YeneTube
119K subscribers
31.3K photos
483 videos
79 files
3.85K links
መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa
Download Telegram
የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፊል የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ገለፁ

በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም. በመላ ሀገሪቱ የተጀመረውን የከፊል የስራ ማቆም አድማ ለማካሄድ ሲሞክሩ ከመንግሥት አካላት ማስፈራሪያና ጫና እንደደረሰባቸው አስታወቁ።

#በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ በሚገኘው የማዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጎባ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና የሰራተኛ የሆኑ አንድ ግለሰብ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጹት የጤና ባለሙያዎች አድማውን ለማድረግ ሲሞክሩ ከአካባቢው ባለስልጣናት ጫና እንደገጠማቸው አስረድተዋል።

ባለሙያው "ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው" ያሉ ሲሆን፤ ሆስፒታሉ ከማለዳ ጀምሮ "በመንግስት የስራ ሀላፊዎች የተሞላ" እንደነበር ጨምረው ተናግረዋል።

ሌላኛው በአማራ ክልል ደቡብ #ወሎ ዞን በአቀስታ ከተማ የአቀስታ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ የጤና ባለሙያ በበኩላቸው በድንገተኛ ክፍል የተመደበ አንድ ሀኪም "በፀጥታ ሀይሎች" ተይዞ የተለመደውን የህሙማን ህክምና አገልግሎት እንዲሰጥ አልያም "ወደ እስር ቤት እንዲሄድ" እንደተነገረው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው ዕለት ተጠርቷል የተባለውን የህክምና ባለሙያዎች አድማ ለመታዘብ በሶስት ዋና ዋና የመንግስት ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣ #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #በየካቲት12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ቅኝት ያደረግን ሲሆን በእነዚሁ ተቋማት ከሰዓት በኋላ ስራ የተጀመረ ይሁን እንጂ ጠዋት ላይ የከፊል የስራ ማቆም መካሄዱን ታዝበናል።

የአዲስ ስታንዳርድ ዘገባ ይመልከቱ

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7748
👍40🔥5👀32😭2
የጤና ባለሙያዎች ሙሉ ለሙሉ የስራ ማቆም አድማ መጀመራቸውን ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ!

በመላ ሀገሪቱ የተጀመረው የጤና ባለሙያዎች የስራ ማቆም አድማ ስድስተኛ ቀኑን በያዘበት በዛሬው ዕለት ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ንቅናቄ ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም ጥሪ ማስተላለፉን ተከትሎ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ አንዳንድ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎቶች መስጠት ማቆማቸው ተገለጸ።

#በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ፍቼ ከተማ በሚገኘው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ የጤና ባለሙያ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት በሆስፒታሉ የሚገኙ አጠቃላይ ሐኪሞች "ሙሉ በሙሉ የስራ ማቆም አድማውን እየተሳተፉ ነው ሌሎች የሰራተኛ አባላት ግን አሁንም እየሰሩ ናቸው" ብለዋል።

አዲስ ስታንዳርድ በዛሬው ዕለት ማለዳ ላይ  በሶስት ዋና ዋና ሆስፒታሎች ማለትም በዳግማዊ #ምኒልክ ሪፈራል ሆስፒታል፣  #በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል እና #የካቲት 12 ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል ባደረገው ጉብኝት የአገልግሎት መስተጓጎል በስፋት ያስተዋለ ሲሆን የተወሰኑ የድንገተኛ ህክምና ክፍሎች ብቻ ስራቸውን ሲቀጥሉ ለመታዘብ ተችሏል።

በተያያዘ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትሕ (#ኢዜማ) ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መንግስት “የጤና ባለሙያዎቹን ጥያቄያቸውን ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ለማሳየት ሙከራ እንኳ አላደረገም” ሲል ተችቷል “ማስፈራሪያ አዘል አቅላይ መንገድን መከተሉ ሃላፊነትን በአግባቡ ካለመወጣት የሚመነጭ የመንግስት ስህተት ነው” ብሏል።

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ :-
https://addisstandard.com/Amharic/?p=7822
👍108😭218😁5