Yismake Worku
20.6K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
እጅግ አምርሬ አዘንኩ:: የእኔ "ሸምጋይ"፣ አርቲስት ሰሎሞን ዓለሙ እንዳረፈ ሰማሁ:: እጅግ የሀሳብ ሰው ነበር:: የእኔን እና የእርሱን ወዳጅነት የሚያውቅ ያውቀዋል:: እኔ ደግሞ ተከራካሪ ነበርኩ:: እኔን ለማስረዳት የማይፈነቅለው ድንጋይ አልነበረም:: የማያስበው ሀሳብ አልነበረም:: ግን ነገሮቹ አልመቻችለት ብለው ነው እንጂ በቴአትር መልክ ሀሳቦቹን ለመፃፍ ሀሳብ ነበረው::

እንዲያውም "ሸምጋይ" የሚለውን ተከታታይ ድራማ ወደ ልብ ወለድ ለመቀየር ሀሳብ ነበረን:: እርሱ "ሸምጋይ" ይባል ሲለኝ እኔ ደግሞ በ "አብዬ ዘርጋው" ስም ይታተም ስንል ገና መፅሀፉ ሳይፃፍ በርዕሱ ስንከራከር ነበር:: "ሸምጋይ" ድራማ በአንድ ተደጉሶ እንደተቀመጠ ነግሮኝ ነበር:: የጥበብ ሰዎች ሆይ ስለዚህ ፈልጉና ቢያንስ በልቦለድ መልኩ ባይሆን እንኳ በድራማ መልክ አሳትሙለትና የስሙ መጠሪያ ይሁን:: ሀዘኔ የፀና ነው:: ነፍስህን በአፀደ ገነት ያሳርፍልን::


@yismakeworku
😢127👍58
"አዱሬን ሌንጫ ፎገርቴ" 😍

ROPHNAN

ትርጉም: ድመት አንበሳን ፎገረች
180👍73🔥17👎12😢2
በድጋሚ በሴቶች ማራቶን ወርቅ አግኝተናል።

እንኳን ደስ አለሽ ኢትዮጵያ
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
88👍48🔥2
ብቸኝነት ከተሰማችሁ ይሄን አንብቡት ⬇️ አልያም ደሞ ብቸኝነት ለሚሰማው ወዳጃችሁ "ሼር" አድርጉለት።

ብቸኝነት ሲሰማህ ማሰብ ከቻልክ የአሳብህ ጓደኛ ነህ። ማሰብ ካልቻልክ ብቻህን ነህ። መነጠል የስጋ ሳይሆን የአሳብ ስሜት ነው። ብቸኝነትህን አሳብህ ሲጋራ የአሳብ ጓደኛ አለህ። ብቸኝነትም ጓደኝነትም ስጋ አይደለም። የአብሮነትና የመነጠል ስሜት ነው።
ከሰው ጋር ስትሆን ለብቻህ እንደሆንክ ከተሰማህ በግርግር መሀል ብቸኛ ነህ። በስጋህ ብቻህን ሆነህ ከአሳብህ ጋር አብረህ ከሆንክ አንተማ ጓደኛ አለህ። ከቻልክ የወዳጅ አስፈላጊነትን ቀንስ። ሰው ብታጣም ያጣኸው ስጋ ነው። አብሮህ የሆነ አላቂ ነው። ዛሬ የሚቀርብህ ነገ የሚርቅ ነው። ወሳኙ ጉዳይ ህሊናህን አለማጣትህ ነው። የሌላ ስጋ ሲለይ አሳብህ ካንተ ጋር ነው።
.
መለየት የስጋ ነው። ብቻህን እንዳልሆንክ ከተሰማህ የአንተ ጓደኛ ስሜትህ ነው።
@yismakeworku
115👍65😢9🥰2👏2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ልጆች እና መጻሕፍት ምን እና ምን ናቸው?

