ጋሽ ስብሐት በህይዎት ሳለ፤ አሁንም አልሞተም። ለእኔ የፃፈ አይሞትም (ጀግና አይሞትም እንደሚባል ሁሉ። በተንኮል ግን ለዘላለም መኖር አይቻልም)።
አንድ ቀን "ሌቱም አይነጋልኝን" የመሰለ ልቦለድ ፅፈሀል። ዙሩ እንዲሞላ ...ለምን "ቀኑም አይመሽልኝ" ብለህ አትጽፍም? አልኩት ለጋሽ ስብሀት። አንተ እንደምትለው እኮ በወዘተርፈ የሚኖሩ ማለትም ቀኑ የማይመሽላቸው ሰዎች አሉ። ብዙ ሰዎች በወዘተርፈ ነው የሚኖሩት ስለው።
"ጥሩ ሀሳብ ነው። ግን እኔ አልጽፈውም። ስለዚህ አንተ እየጻፍክ አምጣውና እንወያይበት" አለኝ።
በዛ ጊዜ የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነበርኩና በየወሩ ብዙ ምዕራፍ እየያዝኩ እሄዳለሁ። አነብለታለሁ። ያርመኛል። ሳልጨርሰው ሞት ቀደመው (ለእኔ ባይሞትም) ከዛ በሁዋላ ጊዜ ፈጀብኝ።
@yismakeworku

👍125🔥38❤33👏15🥰1
ብቸኝነት ሲሰማህ ማሰብ ከቻልክ የአሳብህ ጓደኛ ነህ። ማሰብ ካልቻልክ ብቻህን ነህ። መነጠል የስጋ ሳይሆን የአሳብ ስሜት ነው። ብቸኝነትህን አሳብህ ሲጋራ የአሳብ ጓደኛ አለህ። ብቸኝነትም ጓደኝነትም ስጋ አይደለም። የአብሮነትና የመነጠል ስሜት ነው።
ከሰው ጋር ስትሆን ለብቻህ እንደሆንክ ከተሰማህ በግርግር መሀል ብቸኛ ነህ። በስጋህ ብቻህን ሆነህ ከአሳብህ ጋር አብረህ ከሆንክ አንተማ ጓደኛ አለህ። ከቻልክ የወዳጅ አስፈላጊነትን ቀንስ። ሰው ብታጣም ያጣኸው ስጋ ነው። አብሮህ የሆነ አላቂ ነው። ዛሬ የሚቀርብህ ነገ የሚርቅ ነው። ወሳኙ ጉዳይ ህሊናህን አለማጣትህ ነው። የሌላ ስጋ ሲለይ አሳብህ ካንተ ጋር ነው።
.
መለየት የስጋ ነው። ብቻህን እንዳልሆንክ ከተሰማህ የአንተ ጓደኛ ስሜትህ ነው።
ይስማዕከ ወርቁ!

🥰108👍90❤35👏6🍾2
ወዴት ነህ ይለኛል፣
ሊያሳፍረኝ ታክሲ፣
ሊጭነኝ ወያላ፤
እኔና ሀገሬ፣
እኔድበት መንገድ፣
ግብ እንዳለን ሁላ!
/ይስማዕከ ወርቁ/
ሊያሳፍረኝ ታክሲ፣
ሊጭነኝ ወያላ፤
እኔና ሀገሬ፣
እኔድበት መንገድ፣
ግብ እንዳለን ሁላ!
/ይስማዕከ ወርቁ/
❤214👍55😢34👏15🔥4
መሆን ከተመኘህ ፣ ዛፍነትን ምረጥ
ቆርጠዉህ ሲሄዱ ፣ ሺ ሆነህ አቆጥቁጥ
(ይስማዕከ ወርቁ)
ፎቶው በስራ ላይ እያለን የተነሳ ነው።
ቆርጠዉህ ሲሄዱ ፣ ሺ ሆነህ አቆጥቁጥ
(ይስማዕከ ወርቁ)
ፎቶው በስራ ላይ እያለን የተነሳ ነው።
👍230❤48👏8🔥4
"በዚህ ዘመን ሰዎችን ባለፈ ታሪካቸው ማመን ሞኝነት ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ከመልአክነት ወደ ፍፁም ሰይጣንነት ሲቀየሩ አይተናል። ትናንት የኮሚኒዝም መዘምራን የነበሩት ዛሬ የካፒታሊዝም ጳጳሳት ሆነዋል፡፡ የሰው ልጅ እንኳንስ አቋሙን ጥብቅ ሃይማኖቱን ሲቀያይር ማየት የተለመደ ነው፡፡ የት ይደርሳል የተባለ በፍቅር ያበደ ትዳር ሲፈርስ አይተናል፡፡
ሰዎችን በመሃላ አስሮ መልቀቅ የዚህ ዘመን ሊቅ ነው..."
