የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.58K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከየካቲት_10_13_2017 ዓ.ም ለሁለት መቶ የሰንበት አስተማሪዎች በልጆች አገልግሎት ጉዳይ ላይ ሰጠ።
ከቢሊግራሃም እቫንጀልስቲክ አሶሴሽን እህት ድርጅት ከሆነው ሰማሪታን ፐርስ የተባለው ተቋም አንድ ዘርፍ የለው ሲሆን በዚህም ልጆችን መሰራት አድረጎ የሚሰራ ተቋም ነው።
የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከኦሲሲ ኦፕሬሽን ክሪስማስ ቻይልድ፣ ከዚህ ድርጅት ጋር በጣም በቅርበት እየሰራ ሲሆን በቅርቡ በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል በተለይም በጦርነት የተጎዱትን ልጆች በጥቂቱም ቢሆን ያላቸውን መጎዳት ሊቀርፍላቸው ይችላል ብለው በማመን ሁለት ኮንቴይነር የስጦታ እቃዎች ወደ ኢትዮጵያ ገብቶአል፡፡
ይህንን ስጦታ አስመልክቶ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለሆኑቱ የካቲት 7 ለ52 የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የቁርስ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በዛ ላይ ስለፕሮግራም መግለጫ ተሰቶዋል፡፡
ከየካቲት 10_ 13 በአጠቃላይ ለሁለት መቶ የሰንበት አስተማሪዎች በልጆች አገልግሎት ጉዳይ ላይ ከዚህ ተቋም ከዩጋንዳ ፣ከኬንያ እና ከብሩንዲ የመጡ አሰልጠኞች ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
እነዚህ ስልጠናዎች በጉዲና ቱምሳ፣ በሀያት የጉባዔ እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያንና ፣በኮልፌ መካነ ኢየሱስ ተሰቶዋል፡፡ አጠቃላይ በዚህ ስልጠና ሁለት መቶ ያህል የሰንበት አስተማሪዎች ከመቶ ዘጠና አከባቢ የመጡ የሰንበት አስተማሪዎች ስልጠናውን መካፈል ችለዋል፡፡
4👍3🙏1
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
#የኢትዮዽያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_ከየካቲት_10_13_2017 ዓ.ም ለሁለት መቶ የሰንበት አስተማሪዎች በልጆች አገልግሎት ጉዳይ ላይ ሰጠ። ከቢሊግራሃም እቫንጀልስቲክ አሶሴሽን እህት ድርጅት ከሆነው ሰማሪታን ፐርስ የተባለው ተቋም አንድ ዘርፍ የለው ሲሆን በዚህም ልጆችን መሰራት አድረጎ የሚሰራ ተቋም ነው። የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል ከኦሲሲ ኦፕሬሽን…
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ጠቅላይ ፀሐፊ ቄስ ደረጀ በመገኘት እየተሰራ የለውን ስራ አድንቀው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ይህንኑ ስልጠና በሰሜኑ ህገራችን ክፍል እንደግመዋለን ብለን እናስባለን ፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን በሚቀጥሉት አመታት ከዚሁ ተቋም ጋር ተመሳሳይ ስራዎችን እንሰራለን ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡
እንደሚታወቀው የዚህ የልጆች አገልግሎት ጉዳይ በጣም ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ እና በተቻለ መጠን ቅድሚያ መሰጠቱ ብቻ ሳይሆን በብዙ መልኩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ አገልግሎት እንደሆነ ካውንስሉ ያምናል በዚህ መልክ የልጆች አስተማሪዎችን በማሰልጠናችን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡
ቤተ እምነቶቻችን አጥቢያ ቤተ ክርስቲያኖቻችን ልከው ያሰለጠኗቸውን የሰንበት አስተማሪዎች በሚገባ ይጠቀሙባቸዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ሲሉ የኢትዮዽያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል የውጪ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ መጋቢ አሸብር ከተማ ገልጸዋል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍4🙏2
#መለኮታዊ_ጉብኝት_ለኢትዮጵያ
