የ #ኢዜማ ሊቀመንበር ነገ የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን ይፋ ያደርጋሉ። ቦታ – ጊዮን ሆቴል ብሉ ሳሎን ቀን – ነገ ሐሙስ ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ·ም ሰዓት – 8:00 ሁሉም የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙኃን ተገኝተው እንዲዘግቡ ጥሪ ተደርጓል።
@YeneTube @FikerAssefa
@YeneTube @FikerAssefa
የኢትዮጵያ ዜጎች ማህበራዊ ፍትህ ህዝባዊ ስብሰባ!!
#ኢዜማ ነገ እሁድ የመጀመሪያ ህዝባዊ ስብሰባውን በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ ያደርጋል።
Via:-Nardos
@YeneTube @FikerAssefa
#ኢዜማ ነገ እሁድ የመጀመሪያ ህዝባዊ ስብሰባውን በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ ያደርጋል።
Via:-Nardos
@YeneTube @FikerAssefa
⬆️የከንባታ ሕዝቦች ኮንግረስ (ከሕኮ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ)ን ተቀላቀለ።
የከንባታ ሕዝቦች ኮንግረስ ሐምሌ 28 ቀን 1983 ዓ·ም ተመሥርቶ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የቆየ የፖለቲካ ድርጅት ሲሆን የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ፣ ምክር ቤት እና ጠቅላላ ጉባዔ በየደረጃው ባሳለፉት ውሳኔ መሠረት ኮንግረሱን በማክሰም ከግንቦት 22 ቀን 2011 ዓ·ም ጀምሮ ከኢዜማ ጋር መቀላቀሉን በኢዜማ ጽሕፈት ቤት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ተደርጓል።
ከዚህ ቀደም የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ይፈጥሯቸው ከነበሩ ቅንጅቶች፣ ግንባሮች እና ህብረቶች በተለየ መልኩ ራሳቸውን ያከሰሙ ድርጅቶች በምርጫ ወረዳ የተዘረጉ መዋቅሮችን በመቀላቀል እንደ አዲስ ፓርቲ የተመሠረተው ኢዜማ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋርም በተመሳሳይ መርህ አብሮ ለመሥራት በሩ ክፍት እንደሆነ ተገልጿል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ፣ በተናጥል የሚደረግ ትግል ለድል እንደማያበቃ በመረዳት ሌሎች ፓርቲዎችም የከምባታ ሕዝቦች ኮንግረስን ፈለግ በመከተል ኢዜማን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ተላልፏል።
ግንቦት 1 እና 2 ቀን መሥራች ጉባዔ በማድረግ በይፋ የተመሠረተው ኢዜማ አስፈላጊውን የምዝገባ ሰነዶች በማሟላት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምዝገባ ሰርተፍኬት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ቦርዱም ጥያቄውን ተቀብሎ በምዝገባ ሂደት ላይ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ መጻፉ ይታወሳል።

#ኢዜማ
ትላንት በሞጣ ከተማ በእምነት ተቋማት ላይ በደረሰው ጥቃት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።
በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርስ ጥቃት በምንም ምክንያት ተቀባይነት የሌለው እና ጥቃቱ በየትኛውም የእምነት ተቋም ላይ ሲደርስ ሁሉም ማኅበረሰብ በአንድነት ቆሞ ሊያወግዘው የሚገባ ተግባር ነው።
መንግሥት በእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ጨርሶ ሊታገስ አይገባም። በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈፀም ጥቃት የዜጎች የእምነት ነፃነት ላይ የሚፈፀም ወንጀል ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲሰፍን የምንፈልገው ሀገራዊ መረጋጋት እና ሰላም ላይ ከፍተኛ እንቅፋት የሚፈጥር የወንጀል ድርጊት መሆኑን በመረዳት መንግሥት በአጥፊዎች ላይ ተገቢውን የህግ እርምጃ መወሰድ አለበት።
ከእንደዚህ ዓይነቱ አጋጣሚ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት እየሞከሩ የሚገኙ ኃይሎች ከዚህ ኃላፊነት ከጎደለው አካሄድ እንዲታቀቡ አጥብቀን እናሳስባለን።
መንግሥት ትላንት በሞጣ የተፈፀመው ዓይነት ጥቃት በድንገት የሚከሰት አለመሆኑን በመረዳት ለወደፊቱ እንዲህ ዓይነት ጥፋት ከመከሰቱ አስቀድሞ መከላከል የሚቻልበት አቅም መፍጠር ላይ አትኩሮት አድርጎ መሥራት ይገባዋል።
የአጥፊዎቹ ድርጊት በከተማው የሚኖሩ የሁለቱን እምነት ተከታዮች ለዘመናት በሰላም አብሮ በመኖር ያላቸውን ታሪክ በፍጹም የማይገልፅ ቢሆንም፣ በደረሰው ጥፋት ምክንያት ወደፊት በዜጎች መሀከል የሚኖረው ግንኙነት ላይ ሊፈጠር የሚችለውን መቃቃር የሞጣ ከተማ ነዋሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች አና የከተማው አስተዳደር የከተማው ሕዝብን በማረጋጋት፣ የውይይት መድረኮችን በማዘጋጀትና እና አጥፊዎችን አጋልጦ በመስጠት የማያዳግም መፍትሄ ሊያስቀመጡ ይገባቸዋል።
የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት
@Yenetube @Fikerassefa