---
ዮቶድ - ዴርቶጋዳ 5
(ይስማዕከ ወርቁ)
ሰዎችን በመሃላ አስሮ መልቀቅ የዚህ ዘመን ሊቅ ነው..."
---
ዮቶድ - ዴርቶጋዳ 5
(ይስማዕከ ወርቁ)
🥰126👍90❤42👏13🔥4
"ህልሜን አላቀልጥም"
(ይስማዕከ ወርቁ፡ ከጀርመን)
;
ወታደርም ቢባል
ያው በቀቀናም ነው፣
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
አሸናፊም ብትል
ይፈራል ነገውን
ፍርሃት አለው ነውጡ፣
ንጉሠ ነገሥትም
ፍርሃት አለ ቆጡ፣
አንበሳ ደቦሉም
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
ማንኛውም ብትል
ጠልፎ የሚጥል ሰው
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
"ብተወውስ" ብሎ
ይፈራል ታንቲራ፤
እኔ ግን የምልህ
ህልምህን አትፍራ፣
ድፈረው፣ ድፈረው
ወንጀለኛ አይልህም ፍርድ ቤቱ ደፍሮ
አቃቤ ህግ አይከስ፣
እንዲያውም ይፈራል-ይፈራል ወጥሮ
ህልምህን የምተው...
ወመኔ 'ሚዘራው
ገንዘብ ስላጣህ ነው?
ተስፋ ስላጣህ ነው?
ያዘው ግፋ ብሎ
ተስፋን የሚመግብ
ቤተሰብ ነው ያጣህ?
ወይስ ነው ከጀርባህ
ኦና ሆኖ ታየህ?
እኔ ግን የምልህ
እኔ የምመክርህ፣
እንዳትመለስ ነው
ከተስፋ ከእድልህ
እኔ የሚታየኝ
እኔ እንደሚሰማኝ፣
ችግርም ብትፈጥር
በራስህ ላይ ወጥር
ለውጥ አምጣ
ለውጥ አምጣ
ቀን አውጣ
ቀን አውጣ
ችግርና ፍዳህ የመኖርህ ትርጉም
ላብ ነህ ለዚህ ምድር
ወዝ ነህ ለዚህ ዓለም፡፡
ወዝና ጊዜየን በቁሜ ብቀማም
እንደ አሸን ተራግፈው
ጓደኞቼን ባጣም
ወደሁዋላ ስዞር
አንድም ሰው ባይመጣም
ተስፋዬን አልሸጥም
ህልሜን አላቀልጥም፡፡
-----------------------
(ፀሐፊ-ይስማዕከ; ህዳር 14፣ 2011 ዓ.ም)
(ይስማዕከ ወርቁ፡ ከጀርመን)
;
ወታደርም ቢባል
ያው በቀቀናም ነው፣
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
አሸናፊም ብትል
ይፈራል ነገውን
ፍርሃት አለው ነውጡ፣
ንጉሠ ነገሥትም
ፍርሃት አለ ቆጡ፣
አንበሳ ደቦሉም
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
ማንኛውም ብትል
ጠልፎ የሚጥል ሰው
ፍርሃት አለ ውስጡ፣
"ብተወውስ" ብሎ
ይፈራል ታንቲራ፤
እኔ ግን የምልህ
ህልምህን አትፍራ፣
ድፈረው፣ ድፈረው
ወንጀለኛ አይልህም ፍርድ ቤቱ ደፍሮ
አቃቤ ህግ አይከስ፣
እንዲያውም ይፈራል-ይፈራል ወጥሮ
ህልምህን የምተው...
ወመኔ 'ሚዘራው
ገንዘብ ስላጣህ ነው?
ተስፋ ስላጣህ ነው?
ያዘው ግፋ ብሎ
ተስፋን የሚመግብ
ቤተሰብ ነው ያጣህ?
ወይስ ነው ከጀርባህ
ኦና ሆኖ ታየህ?