@yismakeworku
210👍66🔥13🥰3👏2
የጥቅምት መስክ ነኝ !!
(በእውቀቱ ስዩም)

ሰው ለሰው ይፈርዳል
ልብን ዘልቆ ሳያይ
ላልቃሽ እያዘነ
በፈካ ገፅ ውስጥ ያደፈጠን ስቃይ
-ማነው የመዘነ?
የይስሙላም ይሁን: ከልብ ያለቀሰ
አያጣም አይዞህ ባይ
ካንጀት ይሁን ካንገት : እንባ ላፈሰሰ
አይጠፋም ከምንገድ : መሀረብ አቀባይ
ይብላኝ ላሳሳች ፊት: አፅናኝ ለማይጋብዝ
አንዳንድ ሀዘን አለ
ከላይ ተሰውሮ : ልብ የሚበዘብዝ
የጥቅምት ብሩህ መስክ: አደይ የለበሰ
ስንቱን ጉድ አዝሎታል: ስሩ ከተማሰ!!
የጥቅምት መስክ ነኝ : አደይ ያደመቀው
ፈገግታ ቢውጠው: ዘበት ቢደብቀው
የኔን ብቻ ህመም: እኔው ነኝ የማውቀው::
(ተከፍተው የተከፉ ለማይመስሉ)
👍11840🔥9🥰2
ለቴሌግራም ምስለ ገፅ (Profile Picture) ማሳመሪያ እንካችሁ...

(ከበውቄ ግጥም የተቀነጨበ)

@yismakeworku
👍10043👎4
"ራማቶሃራ" የተሰኘው መፅሀፌን በትረካ መልክ የምትፈልጉ ምን ያክሎቻችሁ ናችሁ!? የቁጥር መጠናችሁ ከታች ያሉት አማራጮች እንዳውቅ ያስችለኛል።

እፈልጋለሁ
አልፈልግም
356👍204
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጌታነህ መኩሪያ የተባለው ይህ የደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ተማሪ "ኢትዮጵያ"ን እንዲህ በሚያምር ድምፁ ሲያንቆለጳጵሳት በ "ቲክቶክ" ተመልክቼ በመውደዴ ወደዚህ አመጣሁት።

የልጁን የቲክቶክ አድራሻ በዚህ መከተል ትችላላችሁ : https://www.tiktok.com/@getyemekuria/video/7131792225230523654?_r=1
👍9037🔥9
"ራማቶሓራ" ን ከወዳጄ ጋ በትብብር ከዛሬ ማታ ሶስት ሰዓት ጀምሮ በትረካ መልክ በዚህ ቻናል ይደርሳል።

የብራና ገፅ : አመሰግናለሁ።

#ሼር በማድረግ ለብዙ ሰው እንዲደርስ እርዱኝ
@yismakeworku
151👍75
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 1 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፩
File Size: 23.9MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
👍217132🔥7🥰3
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 2 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፪
File Size: 24.2MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
👍11558🔥11
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 3 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፫
File Size: 17.7MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
👍7531🔥10
ራማቶሓራ የመፅሀፍ ትረካን ምን ያክሎቻችሁ እየተከታተላችሁት ነው?

አዎ፣ ተመችቶኛል
አይ፣ አልተመቸኝም


(ቀጣዩ ክፍል ማክሰኞ ይቀርባል)

@yismakeworku
130👍73🔥5👎1
"ቀን ገንቢ" በሚል ርዕስ የማስነብባቸውን ፅሁፎች በዚህ የቴሌግራም ቻናል ተከታተሉ።

ፅሁፎቹን ካነበባችሁ በኋላ በእርግጥም ቀናችሁ እንደሚገነባ፣ ተስፋችሁ እንደሚያብብ፣ የዛለው ማንነታችሁ እንደሚጠነክር፣ መልካም እይታ እንደምታገኙ ስነግራችሁ በሙሉ የራስ መተማመን ነው።

