Forwarded from Yismake Worku
ከአዲስ አበባ ጎዳናዎች ውስጥ መገናኛ የሚባለው ሰፈር ይነግስብኛል። ብዙ ጊዜም ሰዎች በአካባቢው ስዘዋወር ያስተውሉኝና ይጠይቁኛል። ትወደዋለህን?
እንዴታ እላለሁ። ምክንያቱም ከእሁድ እስከ እሁድ ሰው አለ። ከደግነት እስከ ክፋት አጥር የታጠረ፣ ከተስፋ እስከ ቅዠት፣ ከፍቅር እስከ በቀል ያረገዘ ሆድ፣ ብቻ ብዙ ብዙ የሚታይበት አድባር ነው። እኔም ከነዚህ ውስጥ ተቋዳሽ ነኝ።
ከእለታት በአንድ ቀን ተንቀሳቃሽ ስልክ መግዛት ፈልጌ ስውተረተር የደግነት እግር አንድ ሰው ጋር ጣለኝና ተዋወቅኩት። ተግባቢ፣ ትሁት ነው። በዛ ላይ ታማኝና ስራ ወዳድ ነው። እምነት እንደሚያሸንፈኝ ብዙ ጊዜ አጋርቺያችኋለሁ።
አሁንም እላለሁ።
ሞባይል (ተንቀሳቃሽ ስልክ) ፣ ታብሌት መሸመት ከፈለጋችሁ እንግዲያውስ በኔ ጥቆማ ቅድም የነገርኳችሁን ገፀ ባህሪ ወደ ተላበሰው ሰው ልምራችሁ።
#ቃል_ሞባይል ይሰኛል
አድራሻ:- መገናኛ ፣ ቤተልሄም ፕላዛ፣ ሁለተኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር:- +251913453131
ለመልካም ሰው እውቅና መስጠቴ ይቀጥላል።
እንዴታ እላለሁ። ምክንያቱም ከእሁድ እስከ እሁድ ሰው አለ። ከደግነት እስከ ክፋት አጥር የታጠረ፣ ከተስፋ እስከ ቅዠት፣ ከፍቅር እስከ በቀል ያረገዘ ሆድ፣ ብቻ ብዙ ብዙ የሚታይበት አድባር ነው። እኔም ከነዚህ ውስጥ ተቋዳሽ ነኝ።
ከእለታት በአንድ ቀን ተንቀሳቃሽ ስልክ መግዛት ፈልጌ ስውተረተር የደግነት እግር አንድ ሰው ጋር ጣለኝና ተዋወቅኩት። ተግባቢ፣ ትሁት ነው። በዛ ላይ ታማኝና ስራ ወዳድ ነው። እምነት እንደሚያሸንፈኝ ብዙ ጊዜ አጋርቺያችኋለሁ።
አሁንም እላለሁ።
ሞባይል (ተንቀሳቃሽ ስልክ) ፣ ታብሌት መሸመት ከፈለጋችሁ እንግዲያውስ በኔ ጥቆማ ቅድም የነገርኳችሁን ገፀ ባህሪ ወደ ተላበሰው ሰው ልምራችሁ።
#ቃል_ሞባይል ይሰኛል
አድራሻ:- መገናኛ ፣ ቤተልሄም ፕላዛ፣ ሁለተኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር:- +251913453131
ለመልካም ሰው እውቅና መስጠቴ ይቀጥላል።
👍2❤1
የጓደኛዬን የበውቀቱ ስዩም የግጥም መድብል አድራሻውን ተጠቅማችሁ አንብቡት!
አድራሻ 👉🏾 http://www.good-amharic-books.com/library?getbook=4382
አድራሻ 👉🏾 http://www.good-amharic-books.com/library?getbook=4382
መጥፎ ሰው ማለት እየፈለከው የማይፈልግህ ሳይሆን ሳትፈልገው ፈልጎህ የመፈለግ ስሜት ከፈጠረብህ በኋላ የማይፈለግህ ሰው ነው።
@yismakeworku
@yismakeworku
ሻሎም!