የ #ኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) ከፍተኛ አመራሮች ሞጣ ከተማ በመገኘት ባለፈው ሳምንት ጥቃት የደረሰባቸውን የእምነት ተቋማት እና የንግድ ቤቶች ጎበኙ።
ጉብኝቱን ያደረጉት የኢዜማ ሊቀመንበር የሺዋስ አሰፋ እና የሴቶች ጉዳይ ተጠሪ ከውሰር እድሪስ ከአካባቢው የኢዜማ አደራጆች ጋር በጋራ በመሆን ነው።
በጉብኝቱ ወቅት አመራሮቹ በእምነት ተቋማት ላይ እና በንጹሃን ዜጎች ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው ድርጊቱን አውግዘዋል። ከፍተኛ አመራሮቹ ከተማዋን ለማረጋጋት እና የሃይማኖት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት ከተዋቀረው ኮሚቴ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ ላይ ተገኝተው የነበሩ የአካባቢው ባለሃብቶች ለመልሶ ግንባታ የሚሆን እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።
የከተማው ወጣት በወንድማማችነት ሰላሙን እንዲያስከብር፣ ጥቃቱን ያደረሱ ሰዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና የእምነት ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት ሁሉም ማኅበረሰብ የተቻለውን እንዲያግዝ ኢዜማ መልዕክት እንዲያስተላለፍ ከኮሚቴው የቀረበውን ጥያቄ አመራሮቹ በሙሉ ልብ ተቀብለዋል።

በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይና በስፍራው በተሰማሩ የፀጥታ አባላት ላይ ስለተፈፀመው ግድያ ፍትህ እንጠይቃለን!
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይና በስፍራው በተሰማሩ የፖሊስ አባላት ላይ ስለተፈፀመው የጅምላ ግድያ ያቀረበው ሪፖርት ከፍተኛ ሀዘን እና ድንጋጤን ፈጥሮብናል፡፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (#ኢዜማ) በተጎጂዎችና በተጎጂ ቤተሰቦች፤ በአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም እንዲህ ያለ አስነዋሪ ድርጊት በአገራቸው ቦታ እንዳይኖረው በሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ስም ኮሚሽኑን ማመስገን ይፈልጋል፡፡ ሕዝብና አገር የሚጠቀሙት የገዢዎችን ፊት እያዩ ሳይሆን በመረጃ ላይ በተመሰረተ እውነት በሀቀኝነት በሚሰሩ ተቋማት በመሆኑ የሚዲያ፣ የፀጥታና የፍትህ ተቋማት የኢሰመኮን አርዓያነት እንዲከተሉ እንጠይቃለን፡፡
በከረዩ የሚችሌ ገዳ የጅላ አባላት ላይ የተፈፀመው ያለ ፍርድ ግድያ (Execution without trial) ኢዜማ በአገራችን እንዲሰፍን የሚታገልለት የሕግ የበላይነት ከፍተኛ አደጋ ውስጥ መወድቁን ያሳያል፡፡ ዜጎች በእዚህ መልኩ ክቡር የሆነ ሕይወታቸውን እንዲያጡ ምንም ዓይነት ምክንያት ሊቀርብ አይችልም፡፡ ግድያውን ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በጋራ እንዲያወግዙት እየጠየቅን መንግስት ከጅምላ ግድያው ጋር በተያያዘ እጃቸው ያለበትን የፀጥታ እና የአስተዳደር አካላት ሁሉ በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ እንጠይቃለን፡፡ የዜጎች ደኅንነትን መጠበቅ የመንግስት ተቀዳሚ ተግባሩ ሲሆን በአካባቢው የፀጥታ አካላት ላይ ጥቃት የፈፀመውንም “ታጣቂ ቡድን” ተከታትሎ ለፀጥታ ሀይሉም ሆነ ለማኅበረሰቡ ስጋት እንዳይሆን በስልት መስራት ግዴታው እንደሆነ መንግስትን ልናስታውስ እንወዳለን፡፡
በግብር ከፋዩ ሕዝብ ሀብት የሚተዳደሩ የመንግስት የመገናኛ ተቋማት ግድያው በተፈፀመበት ወቅት አውቀውም ይሁን በስህተት በጉዳዩ ላይ ለሕዝብ የሰጡት በሀሰት የተቀናበረ መረጃ የተቋማቱን አደገኛ አካሄድ ዛሬም በግልፅ አሳይቷል፡፡ ሰፊ ተደራሽነት ያላቸውና የሕዝብ ሀብት የሆኑ የመንግስት ሚዲያዎች በጓዳቸው ካለ የትላንት ታሪካቸው ተምረው ለተቋቋሙበት ዓላማ፣ ለሕግና ለእውነት ብቻ እንዲሰሩ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ይህን እኩይ ተግባር በተሳሰተ መንገድ የዘገቡ ሚዲያዎች ሁሉ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው የኮሚሽኑን ሪፖርት አልያም በራሳቸው መንገድ የተፈጠረውን ትክክለኛ ኩነት በድጋሜ ለሕዝብ እንዲያደርሱ እንጠይቃለን፡፡
ፍትህን በፅኑ እንጠይቃለን፡፡
ኢዜማ
ኢትዮጵያ

