Yismake Worku
20.6K subscribers
334 photos
9 videos
1 file
69 links
Bilingual content in English & Amharic, author tips, book reviews, behind-the-scenes writing insights, and interactive community discussions.

Buy ads: https://telega.io/c/yismakeworku
Download Telegram
አመሰግናለሁ።
👍8
ወዳጆቼ በዚህ መድረክ በይበልጥ ምን እንድታገኙ ትሻላችሁ?
🅰 ጽሁፍና ግጥሞቼን
🅱 ስለኔ ወቅታዊ መረጃዎች
#ዛምራ ሁለተኛ እትም ቀርቧል። መጽሀፏን ፈልጋችሁ ያጣችሁ ከነገ ጀምሮ በድጋሚ እንደምትገኝ ለማሳወቅ እወዳለሁ።
👍11
ለምታከብሩት በሙሉ እንኳን ለፆመ ፍልሰታ አደረሳችሁ።

ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጉም ስናነሣ ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ /የተገኘ/ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ ከምድር ከመቃብር መለየት፣ ማረግ፤ ወደ ላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ያመለክታል፡፡

በዚህ መሰረት ጾመ ፍልሰታ በአጠቃላይ የእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋዋን ከመቃብር መለየትና ወደ ገነት ማረጉን የሚያመለክት ሲሆን ቅድስት ቤተክርስቲያን ምዕመናን እንዲጾሙት ከምታዘው አጽዋም አንዱና ለዓመቱ ደግሞ የመጨረሻው ጾም ነው፡፡

ይህ ጾመ ፍልሰታ በሌላ አጠራሩ ጾመ ማርያምም በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ወቅት በብዛት የሚወሳው /የሚነገረው/ቃለ እግዚአብሔር በአብዛኛው ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር የተያያዘ በመሆኑና የእርስዋ የሥጋዋ ፍልሰት መታሰቢያ በመሆኑ ጾመ ማርያም ተባለ፡፡

መልካም የጾም ወቅት ይሁንልን!
@yismakeworku
6👍3
Forwarded from Yismake Worku
በፌስቡክ ገጽ በተደጋጋሚ ከሚደርሱኝ ጥያቄዎች መካከል ከዚህ በፊት ተጀምሮ የነበረው ከዛም ተማሪዎችን ሲያስተምር የነበረው የእንግሊዝኛ ቋንቋ መማርያ ቻናል የት ጠፋ የሚል ነው።

በመሆኑም በጣም ብዙ ሰዎች እየተመዘገቡ የጊዜ መጣበብ ስላለ በፕሮግራም ትምህርቱ ሊጀመር እንደሆነ ነግረውኛል - አዘጋጆቹ።

ስለዚህ የመጀመሪያውን የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት የሚያገኙት በውጭ ሀገራት እና አረብ ሀገራት የሚኖሩ ሰዎች ናቸው።

በእነዚህ ሀገራት የምትኖሩ እንግሊዝኛ ቋንቋ መማር የምትፈልጉ ብቻ @ethioenglizegnaBot በመግባት እንድትመዘገቡ እና ትምህርት እንድትጀምሩ ይላሉ። 10 ተማሪዎች ብቻ ነው ሊያስተምሩ ያቀዱት እና ወደ @ethioenglizegnaBot በመግባት ስለ ምዝገባው እና ዋጋው ጠይቃችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ።


በጎ ስራ ለሚሰራ እውቅና መስጠቴ ይቀጥላል!
@yismakeworku
👍1
ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ <<ተመስገን>> በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!

እጅግ የምወደው የሙያ አባቴ ደራሲ ስብአት ገብረ እግዚአብሔር

@yismakeworku
👍272
. . .ናቅን
መቻቻልን ናቅን ለፀብ አሟሟቅን
ለአመፅ ስንነሳ ለሰላም ወደቅን
አገር ስትቃጠል ከዳር ሆነን ሞቅን . . .

ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን
@yismakeworku
1👍1
ከክፋት ዘመን መድረስ እድሜ አይባልም!
---
@yismakeworku
1
የፌስቡክ ገጼ ላይ ማስታወቂያውን የተመለከታችሁ በሙሉ @Yismake_workubot በመግባት ላኩልኝ።
ማስታወቂያ!
ሰላም ወዳጆች የፌስቡክ ገጽ ከሁለት መቶ ሃያ አንድ ሺ ተከታዮች እንዳሉት እሙን ነው። ስለሆነም ሁላችንም እንደ አንድ ቤተሰብ አንዳንድ ስራዎች በጋራ እንድንሰራ እጠይቃለሁ።
፩. በሳምንት ለሁለት ቀናት /ማክሰኞ እና አርብ/ የእርዳታ ማሰባሰብ ፕሮግራም ይሆናል። ስለሆነም እናንተ ሁሌም ማክሰኞ እና አርብ 3 ሰዓት ማታ ላይ ለምንለጥፈው የእርዳታ ጥሪ የቻላችሁትን በመለገስ ካልሆነም ደሞ #ሼር የተባለ መድፍ ይዛችሁ በመተኮስ መተባበር ትችላላችሁ።

፪. ጀማሪ ድምፃውያን ወይም ገጣሚያን ራስዎን በቪዲዮ እየቀረፁ ስራዎን ካቀረቡ በኋላ ለኛ ይላኩልን። በሳምንት አንድ ቀን /ቅዳሜ ማታ 4 ሰዓት/ ላይ ለህዝቡ እናስተላልፍልዎታለን። እውቅና እና ምክር እንዲያገኙ ያስችልዎታልና።
- - -
የቴሌግራም ቻናል በመቀላቀል ጀማሪ ድምፃውያን እና ገጣሚያን ስራዎቻችሁን እንዲሁም እንዲተላለፍ የምትፈልጉትን የእርዳታ ጥሪ ካለም አሳውቁኝ።
@Yismake_workubot በመግባት ንገሩኝ። በወረፋ ይፋ ይሆናል።
ጥናት

በዚህ ቻናል ውስጥ የት የሚኖር ዜጋ ይበልጥኑ አለ?

🅰 አረብ ሀገራት
🅱 ኢትዮጵያ
🅾 በአውሮፓ እና አሜሪካ

መልስዎን በመስጠት ይተባበሩኝ
👍2
Yismake Worku via @like
ወዳጆች፤ ቤትዎ ተቀምጠው የሚሰሩት ስራ እንካችሁ ብትባሉ እሺ ብለው ይቀበላሉ? በቅርቡ ከሰዎቹ ጋር ተማክሬ ሁኔታውን አሳውቃችኋለሁ። በተወሰነ ደረጃ ገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ብዬ በማሰብ ነው። ምን ያክሎቻችሁ ዝግጁ ናችሁ? 👍 በመጫን ስንቶቻችሁ እንደምትፈልጉት እና ለመስራት እንደተዘጋጃችሁ እንዳውቅ አድርጉኝ። ይሄን መልዕክት #ሼር በማድረግ አግዙኝ! ወዳጆቻችሁም እንዲያውቁ አድርጉ። @yismakeworku
ቤትዎ ተቀምጠው የሚሰሩት ስራ እንካችሁ ልላችሁ ነው አመጣጤ።

በተወሰነ ደረጃ ገቢ ማስገኛ መንገድ ነው ብዬ አስባለሁ።

በዚህ ጭንቅ ጊዜ እንደዚህ አይነት የወጣቶችን ስራም ጎን ለጎን ማሳወቅ እና ማበረታታት አለብን።

የቴሌግራም ቻናሉን Join ብላችሁ ስራውን ለመስራት ተዘጋጁ።

join ያድርጉ👇 https://tttttt.me/joinchat/LLNXHoKxuIo4OWM0
👍1
ማንበብ የዘመናዊነት ምልክት ነው። ትውልድ በንባብ ይታነፃል። የተንሸዋረረ አስተሳሰብ ይስተካከላል።

@yismakeworku
👍4
በ2013 ዓ.ም በህይወታችሁ ውስጥ የተፈጠረ ደስ የሚያሰኝ ነገር ምንድር ነው?

@Yismake_workubot አሳውቁኝ።

@yismakeworku
👍1
#ሳሚ_ኮምፒውተር

አዳዲስ እና "ዩዝድ" ላፕቶፖችን በተመጣጣኝ ዋጋ ከአንድ አመት ዋስትና ጋር ይሰጣል።

ዋጋቸውና የላፕቶፖችን አይነቶች ቴሌግራም ቻናላቸው ጋር እዩት።
አሁን ደግሞ ሰርፕራይዝ አለን እያሉ ነው። ቻናላቸው ጋ ግቡና ተመልከቱት👇👇👇👇
https://tttttt.me/joinchat/R0VHwY5lo438bB5d
👍1
ነገ አዲስ አመት ነው። የተወለድኩበት ቀንም ነው።

መልካም ልደት ለኢትዮጵያ
መልካም ልደት ለእኔ
@yismakeworku
👍151
እኔን እንደ ጭቃ ጠፍጥፌ ልሥራህ ከሚለኝ ቦዘኔ ጋር በፍፁም አልጓዝም። በአዲሱ አመት ከቅርብ ምቀኞች ራሳችሁን ጠብቁ። ድንጋይ የሚያሞቀውን ቦዘኔ ትታችሁት ወደፊት ተጓዙ! እዚህ ዘንድ አንዲት "የቀንዳውጣ ኑሮ" ላይ የተሰደረች ግጥም ትዝ አለችኝ።
"...ዘመን አይፈረጥጥ፣
ቀንም መሽቶ አይነጋ፣
ሰው ነው የሚጨልም፣
ሰው ነው የሚነጋ።"
ከሚያነጋላችሁ ሰው ጋር ነው መጓዝ ያለባችሁ። ከፊት ለፊታችሁ እንቅፋት ከሚያስቀምጥ ሰው ጋር፣ በአዲሱ አመት አንድም ርምጃ በፍፁም አትራመዱ። መልካም ሰንበት!

ሀሳቤን የምትጋሩ👍
የማትጋሩ ደሞ 👎
@yismakeworku
👍405