መልዕክት ለመናገር ነው የመጣሁት።
የቁራ መልዕክተኛነቴን አምኛለሁ ምክንያቱም ዘግይቻለሁና።
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትን በቀላሉ በቴሌግራም መድረክ የሚያስተምረው ወዳጄ ነገ ትምህርቱን እንደሚጀምር አስታውቆኛል። በመሆኑም መማማር የሚፈልግ ካለ @ethioenglizegna ውሥጥ ገብታችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
@ethioenglizegna
መልዕክት ለመናገር ነው የመጣሁት።
የቁራ መልዕክተኛነቴን አምኛለሁ ምክንያቱም ዘግይቻለሁና።
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትን በቀላሉ በቴሌግራም መድረክ የሚያስተምረው ወዳጄ ነገ ትምህርቱን እንደሚጀምር አስታውቆኛል። በመሆኑም መማማር የሚፈልግ ካለ @ethioenglizegna ውሥጥ ገብታችሁ ቤተሰብ ሁኑ።
@ethioenglizegna
ህይወት ነች ወላዋይ
ከላይ ሲሏት ከታች፣ ከታች ሲሏት ከላይ
ሲሳይ ሲደራረብ፣ መሬት የምትገኝ
መሬት ልመጅ ሲሏት፣ ሲሳይ የምትመኝ
ከሞላችም ከሩብ
ስትጎል ለሩብ ጉዳይ
ነሳች ሲባል ሰጪ፣ ሰጠች ሲባል በዳይ
ህይወት ነች ወላዋይ።
(ይስማዕከ)
@yismakeworku
አሁን የተቀነጨበ
ከላይ ሲሏት ከታች፣ ከታች ሲሏት ከላይ
ሲሳይ ሲደራረብ፣ መሬት የምትገኝ
መሬት ልመጅ ሲሏት፣ ሲሳይ የምትመኝ
ከሞላችም ከሩብ
ስትጎል ለሩብ ጉዳይ
ነሳች ሲባል ሰጪ፣ ሰጠች ሲባል በዳይ
ህይወት ነች ወላዋይ።
(ይስማዕከ)
@yismakeworku
አሁን የተቀነጨበ
👍1
ያለ ፉክክር ህይወት አምራ አትታይም። ለምሳሌ "ዲም ላይት"የሚባለውን ቁስ አስተውሉት። ዝብርቅርቅነት ውበት መሆንን ያሳየናል
@yismakeworku
@yismakeworku
Forwarded from Yismake Worku
ፍቅር ፈራን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን
========//==========
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን መቀራረብ ፈራን
እንዳልተዛመድን እንዳልተዋለድን
ፈርተን መዋደድን ጉርብትናን ናድን
እኛነትን ትተን እኔነትን ለመድን
"ፈራን"
ፍቅርን ፈራን ጥላቻን ሰራን ብቸኝነት ጠራን
በጋራ ቤታችን አጥር ድንበር ሰራን
"ናቅን"
በልዩነት ደምቀን ያልኖርን ያህል አንድም ቀን
እልህ ተናነቅን
"ናቅን"
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን
"ጠላን"
መወያየት ጠላን መነጋገር ጠላን
መደማመጥ ጠፍቶ መነቋቆር በዝቶ
መናናቅ በርክቶ
መመካከርን ስንረሳ መከባበርን ስንረሳ
እጃችን በወንድማችን ላይ ዱላ አነሳ
የቃየል ምቀኝነት በልባችን ላይ ነግሳ
"ራቅን"
የተስፋ ሻማችን ተለኩሶ
