YeneTube
116K subscribers
31.6K photos
485 videos
79 files
3.92K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
#Deberbirhan #ደብርብርሀን ዩንቨርስቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ የ2011 የትምህርት ዘመን መግቢያ ጥቅምት 1 እና 2 ቀን 2011 ዓ.ም. መሆኑን መግለፃችን ይታወቃል።

ሆኖም ግን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የመግቢያ ጊዜው ላልተወሰነ ጊዜ #የተራዘመ መሆኑን ከታላቅ #ይቅርታ ጋር እየገለፅን የመግቢያ ጊዜውን በትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲያችን በኩል ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።

ይህንን መልዕክትም ለሁሉም ተማሪዎቻችን እንዲደርስ ለምታደርጉልን በሙሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

©ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
@YeneTube @Fikerassefa
የሲዳማ ህዝብ ከዓመታት በፊት ያቀረበዉ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ዘግይቶም ቢሆን ምላሽ ማግኘት በመጀመሩ መላው #የሲዳማ ብሔር #እንዲረጋጋ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ #ሲአን ጠየቀ። የንቅናቄው ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ደስላኝ ሜሳ፣ «ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ ተቀብሎ ህዝበ ውሳኔ
ለማድረግ መዘጋጀቱን አረጋግጧል።» ብለዋል።

በዚሕም ምክንያት የሲዳማ ሕዝብ የህዝበ ውሳኔውን ሂደት እንዲጠባበቅ ንቅናቄው ጥሪ ማስተላለፉን አቶ ደሳላኝ ለሐዋሳዉ ዘጋቢያችን ለሸዋንግዛዉ ወጋየሁ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አመልከተዋል። ይሁንና አቶ ደሳለኝ እንደሚሉት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝበ ዉሳኔዉ ሊደረግ ከሚገባዉን ቀን #አዘግይቷል ብሎ ንቅንቄያቸዉ እንደሚያምን ጠቅሰዉ ለዚሕም ቦርዱ፣ ሕዝቡን #ይቅርታ_መጠየቅ_ይገባዋል_ብለዋል

በሲዳማ ዞን የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሲዳማ አርነት ንቅናቄ ( ሲአን ) ፣ የሲዳማ ሀድቾ ዴሞክራሲያዊ ደርጅት ( ሲሀዴድ ) እና የሲዳማ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ሲብዴፓ )፣ የሲዳማ ህዝብ በክልል ለመደራጀት የሚያስችለው የህዝበ ውሳኔ የሚደረግበትን ቀን መንግሥት በአምስት ቀናት ዉስጥ ይፋ እንዲያድርግ ባለፈዉ ሳምንት መጀመሪያ ጠይቀዉ ነበር። የተቀሩት ሁለቱ ፓርቲዎች አስከ አሁን ሥለ ጉዳዩ በይፋ ያሉት ነገር የለም።

ምንጭ:- DW
@YeneTube @FikerAssefa
በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ከተሞች በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ለጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት ምክኒያት የሆነው አቶ ጀዋር መሀመድ በፌስቡክና በቴሌቪዥን ያስተላለፈው እጅግ ኃላፊነት የጎደለው ቅስቀሳ ስለሆነ በአስቸኳይ የኢትዮጵያን ህዝብ #ይቅርታ እንዲጠይቅና በወንጀል ሊጠየቅ ይገባል ብሏል እስክንድር ነጋ።

እስክንድር ነጋ ለኢሳት ቴሌቪዥን ከትናገረው የተወሰደ
@YeneTube @Fikerassefa