ሰዎች እንደሚወዱህ ቢነግሩህም መውደዳቸው ትክክል የሚሆነው አንተ እንደወደዱህ እንዲሰማህ ማድረግ ሲችሉ ነው።
እንወድሃለን በሚሉት ደረጃ መውደዳቸው ካልተሰማህ በአካል እነሱ መሃል ብትሆንም በስሜትህ ግን ብቸኛ ነህ።
@yismakeworku

ቅኔ ቤት እየተማርኩ እያለ ስለ አክሱም ሐውልት የነገሩኝ መነኩሴ ነበሩ፡፡ "የወደቀው ትልቁ የአክሱም ሐውልት ሲቆም ኢትዮጵያ ታድጋለች" ብለው ነገሩኝ፡፡ "ትንቢት አለ" አሉኝ፡፡
እኔም የነገሩኝ ትንቢት ደርሶ ሐውልቱ እስኪቆም በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ፡፡ ከጣልያን ሀገር ተጓጉዞ ሌላኛው ዘመዱ ከተፍ ብሎ አጠገቡ ተተከለ፡፡ የአክሱም ለእንትን ምኑ ነው ተብለን ስንናቅም ነበር፡፡ (በቀደመው ጊዜ ባሮች ነበሩ ሐውልት የሚተክሉት፡፡ ለምሳሌ የግብፅን ፒራሚድ ያቆሙት ግብፆች አይደሉም፡፡ እስራኤላውያን ነበሩ፡፡ ታዲያ 'በተከለ' ከሆነ ለግብፅ ሳይሆን ለእስራኤል ነበር ፒራሚዱ የሚገባው፡፡ አሁን ግን የቱሪዝም ገቢ እየተበላበት ለግብፅ ፒራሚዷ ነው ገቢዋ፡፡ አክሱምንም 'ያሠሩት' በወቅቱ ለተቀበሩት ነገሥታት ቢሆኑም ባሮች ናቸው፡፡ 'የሠሩት' አላልኩም፤ 'ያሠሩት' ነው ያልኩት፡፡ ማን ባሪያ እንደሆነ እነርሱ ይወቁ፡፡ እኛ ምን አገባን! አልሠራችሁትም፣ ምናችሁ ነው ተብለናል)
አቤት የወጣበት ወጪ! ፖለቲካውም በጎኑ ተጧጧፈ፡፡ ለዘመናት እንዲመጣ ሲጎተጉቱ የነበሩት ሰዎችም በመጣበት ወቅት ደስታቸውን እየገለፁ ቢሰነብቱም፣ ውሎ አድሮ ውሻል ሲገባለት ከትልቁ ሐውልት ላይ እንዘጭ እንዳይልበት ፀሎታቸውን ጀመሩ፡፡
የዚህ ሀገር ዲቃላ (ሊበራዝም፣ ካፒታሊዝም፣ ሶሻሊዝም... 'ዝም'ስለሚሉ ነው ዲቃላ ያልኳቸው) ፖለቲከኞች ለያኔው ቆመሩበትና ወዲያው የመጓጓዣ አበሉ ሲያልቅ ዘወር አሉ፡፡
ሶስት ጊዜ ይሆናል፣ አክሱም ጽዮን ማርያምን ልሳለም ሄጄ ነበር፡፡ በሶስቱም ጊዜ ሐውልቱን ጎብኝቼዋለሁ፡፡ እየዘመመ፣ እየዘመመ፣ እየዘመመ መጣ፡፡ ዘሞ ከትልቁ ሐውልት ላይ እንዳይከመርበት በዛውም እንደገና ለአክሱም ጽዮን ማርያም ተማፀንኩ፡፡ "የወደቀው ትልቁ ሐውልት አንድ ጊዜ ይነሳል እያልኩ፣ ያውም የኢትዮጵያ ትንሳኤ ይሆናል እያልኩ፣ ከልጅነቴ አንስቶ ስማፀንሽ ምነው ጽዮን፣ ደግሞ ዘሞ ሊወድቅበት ነው?" እያልኩ ፀለይኩ፡፡
የእኛ ሀገር የፖለቲካ ሊቀ ዲያቆኖች እንደሳምሶን "ነፍስዬ ትፃዕ ምስለ ኤሎፍላውያን!" መነቅነቅ ነው እንጂ ሥራቸው እንደ ያዕቆብ መሰላሉን አያቆሙም፡፡ (ሀገሪቷን መነቅነቅ፣ ያልደፈረሰውን እንዲደፈርስ ማድረግ ) ካቆሙም ለስልጣን መወጣጫነት ነው፡፡
ጥያቄ አንድ፦
የአክሱም ሐውልት የመጣው የሚቆመው መቼ ነው?
ጥያቄ ሁለት፦
የአክሱም ሐውልት የወደቀውስ የሚቆመው መቼ ነው?
ጥያቄ ሶስት፦
ጣናስ የእንቦጭ አረም የሚፀዳለት መቼ ነው?
... እነዚህ ሁሉ በደና ጊዜ ከቱሪዝም ገቢ የምናጋብስባቸው ወርቆቻችን ናቸው፡፡ ይህን ያላስተካከለ ፖለቲከኛ ምርጫ ሲመጣ ምን ብሎ በአክሱም ሊቀሰቅስ ነው? ምን ብሎ በጣና ዳርቻ ሊቀሰቅስ ነው?
"ብቻ ምረጡኝ እንጂ እኔ የአክሱምን ሐውልት ከጣሊያን የመጣውንም እዚህ የወደቀውንም እተክላለሁ፡፡ ብቻ ምረጡኝ እንጂ እኔ እንቦጭን ከጣና ላይ አጠፋለሁ..." እያለ ምርጫውን አጧጡፎ ሲያበቃ፣ የተወካዮች ምክር ቤት ገብቶ እንቅልፉን የሚደልቅ አረጭ መቼም አታጡም፡፡ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአረጭ ፖለቲካ ነው፡፡ አረጭ ማለት (ለማታውቁት ) የደም መጣጭ ፖለቲካ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ደም የሚመጡ ፖለቲከኞች መናኻሪያ ነው ስል ነው፡፡
@yismakeworku @yismakeworkuBot

👍6
ኮሜዲያን ደረጀ ሀይሌ!!
በዘረኝነት የጎበጠውን ህዝቤን በቁም ነገር እንደውሃ እያሳሳቅህ እንደምትመልሰው እና ዘወትር እንደምትለው፣ "አትጥበቡ!" እንደምትለን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ ስንት በጥባጮች ባሉበት ቦታ ነው የገባህበት (you tube)፡፡ ስለ ቅድስት ሀገራችን ሳቅ እንደምታዘምርልን ተስፋዬ ባንተ ላይ ነው፡፡ እኛም እጆጃችንን ዘወትር ወደ አንተ እንጀራ እንሰዳለን፡፡ ጨብጠኝ! (በስልክህ ጨብጠኝ)
https://youtube.com/channel/UClYehgGvOC8nPWbYjATCOug

YouTube
Mlikit media - ምልክት ሚዲያ
=================================================
ምልክት ቲዩብ አጫጭር አስተማሪ እና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረቱ ድራማዎችን ወደ እናንተ የሚያቀርብ የዩቲዩብ ቻናል ነው።
ላይክ ሸር ሰብስክራይብ በማድረግ የቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ
======================================

Yismake Worku via @like
ሻሎም ወዳጆቼ እንደምንድን ናችሁ!?
ዛሬ ወደ አዲስ አመት መሻገሪያ ድልድይ በሆነችው ጳጉሜ ላይ ሆኜ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ነበር አመጣጤ።
መልሳችሁ ለመልካም ስራ ይረዳኛልና ፤ ይሄን የቴሌግራም "ቻናሌን" ከተቀላቀላችሁ ውስጥ ባህርዳር እና አካባቢዋ ላይ የምትኖሩ ወዳጆች ብቻ 👍 በመንካት ብዛታችሁን አሳውቁኝ። አልያም ደሞ @yismakeworkuBot ጋር በመግባት ባህርዳርና አካባቢዋ ጋር የምትኖሩ መሆናችሁን ንገሩኝ።

👍2
Yismake Worku via @like
አዲስ አላም፣ አዲስ ህልም፣ አዲስ ስኬት ከእናንተ ጋር ሊራመዱ በዝግጅት ላይ ናቸው። በጉዙው ላይ መድከሙን እርሱት። ድክመታችሁን አስተካክሉት። በእርግጠኝነት ስኬት የናንተ ትሆናለች።
መልካም አዲስ አመት🌼
ከ @yismakeworku ለ እናንተ
መልካም አዲስ አመት🌼
ከ @yismakeworku ለ እናንተ
ይሄ በቴሌግራም አድራሻዬ ብዙ ጊዜ ከሚላኩት መልዕክቶች አንደኛው ነው።
በግል መማር እንደምትፈልጉ ስነግረው እጅግ በልዩ ቅናሽ ሊያስተምራችሁ እየሞከረ ነው። ዋጋውን እና የክፍያ ስርዓቱ እንዴት እንደሆነ ደሞ እኔ አሁን እዚሁ ላይ እለጥፍላችኋለሁ። አልያም @ethioenglizegna ጋር ገብታችሁ እዩ።

የእንግሊዘኛን ቋንቋ በግል የመማር ልዩ የትምህርት አሰራር እና ክፍያ፦
እጅግ በልዩ ቅናሽ ትምህርቱ የሚካሄደው በ22 ምዕራፎች /ፓኬጅ/ ተከሽኖ ነው። ተማሪው ከምዕራፎች ውስጥ የፈለገውን እና ማወቅ አለብኝ የሚለውን ምዕራፍ መርጦ ይማራል።
ምዕራፎቹም:-
1. ጤና ይስጥልኝ
/ስለ ሰላምታ ማለት ያሉብን ነገሮች የሚገልፅ የት/ት ምዕራፍ/
2. እንተዋወቅ /ስለ ትውውቅ/
3. እያወራን ሳለ
/በወሪያችን መሃል የምንላቸው ነገሮች/
4. ልክ ነህ/ተሳስተሃል
/ንግግራችን ላይ አንድ ሰው ልክም ሲሆን ሲሳሳትም ፣ ስንስማማም ሳንስማማም ምን ማለት አለብን እና ሌሎች/
5. ደህና ሁኑ
/ስንብትን በተመለከተ የሚያስተምር ምዕራፍ/
6. ግብዣ
/ተጋብዛችሁም ሆነ ጋብዛችሁ ማለት የሚገባችሁ ንግግሮች/
7. እንግዳ
/እንግዳ ስትሆኑም ሆነ ሲመጣ ማለት ያሉባችሁን ንግግሮች የሚያስረዳ ምዕራፍ/
8. ስሜት
/ከወሲብ ጀምሮ የደስታ ሀዘን ጭንቀት ወዘት ስሜቶች ሲኖሩብን እንዴት መናገር እንዳለብን የሚያሳይ የትምህርት ምዕራፍ/
9. ይቅርታ
/ስንጠይቅም ሆነ ስንቀበል/
10. ስልክ
/ስንደውልም ሆነ ሲደወልልን ማለት ያሉበን ነገሮች/
11. ትምህርት
/ትምህርት ላይ ስንሆን ማለት የሚገቡን የንግግር ስልቶች/
12. ምስጋና
/ምስጋና ስናቀርብም ሆነ ሲሰጠን ማለት ያሉብን ንግግሮች/
13. ቤተሰብ
14. ምግብ ቤት