#እናወግዛለን!!
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በጎንደር ከተማ በትላንትናው እለት፤ ሚያዝያ 18 ቀን 2014 ዓ.ም በተፈጠረው ግጭት እና በጠፋው የሰው ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልጻለን፣ ድርጊቱንም እናወግዛለን!
ሀገር የሁላችን ናት፡፡ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ከልካይ ምክንያት በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች መብታቸው ተከብሮ ሊኖሩ ይገባል፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁንም ክቡሩ የሰው ህይወት እንደዘበት የሚቀጠፍባት ሀገር እንደሆነች ቀጥላለች፡፡
በተቀናጀ ሁኔታ የሀገርን እና ህዝቧን ደህንነት ለማስጠበቅ መስራት አስቸኳይ እና አንገብጋቢ አጀንዳው እንዲሆን አሁንም መንግስትን እናሳስባለን፡፡
መንግስት ጉዳዩን በፍጥነት አጣርቶ አጥፊዎችን ለፍርድ እንዲያቀርብ እንዲሁም ችግሩ እንዳይስፋፋ እና የበለጠ ጥፋት እንዳያመጣ እንዲቆጣጠር እንጠይቃለን!
የኢትዮጵያ ህዝብ አብሮ የመኖር እሴቱን ከሚሸረሽሩ ተግባራት እራሱን እንዲጠብቅ እየጠየቅን የሀይማኖት መሪዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ህዝብን የማረጋጋት ስራ እንዲሰሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን!

የጤና ባለሙያዎች ሙሉ ለሙሉ የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ!
በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ስድስተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ዕለት ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ አንዳንድ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎቶች መስጠት ማቆማቸው ተገለጸ።
#በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ በሚገኘው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ የጤና ባለሙያ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት በሆስፒታሉ የሚገኙ አጠቃላይ ሐኪሞች "ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም አድማውን እየተሳተፉ ነው ሌሎች የሰራተኛ አባላት ግን አሁንም እየሰሩ ናቸው" ብለዋል።
አዲስ ስታንዳርድ በዛሬው ዕለት ማለዳ ላይ በሶስት ዋና ዋና ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ባደረገው ጉብኝት የአገልግሎት መስተጓጎል በስፋት ያስተዋለ ሲሆን የተወሰኑ የድንገተኛ ህክምና ክፍሎች ብቻ ስራቸውን ሲቀጥሉ ለመታዘብ ተችሏል።
በተያያዘ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መንግስት “የጤና ባለሙያዎቹን ጥያቄያቸውን ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ለማሳየት ሙከራ እንኳ አላደረገም” ሲል ተችቷል “ማስፈራሪያ አዘል አቅላይ መንገድን መከተሉ ሃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የሚመነጭ የመንግስት ስህተት ነው” ብሏል።
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ :-
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7822

Addis standard
የጤና ባለሙያዎች ሙሉ ለሙሉ የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11/ 2017 ዓ/ም፦ በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ስድስተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ዕለት ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ አንዳንድ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎቶች መስጠት ማቆማቸው ተገለጸ። በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ የሚገኘው…
👍108😭21❤8😁5