YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.86K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የለገጣፎ ከንቲባ ወ/ሮ #ሀቢባ_ሲራጅ ዛሬ #ዋንጫ የተሸለሙት የከተሞች የአትሌቲክስ ክለብ በማቋቋም ጥረት ከኦሮሚያ 3ኛ ደረጃን አግኝተው ነው።

⬆️ጌጡ ተመስገን ያሰራጨው ዜና አሁን #ኤልያስ_መሰራት አጣርቶ #Fake_News ነው ብሎታል።

የራሳችን መንገድ ተጠቅመን እስክናጣራ የዘገብነው ዜና የምናጠፋ ይሆናል።

ከታላቅ ይቅርታ ጋር‼️
@Yenetube @FikerAssefa
#Fake News Alert ‼️

"የሀዋሳ ከተማ እና አካባቢዋ ጸጥታ በመከላከያ እና በፌደራል ፓሊስ ዕዝ ሥር እንደሆነ ተውስኗል"

የሚል #የዉሸት_ዜና ከመሸ በመሰራጨት ላይ ይገኛል የዚህ ዜና እውነታ ለማጣራት ሙከራ አድርገና የደረስንበት ከእውነት የራቀ መሆኑን ለመረዳት ችለናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃው አለኝ የምትሉ መረጃ በ @FikerAssefa ላይ መላክ ትችላላችሁ።
#Share #Share
@YeneTube @FikerAssefa
#Fake_News_Alert

የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ጉዳት አድርሷል የሚባለው ወሬ ሐሰት ነው- የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር አልፎ ወደ አፋር ክልል በመግባት ጉዳት አደረሰ በሚል የሚሰራጨው ወሬ ሐሰት ነው” ሲል የኢፌዲሪ መከላከያ ሚኒስቴር ገለፀ።

“የጅቡቲ ጦር የኢትዮጵያን ድንብር ተሻግሮ በአፋር በኩል ዜጎች ላይ ጉዳት አደረሰ” የሚለው ወሬ ሐሰት መሆኑን በመከላከያ ሚኒስቴር የምክትል ኤታማዥር ሹም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ተናግረዋል።
በተለያዩ የማሕበራዊ ሚዲዎችና አንዳንድ የመገናኛ ብዙሃን “በአፋር ድንበር በኩል የጅቡቲ ጦር ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ ጉዳት አደረሰ” በሚል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ መሆኑም ተገልጿል።

ጅቡቲም ኢትዮጵያን የመውረር ሐሳብ እንደማታራምድና የሁለቱ አገሮች ወዳጅነት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ጥብቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሁለቱ አገሮች መካከል ለግጭት የሚዳርግ ምንም አይነት ተጨባጭ ምክንያት አለመኖሩን የገለጹት ኮሎኔል ተስፋዬ እየተሰራጨ ያለው መረጃም ትክክል አለመሆኑን አብራርተዋል።
ይሁን እንጂ በአካባቢው አልፎ አልፎ በግጦሽ፣ ውሃና በሌሎች ምክንያቶች የሚከሰቱ ግጭቶች መኖራቸውን አስታውሰው፤ በክልሉ በዜጎች ላይ የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ የመከላከያ ሰራዊት በስፍራው ተገኝቶ ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ተናግረዋል።

Via:- ENA
@YeneTube @Fikerassefa