YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
በሰላም ገብተዋል!!የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን አጠናቀው አስመራ ገብተዋል።

የፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ከፍ ወዳለ ተስፋ ወዳለው ደረጃ ማሸጋገሩን ነው የሀገሪቱ መንግስት የገለፀው።

#ፋና

@Yenetube @Fikerassefa
ወደቡ ወደ ስራ ሊገባ ነው!!! የአሰብ ወደብን ለመጠቀም ፈጣን እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

••>የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የገለፁት።

••>አቶ መለስ በመግለጫቸው የአሰብ ወደብን ለመጠቀም በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው፤ የመንገድ ጥገና ስራም እየተካሄ ይገኛል ብለዋል።

••>አቶ መለስ አክለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን መደበኛ በረራም በነገው እለት በይፋ እንደሚጀምር ገልፀዋል።

••>በነገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራም 465 ሰዎች ወደ አስመራ ይጓዛሉም ብለዋል።


#ፋና
@Yenetube @Fikerassefa
ሊወያዩ ነው!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከመምህራን ጋር ሊወያዩ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ የፊታችን ሰኞ ሀምሌ 16 2010 ዓ.ም ነው ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ውይይቱ ላይም ከ45 የመንግሰት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና 4 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተወጣጡ 3 ሺህ መምህራን እንደሚሳተፉም ተገልጿል።

በመድረኩም በተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ እና ምሁራን የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ በሚችሉበት ሁኔታ ዙሪያ ውይይት የሚካሄድ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

የውይይት መድረኩንም የትምህርት ሚኒስቴር ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑንም ገልጿል።

የትምህርት ተቋማቱ መምህራንን በጾታ፣በትምህርት አይነትና በደረጃ አመጣጥነው መርጠው እንዲልኩ እና ተቋማቱ የተመሰረቱበትን ጊዜ መሰረት በማድረግ ኮታ እንደተሰጣቸውም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

#ፋና ቢሲ
@Yenetube @Fikerassefa
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ፋና ስለ አለምፀሀይ ወዳጆ የሰራው ሰገባ ስራዎቿን እና ታሪኳን ዳሷል።

🖍 አለምፀሀይ ወዳጆ ወደ ሀገር ቤት ስትገባ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታ።

@YeneTube @Fikerassefa
#የገዥው ፓርቲ ንብረቶች የሆኑት #ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት (ራዲዮ ፋናና ፋና ቴሌቭዥን)፣ #ዋልታ ( ዋልታ ቴሌቭዥን) እንዲሁም በሁለቱ ድርጅቶች ጥምረት የተመሰረተው #ዋፋ ፕሮሞሽን የተባለው የማስታወቂያ ድርጅት #ከኢሕአዴግ ጉባዔ ተከትሎ #የህዝብ ንብረት እንዲሆኑ ዕቅድ #ቀረበ

📌 የፓርቲ አባል የሆኑ #የድርጅቶቹ አመራሮችም በቦታቸው እንደማይቀጥሉ የዋዜማ ራዲዮ ዘገባ ያመለክታል።
ምንጭ ፦ዋዜማ ራዲዮ
@yenetube @mycase27