YeneTube
118K subscribers
31.4K photos
485 videos
79 files
3.87K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የአፋር ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አብዴፓ) 7ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከህዳር 24 እስከ 26 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታወቀ።

የፓርቲው ጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ አሊ አብደላ #ለኢዜአ እንደገለጹት በጉባኤው ነባር አመራሮችን በክብር በመሸነት ብቃት ያላቸው ወጣቶችን ወደ #ኃላፊነት ይመጣሉ።

"በጉባኤው 593 ሰዎች በድምፅና 107ቱ ያለድምጽ ይሳተፋሉ" ብለዋል ።
በፓርቲው የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የአመራርነት ዘመን #ከ10 ዓመት በላይ እንዳይበልጥ የሚገድብ ሰነድ ቀርቦ በአባላት ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል ።
የፓርቲው ያለፉት ሶስት ዓመታት የስራ #አፈጻጸምን በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ አቶ አሊ ተናግረዋል።
@YeneTube @Fikerassefa
የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የፈተና ውጤት ይፋ ሆነ!

ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ የፈተና ውጤትን ይፋ አደረገ።የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አርዓያ ገብረ እግዚአብሄር በ2011 ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ፈተና ዙሪያ ከፋና ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ከተፈታኞቹ መካከልም #ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎች #አራት_ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

75 ነጥብ 5 በመቶ ያህል ተፈታኞች 2.0 እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያመጡ መሆናቸውን ዳይሬክተሩ ጠቅሰዋል።2.0 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡት ተማሪዎች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል። ከተፈታኞቹ መካከል ወንዶች 682 ሺህ 572 ሲሆኑ 572 ሺህ 997 ሴቶች ናቸው፡፡ከእነዚህ መካከል 894 ሺህ 318 በመደበኛ፣ 354 ሺህ 782 በግል እና 6 ሺህ 469 ደግሞ በማታው ክፈለ ጊዜ ተፈታኞች እንደነበሩ ነው የተገለጸው።

በዘንድሮው የ10ኛ ክፍል ፈተና ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ለፈተና መቀመጣቸውን የኤጀንሲ መረጃ ያመላክታል።ባለፈው አመት ሁለት እና ከዚያ በላይ ነጥብ ያስመዘገቡት ተፈታኞች 71 በመቶ መሆናቸው የሚታወስ ነው።ተማሪዎች ውጤታቸውን በኤጀንሲው ድረ ገጽ http://
app.neaea.gov.et ወይም www.neaea.gov.et እንዲሁም በአጭር የጽሁፍ መልዕክት 8181 ላይ ID- ብለው የአድሚሽን ቁጥራቸውን በማስገባት መመልከት ይችላሉ።

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa