የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ ግሬት ኮሚሽን የእግዚአብሔር መንግሰት ዜግነት እና የወንጌል አማኝ ተልዕኮ በዓለም ዓቀፋዊና አገራዊ አውድ በሚል ርዕሰ ለ8ኛ ዙር በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የመሪዎች ስልጠና እየተካሄደ ነው ።

ጥር 20/2017/ ዓ.ም የኢትዮጵያ ግሬት ኮሚሽን የእግዚአብሔር መንግት ዜግነት እና የወንጌል አማኝ ተልዕኮ በዓለም ዓቀፋዊና አገራዊ አውድ በሚል ርዕሰ በቀጠና ሁለት ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን የመሪዎች ስልጠና ተሰጠ።የዚህ ስልጠና አላማ የእግዚአብሔር መንግስት ትምጣ የሚል እንደሆነ የግሬት ኮሚሸን ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ አልታዬ ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ በመክፈቻው ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም የኢትዮጵያ ትልቅ ተስፋ የእግዚአብሔር መንግስት መምጣት ነው የቤተክርስቲያን መሪዎች በዚህ ላይ ትኩረት ሰታቹ ልትሰሩይገባል ሲሉ አጽንኦት ስተዋል ።የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል በሀገርና ከሀገር ወጪ እየሰራ የለውን ስራ በመግለፅ ወንጌልን እንኑረው በሁሉም ስፍራ እንግለጠው ሰሉ ገልጸዋል በማስከተልም የኢትዮጵያ ግሬት ኮሚሸን ከአብያተክርስቲያናት ጋር በመሆን እየሰራ ስላለው ስራ አመስግነዋል ።
በዚህ ስልጠና ከአዲስ አበባና ከሸገር አከባቢ ከተለያዩ ክፍለ ሀገራት የመጡ መሪዎችና ተጋባዥ እንግዶች በስልጠናው ላይ እየተሳተፉ ነው።በግሬት ኮሚሽን የተዘጋጀው ይህ ስለጠና እስከ ጥር 22 ቀን /2017 ዓ.ም የሚቀጥል እንደሆነ በመርሐግብሩ ላይ ተገልጸዋል ።


#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
6👍3🙏1
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_ከኢትዮጵያ_መጸሐፍ_ቅዱስ_ማህበር_ጋር_በመተባበር_በኢትዮጵያ_ዘላቂ_ሰላም_ጉደይ_ላይ_የተዘጋጀ_አውደ_ጥናት_ተካሄደ

ጥር 16 ቀን 2017/ ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ከኢትዮጵያ መጸሐፍ ቅዱስ ማህበር ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ጉደይ ላይ የተዘጋጀ አውደ ጥናት በስካይላይት ሆቴል የተካሄደ ሲሆን የካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፊ ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እስኪ መጣ ድረስ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል ስራውን ይቀጥላል ሲሉ ገልፀው በሀገር ደረጃ የኢትዮጵያ መጸሐፍ ቅዱስ ማህበር እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀው ልባዊ ምስጋናቸውን ገልጸዋል ።


ቀሲስ ሊቅ ትጉዋን ይልማ ጌታሁን የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር በሀገር ደረጃ በሰላም ዙሪያ ምን አይነት ተጽእኖ እየፈጠረን ነው ብለን ልንጠይቅ ይገባል ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ።በዚህ መርሐግብር ላይ ከተለያዩ አብያተክርስቲያናት የተወከሉ መሪዎች በሰላም ዙሪያ ላይ እየሰራው የሚገኙት የልምድ ማካፈል ጊዜ አከናውነዋል።
በዶ/ር ሳምሶን እስጢፋኖስና በቄስ ዶ/ር ገለታ ሲሜሶ ቀጣይ አካሄዶችና እርምጃዎች ላይ ጠቃሚ አሳቦችን በማቅረብና ውይይት በማድረግ መርሐግብሩ በጸሎት ተጠናቋል ።



#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ -
https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦
https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :-
https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍43