት ለስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቷል ።