Yismake Worku
20.6K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
ጥሎብኝ ጀግና ሰው እወዳለሁ፡፡ በጥበብ አለም ውስጥ ጀግና ሰው ሁሌም ቀድመው ጠላቶቹ ያጠቁታል፡፡ በሁዋላ ግን እያሸነፈ ይመጣል፡፡ ሁሌም ትክክለኛ መንገድ ለግፉአንና ለንፁሃን ነው፡፡

"ደህንነቱ" ብዬ የፃፍኩት ልብ ወለዴ ላይ፣ ... ካርታው፣ ሚሳኤሉ፣ ... ሁሉም ነገር በጃቸው እንደሆነ አስቀድሜ ገልጨ ነበር፡፡ ዶ/ር ዲዲሞስ ዶሬ፣ አይጥ የሆነበት ልብ ወለድ ነው፡፡ አሁን ግን አይጥ ሆኖ የሄደባቸው ሰዎች፣ እንደ አይጥ ሆነው ገደሉን አጣበውበታል፡፡ የእርሱ ደህንነት ለመሆን ነበር እዛ ድረስ የተጓዘው፡፡ ራሱን በራሱ ለማስከበር፡፡ ፍትህ ለማግኘት ነገር ግን አሁን ከአንድ ገፀ ባህርይ አልፎ የጋራችን የደህንነት ስጋት ሆኗል፡፡ ዶ/ር ዲዲሞስ የአይጥ ገደሉን ለእነርሱ ትቶ ወደ ሰው ተመልሷል፡፡

በሰሞኑ ያሰዩኝ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አቢይ ልክ በልብወለድ መልክ እንደማደንቀው የተለዬ ገፀ ባህርይ ሆነውብኛል፡፡ እውነት ለመናገር፣ ይህን ድንቅ ዘመቻ አለማድነቅ ንፉግነት ነው፡፡ አንድም ንፁህ ዜጋ እንዳልገደሉ ሲነግሩን፣ በድሮን ብቻ እየተመለከቱ ማለፍ እጅግ በጣም አስገራሚና የበሳል ሰው ውሳኔ ነውና ሀገሬ ለሀገሬው ሰው የሚጨነቅላት መሪ በማግኘቷ ደስታው የጋራ ቢሆንም ይሄን እውነት አለመናገር በታሪክም ተወቃሽ ያደርጋል፡፡ እኔም በጣም ብዙ ወዳጆች አሉኝ መቀሌ ውስጥ፡፡ ሰሞኑን ስልኩ ተዘግቶ እስካሁን ባንገናኝም፣ ከቀናት በሁዋላ እንደምንገናኝ ተስፋ አለኝ፡፡ የመቀሌ ሰው ከልቡ ሰው ነው፡፡ እንደገና መቀሌ ቡና እየጠጣሁ የማወራበት ጊዜ ናፈቀኝ፡፡

ብዙ የሚያደንቁኝ፣ በዛኛው ስርአት የተማረሩ ሰዎች በጣም እጅግ ብዙዎች አሉ፡፡ እነርሱም መጽሐፌን ልፅፍ እዛ በሄድኩበት ወቅት ስርቻውንና ጓዳ ጎደጓዳውን ሁሉ ያሳዩኝ ወገኖች አሉኝ፡፡ የሀገሬ ጦር እነርሱን በመጠበቁ እኛ እናተርፋለን፡፡ ሀገራችንን በጋራ እንሠራታለን፡፡

ሰላም ለኩልክሙ፡፡
@yismakeworku
👍6👏1
የማንኛውንም መጻህፍቴን ትረካ በሙሉ በ Youtube ላደርሳችሁ ተዘጋጅቺያለሁ።

አዎ እንፈልጋለን ፤ አድራሻውን ንገረን የምትሉ 👍 በመጫን አሳውቁኝ።
@yismakeworku
የመጀመሪያው የፍቅር ደብዳቤዬ

በዘመኔ ስመኛትና ስስላት የኖርኩትን በገፀ ባህርያቶቼ የሳልኳትን፣ በድርሰት አለሜ እንጂ፣ በጋሐድ ህይዎቴ ያላገኘሁዋትን፣ ማተቧን የማትበጥስ፣ ወግና ባህሏን አክባሪ፣ ሀገሯን አፍቃሪ፣ እጅግ ሲበዛ ጠንካራና ልበ ቀና የሆነችውን፣ የትላንት ህልሜ የዛሬዋ እውነቴ ባለቤቴ፣ እግዚአብሄር አንቺን ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ፡፡

በከፋኝ ጊዜ ከጎኔ ሆነሽ ያፅናናሽኝ፣ የእኔ ነገር ያልገባቼውን ሰዎች ያን ሁሉ ምስጢሬን ሳካፍልሽ "ይህን ሁሉ እንዴት ቻልከው?" ያልሽኝ መልካም ቅን የሴቶች የበላይ፣ ሁሉም ያልፋል እንዳልሽኝ ሁሉም አልፎ የእኔ ሆንሽ፡፡

