የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል ECGBC
9.67K subscribers
9.61K photos
133 videos
1 file
1.55K links
ይህ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውስንል የቴሌግራም ቻናል ነው።

"ወንድሞች በህብረት ቢቀመጡ፤ እነሆ፤ መልካም ነው፤ እነሆም፤ ያማረ ነው።
Download Telegram
#የኢትዮጵያ_ወንጌል_አማኞች_አብያተክርስቲያናት_ካውንስል_46ኛው_የሥራ_አስፈጻሚ_ኮሚቴ_ስብሰባ_በጉዲና_ቱምሳ_ሁለገብ_ማሰልጠኛ_ማዕከል_ተካሄደ
ጥር 22 ቀን 2017/ዓ.ም የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል 46ኛው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ በጉዲና ቱምሳ ሁለገብ ማሰልጠኛ ማዕከል አካሄዶዋል። ቄስ ተሾመ አመኑ የአግዚአብሔር ቃል ያካፈሉ ሲሆን በካውንስሉ የተሰሩ የሥራ ሪፖርት ተደምጧል ።ከነዚህም መካከል የካውንስሉ የውጭ ግንኙነት መመሪያ ፣የታሪክ መጽሐፍ ዝግጅት ኮሚቴ ፣የመጽሐፍ ቅዱስ ይዘት ኮሚቴ እና የልጆች ፌሰቲሻል ፕሮግራምን በተመለከተ በነዚህ ርዕሰ ጉዳዬች ሪፖርት ቀርቦዋል።
የካቲት 29-30 ካውንስሉ ከቢሊግርሃም ኢሻንጀልስቲክ አሶሴሽን ጋር በመተባበር በመስቀል አደባባይ ያዘጋጀውን ፕሮግራም በሚመለከት አስካሁን የተሰሩትንና ልሰሩ በሚገባቸው ጉደይ ላይ ውይይት ተደርጓል ።የበዓለ ሃምሳ ቀን አከባበር በኢትዮጵያ ቅድመ ዝግጅትን አስመልክቶ ትልቅ የሆነ ውይይት እና አቅጣጫዎች ተቀምጦአል ።
በዚህ ስብሰባ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አሳቦች የተነሱ ሲሆን በካውንስሉ ፕሬዚዳንት ጣሰው ገብሬ(ዶ/ር) ፣በምክትል ፕሬዚዳንት ሐዋርያው ዮሐንስ ግርማ እና በካውንስሉ ጠቅላይ ጸሐፈ ደረጀ ጀምበሩ ምላሽ ተሰጥቶበታል ።ቀጣይ የቦርድ እና የጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ቀን በመወሰን ተጠናቋል ።
#ለበለጠ_መረጃ
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/EGBCC/
ዩትዩብ፡ - https://www.youtube.com/@ethiopiancouncilgospelbeli4732
ቴሌግራም፦ https://tttttt.me/EGBCC
tiktok :- https://www.tiktok.com/@evangelical_tv
ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!
👍2