ወጋገኑ መታየት ሲጀምር አድማሱን ጥሶ
እኛ ግን ራቅን ብሩህ ነገን ራቅን
ዛሬን ተጣበቅን ትላንትን ናፈቅን
========//==========
ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን
👍2
እንደ ክረምት ዝናብ
ችግሬ ይረግፋል
ምስኪን ትከሻዬ
እሱን ይቀበላል
ሰዎቹም ይላሉ
እንዴት ቻለው እሱ
ሁሌም ብልጭ ይላል
አይከደን ጥርሱ
የተበደለ ሰው
ችግር ላላት ነፍሱ
ኑሮ እንዴት ነው ቢሉት
ፈገግታ ነው መልሱ
@yismakeworku
ችግሬ ይረግፋል
ምስኪን ትከሻዬ
እሱን ይቀበላል
ሰዎቹም ይላሉ
እንዴት ቻለው እሱ
ሁሌም ብልጭ ይላል
አይከደን ጥርሱ
የተበደለ ሰው
ችግር ላላት ነፍሱ
ኑሮ እንዴት ነው ቢሉት
ፈገግታ ነው መልሱ
@yismakeworku
ችግር አጎበጠኝ
መሬት ልደፋ ነው፣ አምላኬም ዝም አለ
ጋኑን ጨብጬ ሳል
ቁልፉ ግን የታለ
እያልኩኝ ሳማርር
ድፍን ኦናው ልቤ
ምኑን አስተዋለ
ለካ
የአምላኬ እጆች
ወደ ታች ሲደፍቀኝ
በአምሳለ ችግር
ቁልፌን ስላየው ነው
ከታች ከራሴ እግር
@yismakeworku
መሬት ልደፋ ነው፣ አምላኬም ዝም አለ
ጋኑን ጨብጬ ሳል
ቁልፉ ግን የታለ
እያልኩኝ ሳማርር
ድፍን ኦናው ልቤ
ምኑን አስተዋለ
ለካ
የአምላኬ እጆች
ወደ ታች ሲደፍቀኝ
በአምሳለ ችግር
ቁልፌን ስላየው ነው
ከታች ከራሴ እግር
@yismakeworku
ሻሎም!
ወዳጄ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት በቴሌግራም ከሰኞ ጀምሮ በደንብ አስተምራለሁና ይሄንን አዋጅ አሳውቅልኝ አለኝ።
ስለሆነም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትን በቴሌግራም መማማር የሚፈልግ ካለ ይሄን ተቀላቀሉ @ethioenglizegna
ወዳጄ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት በቴሌግራም ከሰኞ ጀምሮ በደንብ አስተምራለሁና ይሄንን አዋጅ አሳውቅልኝ አለኝ።
ስለሆነም የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርትን በቴሌግራም መማማር የሚፈልግ ካለ ይሄን ተቀላቀሉ @ethioenglizegna
አንድ ደስ የሚል ጥያቄ ተጠየቅኩ፡፡ የዴርቶጋዳ ተከታታይ
ሥራዎችን ልናሳትምልህ ነበር የሚል ጥያቄ ተጠየቅኩ፡፡
ይህ ደስ የሚል ጥያቄ ነው፡፡ በአንድ ላይ ለመታተም ግን
ገፃቸው በዙ ነው፡፡ ለአንባቢ ይወደዳል ብዬ ተከራከርኩ፡፡
1,176ገፅ ነው ያለው፡፡ አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰባ ስድስት
ገፅ ይሆናሉ ተከታታዮቹ፡፡ ማለትም፣ ዴርቶጋዳ፣
ራማቶሓራ፣ ዣንቶዣራ፣ ዮራቶራድ፣ ዮቶድ በአንድ ጥራዝ
ቢሆኑ፡፡
እነዚህን በአንድ ቅፅ ለማሳተም ደግሞ በእኛ ሀገር
ማተሚያ ቤት ውድ ነው፡፡ አቡዳቢ ተሞከረ፡፡ እርሱን እኛ
