YeneTube
117K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.9K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#በምዕራብ ጎንደር ዞን ከትናንት የተሻለ መረጋጋት አለ የዞኑ #አስተዳደር

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ መልካሙ በስልክ ባደረሱን መረጃ መሠረት ዞኑ #ከትናንት በተሻለ ሰላሙ ተመልሷል፡፡

‹‹ትናንት ሰላም ቢሆኑም ‹ስጋት ነበረባቸው› ያልኳቸው #የሽንፋና መተማ ዮሐንስ አካባቢዎች ዛሬ የተሻለ ሰላማዊ ናቸው፡፡ ከሕዝቡና ከፀጥታ አካሉ ጋር በመሆን አጥፊዎችን የመለዬት ሥራም እየሠራን ነው›› ብለዋል አቶ ሞላ፡፡

ትናንት ከገንዳ ውኃ ወደ ነጋዴ ባሕር በሚወስደው መንገድ ላይ መኪና አስቁመው ለመዝረፍ የሞከሩ #አራት ታጣቂዎችና አራት ጀሌዎች (መሳሪያ ያልታጠቁ) በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው ‹‹ባለፈው ግጭቱን ያነሳሱትን የመለዬት ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል›› ብለዋል፡፡

የምዕራብ ጎንደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር #ጌትነት አልታሰብ በበኩላቸው ‹‹የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ሙሉ በሙሉ ወደ ሥራ ገብቷል፤ አልፎ አልፎም ለተሽከርካሪዎች ድንገተኛ እጀባ እያደረግን ሰላሙን የበለጠ ለማረጋገጥ እየሠራን ነው›› ብለዋል፡፡

የፀጥታ መዋቅሩ የዞኑ ሰላም አስተማማኝ እንዲሆን ያለዕረፍት ሥራ ላይ መሆኑንም ኮማደሩ ገልጸዋል፡፡
ምንጭ ፦አብመድ
@yenetube @mycase27