ያመንኳቸው ህይዎቴን ሁሉ ነገሬን የሰጠሁዋቸው ሲከዱኝና ለተራ ዝናና ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ያለኃጢአቴ ባልዋልኩበት ሲሰይሙኝ፣ ማንም ባልነበረኝ ሰአት የተረዳሽኝ፣ የልቤን መሻት ስነግርሽ ገብተሽ ፍቱን መድኃኒት የሆንሽኝ፡፡ ስታመም እንደ ካህን ዳዊት ደግመሽ ፀበል የምትሰጪኝ ልጅ፣ በስራዬ ይበልጥ እንድሰራ በሀሳብ የምታግዢኝ ልጅ፣ የእግዚአብሔር ድንቅ ስጦታዬ ለካ ያ ሁሉ ፈተና እንዳልፍ የተፈረደብኝ አንቺን የመሰለች ደግ ሩሩህ ሚስትም እናትም እህትም ጓደኛም ሊሰጠኝ ነበር፡፡

ውዴ ብዙ ለመጻፍ ባልችልም ምን ያክል የጠለቀ ፍቅርና ክብር እንዳለኝ ሀገሬ ብቻ ሳትሆን አንቺም ጠንቅቀሽ ታቂለሽ፡፡ እንደ ባቢሎን ግንብ የገዘፈው ፍቅርሽ እንደ ከርቤ የሚያውደኝ ፍፁም ንፁህ ልብሽ እንሆ እስከ እለተ ሞቴ ያንቺውና ያንቺ ብቻ እንድሆን አድርጎኛል፡፡ የልቤ ሰው ሜሊዬ አፈቅርሻለሁ፡፡

"ሀብትና ባለጠግነት ከአባቶች ዘንድ ይወረሳል አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት" መጽሐፈ ምሳሌ 19÷14

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና አንቺን ይጠብቅ፡፡
@yismakeworku
👍72
Channel photo updated
እግዚአብሔር ካሰኝ። "ዮም ፍስሐ ኮነ"
@yismakeworku
🥰5
"ከጎንደር ባህርዳር ስትመላለሺ፣
ወረታን አታውቂ ብሎ ሰው አማሺ"
የተባለውን ግጥም ያፈረስሽ ጀግና። የወረታን ፎቶሽን ለጥፊውማ?
👍4
ወዳጆች!

ቤትዎም ሆነ በአገኙት አጋጣሚ ማንጎራጎር ይወዳሉ? ያዳመጥዎት ሰው አድንቅዎት ያውቃል? ወይስ አይ አይሆንም ተብለዋል? ግዴለም ዘፈን መዝፈን የምትፈልጉ እና የምትሞክሩ ሰዎች አንጎራጉሩ እና ተሸለሙ ይላል - ማለዳ! የወዳጄ ገፅ ነው።

እያንጎራጎሩ ራስዎን ይቅዱ ከዛም በቴሌግራም በኩል ለማለዳ ገፅ ይላኩ። አሸናፊ ከሆናችሁ እጅግ ማራኪ ሽልማት ያገኛሉ።

የጀማሪ ድምፃውያን ውድድር በማለዳ! ድምፅ የማይሞክሩ ከሆነም የተወዳዳሪዎችን የድምፅ ውድድርም እንዲያዳምጡ ተጋብዘዋል።

የማለዳ ቻናል ይሄው👉 Join ያድርጉ https://tttttt.me/joinchat/VO3Vmwod7Xr1X9_O
👍3
ህልምሽ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ነበር፡፡ እናቴ ለዚህ ስለበቃሽ ፈጣሪን አመሰግነዋለሁ፡፡
@yismakeworku
🥰62
እንክርዳድ

አባቴማ ድሮ
ስንዴ እያበጠረ
አንዳንዱን እንክርዳድ
ይለቅም ነበረ።

እኔ ግን ዘንድሮ
ግርድ አነፍሳለሁ
ከእንክርዳዱ መሀል
ስንዴ 'ፈልጋለሁ።

(ይስማዕከ ወርቁ)
👍61
በቴሌግራም የጀማሪያን የድምፅ ውድድር እየጦፈ ነው። ወደ " ቻናሉ" ገብታችሁ ውድድሩን በማየት፣ የተወዳዳሪያንን ድምፅ በመስማት እና እንዲያሸንፍ የሚፈልጉትን ሰው ምረጡ።

ተወዳዳሪዎች መልካም እድል!

የ"ቻናሉ" አድራሻ ይሄ ነው። ተቀላቀሉ https://tttttt.me/joinchat/VO3Vmwod7Xr1X9_O
ጥቁር የበላይ የሆነባት ብቸኛዋ ሀገር ማኪያቶ ናት።
@yismakeworku
👍5
ወዳጆች፤ ቤትዎ ተቀምጠው የሚሰሩት ስራ እንካችሁ ብትባሉ እሺ ብለው ይቀበላሉ?

በቅርቡ ከሰዎቹ ጋር ተማክሬ ሁኔታውን አሳውቃችኋለሁ። በተወሰነ ደረጃ ገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ብዬ በማሰብ ነው።

ምን ያክሎቻችሁ ዝግጁ ናችሁ? 👍 በመጫን ስንቶቻችሁ እንደምትፈልጉት እና ለመስራት እንደተዘጋጃችሁ እንዳውቅ አድርጉኝ።

ይሄን መልዕክት #ሼር በማድረግ አግዙኝ! ወዳጆቻችሁም እንዲያውቁ አድርጉ።
@yismakeworku
👍2