እንጨነቅበት ብለው በአንድ ላይ ጠረዙአቸው፡፡ ያኔ
ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ አበረቱኝ፡፡ ቀሰቀሱኝ፡፡ ሁሉም በአንድ
በመጠረዛቸው፣ ለትውልድ ይተላለፉ አሉ፡፡ እኔም መርቄ
ለመቀበል እየተዘጋጀሁ ነው፡፡ እናንተም መርቋቸው፡፡እኔም
ተነብቤ ለመተቸት ሊያበቁኝ እየመጡ ነው፡፡ ለመተቸት
ዝግጁ ነኝ፡፡ ግን ሙሉውን ያላነበበ ተቺ አሁንም
አልቀበልም፡፡ የኢትዮጵያ ደራሲ ከመተቸት በቀር ገንዘብ
አያገኝም፡፡ ገንዘቡ፣ አንድ እጁ (ብዙው) ለማተሚያ ቤት፣
አንድ እጁ ለአከፋፋይ፣ በመጨረሻ የደራሲው ጉርሻ
የሚሆነው ጥቂት ገንዘብ እና ብዙ ትችት ሳይሆን ከንቱ
ስድብ ነው፡፡ እኔም ብቻ አንብቡ እንጂ ባላነበበ ተቺ
ትችቴን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡
አንድ ጊዜ በኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የመላው አፍሪካ
ጸሀፍት ተሰባስበው ዝግጅት ነበረ፡፡ እኔም ተጋብዤ ነበር፡፡
በአፍሪካ ደረጃ በራሷ ቋንቋ ተፅፎ ተነባቢ የሆነ መጽሐፍ
ሲታጭ አንዱ የእኔ ሆነ፡፡ በዛ ወቅት ሁለቱ ብቻ ነበር
የወጡት፡፡ ዴርቶጋዳ እና ራማቶሓራ፡፡ ሌሎቹ
እንደተለመደው የህትመት ብርሃንን አላዩም ነበር
ተከታታዮቹ፡፡በእንግሊዘኛ ቋንቋ ዶክተር ተስፋዬ የሚባሉ
ምሁር አቀረቡት፡፡ እኔን አያውቁኝም፡፡
... ዶክተሩ በእኔ ስራዎች ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ ላይ
(በእንግሊዝኛ ነው ፅሁፉ የቀረበው) በጥናቱ ላይ
ውይይት ተጀመረ፡፡ አንድ ሱዳናዊ የሰጠው አስተያዬት ግን
እስከ አሁን በውስጤ ይመላለሳል፡፡ "ከኬንያ ጫፍ ጀምሮ፣
እስከ እኔ ሀገር ሱዳን ድረስ እንጽፋለን፡፡ የምንጽፈው ግን
በቅኝ ገዥዎቻችን ቋንቋ ነው፡፡ በናይጀሪያ አካባቢ ጥሩ
የስነ ፅሁፍ ሰዎች እንዳሉ ይነገራል (ወደ እነሱ ዞሮ)፡፡
ግን በቅኝ ገዢዎቻችን ቋንቋ ነው የፃፉት፡፡ እናንተ
ኢትዮጵያውያን ግን ልዩ ናችሁ፡፡ እናንተ ለእናንተ
ትጽፋላችሁ፡፡ እናንተ እስከ ዛሬ ድረስ በየእለቱ ቅኝ
አልተገዛችሁም፡፡ በእናንተ ቋንቋ ትፅፋላችሁ!) " ... እኔ
እግሬን ዘረጋሁ፡፡ ለካ በራስ ቋንቋ መጽሐፍም ቅኝ
አለመገዛትን እንዲህ ያመለክታል፡፡ ከዚህ አስተያዬት በፊት
ግን በር አካባቢ እግሬን ኮድኩጄ ተቀምጨ ነበር፡፡ ከዚህ
አስተያየት በሁዋላ ዶክተር ተስፋዬን አገኘሁዋቸው፡፡
ያልተማረው ኢህአዴግ አርባ ምሁራንን ከአዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ሲያባርር፣ እንግሊዝ ሀገር ያስተምሩ ነበር፡፡
ያውም በስነ ጽሁፍ፡፡ ይህንን ካልኩ ዘንዳ ሙሉውን
ሳታነቡ ከትቺት እንድትቆጠቡ እያሳሰብኩ (ምን ይላል?