#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻሁን አጋሩት ፣ እነሱም ተጠቃሚ ይሁኑ።

"ቀን ገንቢ" ዘወትር ሰኞ ፣ ረቡዕ ፣ አርብ ከቀኑ 6:00 ላይ በዚሁ የቴሌግራም ቻናል ይለጠፋል።

ዛሬ ለሚጀመረው ቀዳማዊ "ቀን ገንቢ" ፅሁፍ ዝግጁ ናችሁ?
ከሆናችሁ ይቺን በመንካት ምን ያክል እንደሆናችሁ አሳዩኝ።
👍12438
#ቀን_ገንቢ
ምዕራፍ ፩: ክፍል ፩


የራስ ዋጋ
------------

በአንድ ሰሚናር ውስጥ ሁለት መቶና በላይ ሰዎች በታደሙበት ታዋቂው ንግግር አድረጊ ተጋብዞ በቦታው ተገኝቷል፡፡ ተናጋሪው ለለቱ ማስተላለፍ የፈለገውን መልዕክት ለማጠናከር ያግዘው ዘንድ ንግግሩን የጀመረው የሃምሣ ብር ኖት በእጁ ይዞ በማሳየት “ከመካከላችሁ ይህንን የሃምሣ ብር ኖት የሚፈልግ ማን ነው!?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ ታዳሚውም በተከታታይ ሁሉም እጁን አንድ ባንድ አወጣ፡፡ ተናገሪው ቀጠለ “ከመካከላችሁ ለአንዳችሁ መስጠት እፈልጋለሁ ነገር ግን ከዛ በፊት” አለና የሃምሳ ብር ኖቱን በእጁ በማፋተግ እንዲጨማተር ካደረገ በኋላ “አሁንስ የሚፈልገው ይኖራል!?” ሲል በድጋሜ ጥያቄ አቀረበ፡፡
አሁንም የታዳሚዎች እጅ እፈልጋለሁ በሚል ስሜት ተዘረጋ፡፡ በጣም ጥሩ አለ ተናገሪው እንደዚህ ባደርግስ ብሎ የሃምሣ ብር ኖቱን እግሩ ሥር ጥሎ በጫመው ምድሩ ጋር ካፋተገ በኋላ አሁን “እደምትመለከቱት በጣም ቆሽሿል:: ተጨማትሯልም:: አሁንስ ትትፈልጉታላችሁ!? አሁንም የፈላጊዎች እጅ በአንድነት ተነሳ፡፡ “ወገኖች አሁን በጣም ወሳኝና መሰረታዊ ትምህርት እንደቀሰማችሁ አምናለሁ፡፡ ምንም እንኳን ብሩ ላይ ማናቸውንም ነገር ባደርግበት፣ ባቆሽሸውም፣ ባጨማትረውም፤ ብሩን የራሳችሁ የማድረግ ፍላጎታችሁ እንዳለ ነው፡፡ አልቀነሰም፡፡ ምክንያቱም የብሩ ኖቱ ቢበሳቆልም ቢጎዳም እንደ ብርነቱ የሚሰጠውን ዋጋ ወይም ጠቀሜታ አልቀነሰበትምና፡፡ እስካሁንም ዋጋው ያው ሃመሳ ብር ነው፡፡” አላቸው፡፡

ብዙውን ጊዜ በሕይዎት ውጣውረድ በምናሳልፋቸው ውሳኔዎች ፣ በሚፈጠሩት ክስተቶች መውደቅ መሰነሳቱ፤ መደቆሱ ያለና የሚኖር ነው፡፡ በተፈጠሩት የህይዎት ፈታኝ ክስቶቶች ዋጋ ያጣን ያህል ሊሰማን ይችላል፡፡ ነገር ግን ምንም ይሁን ምን፣ ያለፍንበት የሕይዎት ጎዳና ምንም ያህል አባጣ ጎርባጣም ቢሆን እኛ ማለት እኛ ነንና የእኛነታችንን፣ የራሳችንን ዋጋ አናጣምም ማጣትም የለብንም ፡፡


#ሼር

@yismakeworku
👍17747🔥5
ከ "ምሽቴ" ጋ

@yismakeworku
👍203127
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 4 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፬
File Size: 24.7MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
59👍26🔥5
#ቀን_ገንቢ
ምዕራፍ ፩ : ክፍል ፪


