Yismake Worku
Photo
"ፍቅሬን በይስማዕከ መፅሀፎች" (ተገጠመ በህይዎት ዘውዴ)
እኔ እወድሃለሁ
ውብ ነው ንግግርህ እንደ ዴርቶጋዳ፣
ከምትወደው በላይ ሚራዥን ሜሮዳ፣
ከልቤ ወድጄህ ገብቻለሁ እዳ።
እኔ እወድሃለው!
እንደጣና ገዳም የይስማእከ አሳሳል፣
እንደ ሻጊዝ እውቀት የዲወላ ተንኮል።
እኔ እወድሃለሁ !
እንደ ክቡር ድንጋይ የረቀቀ ቅኔ፣
ከቃላት በላይ ነው ያንተ ፍቅር ለ'ኔ።
በልጅነት አቅሜ ያኔ እንዳነበብኩት፣
ባልረዳው እንኳን አይቼ እንዳለፍኩት።
እንደ ሜሎስ መፅሀፍ ትናፍቀኛለህ፣
በፍቅርህ የሳት ሰይፍ ልቤን እየበላህ።
ፍቅርህ ኦጋዴን ነው የበረሀ ሙቀት፣
ትንፋሽህ ይርጋለም የለምለም ምልክት።
ወደ ልቤግባ ከቤቴ ተከርቼም ፣
ወ'ድሃለውና አልቃወምህም።
እንደ ተልሚድ ድርሰት አምዕሮዬን ግዛው፣
በድሬ ተሻግረህ እንገናኝ እዚያው ።
የት ነው አትበለኝ!
ብትፈልግ ፒያሳ ከአቡነ ጴጥሮስ፣
ከሀውልቱ ደርባ አራዳው ጊወርጊስ።
ወይም ደግሞ ጣና ከሀይቁ ዳርቻ፣
እጠብቅሀለሁ ናልኝ አንተ ብቻ።
አንተ እንደተመቼህ!
ከፈለክ መቖለ ወይም ደግሞ አክሱም፣
ከተራራው አናት ብትፈልግ ድል ይብዛም።
ሳልሰስት ዘላለም እጠብቅሀለው፣
ፍቅርህ ለእኔነቴ እንደ ሀገሬ ነው።
አዎ እንደዚያች ሀገር!
በዴርቶጋዳ ላይ እንደተሳለችው፣
በምናብ አይተናት በውነት የጠፋቸው።
እናማ ፍቅሬ ሆይ!
መውደዴን ጨርሼ ዘርዝሬ ባልነግርህ፣
ከዛምራ በላይ ነው እኔ አንተን ስወድህ፣
ግን እንዲህ ሳፈቅርህ ባ'ክህ እንዳትኮራ፣
አይበጅህም እና ግፍን እንዳትሰራ፣
ግፉአዓኖች በዝተው ገፊም ተበራክቶ፣
ልክ እንደ ሀገሬ ብትገፋኝም ከቶ፣
በተስፋ ቃል ኪዳን ሁሌም ወ'ድሃለው፣
ፍቅርህ በልቤ ውስጥ ረቂቅ ተልሚድ ነው።
ተልሚድ ማለት ደግሞ
የረቀቀ ቅኔ የተሰወረ ቃል፣
ትርጉሙን ለማወቅ
ከራስ ተነጥሎ መሄድ ይጠይቃል።
ብቻ እስከማገኝህ ፍቅርህን ተርቤ፣
ደህንነቱን እንጃ የወደደህ ልቤ።
❤❤❤❤❤❤
(ሁላሁችንም አመሰግናችኋለሁ። የዚህ ሸጋ ግጥም ባለቤት "ህይዎት ዘውዴ" ስትሆን የስዕሉ ባለቤት ደግሞ "ማርታ ሳንታ" ናት። ህይዎቴ ተነቃቃ። ሁለቱም የልደቴ ስጦታዎች ናቸው። ለመለጠፍ ተቸግሬና ጉረኛ ላለመባል ነው እንጂ ብዙ አነቃቂ ነገሮች ደርሰውኛል። ከሽማግሌ እስከ እነ እማማ፣ ከወይዛዝርት እስከ ወጣት። ሁሉንም አንባቢዎቼን አመሰግናችኋለሁ። እነዚህ ደግሞ በምወደው ግጥምና በምወደው ስዕል ወደ ልጅነቴ መለሱኝ። 'እምቢ አላረጅም' የሚለውን አስታወሳችሁኝ። እውነት ለመናገር እስካሁን ያሳለፍኩት ጊዜ የብዙ ሰው እድሜ ይመስለኛል። የእኔ ህይዎት Triller ፊልም ይመስላል። እረፍት አልባ ፊልም። አንዱን ገፀ ባህሪ አባብዬ ስሸኘው አንዱ ሽመሉን ልጦ ይመጣል። ህይዎቴ እረፍት አልባ ነበር። እኔ ስተርከው በራሴ ላይ የሚደርሰውንና የሚቀጥለው ደግሞ እንዲህ ሆኖ እንደሚፈፀም በማዎቄ ነው። እንዲህ እንዲህ ያሉ አንባቢዎች አሉኝ። እኔ ምርቃት አልችልም። የጥበቡን መንገድ አብልጦ ይስጣችሁ። አሜን በሉ። የ40 ምናምን ቀን ሽማግሌ ሲመርቃችሁ ሁለት እጆቻችሁን እንደወረቀት ከታች ዘርግታችሁ ዓይኖቻችሁን ወደፈጣሪ አንጋጣችሁ አሜን በሉ)
ይስማዕከ ወርቁ❤❤❤❤❤❤

❤137👍36👏5🥰2
በዚህ የቴሌግራም ገፅ ወይም ከ235 ሺ በላይ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፅ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ ቤተሰቦች @AdvertOnPageBot በተሰኘው መድረክ ብታሳውቁኝ የሶሻል ሚዲያ ተቆጣጣሪው ሁሉንም ያሳውቃችኋል።
ማስታወሻ : ከማስታወቂያ የሚገኘው 50% ገቢ ለእርዳታ ድርጅት ይውላል።
መልካም!
ማስታወሻ : ከማስታወቂያ የሚገኘው 50% ገቢ ለእርዳታ ድርጅት ይውላል።
መልካም!
👍70
ትልቁ ችግሬ እኔ በራሴ የሆንኩትን ራሴን በትክክል የሚረዳ ማግኘት
አለመቻሌ ነው። ሁሉም ራሱን ሆኖ የሚኖር ሳይሆን ሌላውን አይቶ
የሚያኗኑር በመሆኑ ራሴን ስሆን በተሳሳተ መንገድ የሚረዳኝ ብዙ ነው።
አጥቼ ራሴን ሀኜ ስቀርብ ለማኝ፣ አግንቼ ራሴን ሆኜ ስቀርብ ሌባ አድርጎ የሚረዳ ብዙ ነው። ወደህ ስትቀርብ ተሸናፊ፣ ትተህ ስትርቅ ጠላት የሚያደርገው ብዙ ነው።
በግሌ የሰው አስፈላጊነት ባያስፈልገኝም ሰው የራሴን መሆን ትቶ በስህተት እንዲረዳኝ ግን አልፈልግም። በሰው ዘንድ በብዙ ጥርጣሬ ልታይ ብችልም በመጥፎ ጎኑ መታየት አልፈልግም።
የማልፈልገው መጥፎ ሆኜ መጠርጠርን ሳይሆን እንደጠረጠሩኝ መጥፎ ሆኜ መገኘት ስለማልችል ነው። ብችልማ ችግር የለውም። መጥፎ አድርገውኝ ሲጠረጥሩ የጠረጠሩትን ሆኖ መገኘት ነው።
እኔ የሚደብረኝ ነገር ራሴን ግልፅ አድርጌ አንዲያውቅ ያደረኩት ሰው ተደብቆ ስለኔ የሚፈጥረው ስሜት ነው። ከእኔ የሚፈልገው የእኔን እውነት የሚወክል እውቀት ነው ወይስ በራሱ የስሜት ሸራ የእኔን ምስል መሳል ነው? እኔን ለማወቅ ከኔ የሚጠበቀው ግዴታ ስለእኔ እውነታ መረጃ መስጠት ብቻ ነው።
እኔ እሱ ስለኔ የሚፈጥረው ስሜት መወሰን ስለማልችል ስለኔ የሰጠሁትን መረጃ አለማመኑ አያሳስበኝም።

❤133👍58
እኔን እንደ ጭቃ ጠፍጥፌ ልሥራህ ከሚለኝ ቦዘኔ ጋር በፍፁም አልጓዝም። በአዲሱ አመት ከቅርብ ምቀኞች ራሳችሁን ጠብቁ።
ድንጋይ የሚያሞቀውን ቦዘኔ ትታችሁት ወደፊት ተጓዙ! እዚህ ዘንድ አንዲት "የቀንዳውጣ ኑሮ" ላይ የተሰደረች ግጥም ትዝ አለችኝ።
"...ዘመን አይፈረጥጥ፣
ቀንም መሽቶ አይነጋ፣
ሰው ነው የሚጨልም፣
ሰው ነው የሚነጋ።"
ከሚያነጋላችሁ ሰው ጋር ነው መጓዝ ያለባችሁ። ከፊት ለፊታችሁ እንቅፋት ከሚያስቀምጥ ሰው ጋር፣ በአዲሱ አመት አንድም እርምጃ በፍፁም አትራመዱ።
መልካም ቀን ይሁንላችሁ 👍

👍157❤52😁2
በዚህ የቴሌግራም ገፅ ወይም ከ236,000 በላይ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፅ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ ቤተሰቦች @AdvertOnPageBot በተሰኘው መድረክ ስለ ድርጅታችሁ፣ ማስተዋወቅ ስለፈለጋችሁበት ሁናቴ ብታሳውቁኝ የሶሻል ሚዲያ ተቆጣጣሪው ሁሉንም ያሳውቃችኋል።
መልዕክት / ማስታወቂያ ለማስነገር ምን ያስፈልጋል ?
✅ ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ።
✅ ክፍያ በተመለከተ በመነጋገር መፈፀም ይቻላል።
✅ ረጅም ጊዜ ማስታወቂያ ከሆነ ውል ማዘጋጀት።
መልዕክት / ማስታወቂያ ለማስነገር ምን ያስፈልጋል ?
✅ ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ።
✅ ክፍያ በተመለከተ በመነጋገር መፈፀም ይቻላል።
✅ ረጅም ጊዜ ማስታወቂያ ከሆነ ውል ማዘጋጀት።
👍5❤4🔥3
መጥፎ ሰው ማለት እየፈለከው የማይፈልግህ ሳይሆን ሳትፈልገው ፈልጎህ የመፈለግ ስሜት ፈጥሮ የማይፈለግህ ሰው ነው!
ይኼው ነው!
ይኼው ነው!
❤102👍40
ጠላቴ ይቅርታ
ጠላቴ ሆይ በርታ፣
ተበራታ በርታ፡፡
ፊቴም እንዲወዛ፣
እግሬ እንዲወረዛ፡፡
ጠላቴ ሲበዛ፣
ጦሬም እንዲበዛ፡፡
"ሰው አለሁ እንዲለኝ"
በርታና በድለኝ፡፡
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ እግር የሚወለድፍ፣
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ የሚያስቀድመውን መድፍ፣
ህልሜን ልይዘው ስል፣ እጄን የሚመታ፡፡
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ እግሬን የሚመታ፡፡
ጠላት የሌለው ሰው፣ ቢወጣ ቢወርድም፣
ወይ ህልም አላለመም፣ ወደ ህልሙ አይሄድም፡፡
ውሎዬ እንዲሰምር፣ ቀኔን የሚመቀኝ፣
አዳሬ እንዲሰምር፣ ሌሊት የሚመቀኝ፣
ጠላቴን አትንሳኝ፣
ጠላት አታሳጣኝ፡፡
ተባለ ምኑን ሰው ፣
ጠላት የሌለው ሰው!
እባክህ ፈጣሪ፣ ጥሩ ጠላት ፍጠር፣
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ የሚያስቀድም ጠጠር፡፡
---
ይስማዕከ ወርቁ
ጠላቴ ሆይ በርታ፣
ተበራታ በርታ፡፡
ፊቴም እንዲወዛ፣
እግሬ እንዲወረዛ፡፡
ጠላቴ ሲበዛ፣
ጦሬም እንዲበዛ፡፡
"ሰው አለሁ እንዲለኝ"
በርታና በድለኝ፡፡
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ እግር የሚወለድፍ፣
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ የሚያስቀድመውን መድፍ፣
ህልሜን ልይዘው ስል፣ እጄን የሚመታ፡፡
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ እግሬን የሚመታ፡፡
ጠላት የሌለው ሰው፣ ቢወጣ ቢወርድም፣
ወይ ህልም አላለመም፣ ወደ ህልሙ አይሄድም፡፡
ውሎዬ እንዲሰምር፣ ቀኔን የሚመቀኝ፣
አዳሬ እንዲሰምር፣ ሌሊት የሚመቀኝ፣
ጠላቴን አትንሳኝ፣
ጠላት አታሳጣኝ፡፡
ተባለ ምኑን ሰው ፣
ጠላት የሌለው ሰው!
እባክህ ፈጣሪ፣ ጥሩ ጠላት ፍጠር፣
ወደ ህልሜ ስጓዝ፣ የሚያስቀድም ጠጠር፡፡
---
ይስማዕከ ወርቁ
👍111❤36🔥8
መምህር ኤስድሮስ የተባሉት ሊቅ ያስተማሩትን የመንፈስ ልጃቸዉን ሲመክሩ እንዲህ አሉት፡፡
"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"
@yismakeworku
"ልጄ ከመሃይም አትጣላ ፣ ደጋፊው ብዙ ስለሆነ ያሸንፍሃል"
@yismakeworku
❤143👍48🔥1