የኢትዮጵያ ቃ/ሕ/ቤ/ክ ልማት እና ሰብዓዊ ድጋፍ ኮሚሽን 1.6 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ የምግብ ዱቄትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ ለማሕበረሰብ አደረገ።
የኢትዮጵያ ቃ/ሕ/ቤ/ክ የሰብአዊ ድጋፍና ልማት ኮሚሽን 1.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ የምግብ ዱቄትና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በጸጋ ቃ/ሕ/ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተቀናጀ የልጆች እና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት ለተመረጡ የማህበርሰብ ክፍሎች ድጋፍ አድርጓል።
በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በፀጋ ቃለ ሕይወት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተቀናጀ የልጆች እና ወጣቶች ልማት ፕሮጀክት ዳይሬክተር ዶክተር አስቴር ነጋ ጥበብ ቤተ ክርስቲያኒቱ ላለፉት 28 ዓመታት በዚህ ፕሮጀክት በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ልጆችንና ቤተሰቦችን ስትደግፍ መቆየቷን ገልጸዋል ፡፡
የተደረገው የድጋፍ አይነትም 25 ኪ.ግ የምግብ ዱቄት፣ 5 ሊትር ዛይት፣ የሴቶች የንጹህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ያጠቃለለ ሲሆን 217 ቤተሰቦችም ድጋፉ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።
ባለፉት 28 ዓመታት በተሰሩ ስራዎች በርካታ ልጆች በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ተሰማረተው ለአገር እና ለቤተ ክርስቲያን እድገት የበኩላቸውን አስተዋጾ እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ዶክተር አስቴር በዓመት 6 ሚሊዮን ብር በመመደብ ልጆች በአምሮአዊ ፣በመንፈሳዊ እና በማህበራዊ ሕይወታቸው የበቁ እና ያደጉ እንዲሆኑ ፕሮጀክቱ አጠንክሮ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
የዚህ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ከኮምፓሽን ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የተገኘ ሲሆን በልማት ኮሚሽኑ አመራር ሰጭነት በጸጋ ቃ/ሕ/ አጥቢያ ቤተክርስቲያን እየተሰራ ያለ ፕሮጀክት መሆኑ ተገልጿል።

❤6
በኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የደቡብ ምስራቅ አዲስ አበባ እና አካባቢው ክልል የልጆች አስተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ።
ሰኔ 21/2017 ዓ.ም በገርጂ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ በተካሄደው ስልጠና ላይ በክልሉ ከሚገኙ 98 አጥቢያዎች የተወጣጡ 350 የልጆች አስተማሪዎች ተገኝተዋል።
የዝማሬ እና የጸሎት ጊዜ የተደረገ ሲሆን ነብይ ብስራት የእግዚአብሔር ቃል በማቅረብ ጸሎት አድርገዋል።
በመቀጠልም የክልሉ የወጣቶቸ አገልግሎት ክፍል ሀላፊ የሆኑት መጋቢ ኤልያስ አየለ አዲሱ የልጆች ማስተማርያ መጸሃፍ ጠቃሚነቱን አጽንኦት በመስጠት በመናገር በቀጣይ ክልሉ በልጆች አገልግሎት ላይ ሊያከናውናቸው የታሰበውን ተናግረዋል።
መረጃው የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ነው።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!

❤9👍6
በኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ዘንድ የመጀመሪያው የሆነው "አውነት እና ፍቅር" የተሰኘው ትያትር ተመረቀ።
ሰኔ 29/2017 ዓ.ም በፕሮቪዥን ፈልሞች የተዘጋጀው "እውነት እና ፍቅር " ትያትር በቫምዱስ ሲኒማ ተመርቋል።
የትያትሩ ደራሲና ዳይሬክተር ሄኖክ በቀለ “በኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች ዘንድ እንደዚህ አይነት ስራ አልተለመደም።” ያሉ ሲሆን ይህ የመጀመሪያ ቢሆንም ከዚህ በኋላ ብዙ ስራዎችን በትያትር መልኩ ለመስራት እንዳቀዱ ተናግረዋል ።
እውነት እና ፍቅር እውነትን በቀጥታ መናገርና ፍቅርን መስጠት ላይ የሚያተኩር ሆኖ በሁለቱ መሀል ያለውን ውዝግብ የሚያሳይ እንደሆነ ደራሲው ገልጿል።
ትያትሩ 55 ደቃቅ ርዝመት የለው ሲሆን በዚህ ትያትር ላይ 4 ዋና ዋና ተዋናዮችና በረካታ ሰዎች በስራው ላይ ተሳትፈዋል ።"በእውነት እና ፍቅር" ትያትር ላይ ለተሳተፉት በሙሉ ያውቅና ሰርተፍኬት ተሰቷቸዋል።
ፕሮቪዥን ፈልሞች ላለፉት ሁለት ዓመታት በጂዶ-ክርስቲያናዊ የሥነ-ምግባር ዕሴት ላይ ታንጾ በጥበብ ዘርፍ እየሠራ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን የተቋቋመውም በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት አባል ከሆኑ ቤተ ዕምነት የተወጣጡ የትያትር፣የሚድያ እና የፊልም ባለሙያዎች መሆኑ ተገልጿል።
በዚህ የምረቃ መርሐግብር ላይ አርቲስቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። በቀጣይም በየሳምንቱ በሻምዱስ የምታይ መሆኑ ተገልጿል።