ሁለት ዘሮች
--------------


ሁለት ዘሮች ናቸው፡፡ በአካባቢው የተፈጠረ ንፋስ ከቅርፊታቸው ነጥሎ እያንሳፈፈ አጓጉዞ በላመ፣ በለሰለሰ አፈር ላይ ጎን ለጎን ቀላቀላቸው፡፡ ዘሮቹም ከለሰለሰ አፈር ላይ ማረፋቸውን በተረዱ ጊዜ በጉርብትና መንፈስ ውይይት ጀመሩ፡፡

አንደኛው ዘር፡ “በዚህ በእንደዚ ለመብቀን በተዘጋጀ ማሳ ላይ ሳርፍማ መብቀን እፈልጋለሁ፡፡ ሥሮቼንም ወደ ጥልቁ አፈር በመላክ፤ ቅርንጫፎቼን ከምድር በላይ ከፍ አድርጌ እንደ ባነር በመዘርጋት የበልግ ወራት መድረሱን፤ ልምላሜ መምጣቱን ማወጅ ይገባኛል፡፡ የጠዋቷን ፀሐይም የተፈጥሮ ስጦጣየን መመገብ ይገባኛል እፈልጋለሁም፡፡” ሲል ሀሳብን ለባልጀራው ሰነዘረለት፡፡ እናም በቅሎ ማደግ ጀመረ፡፡

ሁለተኛው ዘርም በፈንታው እንዲህ አለ፡ መጀመሪያ ሀሳቡን ህምምም.. ሲል በመደመም ጀመረ፡፡ “ስሬን ወደ ጥልቁ አፈር ብለቀው በዛ ጨለማ ውስጥ ምን እንደሚገጥመኝ ከየት አውቅና ነው! ጉንቁሎቼን ባጎነቁልስ የቀንድ አውጣ ምግብ መሆኔ አይደለምን! እንዲሁም ደግሞ አበቦቼን ባፈነድቃቸው ህፃናቶች ቆርጠው ምድር ላይ በመጣል መጫዎቻ ያደርጉኛል፡፡ ስለሆነም ከዚህ ሁሉ የምጠበቅበት ምቹ ሁኔታ እስኪፈጠር መጠበቁ የተሻለ ሳይሆን አይቀርም” ሲል የመብቀል የሕይወት ተልዕኮውን ገታው፡፡

ይህን ሀሳባቸውን ከተነጋገሩ ከሰዓታት በኋላ በአካባቢው ምግቧን ፍለጋ ምድርን ስትጭር የነበረች ዶሮ ለመብቀል ምቹ ሁኔታን ሲጠብቅ የነበረውን ዘር አገኘችና ተመገበችው፡፡ ሥራን ለመስራት የማይመጣን ምቹ ሁኔታን መተበቅ ስራ እንዳንሰራ ከማድረግ ውጪ የሚፈጥረው ፋይዳ የለውም፡፡ እንቅፋትም እስከመጨረሻው ስለማየውቅ በዓለማችን እስካሁን ተሰሩ ወሳይኝ የሚባሉ ስራዎች በሙሉ በችግር ውስጥ እንጅ በተደላደለ ሁኔታ እንደልሆነ አብዛኛው መረጃ ይናገራል፡፡ There is no ideal condition for everything we can do what we have to do even in adverse condition.

/ምስጋናው ግሸን/

#ሼር
@yismakeworku
👍7944
ራማቶሐራ ፡ ትረካ - ክፍል 5 [ Ra...
የብራና ገፅ / Page of Birana
ራማቶሓራ ትረካ:
ክፍል ፭ / 5
File Size: 39.6MB

ዘወትር: እሁድ፣ ማክሰኞ ፣ ሀሙስና ቅዳሜ ምሽት 3:00 ላይ በዚሁ በቴሌግራም ገፄ ወደ እናንተ ይቀርባል።


#ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አጋሩት

ትረካ በ:- የብራና ገፅ
@yismakeworku
51👍43🔥5😢4