/ምግብ ቤት ላይ ማለት ያሉብን የእንግሊዘኛ ቋንቋዎች/
15. ጉዞና ትራንስፖርት
16. ፖሊስ እና አደጋዎች
/አደጋ ቢፈጠር እንዲሁም ፖሊስ ጋ በእንግሊዘኛ ለማውራት ማለት ያሉብን ነገሮች/
17. ሆቴል
18. በስራ ዙሪያ
19. ግብይት
20. ጤና
21.ገንዘብ
#22. ሌሎች ጠቃሚ ንግግሮች
/ይሄ ብዙ ነገሮችን በውስጡ የያዘ ምዕራፍ ነው/
ክፍያን በተመለከተ:-
ከተራ ቁጥር 3 ፣ 8 ፣ 15 እና 22 ውጪ እያንዳንዱን ምዕራፎች በ50 ብር ክፍያ ብቻ ትምህርቱን ሊያገኝ ይችላል።
ተ.ቁ 3 :- 100 ብር
ተ.ቁ 8 :- 150 ብር
ተ.ቁ 15 :- 75 ብር
ተ.ቁ 22 :- 300 ብር መሆኑን እንገልፃለን።
መመዝገብ እና ትምህርት መጀመር የምትፈልጉ @ethioenglizegnaBot ላይ ገብታችሁ አሳውቁን።
ኢትዮ እንግሊዘኛ!
እየሸለመ የሚያስተምር ብቸኛው ቻናል

መምህር ኤስድሮስ የተባሉት ሊቅ ያስተማሩትን የመንፈስ ልጃቸዉን ሲመክሩ እንዲህ አሉት፡፡
"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"
@yismakeworku
"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"
@yismakeworku
👍8
Yismake Worku via @like
እንደ ክረምት ዝናብ ፣ችግሬ ይረግፋል
ምስኪን ትከሻዬ ፣እሱን ይቀበላል
ሰዎቹም ይላሉ ፣እንዴት ቻለው እሱ
ሁሌም ብልጭ ይላል ፣ አይከደን ጥርሱ
የተበደለ ሰው፣ ችግር ላላት ነፍሱ
ኑሮ እንዴት ነው ቢሉት፣ ፈገግታ ነው መልሱ
@yismakeworku
ምስኪን ትከሻዬ ፣እሱን ይቀበላል
ሰዎቹም ይላሉ ፣እንዴት ቻለው እሱ
ሁሌም ብልጭ ይላል ፣ አይከደን ጥርሱ
የተበደለ ሰው፣ ችግር ላላት ነፍሱ
ኑሮ እንዴት ነው ቢሉት፣ ፈገግታ ነው መልሱ
@yismakeworku
ከማስታወሻዬ ጥቂት ልበል
አንድ ጊዜ ተመስገን ደሳለኝ ለፍርድ የቀረበበት ቀን ነው፡፡ ጀግናው ፕሮፌሰር መስፍን ለጊዜው በምስክርነት ቆመው ተመስገን ከእስር ዳነ፡፡ እኔ፣ ተሜ፣ በዕውቀቱ ስዩም እና ፕሮፌሰር መስፍን ሥጋ ቤት ገባን፡፡ አዘዝን፡፡ መጣ፡፡ ለበዕውቀቱ ቢላዋ ከፊቱ አለ፡፡ ፕሮፍ፣ እኔ...ቢላዋችንና
የመረጥነውን ሥጋ አንስተን መምተር ጀመርን፡፡ "አንተ አትበላም" አሉት በዕውቄን፡፡ "እኔ አልበላም ሥጋ" አለ በዕውቄ፡፡ "ኦው ቪጂቴርያን ነህ?" አሉትና ፕሮፍ፣ ከላይ እስከታች አዩት፡፡ ያደረገው ጫማ ንፁህ ከቆዳ የተሠራ
ነበር፡፡ ወደ እኔ ዞሩና ፈገግ አሉ፡፡ በዕውቄ ዘወር ሲል "ጎመን በስጋ ስንበላ እኔ ስጋ ስጋውን እበላለሁ እርሱ ደግሞ ጎመን ጎመኑን... አሁን ይሄ ቪጂቴርያን ነው?" አልኳቸው፡፡ ለትዝታ!