❤25👍10
አባካኙ ልጅ የተሰኘው ሙዚቃዊ ፊልም በሸራተን አዲስ ለእይታ ቀረበ።
በዘማሪ ቤተልሔም ተዘራ የተዘጋጀው እና የተለያዩ ዘማሪዎችን ያካተተው ሙዚቃዊ ድራማ በሸራተን አዲስ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ በቅቷል።
መርሃ ግብሩን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሐፊ የሆኑት ቄስ ደረጄ ጀምበሩ በጸሎት እና በንግግር የከፈቱ ሲሆን በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜዎች በወንጌል አማኞች ዘንድ በአመራርነት ያገለገሉ አገልጋዮች እንዲሁም ዘማሪዎች በስፍራው ተገኝተው ነበር።
ዘማሪት ሕሊና ዳዊት፣ መስፍን ጉቱ ፣ መጋቢ እንዳለ ወልደጊዮርጊስ፣ ዘማሪ ገዛኸኝ ሙሴ እና ሌሎችም ዘማሪዎች በስፍራ በመገኘት ጉባኤው በዝማሬ መርተዋል።
የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች ሙዚቀኞች እና ዘማሪዎች ማህበር ሰብሳቢ የሆኑት አገልጋይ ረታ ጳውሎስም የዘማሪት ቤተልሔም ተዘራን የዝማሬ አገልግሎት እና አባካኙ ልጅ የተሰኘውን ሙዚቃዊ ድራማ አስመልክቶ ሙያዊ ዳሰሳ አቅርበዋል።
ባቀረቡትም ሙያዊ ዳሰሳ ዘማሪት ቤተ ልሔም ተዘራ በዜማ ድርሰት፣ በመዝሙር ጭብጥ እና በስነ ጽሁፋዊ ውበት የተዋጣላቸውን ዝማሬዎች እንዳደረሰች የተናገሩ ሲሆን ለእያንዳንዱ ዝማሬዎች የከፈለችውን ዋጋ አድንቀዋል።
የዘማሪት ቤተልሔም ተዘራን አጠቃላይ የዝማሬ ጉዞን አስመልክቶም አጠር ያለ ዶክመንተሪ ለእይታ ቀርቧል።
ከዚህም በተጨማሪ በአገልጋይ መንግስተ አብ የሚመራው የሊቪንግ ዊትነስ አገልግሎት ራዕይ የማካፈል መርሃ ግብር ተካሄዷል።
የእግዚአብሔርን ቃል ያካፈሉት ቄስ ትዕግስቱ ሲሆኑ 2ኛ ሳሙኤል 14:14 ላይ የሚገኘውን ቃል በማንሳት እግዚአብሔር በሰዎች መጥፋት ደስተኛ እንዳልነ እና በምክሩ እንደሚያስብ የተናገሩ ሲሆን እኛም ለሰዎች እንደዚህ አይነት ልብ ሊኖረን እንደሚገባ ተናግረዋል።
በመልካም ስራችን ለምድራችን ብርሃን እና ጨው መሆን ይጠበቅብናል በማለተ የተናገሩት አገልጋይ መንግስተዓብ እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚገባንን ነገር ከማድረግ በመቆጠባችን አማካኝነት በብዙ ወደ ኋላ ቀርተናል በማለት የተናገሩ ሲሆን ሁሉም አማኝ በጋራ ርብርብ በማድረግ በሃገራችን ለሚገኙ ደሆች እና አቅመ ደካሞች ማድረግ የሚቻለውን ነገር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
በሀገራችን እንዲሁም በወንጌል አማኞች ዘንድ በትልልቅ የአመራር ስፍራዎች ላይ በማገልግል ላደረጉት አስተዋጽዖ የምናውቃቸው ጋሽ ሽፈራው ወልደ ሚካኤል የሙሴን ታሪክ በማንሳት ከሚያለቅስ ሕጻን መሪ እናውጣ የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አባካኙ ልጅ የተሰኘው ሙዚቃዊ ፊልምም ለእይታ ቀርቧል።
በፕሮግራሙ ላይም የሊቪንግ ዊትነስ አገልግሎትን ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም የተደረገ ሲሆን ከዛም በኋላ በጋራ በተደረገ አምልኮ ተጠናቋል።

❤8👍1