የቢሊግርሃም ኢቫንጀሊስቲክ አሶሴሽን ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልና ጋር በመተባበር የቢሊ ግራሃም ልጅ ሬቭረንድ ፍራንክሊን ግራሃም ያገለግላሉ
የተለያዩ ዘማሪዎች ከሀገር ውስጥ ከሀገር ውጪ የመጡ አገልጋዮችም በዝማሬ ያገለግላሉ የካቲት 29 - 30 በመስቀል አደባባ አይቀርም ።
👍107
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_የኢትዮጵያ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_አባል_ሆነ፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሲያካሂደው የነበረውን ተቋማዊ ሪፎርም በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር በከፍተኛ ሁኔታ የሚረዳውን የተቋማዊ የዳሰሳ ጥናት እና የጉባኤውን መተዳደርያ ደንብ የማሻሻል ሥራ እንዲያካሂድ የተሰጠውን ኃላፊነት መሰረት በማድረግ ከአንድ ዓመት በላይ ሲዘጋጅ የነበረውን የተቋማዊ ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት እና ለሶስተኛ ጊዜ ማሻሻያ የተደረገበትን የጉባኤውን ረቂቅ መተዳደርያ ደንብ በካፒታል ሆቴል ለኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላላ ጉባኤ አባለት አቅርቧል፡፡
የተቋሙ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት የቀረበላቸውን ሪፖርት እና የማሻሻያ ሰነዶች በጥልቀት ከገመገሙ እና ሰፊ ውይይት ካደረጉ በኋላ በሰነዶቹ ላይ መካተት ያለባቸውን ተጫማሪ ሃሳቦች እንዲካተቱ በማድረግ ሁለቱንም ሰነዶች አፅድቀዋል፡፡
ጉባኤውም በዋናነት የሚከተሉትን ሶስት ዋና ዋና ውሳኔዎች በጋራ አስተላልፏል፡፡
👍52
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካዉንስል_የኢትዮጵያ_የሃይማኖት_ተቋማት_ጉባኤ_አባል_ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሲያካሂደው የነበረውን ተቋማዊ ሪፎርም በተሳካ ሁኔታ ለመተግበር በከፍተኛ ሁኔታ የሚረዳውን የተቋማዊ የዳሰሳ ጥናት እና የጉባኤውን መተዳደርያ ደንብ የማሻሻል ሥራ እንዲያካሂድ የተሰጠውን ኃላፊነት መሰረት በማድረግ ከአንድ ዓመት በላይ ሲዘጋጅ የነበረውን የተቋማዊ…
1. የጉባኤው አባል የነበሩት ሰባት የሃይማኖት ተቋማት ቁጥር ከሰባት ወደ አምስት እንዲቀንስ በማድረግ እና የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስልን የጉባኤው አባል በማድረግ የአደረጃጀት ለውጥ እንዲደረግ ከመወሰኑም ባለፍ ጉባኤው ይበልጥ አካታች የሚሆንበት አሰራር እንዲዘረጋ ከውሳኔ ላይ ደርሷል፤
2. ጉባኤው ለሕዝብ የሚሰጠውን አገልግሎት ይበልጥ ማስፋት ይቻል ዘንድ የራሱ የሆነ የልማት ክፍል በማደራጀት በሰብአዊ ድጋፍ እና በልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች ላይ በስፋት እንዲሳተፍ የሚያስችለውን አሰራር ተግባርዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ውስኗል፡፡
3. ለሶስተኛ ጊዜ ተሻሽሎ የቀረበውን የመተዳደርያ ደንብ በማጽደቅ የጉባኤው ጠቅላይ ጸሐፊ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለተጨማሪ አምስት ዓመታት ጉባኤውን በጠቅላይ ጸሐፊነት እንዲያገለግሉ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
በፀደቀዉ ደንብ መሰረት
. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
. የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት
. የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን
. የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካዉንስል
. የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን
በአባልነት እንደሚይዝ ደንቡ የሚጠቅስ ሲሆን ከዚህ ቀደም የጉባኤው አባል የነበሩ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ፣ የኢትዮጵያ ቃለሕይወት ቤተክርስቲያን እና የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስ በካዉንስሉ እንደሚወከሉ ተጠቅሷል።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
17👍10🙏7