ደራሲ ሆኖ አትተቹኝ ይላል እንዴ) እያላችሁ ይሆናል፡፡ እኔ
አንብቡ እና ተቹኝ ነው ያልኩት፡፡ ሳያነብ የሚተች አንባቢ
ነው ያለን እያልኩ ነው፡፡
@yismakeworku
ሥራዎችን ልናሳትምልህ ነበር የሚል ጥያቄ ተጠየቅኩ፡፡
ይህ ደስ የሚል ጥያቄ ነው፡፡ በአንድ ላይ ለመታተም ግን
ገፃቸው በዙ ነው፡፡ ለአንባቢ ይወደዳል ብዬ ተከራከርኩ፡፡
1,176ገፅ ነው ያለው፡፡ አንድ ሺህ አንድ መቶ ሰባ ስድስት
ገፅ ይሆናሉ ተከታታዮቹ፡፡ ማለትም፣ ዴርቶጋዳ፣
ራማቶሓራ፣ ዣንቶዣራ፣ ዮራቶራድ፣ ዮቶድ በአንድ ጥራዝ
ቢሆኑ፡፡
እነዚህን በአንድ ቅፅ ለማሳተም ደግሞ በእኛ ሀገር
ማተሚያ ቤት ውድ ነው፡፡ አቡዳቢ ተሞከረ፡፡ እርሱን እኛ
እንጨነቅበት ብለው በአንድ ላይ ጠረዙአቸው፡፡ ያኔ
ከእንቅልፌ ነቃሁ፡፡ አበረቱኝ፡፡ ቀሰቀሱኝ፡፡ ሁሉም በአንድ
በመጠረዛቸው፣ ለትውልድ ይተላለፉ አሉ፡፡ እኔም መርቄ
ለመቀበል እየተዘጋጀሁ ነው፡፡ እናንተም መርቋቸው፡፡እኔም
ተነብቤ ለመተቸት ሊያበቁኝ እየመጡ ነው፡፡ ለመተቸት
ዝግጁ ነኝ፡፡ ግን ሙሉውን ያላነበበ ተቺ አሁንም
አልቀበልም፡፡ የኢትዮጵያ ደራሲ ከመተቸት በቀር ገንዘብ
አያገኝም፡፡ ገንዘቡ፣ አንድ እጁ (ብዙው) ለማተሚያ ቤት፣
አንድ እጁ ለአከፋፋይ፣ በመጨረሻ የደራሲው ጉርሻ
የሚሆነው ጥቂት ገንዘብ እና ብዙ ትችት ሳይሆን ከንቱ
ስድብ ነው፡፡ እኔም ብቻ አንብቡ እንጂ ባላነበበ ተቺ
ትችቴን ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፡፡
አንድ ጊዜ በኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የመላው አፍሪካ
ጸሀፍት ተሰባስበው ዝግጅት ነበረ፡፡ እኔም ተጋብዤ ነበር፡፡
በአፍሪካ ደረጃ በራሷ ቋንቋ ተፅፎ ተነባቢ የሆነ መጽሐፍ
ሲታጭ አንዱ የእኔ ሆነ፡፡ በዛ ወቅት ሁለቱ ብቻ ነበር
የወጡት፡፡ ዴርቶጋዳ እና ራማቶሓራ፡፡ ሌሎቹ
እንደተለመደው የህትመት ብርሃንን አላዩም ነበር
ተከታታዮቹ፡፡በእንግሊዘኛ ቋንቋ ዶክተር ተስፋዬ የሚባሉ
ምሁር አቀረቡት፡፡ እኔን አያውቁኝም፡፡
... ዶክተሩ በእኔ ስራዎች ላይ ባቀረቡት ጽሁፍ ላይ
(በእንግሊዝኛ ነው ፅሁፉ የቀረበው) በጥናቱ ላይ
ውይይት ተጀመረ፡፡ አንድ ሱዳናዊ የሰጠው አስተያዬት ግን
እስከ አሁን በውስጤ ይመላለሳል፡፡ "ከኬንያ ጫፍ ጀምሮ፣
እስከ እኔ ሀገር ሱዳን ድረስ እንጽፋለን፡፡ የምንጽፈው ግን