እኔ ግን የምልህ
እኔ የምመክርህ፣
እንዳትመለስ ነው
ከተስፋ ከእድልህ
እኔ የሚታየኝ
እኔ እንደሚሰማኝ፣
ችግርም ብትፈጥር
በራስህ ላይ ወጥር
ለውጥ አምጣ
ለውጥ አምጣ
ቀን አውጣ
ቀን አውጣ
ችግርና ፍዳህ የመኖርህ ትርጉም
ላብ ነህ ለዚህ ምድር
ወዝ ነህ ለዚህ ዓለም፡፡
ወዝና ጊዜየን በቁሜ ብቀማም
እንደ አሸን ተራግፈው
ጓደኞቼን ባጣም
ወደሁዋላ ስዞር
አንድም ሰው ባይመጣም
ተስፋዬን አልሸጥም
ህልሜን አላቀልጥም፡፡
-----------------------
(ፀሐፊ-ይስማዕከ; ህዳር 14፣ 2011 ዓ.ም)
👍167❤59👏14🔥5🥰5
Yismake Worku via @like
ብዙ ሰዎች ማስታወቂያ በማህበራዊ ሚዲያዎቼ ላይ ስለጥፍ አያምርብህም፣ አንተ ጋር አይሄድም፣ አይመጥንህም ይሉኛል። አይመጥንህም ምን ማለት ነው?
የሰው ልጅ ስለ አንድ ሰው የሆነ ስዕል ይስላል፣ ከዛም ያ ሰው ከሱ ስዕል እንዲወጣ አይፈልግም። ዘመኑ ወደድንም ጠላንም በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተመራ ነው ለዛም የተለያዩ ስራዎች ይሰራሉ። ማስታወቂያ አስገዳጅ አይደለም። መንገር፣ እዩልኝ፣ ሞክሩልኝ ብሎ መለፈፍ ነው። ፍላጎቱ ያለው አይቶ ይሞክረዋል፣ የሌለው ደግሞ ያልፈዋል። ይሄም የሚያሳየው አብዛኞቻችን ስለ ገንዘብ፣ ስለ ስራ እንዳልገባን ነው፣ ውጮቹ Financial Literacy ስለሚሉት ነገር ምንም እንደማናውቅ ነው። አቆማለሁ? በጭራሽ! ከችግርተኞች ላይ ፣ ከአደራ ላይ፣ ከሰው ላይ የወሰድኩት ምንም ነገር የለም። ወጣቶች፣ በጎን ስራ መስራት፣ ተስፋን ማየት አታቁሙ።

👍192❤21👏10
❤184👍73
አንድን ወንጀል ተደጋጋሚ ከሚያደርጉ አስቻዮች (Enablers) አንዱ ከወንጀሉ ጋር የተያያዘው የማህበረሰብ የወል ሰነ ልቦና ነው። አስገድዶ መድፈር በሀገራችን እንደ ወረርሽኝ የተሰፋፋ እና ጉዳቱ በተበዳይ ሳያበቃ ማህበራዊ ሰቀቀን (Social trauma)የሚያሰከተል ቢሆንም የወል ስነ ልቦናችን በፈጠረለት አስቻይ ነባራዊ ሁኔታ መደበኛ የዕለት ዜና ሆኖ ቀጥሏል።
ሌሎች ላይ ዘላቂ ጉዳት የሚያደርስ መስል ጸያፍ ድርጊት በማህበራዊ ውግዘትና በህጋዊ ቅጣት መከላከልና መቀነስ ያልተቻለው ድርጊቱን የሚያበረታታ ማህበራዊ ስነ ልቦና እና የህግ ድክመት በመኖሩ ነው። ከለከፋ ጀምሮ እስከ ጠለፋ የሚደርሰው የትንኮሳና የጥቃት ስንሰለት ብዙ ጊዜ ሰዉር ማህበረስባዊ ድጋፍ አለው። ያሉት ጥቂት ውግዘቶችም ቢሆኑ ጥፋቱ ላይ እንጂ ጥፋቱን ያሰቻለው ከባቢ ላይ አያተኩሩም። ተበዳይን በግል ምርጫዋና አለባበሷ የችግሩ ምንጭ ከማድረግ የሚጀምር የወል ስነ ልቦና ባለበት ተጨባጭ ወንጀሉን ለመቀነስ ህግም ሆነ ማህበራዊ ውግዘት አቅም የላቸውም። መሰል ጥቃት ሴቶች ላይ፥ ህጻናት ላይ፥ ሴት ልጅ ያላቸው ወላጆች ላይ፥ በደልን የሚጠየፉ ዜጎች ላይ የተፈጸመ አካላዊውና ሰነ ልቦናዊ ክፉ ጥቃት ቢሆንም ከተራ ወንጀል ያለፈ ትኩረት ያልተሰጠው የወል ሰነ ልቦናችን ስለሚያሳንሰው ነው።
ለከፋን እንደ እርድና፥ ሴሰኝነትንና ጾታዊ አጥቂነትን እንደ ወንዳወንድነት የሚቆጥር የማህበረስብ ሰሪት እጩ ደፋሪዎች በማምረት ተወዳዳሪ የለውም። ለዛም ነው ራቁቱን ኤርታሌ ውስጥ ሊነከር የሚገባው ወንጀለኛ "የህግ ተቀላቢ" የሆነው።
Ibrahim Abdu

👍75😢26❤8
👍137❤18
ወዳጄ በእውቀቱ እንደፃፈው... #ሼር አድርጉት!