👍4
Yismake Worku via @like
ሁልጊዜም ለእኛ ለተራማጆች ቀኑ ልደታችን ቢሆንም ህዳር 7 ግን የልጄ የልደት ቀኑ ነው። የሰባትን ምስጢር በልጄ ውስጥ ፈለግኩት። እርሱም የበደሉህን ሁሉ ይቅር በል ይላል።
@yismakeworku
@yismakeworku
@yismakeworku
@yismakeworku
👍3❤1
Yismake Worku via @like
ወደ እናንተ ደጋግ ሰዎች የበለጠ ለመቅረብም የዩቱብ አካውንት ለመክፈት አስቢያለሁ።
በድረገፁ ውሥጥ
ስለኔ ወቅታዊ መረጃ
ትረከቶች
እና መሰሎች መቅረባቸው እሙን ነው።
እናንተስ ምን አሰባችሁ?
🅰 ሀሳብህን ደግፌዋለሁ
🅱 ሀሳብህን አልደገፍኩትም
።
ፈጣሪ ስለሁሉም ነገር ይመስገን - እናንተን ስለሠጠኝም ጭምር።
በድረገፁ ውሥጥ
ስለኔ ወቅታዊ መረጃ
ትረከቶች
እና መሰሎች መቅረባቸው እሙን ነው።
እናንተስ ምን አሰባችሁ?
🅰 ሀሳብህን ደግፌዋለሁ
🅱 ሀሳብህን አልደገፍኩትም
።
ፈጣሪ ስለሁሉም ነገር ይመስገን - እናንተን ስለሠጠኝም ጭምር።
Forwarded from TAM™¤
አስቾኳይ የእርዳታ ጥሪ ለ እህታችን !!
★ በቅንነት ሼር ሼር ሳያድርጉ እንዳያልፉ
የሕይወት አድን ጥሪ ወገን ለወገን ደራሽ ነውና
#ETHIOPIAN || ሀያት ኢብራሂም ኡመር ትበላለች የ 11class ተማሪ ነች በ ባሌ ጎባ ነዋሪ ስትሆን በደረሰበት ከፍተኛ በሆነ የኩላሊት ህመም ሁለት #ኩላሊቶቹዋ ከጥቅም ውጪ ሆነው ዲያለሲስ እየተደረገላት በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ትገኛልች ።
ውድ ወገኖች ለእህታችን በሃኪሞች በተነገረው የቀድሞ ጤንነቱ እንዲመለስ ያለው አማራጭ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ ብቻ እንደሆነ #የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለማድረግ ወደ ውጭ ሃገር መሄድ ይኖርበታል ለህክምና በጠቅላላ 2,000,000(ሁለት ሚሊዮን ብር)ያስፈልጋታል ውድ ወገኖች ወገን ለወገን ደራሽ ነውና ለህታችን #ህይወት ለመታደግ የእርዳታ እጆቻቹ እድትዘረጉለት ዘንዳ በፈጣሪ ስም እንማፀናለን መርዳት ባትችሉ እንኳን ለሚረዱ ሰው ሼር በማድረግ እድተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን!
የበለጠ መረጃ ለማግኘት በስልክ ቁጥር
+251925386501
እንዲሁም ቤተሰቡዋ ጋር
0920942369
0912823605
በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ !! በቅንነት ሼር ያድርጉ
እስቲ ይስማዕከ ቢያንስ ባንተ በኩል የሚረዳት ሰው ከተገኘ እባክህ። አመሰግናለሁ!