በቅኝ ገዥዎቻችን ቋንቋ ነው፡፡ በናይጀሪያ አካባቢ ጥሩ
የስነ ፅሁፍ ሰዎች እንዳሉ ይነገራል (ወደ እነሱ ዞሮ)፡፡
ግን በቅኝ ገዢዎቻችን ቋንቋ ነው የፃፉት፡፡ እናንተ
ኢትዮጵያውያን ግን ልዩ ናችሁ፡፡ እናንተ ለእናንተ
ትጽፋላችሁ፡፡ እናንተ እስከ ዛሬ ድረስ በየእለቱ ቅኝ
አልተገዛችሁም፡፡ በእናንተ ቋንቋ ትፅፋላችሁ!) " ... እኔ
እግሬን ዘረጋሁ፡፡ ለካ በራስ ቋንቋ መጽሐፍም ቅኝ
አለመገዛትን እንዲህ ያመለክታል፡፡ ከዚህ አስተያዬት በፊት
ግን በር አካባቢ እግሬን ኮድኩጄ ተቀምጨ ነበር፡፡ ከዚህ
አስተያየት በሁዋላ ዶክተር ተስፋዬን አገኘሁዋቸው፡፡
ያልተማረው ኢህአዴግ አርባ ምሁራንን ከአዲስ አበባ
ዩኒቨርስቲ ሲያባርር፣ እንግሊዝ ሀገር ያስተምሩ ነበር፡፡
ያውም በስነ ጽሁፍ፡፡ ይህንን ካልኩ ዘንዳ ሙሉውን
ሳታነቡ ከትቺት እንድትቆጠቡ እያሳሰብኩ (ምን ይላል?
ደራሲ ሆኖ አትተቹኝ ይላል እንዴ) እያላችሁ ይሆናል፡፡ እኔ
አንብቡ እና ተቹኝ ነው ያልኩት፡፡ ሳያነብ የሚተች አንባቢ
ነው ያለን እያልኩ ነው፡፡
@yismakeworku
በአንድ ጥራዝ ላይ የሰፈረው የዴርቶጋዳ ተከታታይ
መጽሐፍ እጄ ላይ ገባ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ
የተሳተፋችሁትን ሁሉ በአንባብያን ስም የሞቀ ምረቃዬን
እነሆ፡፡ ፈጣሪ ያክብርልኝ፡፡በሁሉም መጽሐፍ አከፋፋይ
እጅ ላይ እንደሚገባ ነግረውኛል፡፡
@yismakeworku
መጽሐፍ እጄ ላይ ገባ፡፡ በዚህ መጽሐፍ ላይ
የተሳተፋችሁትን ሁሉ በአንባብያን ስም የሞቀ ምረቃዬን
እነሆ፡፡ ፈጣሪ ያክብርልኝ፡፡በሁሉም መጽሐፍ አከፋፋይ
እጅ ላይ እንደሚገባ ነግረውኛል፡፡
@yismakeworku
Forwarded from Yismake Worku
ህይወት ነች ወላዋይ
ከላይ ሲሏት ከታች፣ ከታች ሲሏት ከላይ
ሲሳይ ሲደራረብ፣ መሬት የምትገኝ
መሬት ልመጅ ሲሏት፣ ሲሳይ የምትመኝ
ከሞላችም ከሩብ
ስትጎል ለሩብ ጉዳይ
ነሳች ሲባል ሰጪ፣ ሰጠች ሲባል በዳይ
ህይወት ነች ወላዋይ።
(ይስማዕከ)
@yismakeworku
አሁን የተቀነጨበ
ከላይ ሲሏት ከታች፣ ከታች ሲሏት ከላይ
ሲሳይ ሲደራረብ፣ መሬት የምትገኝ
መሬት ልመጅ ሲሏት፣ ሲሳይ የምትመኝ
ከሞላችም ከሩብ
ስትጎል ለሩብ ጉዳይ
ነሳች ሲባል ሰጪ፣ ሰጠች ሲባል በዳይ
ህይወት ነች ወላዋይ።
(ይስማዕከ)
@yismakeworku
አሁን የተቀነጨበ
👏1