የሚያሳስበኝ
(በእውቀቱ ስዩም)
ዶስተየቨስኪይ የተባለ የሩስያ ደራሲ ልቦለድ ውስጥ የሚገኝ ኢቫን የተባለ ገጸባህርይ ” ሰውን አውሬ ብሎ መጥራት አራዊትን እንደ መስደብ ይቆጠራል ይላል ፤” ሰው የበጎነት አቅም ያለውን ያህል ፥ በጭካኔ የሚወዳደረው የእንስሳ ዝርያ የለም፤ አንበሳ ሚዳቆን የሚገድለው በልቶ ማደር ስላለበት ነው፤ ሳይቸግረው ያለ አላማ መሰሉን፥ የሚገድል፥ ብጤውን በማሰቀየት የሚደሰት ፍጡር ሰው ብቻ ነው፤
ልጅ ሆኜ በጎችን አሰማራ ነበር፤ ግልገል በግ የሚደፍር ትልቅ በግ አይቼ አላውቅም ፤ ወንዱ በግ ፥ደረሰች በግ ላይ ለመውጣት ራሱ ወቅት ይጠብቃል፤ ለርቢ መድረሷን አሽትቶ ካላረጋገጠ በቀር አይደርስባትም፤
የሰባት አመትዋን ሄቨንን ለመስማት በሚገዘገንን ጭካኔ ደፍሮ የገደላትን ሰውየ “ እንስሳ ፥ወይም አውሬ” ብሎ መጥራት ፍትሀዊ የማይሆነው ለዚህ ነው፤ እንዲህ አይነቱ ቀፋፊ ፍጡር የሚገልጽ ሌላ ቅጽል ተፈጥሮ መዝገበቃላት ውስጥ መካተት አለበት፤
ህግ ካለ ይህ ወንጀለኛ እንደ ምግባሩ ፍዳውን መቀበል ይገባዋል፤ እሱ ብቻ ሳይሆን ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሞከሩ እና የዶለቱ ሁሉ ከቅጣቱ ድርሻቸውን ማንሳት አለባቸው፤
አስገድዶ ደፈራ በዋናነት የወሲብ ጉዳይ አይደለም፤ የፈሪዎች እና የግፈኞች “ሀይል “ መግለጫ ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሰባ ምናምን አመት ሴት የደፈረ ጎረምሳ በአስራት መቀጣቱን የሚገልጽ ዜና ማንበቤ ትዝ ይለኛል ፤ የሰባ አመት ባልቴት እና የሰባት አመት ሴት ሁለቱም ለሩካቤ የሚያሳስብ ነገር የላቸውም፤ ግን ሁለቱም አንድ የሚያደርጋቸው አቅም አልባ መሆናቸው ነው፤ ራሳቸውን ከደፋሪው መከላከል አይችሉም፤ ደፋሪዎች ብዙ ጊዜ ፈሪዎች ናቸው፤ ከሚበልጣቸው ጋራ ወይም ከእኩያቸው ጋራ ጉልበት እንደማይፈታተሹ ያውቁታል፤ በጉልበት የሚያንሳቸውን፤ ሀብት ስልጣን ወይም ወገን የለውም ብለው የሚያስቡትን ከማጥቃት ግን አይመለሱም፤ ብዙ ጊዜ የጥቃት ሰለባዎችን ስናይ ህጻናት፥ የቤት ሰራተኞች፥ እንግዶች፥ የመንገድ ዳር ተዳዳሪዎች ወይም በጦርሜዳ ላይ ያለ ታዳጊ የቀሩ ሴቶች ናቸው፤
ለወላጆች አንድ የጭንቅ ቀን ምክር አለኝ፤ ጨካኝ ፤ጭቦኛና ቀፋፊ ባህርይ ያላቸው ሰዎች
የትም እና መቼም ይኖራሉ፤ሰርሲ ላንስተር እንደተናገረችው Everywhere in the world they hurt little girls ."
ፈታኝ አለም ውስጥ እንደምንኖር አንርሳ፤ ሁሌም በህግ በፈሪሀ እግዚአብሄር እና በባህል በጭምት ፊት ተማምነህ መዘናጋት የለብህም፤የልጆችህ ወታደር መሆን አለብህ ፤ ልጆችሽን እንደ አይንሽ ብሌን ጠብቂ ! ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ፤ግን ሌላ ምን አማራጭ አለ?
#ሼር አድርጉት

👍192❤49
👍162❤56🥰9👏4